YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#update ጀርመን

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በጀርመን የሚያደርጉትን ይፋዊ የስራ ጉብኝት ጀምረዋል።

ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ በበርሊን በከተፈተውና አፍሪካ ኢኮኖሚ ድጋፍ በማደረግ ላይ የሚያተኩረው ቡድን ሃያ ሃገራት #ኢኒሼቲቭ ኮምፓክት ዊዝ አፍሪካ ስብሰባ በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።

በስብሰባው ላይ ከጠቅላይ ሚኒስትር #ዶክተር አብይ በተጨማሪም የጀርመን መራሄተ መንግስት አንጌላ ሜርክልና የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋቂ መሃመት ጨምሮ ሌሎች የአፍሪካ ሀገራትና መሪዎች እየተሳተፉ ነው።

ኮምፓክት ዊዝ አፍሪካ እንደ አውሮፓ አቆጣጠር በ2017 በጀርመን አነሳሽት የተጀመረ ነው።

ኮምፓክት ዊዝ አፍሪካ መሰረተ ልማትን ጨምሮ የግሉን ዘርፍ ኢንቨስትመንት ለማጠናከርና ለማበረታት የተጀመረ ኢኒሼቲቭ ነው።

የአፍሪካ ሀገራት የኢኮኖሚና የፋይናንስ መዋቅራቸውን ሳቢ በማድረግ የግሉ ዘርፍ በኢንቨስትመንት በስፋት እንዲሰማራ የሚደግፍ መርሃ ግብር ነው።

በዚህም በሀገራቱ የሚገኙ የኢንቨስትመንት ዐድሎችን በስፋት ያስተዋውቃል።
በሀገራቱ የሚወሰዱ የማሻሻያ አጀንዳዎችና የፖሊሲ እርምጃዎችንም ይደግፋል።

ኮምፓክት ዊዝ አፍሪካ የቡድን ሃያ አባል ሀገራትን፣ ለለውጥ ዝግጁ ናቸው፣ የለውጥ አሥተሳሰብን ያራምዳሉ የሚባሉ አፍሪካ ሀገራትንና ዓለም ዓቀፍ አጋሮችን ያሰባሰበ ነው።

እስካሁንም #ኢትዮጵያ#ሩዋንዳ#ግብጽ#ጋና#ሴኔጋልና #ሞሮኮን ጨምሮ አሠራ አንድ የአፍሪካ ሀገራት በዚህ ኢንሼቲቭ ተካተዋል።
©FBC
@YENETUBE @MYCASE27