በአዲስ አበባ የሠራተኞችን የትምህርት ማስረጃ ትክክለኛነት የማጣራት ሥራ በአዲስ መልክ ሊጀመር ነው!
በ2016 በጀት ዓመት የሠራተኞችን የትምህርት ማስረጃ ትክክለኛነት የማጣራት ሥራ በአዲስ መልክ እንደሚጀምር የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ አስታወቀ።
በአዲስ አበባ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ የሰው ሀብት ክትትል፣ ድጋፍና ኦዲት ዳይሬክተር አቶ መላኩ ተመስገን ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት፤ ቢሮው የከተማውን አጠቃላይ የሰው ሀብት አስተዳደር ሥርዓት በአደረጃጀት፣ በአሠራር እና በሥራ ስምሪት በበላይነት ይመራል። ከዚህ መነሻነት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር
ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ በ2016 በጀት ዓመት የሠራተኞች የትምህርት ማስረጃን ትክክለኛነት የማረጋገጥ ሥራ በአዲስ መልክ ይጀምራል፡፡
የኢፌዴሪ ትምህርት፣ ሥልጠና ቁጥጥር ባለሥልጣን ማዕከላዊ የሆነ የትምህርት ማስረጃ የማጣሪያ ሥርዓት ማዘጋጀቱ ፍተሻውን ቀላል ያደርገዋል ያሉት አቶ መላኩ፤ ቢሮው በ2016 በጀት ዓመት የሠራተኞችን የትምህርት ማስረጃ ትክክለኛነት የማጣራት ሥራ በአዲስ መልክ እንደሚጀምር ገልጸዋል።
ከ2010 እስከ 2013 ዓ.ም መጀመሪያዎቹ ድረስ ሕገወጥ የትምህርት ማስረጃ ፍተሻ ሲያከናውን መቆየቱን ገልጸው፤ በወቅቱ የትምህርት ማስረጃዎችን ለማጣራት በርካታ ተግዳሮቶች በማጋጠሙ የማጣራት ሥራው ተቋርጦ ቆይቷል። አሁን ባለሥልጣኑ የተመረቁ ተማሪዎችን መረጃ የማጣራት አቅም ያለው በመሆኑ አሠራሩን ያቀለዋል ብለዋል።
ቢሮው ከዚህ በፊት ሲሠራቸው የነበሩ የመረጃ ማጣራት ሥራዎችን በተሞክሮ መልክ በመውሰድ በ2016 በጀት ዓመት በመጀመሪያ ዲግሪ እና ከዚያ በላይ የተመረቁ ሠራተኞችን የትምህርት ማስረጃ የማጣራት ሥራ ይጀምራል። ለዚህም የተለያዩ ዝግጅት ሥራዎች እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል።
እንደ ዳይሬክተሩ ገለፃ፤ ሕገ ወጥ የትምህርት ማስረጃ መያዝ ተጠያቂነቱ ከባድ ከመሆኑ ባለፈ ወንጀል ነው። ከ2010 እስከ 2013 ዓ.ም ድረስ በነበረ የትምህርት ማስረጃ ፍተሻ ከ626 ተቋማት 450 የሚደርሱ ሕገወጥ የትምህርት ማስረጃዎች በአመራሩ እና በሠራተኛው ላይ ተገኝቷል።
የፍተሻ ሥራው የሚከናወነው የመንግሥት ሥራዎች ተቀላጥፈው እንዲሠሩ እና ኅብረተሰቡ የሚፈልገውን አገልግሎት በፍጥነት እንዲያገኙ እንዲሁም የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት ነው ያሉት ዳይሬክተሩ፤ ፍተሻው በኮሚቴ ተዋቅሮ ከፖሊስ ኮሚሽን ጋር በጥምረት የሚሠራ ነው ብለዋል።
[EPA]
@YeneTube @FikerAssefa

በኢትዮጵያ ለመኸር ወቅት ከታረሰው መሬት አብዛኛው በዘር እንዳልተሸፈነ ተመድ አስታወቀ!
