YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ግምቱ ወደ 28 #ሚሊዮን የሚጠጋ ብር በስድስት ኩንታል ተሞልቶ ከአዲስ አበባ ወደ #ሚዛን ተፈሪ ሲጓዝ በካፋ ዞን የጨና ወረዳ ነዋሪዎች በቁጥጥር ስር ዋለ

ገንዘቡ ለምን አላማና በማን እንደሚጓጓዝ እስካሁን #በፖሊስ ምርመራ እየተደረገበት መሆኑን ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡

📌የምንመለስበት ይሆናል ❗️
©MOHAMMED NURE ENDRIES
@YeneTube @Fikerassefa
#በፖሊስ ቁጥጥር ሥር የዋሉት ጠበቃ #ሔኖክ አክሊሉ እና አቶ #ሚካኤል መላክ ፍርድ ቤት ቀረቡ።

አራዳ በሚገኘው የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የቀረቡት አቶ ሔኖክ እና አቶ ሚካኤል "#የገጠር ሰው አይመራንም በማለት ወጣቶችን አስተባብራችሁ አመጽ ልታነሳሱ ነበር" በሚል መጠርጠራቸውን የሕግ ባለሙያው አቶ ደሙ አስፋው ለ«DW» ተናግረዋል።

አቶ #ሔኖክን ወክለው በፍር ቤቱ ጥብቅና የቆሙት የሕግ ባለሙያ እንደተናገሩት ከፍልስጤም ኤምባሲ ጋር በመተባበር እስራኤልን መመከት የሚል አጋርነት እና ስልጠና ውስጥ ተሳትፈዋል በሚል ጉዳይ ጭምር መጠርጠራቸውን ገልጸዋል።

አቶ ሔኖክ ከዚህ ቀደም በተለያዩ ምክንያቶች ለታሰሩ ሰዎች #ጥብቅና በመቆም ይታወቃሉ።

ጠበቃ ሔኖክ በጸረ-ሽብር ሕግ እና የሰብዓዊ መብት ጉዳዮች ላይ በአዳማ ከተማ በሚደረግ የምክክር መድረክ ይሳተፋሉ ተብሎ #ይጠበቅ ነበር።

ፖሊስ ለምርመራ 15 ቀናት ቢጠይቅም ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን ለጥቅምት 15 ቀጠሮ ሰጥቷል ።
ምንጭ ፦ DW
@yenetube @mycase27
በደቡብ ክልል፣ በከንባታ ጠንባሮ ዞን ዱራሜ ከተማ ከተለያዩ ዩንቨርስቲዎች ባለፉት 4 አመታት ተመርቀው ስራ ማግኘት ያልቻሉ ወደ 400 የሚጠጉ ወጣቶች ቅሬታቸውን ለማሰማት ወደ ዞኑ አስተዳደር በሄዱበት ወቅት #በፖሊስ በሀይል እንዲበተኑ ተደርገዋል።

📌ይህንን ተግባ የፈፀሙ ፓሊሶች በህግ እንዲጠየቁ ታሳስባለች።
@YeneTube @Fikerassefa
⬆️የአዲስ አበባ #ባለአደራ ምክር ቤት /ባልደራስ/ በዛሬው ዕለት ቅዳሜ መጋቢት 21 #በራስ ሆቴል ጠርቶ የነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ #በፖሊስ ክልከላ ጋዜጠኞች #እንዳይገቡ ተደርጓል፡፡

አጠቃላይ ዝግጅቱን ለማስተጓጎል እየተሞከረ ነው፡፡ ይሁን እንጅ የአዲስ አበባ ባለአደራ ም/ቤት (ባልደራስ ) በሆቴሉ በር ላይ መግለጫ ለመስጠት እየተዘጋጀ ነው፡፡

ምንጭ:- ስንታየሁ ቸኮል - አስተባባሪ
@YeneTube @FikerAssefa