YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ይድረስ ለኢትዮ- ቴሌኮም #ሀዋሳ:-

ጉዳዩ:- በአከባቢያችን የሞባያል የኢንተርኔት አገልግሎት በአግባቡ አለመስራትን ይመለከታል

ከላይ ርዕሱ ላይ ለመጥቀስ እንደተሞከረው በአከባቢያችን #በሀዋሳ ከተማ #ሒጠታ ቀበሌ ከሀዋሳ ቪው ሆቴል ጀርባ ወይንም ከአጠና ተራ ጀርባ ባለው አከባቢ የሞባይል ኢንተርኔት አገልግሎት ፍፁም ይሰራል ማለት እንደማይቻል ልናሳውቃችሁ እንወዳለን።

ረጅም ጊዜን (2-3(ዐመት)) እንዳስቆጠረ የሚነገርለት ይህ ችግር ለአከባቢያችን ቴሌኮም ብናመለክትም የሀዋሳ ሪጅን ቴሌኮም ችላ ማለት መምረጡን ጉዳዩን ያስረዱ የአከባቢው ነዋሪዎች ገልፀዋል።

እንዲሁም ኢትዮ-ቴሌኮም ምላሽ እንዲሰጣቸው የየኔቲዩብ ያናገራቸው የአከባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል።
@YeneTube @FikerAssefa