YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.87K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ከመንግሥት መተማመኛ የተሰጠው የቱሉ ካፒ ወርቅ ፕሮጀክት ሥራ ለመጀመር መዘጋጀቱን አስታወቀ!

በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ወለጋ ዞን በከፊ ሚነራልስ ፒኤልሲ አማካይነት ለሚተገበረው የቱሉ ካፒ ወርቅ ልማት ፕሮጀክት፣ መንግሥት የፀጥታ ማስተማማኛ በመስጠቱ፣ ኩባንያው ሥራ ለመጀመር የሚያስችለውን ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታወቀ፡፡

ወደ ሥራ ለመግባት ‹‹ተፈላጊውን ፋይናንስ አላሟላም›› በሚል ከመንግሥት ጋር በውዝግብ የቆየውና ባለፈው ዓመት የተለያዩ ማስጠንቀቂያዎች ሲደርሱት የቆየው የእንግሊዝ ኩባንያ ካፊ ሚነራልስ ባለፉት ስድስት ወራት ወሳኝ የሚባሉ ለውጦች በራሱ፣ እንዲሁም በመንግሥት በኩል በመደረጋቸው ምክንያት፣ ፕሮጀክቱን በይፋ ለመጀመር የሚችልበት ቁመና ላይ እንደሚገኝ ገልጿል፡፡

የከፊ ሚነራልስ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሚስተር ሃሪ አናግኖስታረስ ለሪፖርተር እንዳስረዱት፣ ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ መንግሥት በቅድመ ሁኔታ ሲጠይቀው የነበረው የፕሮጀክት ፋይናንስ ጉዳይ በአሁኑ ወቅት እልባት አግኝቷል፡፡ በተለይ ኢትዮጵያ በመጋቢት ወር 2015 ዓ.ም. የአፍሪካ ፋይናንስ ትብብር ተቋም አባል ከሆነች በኋላ፣ ሁለት ዋነኛ የፕሮጀክት አበዳሪ ባንኮች መተማመኛ በማግኘታቸው ወደ ሥራ ይገባል ብለዋል፡፡

ባለፈው ወር ለቱሉ ካፒ ወርቅ ልማት አስፈላጊ የሆነውን የፋይናንስ ስምምነት እንደተፈራረመ ይፋ ያደረገው ከፊ ሚነራልስ፣ ይህም ስምምነት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ፖሊሲና መርህ መሠረት የተከናወነ መሆኑን አስታውቋል።

ኩባንያው ባለፈው ወር ለሦስት ቀናት የቆየ ዓውደ ጥናት በማካሄድ፣ ከመንግሥት ተወካዮች ጋር በመሆን የድርጊት ዕቅድ በማዘጋጀት፣ በቀጣይ ወራት ውስጥ ፕሮጀክቱን ለማስጀመር የሚያስችል ፈጣን እንቅስቃሴ መጀመሩ ተገልጿል፡፡

Via Reporter
@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
🔥🔥አስቸኳይ ክፍት የስራ ቅጥር💥💥

🔴በሁሉም ስራ ዘርፎች ሰራተኞችን በብዛት እንፈልጋለን። 
🔥ቀጥታ ወደ ስራ ቦታ እንልካለን።

📞 ስልክ:- 09 78 88 18 19
                 09 77 64 18 19

💥ጉዳይ አስፈፃሚ/smart phone ያለው/
      🔹የት/ደረጃ:10
      🔹የስራ ልምድ: 0አመት ጀምሮ
      🔹ደሞዝ:5000+ የቀን አበል
💥ካሸር አሰልጥኖ
      🔹የት/ት ደረጃ= 12/ዲፕሎማ
      🔹ልምድ= 0 አመት
      🔹ደሞዝ= 5,500
💥ባርማን/ባሬስታ
      🔹የት/ት ደረጃ= መፃፍ ማንበብ
      🔹ልምድ= ያለው
      🔹ደሞዝ=በስምምነት
💥ሪሴፕሽን ለገስት ሀውስ/ለሆቴሎች
     🔹የት/ደረጃ:10ኛ- ከዚያ በላይ
     🔹የስራ ልምድ: 0 አመት ጀምሮ    
     🔹ደሞዝ፡ 4,500
💥ቤቲንግ ቤት ካሸር (በፈረቃ)
     🔹የት/ት ደረጃ= 10ኛ በላይ
     🔹የስራ ልምድ=0
     🔹ደሞዝ=5000
💥 ሼፍ/ዋና እና ረዳት/
     🔹የት/ት ደረጃ= 10ኛ በላይ
     🔹የስራ ልምድ=ያለው
     🔹ደሞዝ=6000-10,000

