#በኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ዓለም አቀፍ በረራዎችን ለማደናቀፍ የሞከሩና የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪ ባለሙያዎችን የስራ ማቆም አድማን ሲያስተባብሩ እና ሲመሩ ነበር ተብለው የተጠረጠሩ 9 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ።
የፌደራል ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ጄነራል ተኮላ አይፎክሩ ለፋና ብሮድካስቲነግ ኮርፖሬት እንዳስታወቁት፥ ግለሰቦቹ የበረራ ሂደቱን ለማስተጓጎል በተለይም ከውጭ ሀገራት የሚመጡ አውሮፕላኖች እንዳያርፉ ጥረት ሲያደርጉ ነበር።
እንዲሁም በኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪ ሰራተኞቹ ዘንድ ሲደረግ የቆየውን የስራ ማቆም አድማ አስተባብረዋል እንዲሁም መርተዋል ተብለው ተጠርጥረው ነው በቁጥጥር ስር የዋሉት።
ምክትል ኮሚሽነር ጄነራል ተኮላ፥ ግለሰቦቹ በፍርድ ቤት መያዣ ወጥቶባቸው በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን፥ በአሁኑ ወቅትም ምርመራ እየተደረገባቸው ይገኛል ብለዋል።
©fbc
@yenetube @mycase27

#በኢትዮጵያ እና ኤርትራ ድንበር ላይ የሰፈረው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከዛሬ ጀምሮ ወደ #ጦር ሰፈሩ መሰብሰብ እንደሚጀምር ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አስታወቁ።
በሁለቱ ሀገራት ድንበር አካባቢ ያለው ውጥረት የተሞላበት የጦርነት ስሜት ከአሁን በኋላ “በከፍተኛ ሁኔታ” #እንደሚቀንስም ተናግረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ይህን የተናገሩት የኢትዮጵያን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በቡሬ እና በዛላምበሳ ግንባሮች ያሉ የኢትዮጵያ እና የኤርትራ የመከላከያ ሰራዊት አባላትን ጎብኝተው ከተመለሱ በኋላ በቦሌ አየር ማረፊያ በሰጡት መግለጫ ነው።
“የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከዛሬ ጀምሮ ድንበር አካባቢ ላይ #ውጥረት የነበረውን #የጦርነት ስሜት በከፍተኛ ደረጃ ቀንሶ ወደ ካምፕ በመሰብሰብ የሚያገግምበት፣ የሚሰለጥንበት፣ ራሱን የሚያበቃበት ሁኔታ ይፈጠራል” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ።
ምንጭ፦ Dw

#በኢትዮጵያ ሲቪል አቬዬሽን ባለስልጣን በስራ ማቆም አድማ የተጠረጠሩት 9 ግለሰቦች በኢትዮጵያ አየር መንገድ ላይ ከ70 ሚሊየን 944 ሺህ ብር በላይ ከሲራ ማድረሳቸውን መርማሪ ፓሊስ አስታወቀ።
መርማሪ ፓሊስ ቀሩኝ ያላቸውን ቀሪ የምርመራ ስራዎችን ለማጠናቀቅ የ14 ቀን ጊዜ እንዲሰጠው ጠይቋል።
📌የሁለቱን ክርክር የተመለከተው ፍርድ ቤቱ የተጠርጣሪዎችን የዋስትና ጥያቄ ውድቅ በማድረግ ለፓሊስ ለተጨማሪ ምርመራ የሰባት ቀን ጊዜ በመስጠት ለመስከረም 15 ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል።
©fbc
@yenetube @mycase27
መርማሪ ፓሊስ ቀሩኝ ያላቸውን ቀሪ የምርመራ ስራዎችን ለማጠናቀቅ የ14 ቀን ጊዜ እንዲሰጠው ጠይቋል።
📌የሁለቱን ክርክር የተመለከተው ፍርድ ቤቱ የተጠርጣሪዎችን የዋስትና ጥያቄ ውድቅ በማድረግ ለፓሊስ ለተጨማሪ ምርመራ የሰባት ቀን ጊዜ በመስጠት ለመስከረም 15 ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል።
©fbc
@yenetube @mycase27
⬆️የክቡር ዶ/ር አርቲስት #ጥላሁን_ገሰሰ 78 ኛ ዓመት #የልደት ቀን መታሰቢያ ዝግጅት ዛሬ #በኢትዮጵያ_ብሔራዊ ቲያትር በደመቀ መልኩ እየተከበረ ይገኛል።
የዘንድሮው የልደት መታሰብያ ከቀድሞዎቹ ሁሉ በተለየ መልኩ የደመቀ ነው።
©ሱራፌል
@YeneTube @Fikerassefa

