#እናወግዛለን!!
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) በጎንደር ከተማ በትላንትናው እለት፤ ሚያዝያ 18 ቀን 2014 ዓ.ም በተፈጠረው ግጭት እና በጠፋው የሰው ህይወት የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እንገልጻለን፣ ድርጊቱንም እናወግዛለን!
ሀገር የሁላችን ናት፡፡ ኢትዮጵያውያን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እና ከልካይ ምክንያት በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች መብታቸው ተከብሮ ሊኖሩ ይገባል፡፡ ነገር ግን ኢትዮጵያ አሁንም ክቡሩ የሰው ህይወት እንደዘበት የሚቀጠፍባት ሀገር እንደሆነች ቀጥላለች፡፡
በተቀናጀ ሁኔታ የሀገርን እና ህዝቧን ደህንነት ለማስጠበቅ መስራት አስቸኳይ እና አንገብጋቢ አጀንዳው እንዲሆን አሁንም መንግስትን እናሳስባለን፡፡
መንግስት ጉዳዩን በፍጥነት አጣርቶ አጥፊዎችን ለፍርድ እንዲያቀርብ እንዲሁም ችግሩ እንዳይስፋፋ እና የበለጠ ጥፋት እንዳያመጣ እንዲቆጣጠር እንጠይቃለን!
የኢትዮጵያ ህዝብ አብሮ የመኖር እሴቱን ከሚሸረሽሩ ተግባራት እራሱን እንዲጠብቅ እየጠየቅን የሀይማኖት መሪዎች እና የሀገር ሽማግሌዎች ህዝብን የማረጋጋት ስራ እንዲሰሩ ጥሪያችንን እናቀርባለን!
#ኢዜማ
@Yenetube @Fikerassefa