YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.86K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
YeneTube
Photo
#አዲስ አበባ

በአሜሪካ ኮንግረስ የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ የአፍሪካ ንዑስ ኮሚቴ ሰብሳቢ ኮንግረስማን #ክሪስ_ስሚዝ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ስላለው #ለውጥ አድናቆት ያላቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የአሜሪካ ኮንግረንስ አባላት ልኡካን ቡድን ከኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር #ወርቅነህ _ገበየሁ በአዲስ አበባ ተወያይቷል፡፡

©ETv
@YeneTube @Fikerassefa
#የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር #ወርቅነህ ገበየሁ በ73ኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ #ኒውዮርክ ገቡ፡፡

📌ዶ/ር ወርቅነህ ከጠቅላላ ጉባኤው ጎን ለጎን ከመንግስታቱ ድርጅት ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ምንጭ፡-ኢቢሲ
@yenetube @mycase27
በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረ/ሚኒስትር አምባሳደር #ቲቦር ናጂ ከው/ጉዳይ ሚኒስትር #ወርቅነህ ገበየሁ ጋር በአፍሪቃ ቀንድ እየታየ ባለው ለውጥ ዙሪያ ተወያዩ።

📌አምባሳደር ቲቦር በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ሆነው አገልግለዋል
@yenetube @mycase27
የመንግስታቱ ድርጅት በኤርትራ ላይ ተጥሎ የቆየውን ማዕቀብ በአስቸኳይ እንዲያነሳ #ኢትዮጵያ ጠየቀች።

በኒውዮርክ እየተካሄደ ባለው የመንግስታቱ ድርጅት ጉባዔ ላይ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር #ወርቅነህ_ገበየሁ በጉባዔው ላይ ሀገራቸውን ወክለው ትናንት ምሽቱን ባደረጉት ንግግር በአፍሪካ ቀንድ አዲስ የተፈጠረውን ሰላምና ወዳጅነት አብራርተው ኤርትራ ላይ የተጣለው ማዕቀብ በቶሎ መነሳይ አለበት ብለዋል።

©ዋዜማ ራዲዮ
@YeneTube @Fikerassefa
የኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ዶክተር #ወርቅነህ ገበየሁ በጣልያን-አፍሪካ የሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ ወደ ጣልያን አቀኑ፡፡
@yenetube @mycase27
20ኛው የአፍሪካ ህብረት #አስቸኳይ ጉባኤ በሚኒስትሮች ደረጃ ዛሬ በአዲስ አበባ መምከር ጀምሯል፡፡ ምክክሩ ህዳር 8-9 በመሪዎቸ ደረጃ የሚደረገውን የኮሚሽኑ የማሻሻያ ውሳኔዎች መገምገም ነው #ተብሏል፡፡

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ.ር #ወርቅነህ ገበየሁ እየተካሄደ ባለው የአፍሪካ ህብረት የሚኒስትሮች አስቸኳይ ጉባዔ ላይ ባደረጉት ንግግር የአፍሪካ ህብረት የመዋቅር ማሻሻያ የህብረቱን የ2063 አጀንዳ ተግባራዊ ለማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ምንጭ፡- የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
@yenetube @mycase27