ካሌብ በህይወት እያለ አንድ ቀን እኔ ከሞትኩ ኢትዮጵያ ወስዳችሁ #ቅበሩኝ #በኢትዮጵያ መሬት መቀበር ነው የምፈልገው እያለ ብዙ ጊዜ ሲናገር ስለነበረ ቀብሩ ከነገ ወዲያ ሰኞ እለት የካቲት 23, 2012 ከቀኑ 8:30 በአዲስ አበባ ጉለሌ በጴጥሮስ ወ ጳውሎስ ይፈፀማል ውድ ኢትዮጵያውያን በቦታው ተገኝታችሁ ወንድማችን ካሌብን በክብር ትሽኙ ዘንድ ትጠየቃላችሁ።
ይህንን መልክት ላልሰሙ አስሙልን ብለውናል
#Share
@YeneTube @Fikerassefa
ይህንን መልክት ላልሰሙ አስሙልን ብለውናል
#Share
@YeneTube @Fikerassefa
በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ #ሆስፒታል የጤና ባለሙያዎች የተሻለ ደመወዝን ጨምሮ ሌሎች ጥያቄዎቻቸው ምላሽ እንዲያገኙ የሚጠይቅ ሰልፍ አካሄዱ
#በኢትዮጵያ ውስጥ ካሉት የመንግስት የህክምና ማዕከላት መካከል አንዱ በሆነው በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የሚሰሩ የጤና ባለሙያዎች በመላ ሀገሪቱ ያሉ የጤና ባለሙያተኞች የተሻለ ደመወዝ፣ ጥቅማጥቅሞች እና የስራ ሁኔታዎችን በመጠየቅ ነገ ማክሰኞ ግንቦት 5 ቀን 2017 ዓ.ም ሊያደርጉት ባቀዱት ሀገር አቀፍ የስራ ማቆም አድማ ዋዜማ ዛሬ ሰኞ ማለዳ ላይ ቅድመ የስራ ማቆም አድማ ሰልፍ አካሄዱ።
በሆስፒታሉ ቅጥር ግቢ ውስጥ በተካሄደው በዚህ ሰልፍ ላይ የታደሙት የጤና ባለሙያዎቹ "ጤናማ ዜጎች ጠንካራ ኢኮኖሚ ይገነባሉ!": "ህይወትን እናድናለን የቤት ኪራያችንን ግን መክፈል አልቻልንም" እና "የጤና ሰራተኞች ትንኮሳ ያቁሙ ጥበቃ ይገባናል" የሚሉና ሌሎች መልዕክቶችን ይዘው ታይተዋል።
በሳምንቱ መጨረሻ ላይ ደግሞ በአማራ ክልል በደብረ ታቦር፣ ደብረ ማርቆስ፣ ባህር ዳር ጥበበ ግዮን ሆስፒታል እና ፍለገ ሕይወት ሪፈራል ሆስፒታልን ጨምሮ በተለያዩ ተቋማት የሚሰሩ የጤና ባለሙያዎች ከሀገር አቀፍ ንቅናቄው ጎን በመሆን ሰላማዊ ሰልፍ አካሄደዋል።
@Yenetube @Fikerassefa

👍94❤10😭3
ዜና: "#በኢትዮጵያ የሚገኙ አንዳንድ መገናኛ ብዙሃን ብሔራዊ ጥቅምን ማስቀደም ሲገባቸው የግል ፍላጎታቸውን ለማሳከት የሚሰሩ ናቸው" - ጠ/ሚኒስትር አብይ
"በኢትዮጵያ የሚገኙ አንዳንድ መገናኛ ብዙሃን የግል ፍላጎታቸውን ለማሳከት” የሚሰሩ ናቸው ሲሉ ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ ተቹ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባሳለፍነው ሳምንት በበርካታ የሀገሪቱ የመንግስት መገናኛ ብዙኃን በአራት ክፍል በተላለፈው ቃለምልልሳቸው በመጨረሻው ክፍል ላይ የመገናኛ ብዙሃን ነጻነትን አስመልክተው ገለጻ አድርገዋል፡፡
አንዳንድ መገናኛ ብዙሃን የግል ፍላጎታቸውን ለማሳካት ነው የሚሰሩት ሲሉ የተቹት ጠ/ሚኒስትሩ "እነዚህ መገናኛ ብዙሃን የሃሰት መረጃዎችን እና የፈጠራ ዜናዎችን በማሰራጨት ሕዝቡን ለማሳሳት ሲሞክሩ ተስተውለዋል” ብለዋል።
በገለጻቸውም "ሚዲያ ልክ እንደ እሳት ነው፤ ያጠፋልም ያለማልም፤ እንደቢላዋ ለጥሩ አሊያም ለመጥፎ ነገር ሊውል የሚችል ነው" ብለዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ "በዓለም ላይ ገለልተኛ የሚባል ሚዲያ የለም" ሲሉ ተደምጠዋል፣ “መገናኛ ብዙሃን ብሔራዊ ጥቅምን ያስቀደመ ዘገባ ሊሰሩ ይገባል” ሲሉም አሳስበዋል።
መገናኛ ብዙሃንን ለመልካም አላማ ከተጠቀምናቸው ውጤታቸው ከፍተኛ መሆኑን ገልጸው፥ በተቃራኒው ሚዲያዎች ለጥፋት አላማ የሚውሉ ከሆነ ከፍተኛ አደጋን ያስከትላሉ ሲሉም ገልጸዋል።
በተጨማሪም "የለውጡ መንግስት ለመገናኛ ብዙሃን በሰጠው ነጻነት በኢትዮጵያ በርካታ አዳዲስ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ከ60 በላይ በሚሆኑ ቋንቋዎች እየተላለፉ ይገኛል" ብለዋል፡፡

👎36❤23👍8😁7🔥2