ለበለጠ መረጃ
🏘አድራሻ: አ.አ 22 ጎላጎል ሲደርሱ ወደ ቦሌ በሚወስደው መንገድ ወረድ ብለው  ሎተስ ህንፃ ግራውንድ ላይ ቢ.ቁ 006

👇👇https://tttttt.me/JobsAtHewan
በኦሮሚያ ክልል ባለፉት 11 ወራት በየቀኑ የአራት ሰዎች ህይወት በትራፊክ አደጋ ማለፉ ተነገረ!

በኦሮሚያ ክልል በተጠናቀቀው የ2015 በጀት ዓመት ባለፉት 11 ወራት ውስጥ 3 ሺ 631  የትራፊክ አደጋዎች መከሰታቸውን የክልሉ ትራፊክ ቁጥጥር እና ደህንነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት ኮማንደር በላቸው ትኪ በተለይ ለብስራት ሬዲዮና ቲቪ ተናግረዋል፡፡በደረሰዉ አደጋ 1ሺ 492 ሰዎች ህይወታቸዉን ሲያጡ፣ 1 ሺ ሰዎች ላይ ከባድ እና 1ሺ 28 ሰዎች ላይ ደግሞ ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱን ገልፀዋል።

በአደጋዉም በአማካይ በየቀኑ የአራት ሰዎች ህይወት ማለፉ ተነግሯል።በተከሰተው  አደጋ ከባድ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች የተለያዩ የሰውነት ክፍሎቻቸውን ያጡ ፣በዊልቸር የሚንቀሳቀሱ እና ከፊሎቹ ደግሞ በደረሰባቸው አደጋ በተለያዩ ሆስፒታሎች  አሁኑም የህክምና እየተሰጣቸው ድጋፍ መሆኑን ኮማንደሩ ተናግረዋል፡፡

ከደረሰዉ አደጋ  ከፍተኛ ቁጥር የተመዘገበው በምእራብ አርሲ፣ ምስራቅ ሀረርጌ  ፣ ምስራቅ ወለጋ ፣ምዕራብ ሸዋ ፣ጅማ፣ ሰሜን  ሽዋ ዞኖች እንዲሁም ሱሉልታ፣ገላን፣ለገጣፎ ፣አዳማ ፣ቡራዩ እና ሰበታ  ከተሞችና ክፍለ ከተሞች ላይ  ናቸው።በአለም አቀፍ ደረጃ በየቀኑ በአማካይ 3 ሺ 7 መቶ ሰዎች በትራፊክ አደጋ ህይወታቸውን ያጡ ሲሆን ይህም በአመት ውስጥ በአጠቃላይ 1.3 ሚሊዮን ሰዎች ህይወታቸዉን እንደሚያጡ ጥናቶች ያመላክታሉ::

በተጨማሪም በአማካኝ 71 በመቶ  የሚሆነው አደጋ የሚደርሰው በወንድ አሽከርካሪዎች ነው።በተመሳሳይ በኦሮሚያ ክልል 95 በመቶ የተከሰተው አደጋ የደረሰው በወንድ አሽከርካሪዎች መሆኑ ተገልፆል፡፡