በኢትዮጵያ የመኸር ወቅት አምራች በኾኑ አካባቢዎች፣ በዘንድሮው ወርኀ ክረምት፣ ማሳዎች ታርሰው ለዝሪት ዝግጁ ቢኾኑም፣ አብዛኞቹ በዘር እንዳልተሸፈኑ፣ የተባበሩት መንግሥት ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ(OCHA) ሪፖርት አስታወቀ፡፡ቢሮው፣ ትላንት ባወጣው ሪፖርት፣ በኢትዮጵያ የወርኀ ክረምት የመኸር ወቅት አብቃይ የኾኑ አካባቢዎች፣ ማሳቸውን አርሰው እና አለስልሰው ቢያዘጋጁም፣ በዘር የተሸፈነ መሬታቸው አነስተኛ እንደኾነ አስታወቀ።
በአገሪቱ የመኸር ወቅት አምራች አካባቢዎች፣ መታረስ ካለበት መሬት፣ እስከ አሁን 80 በመቶው ታርሶ ለዝሪት ቢዘጋጅም፣ በዘር የተሸፈነው መሬት አነስተኛ እንደኾነ፣ ኦቻ፣ የግብርና ክላስተርን መረጃ ዋቢ በማድረግ ገልጿል፡፡በዘር በተሸፈነው መሬት መጠን፣ በክልሎች መካከል ልዩነት እንዳለ የጠቆመው ኦቻ፣ ለአብነትም በዐማራ ክልል 50 በመቶ፣ በኦሮሚያ ክልል 80 በመቶ፣ በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል 48 በመቶ፣ በደቡብ ክልል 50 በመቶ እና በትግራይ ክልል ደግሞ 30 በመቶው፣ የታረሰ መሬት እንደተዘራበት አመልክቷል፡፡
በአሁኑ ወቅት፣ ከ20 ሚሊዮን በላይ የሚኾነው የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ የምግብ ድጋፍ እንደሚሻ የገለጸው ኦቻ፣ ቀጣዩ የምርት ኹኔታ በርዳታ ጠባቂው ሕዝብ ቁጥር ላይ ወሳኝ ሚና እንደሚኖረው ጠቁሟል፡፡የዘር ወቅት እያለፈ ባለበት በአሁኑ ወቅት፣ ሰፊ የእርሻ መሬት ላለመሸፈኑ፣ ተፈጥሯዊ እና ሰው ሠራሽ የኾኑ ልዩ ልዩ ምክንያቶች፣ በኦቻ ሪፖርት ውስጥ ተዘርዝረዋል፡፡ ከእነዚህም መካከል፡- በኦሮሚያ እና በዐማራ አንዳንድ አካባቢዎች የተስፋፋው የጸጥታ ችግር እና የግብአት አቅርቦቶች መቀነስ፣ እንዲሁም እንደ ደቡብ፣ ኦሮሚያ እና ሶማሌ ክልሎች ባሉ አንዳንድ አካባቢዎች ደግሞ፣ የጎርፍ መከሠት የመሳሰሉት ይገኙበታል፡፡
ከመኸር ወቅት የግብርና ሥራ ጋራ በተያያዘ፣ በርካታ ችግሮች ካሉባቸው ክልሎች አንዱ የኾነው የትግራይ ክልል የግብርና እና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ የሰብል ልማት ዲሬክተር አቶ ሰሎሞን ገብረ ሥላሴ በሰጡን አስተያየት፣ ከአፈር ማዳበሪያ ግብአት መሟላት አንጻር፣ በተለይ ከዘር በፊት የሚያስፈልገው የማዳበሪያ ዐይነት ከተጠየቀው በእጅጉ ያነሰ መቅረቡን ገልፀዋል፡፡
በጉዳዩ ላይ፣ ከግብርና ሚኒስቴር ሓላፊዎች አስተያየት ለማግኘት ያደረግነው ተደጋጋሚ ሙከራ ሊሳካልን አልቻለም፡፡ ኾኖም፣ በቅርቡ፣ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለተነሡ ጥያቄዎች ማብራሪያ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ በዘንድሮው የመኸር ወቅት ከፍተኛ ምርት እንደሚጠበቅ ተናግረዋል፡፡ ባለፈው ክረምት ከታረሰው የመሬት መጠን፣ በሁለት ሚሊዮን ሄክታር የሚበልጥ ማለትም 15 ሚሊዮን ሄክታር መሬት፣ ዘንድሮ እንደሚታረስ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማብራሪያቸው አመልክተዋል፡፡
በመላ አገሪቱ የሚታየው የአፈር ማዳበሪያ አቅርቦት እጥረት ያጋጠመው፣ በሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት ምክንያት፣ ለዓለም አቀፍ ግብይት ክፍያ የሚፈጸምበት የኤልሲ ሒደት በጊዜ ባለመጠናቀቁ እንደኾነ ያስረዱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ አሁን ግን፣ ግዢው ተፈጽሞ ማዳበሪያ እንዲገባ በመደረግ ላይ ነው፤ ብለዋል፡፡ ይኹንና፣ ከማዳበሪያ አቅርቦት ጋራ በተያያዘ፣ መዘግየት መኖሩን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አልሸሸጉም፡፡ካለፈው ሳምንት ጀምሮ፣ በየቀኑ በአማካይ እስከ 20ሺሕ ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ፣ ከጅቡቲ ወደብ ተነሥቶ ወደተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በመሠራጨት ላይ እንደኾነ፣ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር፣ ትላንት በፌስቡክ ገጹ አስታውቋል፡፡
በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች የሚገኙ በርካታ አርሶ አደሮች፣ ማዳበሪያ የሚጠቀሙበት የዘር ወቅት እያለፈባቸው እንደኾነ ገልጸው፣ ያለማዳበሪያ ዘር ለመዝራት እንደተገደዱ ቅሬታቸውን በማሰማት ላይ እንደኾኑ ይታወቃል፡፡በአንዳንድ አካባቢዎች፣ አርሶ አደሮች ሰልፍ ማድረጋቸውና በዚኽም ከጸጥታ ኃይሎች ጋራ መጋጨታቸው አይዘነጋም፡፡
Via VoA

👍1👎1
ኢትዮጵያና የአለም ባንክ የ400 ሚሊዮን ዶላር የፋይናንስ ድጋፍ ስምምነት ተፈራረሙ!
