YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#እስካሁን 930 ሺህ 150 የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ ቄያቸው ተመልስዋል፦ኮሚሽኑ

በሀገሪቱ በተፈጠረው ግጭት ምክንያት ከተፈናቀሉ ዜጎች መካከል እስካሁን 930 ሺህ 150 ገደማ ሰዎች ወደ ቄያቸው መመለስ መቻሉን ብሔራዊ የአደጋ ስጋት አመራር #ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

በተለያዮ ጊዜያት በኢትዮጵያ በተፈጠረው ግጭት አያሌ ዜጎች ህይወታቸው አልፏል፡፡ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች ከቄያቸው ተፈናቅለው ለእንግልት #መዳረጋቸው ይታወቃል፡፡

ግጭቶቹም በዋናነት #በኦሮሚያና ሶማሌ ክልል፣ በምዕራብ ጉጂና ጌዲዮ፣ :በኦሮሚያና ቤንሻንጉል ጉሙዝ ባሉ አዋሳኝ አካባቢዎች እንዲሁም በሶማሊያ ክልልና በቡራዮ ከተማ #የተከሰቱ ናቸው፡፡

በእነዚህም ግጭቶች ከተፈናቀሉ ዜጎች መካከል እስካሁን 930 ሺህ 150 ገደማ ሰዎች ወደ ነበሩበት አካባቢ መመለስ መቻሉን በብሔራዊ የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ #ደበበ ዘውዴ በተለይ ለኢቢሲ ተናግረዋል፡፡

ተፈናቃዮቹንም ለመደገፍ መንግስት አስቸኳይ እርዳታ እያደረገ ነው ብለዋል፡፡

በአንዳንድ አካባቢዎች ለተፈናቃይ ዜጎች የሚደረገው የድጋፍ ጥረት የተለያዮ ተግዳሮቶች ቢያጋጥሙም ችግሮቹን ለመፍታት #ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ እንደሆነ ተናግረዋል ዳይሬክተሩ፡፡

መንግስት ህብረተሰቡንና ባለድርሻ አካላትን ባሳተፈ መልኩ ተፈናቃይ ዜጎችን የማቋቋም ስራ እየሰራ እንደሆነም ጠቁመዋል፡፡

ይህም ስራ የሚሰራው ተፈናቃዮቹ ካጋጠማቸው አደጋ የሚያገግሙበት ድጋፍ በመስጠትና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት በመፍጠር መሆኑን አቶ #ደበበ ተናግረዋል፡፡

ተፈናቃይ ዜጎች ወደ ነበሩበት አካባቢ ለመመለስ በሚደረገው ጥረት የሚያነሱትን የፀጥታ ስጋት ለማስወገድ የፀጥታ አካላትንና ባህላዊ የሰላም ማስፈኛ መንገዶችን በመጠቀም እየተሰራ ነው #ብለዋል፡፡

ባለፉት ስድስት ወራት በሀገሪቱ በተከሰተ ግጭት በደረሰ መፈናቀልና በድርቅ 8 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ለጉዳት መዳረጋቸውን ከብሔራዊ የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
ምንጭ ፦ኢቢሲ
@YeneTube @Mycase27