እንዲሁም 90 በመቶ የሚሆነው አደጋ በቀኑ ክፍለ ጊዜ የደረሰ ሲሆን 10 በመቶ የሚሆነው ደግሞ በሌሊቱ ያጋጠሙ መሆናቸው ተገልፆል።ከፍጥነት ወሰነ በላይ ማሽከርከር እና የአሸከርካሪዎች ጥንቃቄ ጉድለት፣ ያለ እረፍት ማሸከርከር ፣ለእግረኛ ቅድሚያ አለመስጠር ፣የቴክኒክ ችግር፣ አቅጣጫን መልቅቀ  የአደጋዎቹ መንስኤዎች መሆናቸውን  ኮማንደር በላቸው ትኪ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮና ቲቪ ተናግረዋል፡፡ የደረሰው አደጋ ካለፈው ዓመት  ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ233 አደጋዎች መቀነሱ ተገልፆል፡፡

Via Bisrat FM
@YeneTube @FikerAssefa
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ባደረገው ማጣራት ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃዎች ማግኘቱን አስታወቀ!

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በ2015 የቀረቡለትን የትምህርት ማስረጃ ማጣራት ጥያቄዎችን ተከትሎ ባደረገው የማጣራት ሥራ ሕጋዊነት የሌላቸው ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃዎች ማግኘቱን አስታውቋል፡፡ዩንቨርስቲው የዩኒቨርሲቲው ምሩቃን በአገር አቀፍና በዓለም አቀፍ ተቋማት በሚቀጠሩበት ወይም ተቀጥረው እየሠሩ ባሉበት ጊዜ የሚቀርቡ የትምህርት ማስረጃ ትክክለኛነት ይጣራልን ጥያቄዎችን እየተቀበለ የትምህርት ማስረጃ አጣርቶ በማረጋገጥ በተከታታይ ምላሽ በመስጠት ላይ እንደሚገኝ ገልጿል፡፡

በዚህም መሰረት የማጣራት ሂደት ከአንዳንድ ተቋማት የቀረቡ የዩኒቨርሲቲው ምሩቃን የትምህርት ማስረጃዎች፤ በዩኒቨርሲቲው በተሰጣቸው የተማሪ ውጤት ኮፒ ላይ የአጠቃላይ ነጥብ ለውጥ የተደረገባቸው እንዲሁም ፈጽሞ በዩኒቨርሲቲው ያልተማሩባቸው ሐሰተኛ ዲግሪ ማስረጃዎች መሆናቸውን ማረጋገጡን አስታውቋል፡፡

በመሆኑም መሰል ኃላፊነት የጎደላቸው ተግባራት እንዳይበረታቱ ብሎም ሕዝብና መንግሥት ሙያዊ ብቃት በሌላቸውና ኃላፊነት በጎደላቸው ዜጎች ለጉዳት እንዳይጋለጥ በማሰብ በዩኒቨርሲቲው የትምህርት ማስረጃ ላይ የዘመኑን ቴክኖሎጂ በመጠቀም ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ በማስመሰልና በመቀየር እንዲሁም፤ በዩኒቨርሲቲው ሥምና ሎጎ ያልተማሩበትን ዲግሪ ይዘው የማጭበርበር ተግባር ላይ የተሠማሩና ወደ ፊትም የሚሠማሩ ቢኖሩ ለሕዝብ የማጋለጥ ሥራ በተከታታይነት እንዲሠራ ዩኒቨርሲቲው መወሰኑን ገልጿል፡፡

ስለሆነም ከላይ በተያያዘው የሐሰተኛ ማስረጃ ማጣራት ሪፖርት ላይ ሥማቸው የተጠቀሱ ግለሰቦች፤ በእነዚህ የትምህርት ማስረጃዎች በየትኛውም ተቋም ቢቀጠሩ ማስረጃዎቻቸው ሕጋዊነት የሌላቸው መሆኑን ማረጋገጡን ዩንቨርስቲው አስታውቋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
👍1
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተሰጠው የ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ነገ ይፋ ይሆናል፡፡

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 24፣ 2015 (ትምህርት ቢሮ)  የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ጀነራል ካውንስል በአዲሱ ስርዓተ  ትምህርት መሰረት ለመጀመሪያ ጊዜ በተሰጠው በ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ማለፊያ ነጥብ ላይ ውይይት በማድረግ የማለፊያ ነጥቡን በሙሉ ድምጽ ወስናል፡፡