ኢትዮጵያና የአለም ባንክ ለሰው ሀብት ልማት አገልግሎት የሚውል የ400 ሚሊዮን ዶላር (የ21.8 ቢሊዮን ብር) የፋይናንስ ድጋፍ ስምምነት በበይነ መረብ በተካሄደ ስነ-ስርዓት ተፈራረሙ፡፡በስምምነቱ ከተፈረመው 400 ሚሊዮን ዶላር ውስጥ 350 ሚሊዮን ዶላር የልማት ድጋፍ ሲሆን 50 ሚሊዮን ዶላር ደግሞ ብድር መሆኑ ታውቋል፡፡
የፋይናንስ ድጋፉ ለሰው ሀብት ልማት ማለትም የትምህርትን ጥራትንና ውጤታማነትን ለማሻሻልና የስርዓተ ምግብን አገልግሎት ለማጎልበት የሚውል ሲሆን ከአገልግሎቱም በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ ልጃገረዶችና ታዳጊ ወጣቶች ተጠቃሚ ይሆናሉ ተብሏል፡፡የሰው ሀብት ልማት አገልግሎቱ በግጭትና ድርቅ የተጎዱ አካባቢዎችን የሚያካትት ሲሆን የማህበራዊ አገልግሎቶች አሰጣጥን ለማጠናከርና ተጠያቂነትን ለማስፈንም አስተዋጽዖ እንዳለው ታውቋል፡፡
የፋይናንስ ድጋፉ ውጤታማ የመማር ማስተማር ሂደትን ለማረጋጋጥ የሚያግዝ ከመሆኑም በላይ በተመረጡ ወረዳዎች የስርዓተ ምግብ አገልግሎትን በማጎልበት የህጻናት መቀንጨርን ለመከላከል እንደሚረዳ ታምኖበታል፡፡የገንዘብ ድጋፉ ጥራት ያለው የማህበራዊ አገልግሎትን ለማህበረሰቡ ለማዳረስ በሚደረገው ጥረት ሂደቱን ውጤታማ ለማድረግ በዘርፉ ለተሰማሩ አስፈጻሚዎችና ባለሙያዎች ቴክኒካዊ የአቅም ግንባታ ድጋፍ በማድረግም ውጤታማነትን ለማረጋገጥ እንደሚሰራ ታውቋል፡፡
ኢትዮጵያ ለሰው ሀብት ልማት ቅድሚያ የምትሰጥና ለተግበራዊነቱም የላቀ ትኩረት ሰጥታ እየሰራች የምትገኝ ሲሆን እ.ኤ.አ ከጁላይ 25-26 / 2023 በታንዛኒያ ዳሬ ሰላም ለሚካሄደው ለሰው ሀብት ልማት የመሪዎች ጉባኤም ድጋፍና ቁርጠኝነቷን አረጋግጣለች ተብሏል፡፡የፋይናንስ ድጋፍ ስምምነቱን በኢትዮጵያ በኩል የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ የፈረሙ ሲሆን በአለም ባንክ በኩል ሚስተር ኦስማን ዲዮን በአለም ባንክ የኢትዮጵያ፣ የኤርትራ፣ የሱዳንና የደቡብ ሱዳን ተጠሪ ፈርመዋል ሲል ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም ‹‹ በተያዘው የ2016 በጀት ዓመት ሶስተኛ የቴሌኮም ኦፕሬተር ወደ ኢትዮጵያ ሊገባ እንደሚችል ›› ተናገረ፡፡
ኢትዮ ቴሌኮም ይህን የተናገረው የ2016 በጀት ዓመት የሥራ ዕቅዱን ሐምሌ 20 ቀን 2015 ዓ.ም በስራ አስፈፃሚዋ በኩል ይፋ ባደረገበት ወቅት ነው፡፡‹‹ከሦስት ዓመት የመሪ ዕድገት ስትራቴጂ የተቀዳ ነው ›› የተባለለት የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ ‹‹ በሁሉም ዘርፍ እድገት ለማስመዝገብ ያለመ ነው ›› ተብሎለታል።
ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ፍሬሕወት ታምሩ የተቋማቸውን ሪፖርት ሲያቀርቡ እንደተናገሩት ‹‹ ለሁሉም ተቋማት ለማለት በሚስደፍር መልኩ የተቋሙ ስራ አስተዋፅዖ እያበረከተ ›› ይገኛል፡፡የስራ ዕድል መፍጠርን ጨምሮ የሀገሪቱ አጠቃላይ የኢኮኖሚ እድገት ላይ አስተዋፅዖ እያደረገ ነው የተባለለት ኢትዮ-ቴሌኮም በ2016 በጀት ዓመትም የያዛቸውን እቅዶች በፍሬሕወት በኩል አብራርቷል፡፡
