YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#update አዲስ አበባ
በአዲስ አበባ አንድ የፌደራል ፖሊስ አባል በመጠጥ ሀይል ተገፋፍቶ በፈፀመው ጥቃት የሁለት #ባልደረቦቹን ህይወት አጠፋ
:
በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ በተለምዶ #ወሎ ሰፈር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ አንድ የፌደራል ፖሊስ አባል #በመጠጥ ሀይል ተገፋፍቶ በባልደረቦቹ ላይ ጥቃት መፈፀሙ ተነግሯል።

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል ዘይኑ ጀማል ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፥ የፌደራል ፖሊስ አባሉ በባልደረቦቹ ላይ በፈፀመው ጥቃትም ሁለት የፌደራል ፖሊስ አባላት #ህይወት አልፏል።

ፖሊስ ጥቃቱን ለማስቆም በወሰደው እርምጃም ጥቃቱን የፈፀመው የፌደራል ፖሊስ አባል ህይወቱ ማለፉን ኮሚሽነር #ጀነራል ዘይኑ ጀማል አስታውቀዋል።

በአሁኑ ወቅም በስፍራው ተስተጓጉሎ የነበረው የትራፊክ እና ሌሎች እንቅስቃሴዎች ወደ መደበኛ ሁኔታቸው መመለሳቸውን #ገልፀዋል
ምንጭ ፦ኤፍ ቢ ሲ
@yenetube @mycase27
የጤና ባለሙያዎች በሀገር አቀፍ ደረጃ ከፊል የስራ ማቆም አድማ መጀመራቸውን ተከትሎ ዛቻና ማስፈራሪያ እየደረሰባቸው መሆኑን ገለፁ

በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ የጤና ባለሙያዎች ዛሬ ማክሰኞ ግንቦት 5 ቀን 2017 ዓ.ም. በመላ ሀገሪቱ የተጀመረውን የከፊል የስራ ማቆም አድማ ለማካሄድ ሲሞክሩ ከመንግሥት አካላት ማስፈራሪያና ጫና እንደደረሰባቸው አስታወቁ።

#በኦሮሚያ ክልል ባሌ ዞን ሮቤ ከተማ በሚገኘው የማዳ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ጎባ ሪፈራል ሆስፒታል የህክምና የሰራተኛ የሆኑ አንድ ግለሰብ ለአዲስ ስታንዳርድ እንደገለጹት የጤና ባለሙያዎች አድማውን ለማድረግ ሲሞክሩ ከአካባቢው ባለስልጣናት ጫና እንደገጠማቸው አስረድተዋል።

ባለሙያው "ማስፈራሪያ እየደረሰብን ነው" ያሉ ሲሆን፤ ሆስፒታሉ ከማለዳ ጀምሮ "በመንግስት የስራ ሀላፊዎች የተሞላ" እንደነበር ጨምረው ተናግረዋል።

ሌላኛው በአማራ ክልል ደቡብ #ወሎ ዞን በአቀስታ ከተማ የአቀስታ አጠቃላይ ሆስፒታል የሚሰሩ አንድ የጤና ባለሙያ በበኩላቸው በድንገተኛ ክፍል የተመደበ አንድ ሀኪም "በፀጥታ ሀይሎች" ተይዞ የተለመደውን የህሙማን ህክምና አገልግሎት እንዲሰጥ አልያም "ወደ እስር ቤት እንዲሄድ" እንደተነገረው ለአዲስ ስታንዳርድ ገልጸዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ በዛሬው ዕለት ተጠርቷል የተባለውን የህክምና ባለሙያዎች አድማ ለመታዘብ በሶስት ዋና ዋና የመንግስት ሆስፒታሎች ማለትም በዳግማዊ #ምኒልክ ሪፈራል ሆስፒታል፣ #በዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል እና #በየካቲት12 ሜዲካል ኮሌጅ ሆስፒታል ቅኝት ያደረግን ሲሆን በእነዚሁ ተቋማት ከሰዓት በኋላ ስራ የተጀመረ ይሁን እንጂ ጠዋት ላይ የከፊል የስራ ማቆም መካሄዱን ታዝበናል።

የአዲስ ስታንዳርድ ዘገባ ይመልከቱ

https://addisstandard.com/Amharic/?p=7748
👍40🔥5👀32😭2