ውጤቱንም በማስመልከት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ለሚዲያ አካላት ነገ 4 ሰሃት ላይ ማብራሪያ ከሰጡ በኋላ ይፋ ይሆናል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2015 ዓ.ም የ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ከሰኔ 28-30/10/2015 ዓ.ም ድረስ በ182 የፈተና ጣቢያዎች  ለ75,090 ተማሪዎች ፣ 1,900 ፈታኞችን፣ 700 ሱፐር ቫይዘሮችንና  182 የፈተና ጣቢያ ኃላፊዎችን በማሳተፍ መሰጠቱ ይታወሳል።

@YeneTube @FikerAssefa
በትግራይ ክልል የተከሰተው ሰብዓዊ ቀውስ ዘላቂ መፍትሔ ሊያገኝ እንዳልቻለ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶት ጉባኤ ገለፀ።

ጦርነት ያስከተለው ሰብዓዊ ቀውስ ከፍተኛ በመሆኑ እስካሁን ዘላቂ መፍትሔ ሊያገኝ አልቻለም ብሏል ጉባኤው፡፡በክልሉ ባለው ከፍተኛ የምግብና የመድሀኒት እጥረት በዋናነት የሚያጠቡ እናቶች እና ጨቅላ ህጻናት ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰባቸው መሆኑን ገልፀዋል።

ለተከሰተው ርሀብ፣ ከፍተኛ የሆነ የምግብና የመድሀኒት እጥረት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር እንዲሁም የፌደራል መንግስት ኃላፊነት ስላለባቸው ሰብዓዊ ቀውሱ ከእዚህ የከፋ ጉዳትን ሳያደርስ ለመቆጣጠር የበኩላቸውን ኃላፊነት ሊወጡ ይገባል ብሏል፡፡

የህክምና ተቋማት በትጥቅ ግጭቱ ምክንያት ከደረሰባቸው ጉዳት ለማገገም እየሞከሩ ቢሆንም አሁንም የህክምና ባለሙያዎች የህክምና ቁሳቁስ እጥረትና የህክምና አቅርቦት እና ፍላጎት ተመጣጣኝ አለመሆን ከፍተኛ ችግር መሆኑን አሳውቋል፡፡

[አሐዱ]
@YeneTube @FikerAssefa
👍2
ገንዘብ ሚንስቴርና ስምንት የመንግሥት ስኳር ፋብሪካዎችን ወደ ግል ይዞታ ለማዛወር ለሚያወጣው ጨረታ የምክረ ሃሳብ ማስገቢያው ጊዜ ወደ ቀጣዩ ዓመት መስከረም 24 መራዘሙን ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

የፋብሪካዎቹ የጨረታ ጊዜ የተራዘመው፣ በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ኩባንያዎች ባቀረቡት ጥያቄ መሠሩት መኾኑን ሚንስቴሩ ገልጧል። ቀደም ሲል የተወሰነው የጨረታ መወዳደሪያ የምክረ ሃሳብ ሰነድ ማስገቢያ ቀነ ገደብ ሐምሌ 24 ነበር። መንግሥት 20 ያህል የአገር ውስጥና የውጭ ኩባንያዎች በጨረታው ለመሳተፍ ፍላጎታቸውን እንደገለጡ በቅርቡ እስታውቆ ነበር። ጨረታ የሚወጣባቸው ስኳር ፋብሪካዎች፣ ተንዳኾ፣ ጣና በለስ፣ ቀሰም፣ አርጆ ደዴሳ፣ ኦሞ ኩራዝ ቁጥር 1፣ ኦሞ ኩራዝ ቁጥር 2፣ ኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3 እና ኦሞ ኩራዝ ቁጥር 5 ናቸው።

@YeneTube @FikerAssefa
👍2
ጠ/ሚ ዐቢይ ከዓለም ባንክ ፕሬዝዳንት አጃይ ባንጋ ጋር ተወያዩ!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የዓለም ባንክ ፕሬዝዳንት አጃይ ባንጋን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።ጠቅላይ ሚኒስትሩና የልዑካን ቡድናቸው ባደረጉት የሁለትዮሽ ውይይት በአጠቃላይ የኢትዮጵያን ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳ ላይ ገለጻ አድርገዋል።

የዓለም ባንክ ፕሬዝዳንት በበኩላቸው በሀገር ውስጥ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ብዙ ፈተናዎች ቢያጋጥሙም ኢትዮጵያ ለቁልፍ የልማት ግቦች የሰጠችውን ትኩረት ማድነቃቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መረጃ አመላክቷል።

@YeneTube @FikerAssefa
በ21 የኤፈርት ድርጅቶች ላይ ተጥሎ የነበረው እግድ እንዲነሳ በፍርድ ቤት ተወሰነ!