በዚህም ዕቅዱ ‹‹ የሀገሪቱ ኢኮኖሚ እድገት ሊያስመዘግብ እንደሚችል፣ የውጭ ምንዛሬ መሻሻል ሊያሳይ ስለሚችል፣ መንግስት እያራመደ ያለው ዲጂታላይዜሽን እንዲሁም ሶስተኛው ኦፕሬተር ወደ ሀገር ውስጥ ሊገባ ይችላል ›› የሚሉት አንኳር ጉዳዮች ላይ መሰረት ማድረጉን ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ተናግረዋል፡፡‹‹አዳዲስና ዘመናዊ መሰረተ ልማቶችን ማስፋፊያና ማጠናከሪያ ፕሮጀክቶችን እንደሚተገብር ›› ተቋሙ ገልፆል።
‹‹ ከምሰጠው መደበኛ የቴሌኮም አገልግሎት በተጨማሪም ሌሎች የአገልግሎት ዘርፎች ላይ በመሰማራት የፋይናንስ አቅሜን ላጠናክር አቅጄያለሁ ›› ብሏል - ኢትዮ-ቴሌኮም። 90.5 ቢሊዮን አጠቃላይ ዓመታዊ ገቢ በማግኘት ከተጠናቀቀው የ2015 በጀት ዓመት በ19.4 በመቶ ዕድገት ለማስመዝገብ ማቀዱንም እወቁልኝ ብሏል።
[Asham]

የአለም ባንክ የጅቡቲ ወደብን ለመሃል አገር ይበልጥ ቅርብ ማድረግ ለሚያስችል የፈጣን መንገድ መሰረተ ልማት ፕሮጀክት ብድር አፀደቀ።
ባንኩ ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ የፈቀደው 730 ሚሊየን ዶላር ብድር የሚኤሶ ድሬዳዋ 142 ኪሜ መንገድን ደረጃ ለማሻሻል የሚያግዝ ከመሆኑ ባለፈ ወደ ጅቡቲ በጋላፊ በኩል የሚደረገውን ጊዞ በ146 ኪሜ የሚያሳጥር ነው።የፍጥነት መንገዱ የአዲስ አበባ ጅቢቲ የፈጣን መንገድ እቅድ አካል ሲሆን ከዚህ ክፍል ውስጥ የአዲስ አዳማ እና ድሬዳዋ ደወሌ የክፍያ መንገዶች አገልግሎት እየሰጡ ነው።
ቀሪው የአዳማ አዋሽ እና አዋሽ ሚኤሶ የፈጠን መንገድን በቀጣይ በተለያየ የግንባታ መርህ እንደሚገነባ ይጠበቃል።ከኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር በተገኘው መረጃ መሰረት የጨረታ ሂደትን በማለፍ የሚኤሶ ድሬዳዋ አስፓልት መንገድ ግንባታ በበጀት አመቱ ሁለተኛ አጋማብ ይጀመራል ተብሎ ይጠበቃል።
የመንገዱ ግንባታ ቀደም ሲል በጠጠር ደረጃ የነበረውን መንገድ ወደ አስፋልት የሚያሳድግ ከመሆን ባለፈ ለኢትዮጵያ ዋነኛ የወደብ መዳረሻ የሆነችውን ጅቡቲን በአካባቢው ካሉ አማራጭ አገራት ወደቦች ለመሃል አገር እጅግ ቅርብ የሚያደርግ ነው።
[Capital]

👍1
🔥🔥አስቸኳይ ክፍት የስራ ቅጥር💥💥
🔴በሁሉም ስራ ዘርፎች ሰራተኞችን በብዛት እንፈልጋለን።
🔥ቀጥታ ወደ ስራ ቦታ እንልካለን።
📞 ስልክ:- 09 78 88 18 19
09 77 64 18 19
💥ጉዳይ አስፈፃሚ/smart phone ያለው/
🔹የት/ደረጃ:10
🔹የስራ ልምድ: 0አመት ጀምሮ
🔹ደሞዝ:5000+ የቀን አበል
💥ካሸር አሰልጥኖ
🔹የት/ት ደረጃ= 12/ዲፕሎማ
🔹ልምድ= 0 አመት
🔹ደሞዝ= 5,500
💥ባርማን/ባሬስታ
🔹የት/ት ደረጃ= መፃፍ ማንበብ
🔹ልምድ= ያለው
🔹ደሞዝ=በስምምነት
💥ሪሴፕሽን ለገስት ሀውስ/ለሆቴሎች
🔹የት/ደረጃ:10ኛ- ከዚያ በላይ
🔹የስራ ልምድ: 0 አመት ጀምሮ
🔹ደሞዝ፡ 4,500
💥ቤቲንግ ቤት ካሸር (በፈረቃ)
