YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ውሃ አሞላል ዙሪያ የተቋቋመው የባለሙያዎች ቡድን ሪፖርት ላይ #የኢትዮጵያ#ሱዳንና #ግብፅ የውሃ ሚኒስትሮች በአዲስ አበባ #እየተወያዩ ነዉ

በውይይቱ ላይ የኢፌዴሪ የውሃ፣ መስኖና ኤሌክትሪክ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ፣ የሱዳን የውሃ ሀብት፣ የኤሌክትሪክና የመስኖ ሚኒስትር ኢንጂነር ከድር ጋስመዲን እና የግብፅ የውሃ ሀብትና የመስኖ ሚኒስትር ዶክተር መሀመድ አብዱላቲ እየተሳተፉ ይገኛሉ።

ከሶስቱ ሀገራት የተውጣጡ ተመራማሪዎችን ያካተተው የባለሙያዎች ቡድን የዛሬ ሶስት ወር አካባቢ ነበር ተቋቁሞ ወደ ስራ የገባው።

እስካሁንም ለአራት ጊዜ በመገናኘት በግድቡ የውሃ አሞላል እና አለቃቀቅ ዙሪያ በመምከር ሪፖርቱን አዘጋጅቷል።

📌በዛሬው እለትም ሚኒስትሮቹ በዚህ የባለሙያዎች ሪፖርት ላይ ነው እየተወያዩ ያሉት
ምንጭ ፦FBC
@yenetube @mycase27