YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ማስታወሻ

የአዲስ አበባ #ባለአደራ ምክርቤት ነገ ከቦሌ እና ከአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተሞች ነዋሪዎች ጋር #ይወያያል። በውይይቱም የክፍለ ከተሞቹ ባለ አድራ ምክርቤቶች ይዋቀራሉ ተብሏል። ውይይቱ ነገ ከቀኑ 8 ሰዐት በመድን ዲኮር አዳራሽ #ይካሄዳል

@YeneTube @FikerAssefa
አዲስ አበባ የሚያስተዳድራት አካል የሥራ ጊዜውን #የጨረሰ በመሆኑ ባለድርሻ አካላትን ያካተተ #ባለአደራ አስተዳደር እስከ ጠቅላላ ምርጫ ድረስ እንዲቋቋምና ይህም ተግባራዊ እንዲሆን፣ ከሌሎች የዴሞክራሲ ኃይሎች ጋር በጋራ በመሆን እንደሚታገል አንድነት ለፍትሕና ለዴሞክራሲ ፓርቲ (አንድነት) አስታወቀ፡፡
@YeneTube @FikerAssefa
⬆️የአዲስ አበባ #ባለአደራ ምክር ቤት /ባልደራስ/ በዛሬው ዕለት ቅዳሜ መጋቢት 21 #በራስ ሆቴል ጠርቶ የነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ #በፖሊስ ክልከላ ጋዜጠኞች #እንዳይገቡ ተደርጓል፡፡

አጠቃላይ ዝግጅቱን ለማስተጓጎል እየተሞከረ ነው፡፡ ይሁን እንጅ የአዲስ አበባ ባለአደራ ም/ቤት (ባልደራስ ) በሆቴሉ በር ላይ መግለጫ ለመስጠት እየተዘጋጀ ነው፡፡

ምንጭ:- ስንታየሁ ቸኮል - አስተባባሪ
@YeneTube @FikerAssefa