🔹የት/ት ደረጃ= 10ኛ በላይ
🔹የስራ ልምድ=0
🔹ደሞዝ=5000
💥 ሼፍ/ዋና እና ረዳት/
🔹የት/ት ደረጃ= 10ኛ በላይ
🔹የስራ ልምድ=ያለው
🔹ደሞዝ=6000-10,000
▶ለበለጠ መረጃ
🏘አድራሻ: አ.አ 22 ጎላጎል ሲደርሱ ወደ ቦሌ በሚወስደው መንገድ ወረድ ብለው ሎተስ ህንፃ ግራውንድ ላይ ቢ.ቁ 006
👇👇https://tttttt.me/JobsAtHewan

ኤም ፔሳ በኢትዮጵያ 2 ሚሊዮን የሚሆኑ ደምበኞች እንደሚኖሩኝ ጠብቃለሁ አለ
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በኤም ፔሳ ( M-pesa ) አገልግሎቱ በሞባይል የሚደረግ የገንዘብ ዝዉዉርን ለማከናወን ፈቃድ ከተሰጠዉ በኋላ እስከ ቀጣዩ አመት መጋቢት ወር ድረስ 2 ሚሊዮን ደምበኞች እንደሚያፈራ የሳፋሪኮም ፋይናንስ ኦፊሰር ዲሊፕ ፓል መናገራቸውን ዘ ኢስት አፍሪካን (The East African) ጽፏል።
ፋይናንስ ኦፊሰሩ ከኢትዮ ቴሌኮም ብርቱ ፉክክር እንደሚገጥማቸዉ የገለጹ ሲሆን ፤ የኤም ፔሳ አገልግሎትን እስከ መስከረም መጠናቀቂያ ድረስ በኢትዮጵያ ለማስተዋወቅ እቅድ መያዙንም ነዉ የተናገሩት።
በተጨማሪም እስከ ቀጣዩ አመት መጋቢት ወር ድረስ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ደምበኞች 10 ሚሊዮን እንደሚደርስ ግምታቸዉን አስቀምጠዋል። ብስራት ራዲዮ በቅርቡ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ሶስት ሚሊዮን የደምበኞች ቁጥር ላይ መድረሱን መዘገቡ ይታወሳል።
የፋይናንስ ኦፊሰሩ ኢትዮ ቴሌኮም በቴሌብር የሞባይል ገንዘብ ዝዉዉር በኩል ቴክኖሎጂዉን ለህዝቡ በማሳወቅ እያደረገ ያለዉ አስተዋጽኦ እና እየታየ ያለዉ መነቃቃት ፤ ኤም ፔሳ ወደ ሀገር ዉሰጥ ሲገባ ስራዉን እንደሚያቀልለት ተናግረዋል።
#ዳጉ_ጆርናል
@Yenetube @Fikerassefa

👍2
አስራ ሦስት ሚሊዮን ተጨማሪ ደንበኞችን ማስተናገድ የሚችል ኔትዎርክ ይዘረጋል ተባለ
በኢትዮጵያ በቀጣይ ዓመት አስራ ሦስት ሚሊዮን ተጨማሪ ደንበኞችን ማስተናገድ የሚችል ኔትዎርክ ይዘረጋል ሲል ኢትዮ ቴሌኮም አስታውቋል፡፡
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻም ፍሬህይወት ታምሩ የተቋሙን የ2016 ዕቅድ አስመልክቶ ትናንት በሰጡት መግለጫ የተያዘው ዕቅድ፣ ተቋሙ ቀድሞ የነበረውን 78 ሚሊዮን ደንበኛ ወደ 92 ሚሊዮን ማድረስ ይስችላል ያሉ ሲሆን፤ በዚህም በቀጣይ ዓመት 8 ነጥብ 3 በመቶ የደንበኛ ዕድገት ይመዘገባል ብለዋል።
እንዲሁም 998 አዲስ የሞባይል ጣቢያዎች (ታወር) ይገነባሉ ያሉት ሥራ አስፈጻሚዋ፤ እነዚህም በ140 የገጠር ከተሞች የሚገነቡ መሆናቸውን ገልጸዋል።

"ትልቅሰው ሪል እስቴት "
በመሃል ካዛንችስ እንደራሴ እጅግ ዘመናዊ አፓርትመንቶችን በማስተዋቂያ ዋጋ መሸጥ ጀምረናል ።
ትልቅ ሰው ሪል እስቴት
🌹 የኔክሰስ ሆቴል
🌹 የግራንድ ሆቴል
🌹 የኢግል ፓክ ኢንዱስትሪያል እና
🌹 የስካይ ፔትሮሊየም እህት ኩባንያ ነው
👉ባለ 2 መኝታ
👉ባለ 3 መኝታ
👉የሚገርም ማራኪ እይታ ያላቸው !!!