በትግራይ የመልሶ ማቋቋም ኢንዶውመንት ፈንድ (ኤፈርት) ስር የሚገኙ 21 ድርጅቶች ላይ ተጥሎ የነበረው እግድ እንዲነሳ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ወሰነ።ድርጅቶቹን በጊዜያዊነት ሲያስተዳድር የቆየው የኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ኃላፊነትም እንዲሻር ፍርድ ቤቱ አዝዟል።

እነዚህን ተደራራቢ ትዕዛዞች ባለፈው ሳምንት አርብ ሐምሌ 21፤ 2015 የሰጠው፤ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ የጊዜ ቀጠሮ ወንጀል ጉዳዮች ችሎት ነው።የጊዜ ቀጠሮ ችሎቱ ትዕዛዞቹን ያስተላለፈው፤ ፍትሕ ሚኒስቴር በኤፈርት ስር ያሉ ድርጅቶች ላይ የተሰጠው ዕግድ እና በጊዜያዊነት የማስተዳደር ኃላፊነት እንዲነሳ ጥያቄ ማቅረቡን ተከትሎ ነው።

በጦርነት እና በድርቅ የተጎዳውን የትግራይ ክልል ኢኮኖሚ መልሶ የማሻሻል ዓላማን ይዞ በ1987 ዓ.ም የተመሰረተው ኤፈርት፤ በኮንስትራክሽን፣ ጨርቃ ጨርቅ፣ ግብርና፣ ማዕድን እና ትራንስፖርት ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ድርጅቶችን በስሩ ሲያስተዳድር ቆይቷል።ሱር ኮንስትራክሽን፣ መስፍን ኢንዱስትሪያል ኢንጂነሪንግ፣ ጉና ትሬዲንግ፣ መሰቦ ሲሚንቶ እና አልመዳ ጨርቃ ጨርቅ በኤፈርት ስር ከሚተዳደሩ ግዙፍ ድርጅቶች መካከል ይጠቀሳሉ።

Via Ethiopia Insider
@YeneTube @FikerAssefa
👍1
   "Do or Die..!" 

የተዋጣለት የሺያጪ ቻናል ፈልገዋል..!!!

ቤት ...
መሬት...
መካዝን...
ኢንዳስትሪ...
ኢንቨስትመንት...
ሪል ስቴት ..
ለትርፍ የሚሆኑ ለ 2 ..3..የሚከፈሉ ቦታዎችን ፈልገዋል ..

አዲስ አበባ ውስጥ የግዙፍ የግዢ እና የሽያጪ ቻናላችን ነው

..የምትወዱትን ሰው የሆነ ፍጥረት ወደ ቻናሉ ቤተሰብ በማደረግ መረጃን በቤትዎ ያስገቡ ..

መረጃን በቀላሉ እንዲያገኙ በማደረግ ሀላፊነታችሁን ተወጡ..!!!

   +251937736408
https://tttttt.me/shger21
  Inbox @FikreabAmanu

ለበለጠ መረጃ.. ቻናላችንን  ይቀላቀሉ
https://tttttt.me/+U2S2JyiWsfAzNzc0
የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ ፈተና መሰጠት ጀመረ!

የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ የተፈጥሮ ሳይንስ ፈተና በዛሬው ዕለት በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መሰጠት ጀምሯል።

በዩኒቨርስቲዎች የሚሰጠው ፈተና እስከ ሐምሌ 28 ቀን 2015 ዓ.ም እንደሚቆይ የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

ሚኒስቴሩ ለተማሪዎቹ መልካም የፈተና ጊዜ ተመኝቷል።

የ12ኛ ክፍል የማህበራዊ ሳይንስ ፈተና ከሐምሌ 19 እስከ 21 ቀን 2015 መሰጠቱ ይታወቃል።

በዘንድሮው 12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና በአጠቃላይ 868 ሺህ 74 ተማሪዎች ፈተናውን ይወስዳሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከትምህርት ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

@YeneTube @FikerAssefa
1👍1
በመተማ ወረዳ ከሳምንታት በፊት በታጣቂዎች የታገቱ ስድስት ሰዎች እንደተገደሉ ተሰማ!

በዐማራ ክልል በምዕራብ ጎንደር ዞን በመተማ ወረዳ ከመሸላ በተባለ ቀበሌ፣ ከሦስት ሳምንት በፊት፣ በታጣቂዎች ታግተው የነበሩ ስድስት ግለሰቦች መገደላቸውን፣ ቤተሰቦቻቸው አረጋገጡ፡፡በሌላ በኩል፣ በዚኹ በመተማ ወረዳ፣ የዳስ ጉንዶ ቀበሌ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አከለ መለሰ፣ ለአሜሪካ ድምፅ እንደተናገሩት፣ ከሳምንት በፊት፣ ታጣቂዎች፣ በቀበሌው የእርሻ ሥራቸውን እያከናወኑ በነበሩ አርሶ አደሮች ላይ የግድያ እና የእገታ ድርጊት ፈጽመዋል፡፡

ለታጋች ቤተሰቦችም ስልክ ደውለው፣ በመቶ ሺሕዎች የሚቆጠር የማስለቀቂያ ገንዘብ እንዲከፍሉ እንደጠየቋቸው፣ የቤተሰቦቻቸው አባላት ተናግረዋል፡፡የቀበሌው ዋና አስተዳዳሪ አቶ አከለ መለሰ፣ ለግድያ እና ለእገታ አድራጎቱ፥ በጫካ የነበሩና በእርቀ ሰላም ስም ተመልሰው ወደ ማኅበረሰቡ የተቀላቀሉትን፣ “ጽንፈኛ” ሲሉ የጠሯቸውን፣ የቅማንት ታጣቂዎችን ተጠያቂ አድርገዋል፡፡

የምዕራብ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቢክስ ወርቄ፣ ከሦስት ሳምንታት በፊት፣ በተጠቀሱት የወረዳው አካባቢዎች፣ ግድያ እና እገታ መፈጸሙን አምነው፣ በአካባቢው ታጥቀው በሚንቀሳቀሱ ኃይሎች ላይ ርምጃ እየተወሰደ እንደሚገኝ መግለጻቸው ይታወሳል፡፡

Via VoA
@YeneTube @FikerAssefa
👍1
በአዲስ አበባ የ6ተኛ ክፍል ከተማ አቀፍ መልቀቂያ ፈተና ውጤት ይፋ ተደረገ!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የከተማ አቀፍ የስድስኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤትን በዛሬ ዕለት ይፋ አድርጓል፡፡የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንደገለጹት፤ በከተማ አስተዳደሩ አዲሱን ስርዓተ ትምህርት መሰረት አድርጎ የስድስተኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከ28 ዓመት በሗላ ዘንድሮ ለመጀመሪያጊዜ ተሰጥቷል፡፡

እንደ ዶክተር ዘላለም ገለጻ፤ በከተማ አስተዳደሩ 73 ሺሕ 667 የስድስተኛ ክፍል ተማሪዎች ፈተናውን ወስደዋል፡፡ፈተናው ከወሰዱት ተማሪዎች መካከል 3 ተማሪዎች 99 ከመቶ ያመጡ ሲሆን፤ 477 ተማሪዎች 95 እና ከዛ በላይ ማምጣታቸውን ገልጸዋል። 2 ሺሕ 787 ተማሪዎች 90 እና ከዛ በላይ ያመጡ ሲሆን፤ 59 ሺሕ 105 ተማሪዎች 50 እና ከዛ በላይ ማምጣታቸውን አስታውቀዋል፡፡

