YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.86K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#ጨፌ ኦሮሚያ 3ኛ አስቸኳይ ጉባኤውን ማካሄድ ጀመሯል። ስብሰባው የክልሉን አስፈጻሚ አካላት መልሶ ለማደራጀትና ስልጣንና ሃላፊነታቸውን ለመወሰን የወጣው ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ ለማጽደቅ ነው #ተብሏል

ረቂቅ አዋጁ ችግር የሚስተዋልበትን የአስፈጻሚ አካላት አደረጃጀት፣ የሰው ሃይልና በጀት አጠቃቀም ላይ የሚስተዋለውን ሰፊ ክፍተት ይቀርፋል ተብሎ ይጠበቃል።

ከዚህ ባለፈም በቢሮ ደረጃ ተከማችተው የሚገኙ የአስፈጻሚ አካላት አደረጃጀቶች ታች ካለው ማህበረሰብ ጋር ቀርበው እንዲያገለግሉ ከማድረግ አኳያ ትልቅ ሚና ይኖረዋልም ነው የተባለው።

ጨፌው ከዚህ ባለፈም የክልሉን ጠቅላይ አቃቤ ህግ ለማቋቋም የወጣው ረቂቅ አዋጅ ላይ በመወያየት ያጸድቃል ተብሎም ይጠበቃል።

በተጨማሪም በቁጥር 61/1994 የወጣውን የሰራተኞች አዋጅ ለማሻሻል በወጣው ረቂቅ ላይ ተወያይቶ ማፅደቅም በጨፌው ስብሰባ ከመሚጠበቁት ውስጥ ነው።

©fbc
@yenetube @mycase27
20ኛው የአፍሪካ ህብረት #አስቸኳይ ጉባኤ በሚኒስትሮች ደረጃ ዛሬ በአዲስ አበባ መምከር ጀምሯል፡፡ ምክክሩ ህዳር 8-9 በመሪዎቸ ደረጃ የሚደረገውን የኮሚሽኑ የማሻሻያ ውሳኔዎች መገምገም ነው #ተብሏል፡፡

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ.ር #ወርቅነህ ገበየሁ እየተካሄደ ባለው የአፍሪካ ህብረት የሚኒስትሮች አስቸኳይ ጉባዔ ላይ ባደረጉት ንግግር የአፍሪካ ህብረት የመዋቅር ማሻሻያ የህብረቱን የ2063 አጀንዳ ተግባራዊ ለማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ምንጭ፡- የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
@yenetube @mycase27