YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.86K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ከ|#ኦሮሚያ ክልል ፣ ቡሌሆራ አካበቢ ተፈናቅለው በመጠልያ ጣቢያ የሚኖሩ የቡርጂ ብሔረሰብ አባላት መንግስት ትኩረት እንዲሰጣቸው ብበሰልፍ ጠየቁ።
@YeneTube @Fikerassefa
#ኦሮሚያ_ክልል

በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ህገ ወጥ ድርጊቶች ተሳትፈዋል በሚል የተጠረጠሩ ከ500 በላይ ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የክልሉ አስተዳደርና ፀጥታ ቢሮ አስታወቀ።

በቁጥጥር ስር ከዋሉት መካከል:-
⊙ በጉጂ ዞን በቄሮ ስም መሬት ወረራ የፈጸሙ እና ያስፈጸሙ፣ ህገ ወጥ ኬላ በማቋቋም የትራንስፖርት እንቅስቃሴን ያስተጓጎሉ፣ መንግስት የሚሰጠውን ስልጣን ሁሉ በቄሮ መረጋገጥ አለበት በሚል ያነሳሱ ሰዎች።

⊙ በባሌ ዞን የእርሻ ኢንቨስትመንት ያደናቀፉ።

⊙ በቡኖ በደሌ ዞን በአካባቢው የሚኖሩ የሌላ ብሄር ተወላጆችን የቡና እና የጫት ምርቶች የመነጠሩ።

⊙ በጂማ ዞን የሰዎችን ቡና በመመንጠር ብሎም ቡዳ ነው በሚል ሰው የገገደሉ እና ያስገደሉ ይገኙበታል።
©FBC
@Yenetube @Fikerassefa
"ለአጋቾቹ የምንከፍለው ገንዘብ ስለሌለን በየገበያው እና በየመንደሩ እየለመንን ነው የምንገኘው" -የታጋቾች ቤተሰቦች

ከሁለት ሳምንት በፊት በ #ኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በገርበ ጉራቻ ከተማ አቅራቢያ በታጣቂዎች ታግተው የሚገኙ ተማሪዎችን ለማስለቀቅ፤ አጋቾቹ የጠየቁትን ገንዘብ ለመክፍል የድጋፍ ደብዳቤ በማጻፍ በልመና ላይ እንደሚገኙ የታጋቾች ቤተሰቦች ገለጹ።

አዲስ ስታንዳርድ ያነጋገራቸው የታጋቾች ቤተሰቦች እንደገለፁት ከሆነ የተጠየቁትን ክፍያ ከፍለው የተለቀቁ ተማሪዎች ቢኖሩም ገንዘቡን መክፈል ያልቻሉ ግን እስከአሁን ድረስ በታጣቂዎች ተይዘው እንደሚገኙ አስታውቀዋል::

“እህቴን ትላንትም ዛሬ ጠዋትም አውርቻታለሁ:: ታስራ ነው ያለችው::ከእሷ ጋራ የነበሩ 4 የሚሆኑ ሰዎች የተጠየቁትን እስከ አንድ ሚሊየን የሚደርስ ገንዘብ ከፍለው ወጥተዋል:: እኛ የምንከፍለው ስለሌለን ከወረዳው የድጋፍ ደብዳቤ አጽፈን በየገበያው እና በየመንደሩ እየለመንን ነው የምንገኘው” ሲሉ ለደህንነታቸው ሲባል ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ አንድ የታጋች እህት ገልጸዋል።

“ገንዘቡ የሚሞላልን ከሆነ አጋቾቹ የሚያዘጋጁት ሰው አለ::ለእሱ ሄደን እናስረክባለን::ከዛ ልጅቷን ወደ እኛ ያመጣሉ::ይህን እንድናደርግ ነው አጋቾቹ መመሪያ የሰጡን::” ሲሉ አክለው ገልፀዋል::