👉ግንባታቸው 90% የደረሰ !!!
👉ማስረከቢያ ጊዜ ከ6 ወር -1 አመት
👉ከአማራጭ አከፋፈል ጋር
✍️100% በ1 አመት በ"4"ዙር
✍️50/50 ከባንክ ጋር ከ5-20 አመት
🙏🙏🙏🙏🙏
ለበለጠ መረጃ
@setu1988
+251936606665
በመሃል ካዛንችስ እንደራሴ እጅግ ዘመናዊ አፓርትመንቶችን በማስተዋቂያ ዋጋ መሸጥ ጀምረናል ።
ትልቅ ሰው ሪል እስቴት
🌹 የኔክሰስ ሆቴል
🌹 የግራንድ ሆቴል
🌹 የኢግል ፓክ ኢንዱስትሪያል እና
🌹 የስካይ ፔትሮሊየም እህት ኩባንያ ነው
👉ባለ 2 መኝታ
👉ባለ 3 መኝታ
👉የሚገርም ማራኪ እይታ ያላቸው !!!
👉ግንባታቸው 90% የደረሰ !!!
👉ማስረከቢያ ጊዜ ከ6 ወር -1 አመት
👉ከአማራጭ አከፋፈል ጋር
✍️100% በ1 አመት በ"4"ዙር
✍️50/50 ከባንክ ጋር ከ5-20 አመት
🙏🙏🙏🙏🙏
ለበለጠ መረጃ
@setu1988
+251936606665
🔥🔥አስቸኳይ ክፍት የስራ ቅጥር💥💥
🔴በሁሉም ስራ ዘርፎች ሰራተኞችን በብዛት እንፈልጋለን።
🔥ቀጥታ ወደ ስራ ቦታ እንልካለን።
📞 ስልክ:- 09 78 88 18 19
09 77 64 18 19
💥ጉዳይ አስፈፃሚ/smart phone ያለው/
🔹የት/ደረጃ:10
🔹የስራ ልምድ: 0አመት ጀምሮ
🔹ደሞዝ:5000+ የቀን አበል
💥ካሸር አሰልጥኖ
🔹የት/ት ደረጃ= 12/ዲፕሎማ
🔹ልምድ= 0 አመት
🔹ደሞዝ= 5,500
💥ባርማን/ባሬስታ
🔹የት/ት ደረጃ= መፃፍ ማንበብ
🔹ልምድ= ያለው
🔹ደሞዝ=በስምምነት
💥ሪሴፕሽን ለገስት ሀውስ/ለሆቴሎች
🔹የት/ደረጃ:10ኛ- ከዚያ በላይ
🔹የስራ ልምድ: 0 አመት ጀምሮ
🔹ደሞዝ፡ 4,500
💥ቤቲንግ ቤት ካሸር (በፈረቃ)
🔹የት/ት ደረጃ= 10ኛ በላይ
🔹የስራ ልምድ=0
🔹ደሞዝ=5000
💥 ሼፍ/ዋና እና ረዳት/
🔹የት/ት ደረጃ= 10ኛ በላይ
🔹የስራ ልምድ=ያለው
🔹ደሞዝ=6000-10,000
▶ለበለጠ መረጃ
🏘አድራሻ: አ.አ 22 ጎላጎል ሲደርሱ ወደ ቦሌ በሚወስደው መንገድ ወረድ ብለው ሎተስ ህንፃ ግራውንድ ላይ ቢ.ቁ 006
👇👇https://tttttt.me/JobsAtHewan
🔴በሁሉም ስራ ዘርፎች ሰራተኞችን በብዛት እንፈልጋለን።
🔥ቀጥታ ወደ ስራ ቦታ እንልካለን።
📞 ስልክ:- 09 78 88 18 19
09 77 64 18 19
💥ጉዳይ አስፈፃሚ/smart phone ያለው/
🔹የት/ደረጃ:10
🔹የስራ ልምድ: 0አመት ጀምሮ
🔹ደሞዝ:5000+ የቀን አበል
💥ካሸር አሰልጥኖ
🔹የት/ት ደረጃ= 12/ዲፕሎማ
🔹ልምድ= 0 አመት
🔹ደሞዝ= 5,500
💥ባርማን/ባሬስታ
🔹የት/ት ደረጃ= መፃፍ ማንበብ
🔹ልምድ= ያለው
🔹ደሞዝ=በስምምነት
💥ሪሴፕሽን ለገስት ሀውስ/ለሆቴሎች
🔹የት/ደረጃ:10ኛ- ከዚያ በላይ
🔹የስራ ልምድ: 0 አመት ጀምሮ
🔹ደሞዝ፡ 4,500
💥ቤቲንግ ቤት ካሸር (በፈረቃ)
🔹የት/ት ደረጃ= 10ኛ በላይ
🔹የስራ ልምድ=0
🔹ደሞዝ=5000
💥 ሼፍ/ዋና እና ረዳት/
🔹የት/ት ደረጃ= 10ኛ በላይ
🔹የስራ ልምድ=ያለው
🔹ደሞዝ=6000-10,000
▶ለበለጠ መረጃ
🏘አድራሻ: አ.አ 22 ጎላጎል ሲደርሱ ወደ ቦሌ በሚወስደው መንገድ ወረድ ብለው ሎተስ ህንፃ ግራውንድ ላይ ቢ.ቁ 006
👇👇https://tttttt.me/JobsAtHewan
