YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
አቶ #ሚሊዮን ዛሬ በ|#ሀዋሳ ከተማ ከወጣቶች ጋር በተወያዩበት ወቅት ነው።


"ለሚቀጥሉት 10 አመታት የሀዋሳን ከተማ እንዲያገለግል ታስቦ የተዘጋጀው መሪ እቅድ (Master Plan) በከተማው ዙሪያ በሚኖሩ አርሶ አደሮች ጥያቄ መሰረት ለጊዜው እንዲቆም መደረጉን የደቡብ ክልል ፕሬዝደንት አቶ ሚሊዮን ማቲዮስ ተናገሩ"

©zeki
@YeneTube @Fikerassefa
#ሀዋሳ_ከተማ ⤵️

በደቡብ ክልል ሐዋሳ ከተማ ሰዋች ባልታወቁ አካላት መሽት ተገለው እየተገኙ መሆኑን የከተማዋ ነዋሪዎች ገለፁ።

በደቡብ ክልል ሐዋሳ ከተማ ሰዋች ባልታወቁ አካላት መሽት ተገለው እየተገኙ መሆኑን የከተማዋ ነዋሪዎች ገለፁ።

የከተማዋ ፖሊስ ሁለት ሰዎች ተገለው መገኘታቸውን ገልፆ፣ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራ እያካሄደ መሆኑን ተናግሯል።

©VOA
@YeneTube @Fikerassefa
#​የኢህአዴግ ሊቀ መንበር ዶ/ር አብይ አህመድ ለድርጅታዊ ጉባዔው #ሀዋሳ ከተማ ገቡ

የኢህአዴግ ሊቀ መንበርና የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በ11ኛው የኢህአዴግ ድርጅታዊ ጉባዔ ላይ ለተሳተፍ ሀዋሳ ከተማ ገብተዋል።

11ኛው የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) ድርጅታዊ ጉባዔ “ሀገራዊ አንድነት ለሁለንተናዊ ብልፅግና” በሚል መሪ ቃል #ከነገ ጀምሮ በሀዋሳ ከተማ ይካሄዳል።

በድርጅታዊ ጉባዔው ላይ ለመሳተፍም የኢህአዴግ ሊቀ መንበርና የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በዛሬው እለት ሀዋሳ ከተማ ገብተዋል።

በተጨማሪም የኢህአዴግ ምክትል ሊቀ መንበርና የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ደመቀ መኮንን ድርጅታዊ ጉባዔው ላይ ለመሳተፍ ሀዋሳ ደርሰዋል።

እንዲሁም የኢህአዴግ ድርጅታዊ ጉባኤ ተሳታፊዎችም ሃዋሳ ከተማ መድረሳቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ልዩ ሀላፊ አቶ ፍፁም አረጋ አስታውቀዋል።

11ኛው የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) 11ኛ ድርጅታዊ ጉባዔ ነገ ጠዋት ላይ በሀዋሳ ከተማ እንደሚጀምር ይጠበቃል።
©fbc
@yenetube @mycase27
#ሀዋሳ ከተማ ላለፉት 11 ቀን ተቋርጦ የነበረው የሞባይል ኢንተርኔት እና ባለገመድ ኢንተርኔት አገልግሎት #መጀመሩን የኔቲዩብ ቤተሰቦች ተናግረዋል።
@Yenetube @FikerAssefa
#ኢሬቻ2012 በውቢቷ #ሀዋሳ ከተማ ዛሬ ተከብሯል።

ከተለያዩ ኦሮምያ ክልል የመጡ ቄሮች እና አባገዳዎች ከሲዳማ ህዝብ ጋር ኢሬቻን በሀዋሳ ሲዳማ ባህል አደራሽ አክብረዋል።

@YeneTube @Fikerassefa
#ሀዋሳ_ኮሮና_ቫይረስ_ዝግጅት_ሲፈተሽ

በሀዋሳ ከተማ አንድ በኮሮና ቫይረስ የተጠቃ ግለሰብ አለ ተብሎ በተለይም ዋርካ አከባቢ ከፍተኛ መሸበረ እንዲሁም ግለሰብን የማግለል ሁኔታዎች ነበሩ በቦታው ተገኝተን ለመታዘብ የቻልነው እናካፍሎ።

( በፁሁፋችን መሀል ታማሚው - ኮሮና ቫይረስ ባይሆንም ግለሰብ ታሞ ስለ ነበር ታማሚ በሚል ተጠቅመናል )

ታማሚው ወደ 2:30 ሀዋሳ ዋርካ ሆቴል ወረድ ብሎ ባለ እንግዳ ማረፊያ ጋር ተጠግቶ ህመሙን ለአንድ ግለሰብ ያጋራዋል ከዚያ ያጋራው ግለሰብ #ከፍተኛ_የሳል : #አይን_መቅላት እንዲሁም #መተታጠፊያዬ ያመኛል ብሎ እንዳስረዳው በቀጥታ አቅራቢያው ወዳለ ጤና ጣቢያ ለመጦቀም አመራ ከዚያ የጤና ጣቢያው ባለሙያዎች በጉዳዩ ላይ እያፌዙ እንመጣለን ወይንም 6929 ደውል በማለት ልጁ ተመልሷል።

ታማሚው ልጅ ሳሉ በርትቶበታል ሰውም በቦታው ተስብስቧል ነገር ግን የጤና ጣቢያው ባለሙያዎች ቦታው ላይ አምቡላንስ የዘው ለመምጣት 3 ሰዐታት ፋጅቶባቸዋል።

ባለሙያዎች በአምቡላንስ መጡ የታማሚውን ሙቀት የለኩት በከፍተኛ ፍራቻ ነበር ( ይህ ስልጠና እንደሚጎላቸው ቦታው ላይ ተገኝተን ተመልክተናል) እንዲሁም ታማሚውን በአግባቡ አላስተናገዱትም ነበር።

ታማሚው የተቀመጠበት የነካቸውን ቦታዎች infected ሆነዋል ተብለው የሚገመቱ ቦታዎችን Disinfect ለማድረግ ከቀኑ 10:00 ላይ መተው ነው ርጭት ያደረጉት።

#ሀዋሳ_ከተማ_አስተዳደር_ዝግጅታችሁ_እንደገና_ፈትሹ

ፎቶ:- በቫይረሱ ተጠቅቶ ሊሆን ይችላል በሚል ቦታ ከቫይረሱ እያፅዱ
@Yenetube @Fikerassefa