Via Addis Standard
@YeneTube @FikerAssefa
😭58👍226
ገርበ ጉራቻ አካባቢ ከታገቱት ተማሪዎች ውስጥ 16ቱ ተለቀቁ፤ በታጋቾች ላይ ጾታዊ ጥቃትና ድብደባ ተፈጽሟል ተብሏል‼️
#ኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን #ገርበ_ጉራቻ አካባቢ በታጣቂዎች ከታገቱ ከ167 በላይ የደባርቅ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች መካከል ባለፉት ቀናት 16ቱ በመቶ ሺዎች የሚቆጠር የማስለቀቂያ ገንዘብ ከፍለው መለቀቃቸው ተገለጸ።

በታጋቾቹ ላይ ግርፋት፣ ድብደባ እንዲሁም ጾታዊ ጥቃት መፈጸሙን የተማሪዎቹን እገታ ከቤተሰብ ጋር ሆነው በቅርበት እየተከታተሉ ያሉ ምንጮች ለቢቢሲ ገልጸዋል። 

አንድ የታጋች ተማሪ ቤተሰብ “ታጣቂዎቹ በተማሪዎቹ ፊት ሁለት ሰዎችን መግደላቸውን እያለቀሱ ነግረውናል” ብለዋል።

ከ30 በላይ ይሆናሉ የተባሉት ታጣቂዎቹ ‘ፀጉራቸውን የተሰሩ፣ የሲቪል ልብስ የለበሱ እና የተማሩ’ መሆናቸውን ተማሪዎቹ አመልክተዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
😭42👍19
#ኦሮሚያ ክልል ባለው ግጭት ምክንያት የወባ በሽታ እየተባባሰ መሆኑና የጤና አገልግሎቶች መስተጓጓላቸው ተዘገበ

ለማ ተፈራ የተባሉ የምዕራብ ኦሮሚያ አርሶ አደር በአንድ ወር ውስጥ አራት ልጆቻቸውን በወባ በሽታ በሞት መነጠቃቸውን ገልጸው እየተካሄደ ያለው ግጭት ባይኖር ኖሮ አደጋውን መከላከል ይቻላል ብለው እንደሚያምኑ ለፈረንሳይ የዜና ወኪል ኤኤፍፒ ተናግረዋል።

አርሶ አደሩ "በግጭት ምክንያት መንደራችን ውስጥ የወባ መድሃኒት እና ህክምና እንዳልነበርም" ገልጸዋል።

#ኦሮሞ ነፃነት ሠራዊትና በመንግስት ኃይሎች መካከል በመካሄደ ላይ የሚገኘው ግጭት የጤና አገልግሎቶችን ማቋረጡን በመቀጠሉ ቀውሱ እየተባባሰ መምጣቱን የጤና ባለሙያዎች አስጠንቅቀዋል።

የኦሮሚያ ሀኪሞች ማህበር ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር የሆኑት ገመቹ ቢፍቱ "በክልሉ ባለው የትጥቅ ግጭት ምክንያት የተዘጋጀ ጸረ-ወባ መድሃኒት አቅርቦት ተስተጓጉሏል" ብለዋል።

በአካባቢው የሚገኙ ሐኪሞች ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ በበሽታው የሚያዙ ሰዎች ቁጥር መጨመሩን ሪፖርት አድርገዋል። በምዕራብ ወለጋ የሚገኘው የነጆ አጠቃላይ ሆስፒታል ዳይሬክተር ለገሰ ቡልቻ "ከዚህ ቀደም ካለው በተለየ መልኩ አሁንም በድርቅ ወቅት በርካታ ሰዎች በወባ እየተያዙ ነው" ብለዋል። ዳይሬክተሩ በፈረንጆቹ 2023-2024 በሆስፒታሉ ከታከሙ 26,000 ታካሚዎች ውስጥ 70% የሚሆኑት በወባ በሽታ የተያዙ ናቸው ነው ያሉት።

በተጨማሪም የአየር ንብረት ለውጥ በሽታው ወደ አዳዲስ አካባቢዎች እንዲሰራጭ ሁኔታዎችን በመፍጠር ቀውሱን እያባባሰው ነው ሲሉም ተናግረዋል።

Via AS
@Yenetube @Fikerassefa
👍23😭92