ለአደይ አበባ ብሔራዊ ስታዲየም ግንባታ አዲስ ተቋራጭ ጨረታ ሊወጣ ነው
👉በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃል!
ለረዥም ጊዜ ተቋርጦ የቆየውን የአደይ አበባ ብሔራዊ ስታዲየም ግንባታ በአዲሱ በጀት ዓመት እንደገና ለማስጀመር በጀት መያዙን ባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር ገለጸ።
በቅርቡም ሥራ ተቋራጭ ለመምረጥ ዓለም አቀፍ ጨረታ የሚወጣ መሆኑ ተመልክቷል።
የባህል እና ስፖርት ሚኒስትሩ አቶ ቀጄላ መርዳሳ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፣ በ48 ሄክታር መሬት ላይ የሚገነባውና 62ሺ ተመልካች የመያዝ አቅም ያለው ብሔራዊ ስታዲየም ግንባታን ለማስቀጠል በ2016 ዓ.ም በጀት የተያዘለት በመሆኑ በቅርቡ ዓለም አቀፍ ጨረታ ወጥቶ ግንባታው ይጀመራል።
የብሔራዊ ስታዲየሙ ግንባታ በቻይናው ኩባንያ ይካሄድ እንደነበረ አስታውሰው፤ ግንባታው በኮቪድ-19 ምክንያት ተቋርጦ መቆየቱን ገልፀዋል።
በኋላም የግንባታ ተቋራጩ ለሥራው ያቀረበው የዋጋ ማስተካከያ ከገበያ በላይ የተጋነነ በመሆኑ መንግሥት ከያዘው በጀት ጋር ሊመጣጠን አልቻለም። በዚህም ከግንባታ ተቋራጩ ጋር ያለው ውል እንዲቋረጥ መደረጉን ሚኒስትሩ ተናግረዋል።
ተቋራጩ ኮቪድ-19ን እንደ ምክንያት በማድረግ ስራውን አቀርጦ በመቆየቱ ግንባታውን ለማስቀጠል ከፍተኛ ጥረት ሲደረግ እንደነበር የገለፁት ሚኒስትሩ፤ በጉዳዩ ላይ ተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጠው አስታውሰዋል።
የግንባታ ተቋራጩ ለሥራው አሳማኝ ያልሆነና ከገበያ በላይ የሆነ የዋጋ ማስተካከያ እንዲደረግ መጠየቁን አውስተው፤ የተጠየቀው የዋጋ ማስተካከያ የተጋነነ በመሆኑ ብዙ ድርድር በማድረግ ውል ከማቋረጥ ጋር ተያይዞ ችግሮች እንዳያጋጥሙ ከፍተኛ ጥንቃቄ ተደርጓል።
በዚህም ከተቋራጩ ጋር የነበረው ውል በዚህ ዓመት በመጋቢት ወር 2015ዓ.ም መቋረጡን ሚኒስትሩ አስረድተዋል።
የስታዲየሙ የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ በጥሩ ሁኔታ መከናወኑን የገለፁት ሚኒስትሩ፣ ግንባታውን የጎበኙ የውጭ ሀገር ባለሙያዎች አስተያየትም ሥራው ዓለም አቀፍ ደረጃውን ጠብቆ መከናወኑን እንደሚያሳይ ተናግረዋል።
ስታዲየሙ በውስጡ በርካታ ነገሮችን የያዘ ትልቅ ፕሮጀክት መሆኑን ጠቁመው፤ የበጀት እጥረት ችግር ካላጋጠመ በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ እንደሚጠናቀቅ ገልፀዋል።
የስታዲየሙን ሁለተኛ ምዕራፍ ግንባታ ለማስቀጠል ምን ያህል በጀት እንደተያዘ ይፋ አልሆነም።
የስታዲየሙ የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ በ2 ነጥብ 47 ቢሊዮን ብር በጀት ታህሳስ 2008 ዓ.ም እንደተጀመረ የሚታወስ ሲሆን ፣ ሁለተኛው ምዕራፍ ግንባታ በ5 ነጥብ 57 ቢሊዮን ብር በጀት መጋቢት 2012 ዓ.ም ተጀምሮ በዘጠኝ መቶ ቀናት ለማጠናቀቅ እቅድ ተይዞ እንደነበር ይታወሳል።

