YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#በፖሊስ ቁጥጥር ሥር የዋሉት ጠበቃ #ሔኖክ አክሊሉ እና አቶ #ሚካኤል መላክ ፍርድ ቤት ቀረቡ።

አራዳ በሚገኘው የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የቀረቡት አቶ ሔኖክ እና አቶ ሚካኤል "#የገጠር ሰው አይመራንም በማለት ወጣቶችን አስተባብራችሁ አመጽ ልታነሳሱ ነበር" በሚል መጠርጠራቸውን የሕግ ባለሙያው አቶ ደሙ አስፋው ለ«DW» ተናግረዋል።

አቶ #ሔኖክን ወክለው በፍር ቤቱ ጥብቅና የቆሙት የሕግ ባለሙያ እንደተናገሩት ከፍልስጤም ኤምባሲ ጋር በመተባበር እስራኤልን መመከት የሚል አጋርነት እና ስልጠና ውስጥ ተሳትፈዋል በሚል ጉዳይ ጭምር መጠርጠራቸውን ገልጸዋል።

አቶ ሔኖክ ከዚህ ቀደም በተለያዩ ምክንያቶች ለታሰሩ ሰዎች #ጥብቅና በመቆም ይታወቃሉ።

ጠበቃ ሔኖክ በጸረ-ሽብር ሕግ እና የሰብዓዊ መብት ጉዳዮች ላይ በአዳማ ከተማ በሚደረግ የምክክር መድረክ ይሳተፋሉ ተብሎ #ይጠበቅ ነበር።

ፖሊስ ለምርመራ 15 ቀናት ቢጠይቅም ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን ለጥቅምት 15 ቀጠሮ ሰጥቷል ።
ምንጭ ፦ DW
@yenetube @mycase27