ከ2016 ጀምሮ በግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የመውጫ ፈተና ከሚወስዱ ተማሪዎቻቸው 25 በመቶዎቹን ማሳለፍ ካልቻሉ እርምጃ ይወሰድባቸዋል
የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመውጫ ፈተና ከሚወስዱ ተማሪዎቻቸው ቢያንስ 25 በመቶዎቹን ማሳለፍ ካልቻሉ የትምህርት መስኮቻቸው እንዲታጠፉ የሚያስገድድ መመሪያ ተግባራዊ ሊደረግ ነው።
የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ከ2016 ዓ.ም ጀምሮ በግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተግባራዊ የሚደረግ አዲስ መመሪያ መዘጋጀቱን ገልጿል።
በባለስልጣኑ የከፍተኛ ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ክትትል እና ቁጥጥር መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ከፍያለው አድነው ለፋና ብሮድካስቲንግ እንደተናገሩት፥ የመማር ማስተማር ስራው ጥራቱ የተጠበቀ እንዲሆን አዲስ መመሪያ እና መስፈርት ተዘጋጅቷል።
የሚታዩ ክፍተቶችን በመሙላት የሚጠበቀውን ደረጃ እና ጥራት ማስጠበቅ ያስችላል የተባለው አዲስ መመሪያ እና መስፈርትም ከ2016 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል ነው ያሉት።
በመመሪያው የትምህርት ጥራቱን ለማስጠበቅ በርካታ መለኪያዎች የተቀመጡ ሲሆን፥ አንዱ የመውጫ ፈተናን የሚመለከት መሆኑንም አስረድተዋል።
በዚህም እያንዳንዱ ተቋም ለመውጫ ፈተና ከሚያስቀምጣቸው ተማሪዎች በየትምህርት መስኩ ቢያንስ 25 በመቶዎቹ ማለፍ እንደሚጠበቅባቸው በማንሳት ይህ ካልሆነ ግን የትምህርት ፕሮግራሙ ይሰረዛል ብለዋል።
በተጨማሪም የትምህርት ተቋማቱ ለማስተማር የሚመዘግቧቸውን ተማሪዎች ለባለስልጣኑ የማሳወቅ ግዴታ አለባቸው ተብሏል።
ዘንድሮ በተሰጠው የዩኒቨርሲቲ የመውጫ ፈተና ከግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የመውጫ ፈተናውን ከወሰዱ 72 ሺህ ተማሪዎች ውስጥ የማለፊያ ውጤት 50 እና ከዛ በላይ ያመጡት 12 ሺህ 422 ወይም 17 ነጥብ 2 በመቶ ብቻ መሆናቸው ይታወቃል።
@Yenetube @FikerAssefa

❤1
የፖርቹጋላዊው ተጨዋች ክርስቲያኖ ሮናልዶ የልብ አድናቂ እንደሆነ የሚናገረው አሜሪካዊ እውቅ ዩቲዩበር አይ ሾው ስፒድ ከባድ የራስ ህመም አጋጥሞት ሆስፒታል መግባቱ ተገልጿል።
የ 18ዓመቱ ዩቲዩበር አይ ሾው ስፒድ ባጋጠመው ከባድ የራስ ህመም ምክንያት የቀዶ ጥገና ሊደረግልት እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን ቤተሰቦቹ ከአሜሪካ ወደ ቶክዮ በማምራት ላይ መሆናቸው ተነግሯል።
አይ ሾው ስፒድ በማህበራዊ ትስስር ገፁ በለጠፈው ተንቀሳቃሽ ምስልም " ከባድ በሆነ የራስ ህመም እየተሰቃየሁ ነው አይኔን መግለጥ አልቻልኩም ፣ መመገብም አልችልም።"ሲል ተናግሯል።