የአጠቃላይ ፈተናውን ከወሰዱ ተማሪዎች 80 ነጥብ 2 በመቶ የሚሆኑት 50 እና ከዛ በላይ ማምጣታቸውን ገልጸዋል፡፡ፈተናውን ያለፉ ተማሪዎች በመደበኛ ከተፈተኑት 67 ሺሕ 939 ተማሪዎች 56 ሺሕ 842 50 እና ከዛ በላይ አምጥተዋል፡፡ በዚህም 83 ነጥብ 6 በመቶ የሚሆኑት ማለፋቸውን ተናግረዋል፡፡

የማለፊያ ነጥብን በተመለከተ ለመደበኛ ተማሪዎች 50 እና ከዛ በላይ ያመጡ ተማሪዎች የሚያልፉ ሲሆን፤ ልዩ ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎች 45 እና ከዛ በላይ ያመጡ  ወደ ቀጣዩ ክፍል የሚሸጋገሩ መሆኑን ማስረዳታቸውን ኢፕድ ዘግቧል፡፡104 ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ ተማሪዎችን ማሳለፋቸውን የተነገረ ሲሆን፤ ተማሪዎች ውጤታቸውን ከዛሬ ጀምሮ መመልከት የሚችሉ መሆኑንም ተገልጿል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
👍3
እስራኤላዊ ዜግነት ያላቸውን የ80 ዓመት አዛውንት በማገት 1.5 ሚሊዮን ብር የጠየቀው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ!

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በአለፋ ወረዳ በሰው ማገት ወንጀል የተጠረጠረ ግለሰብ እጅ ከፈንጅ መያዙን የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል፡፡የዞኑ ፖሊስ መምሪያ የወንጀል መከላከል አስተባባሪ ምክትል ኮማንደር ፈንታሁን አስፋው እንዳስታወቁት ማሬ መኳንንት የተባለው ግለሰብ እስራኤላዊ ዜግነት ያላቸውን የ80 ዓመት የእድሜ ባለፀጋ የሆኑትን አቶ ውዱ አደባባይ የተባሉትን ግለሰብ ሰኔ 26/2015 ዓ.ም ከሻሁራ ከተማ ወደ ፍንጅት ቀበሌ ጫካ ውስጥ በመውሰድ አግተው 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር እንዲከፍሉ ድርድር ሲደረግ መቆየቱን አንስተዋል።

በዚህም የአለፋ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ከዞኑ የፖሊስ መምሪያ ጋር ተቀናጅቶ ባደረገው የኦፕሬሽን ስራ የድርጊቱ ዋና ተዋናይ የሆነውን ማሬ መኳንንትን በቁጥጥር ስር ማድረጉንና 2 ግብረ አበሮቹ ለጊዜው ማምለጣቸውን ተናግረዋል፡፡ምክትል ኮማንደሩ አክለውም ኦፕሬሽኑ የተሳካ እንዲሆን ለተባበሩ የህበረተሰብ ክፍሎችና የፖሊስ አባላት ምስጋናቸውን አቅርበው ህብረተሰቡ ከእንዲህ አይነቱ ወንጀል ራሱን ማራቅ እንዳለበት አሳስበዋል ሲል የወረዳው ኮሙዩኒኬሽን ዘግቧል፡፡

[ማዕከላዊ ጎንደር ዞን]
@YeneTube @FikerAssefa
👍1
አዲሱ 12ኛ ክልል፤ በሳምንቱ መጨረሻ ከነባሩ ደቡብ ክልል ስልጣን ሊረከብ ነው!

የደቡብ ክልል ምክር ቤት ከመጪው አርብ ጀምሮ ለሶስት ቀናት በሚያደርገው መደበኛ ጉባኤ፤ በህዝበ ውሳኔ ለተመሰረተው 12ኛው አዲስ ክልል ስልጣን እንደሚያስረክብ የምክር ቤቱ ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር ወ/ሮ አልማዝ ዘውዱ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናገሩ።ከስልጣን ርክክቡ በኋላ የመዋቅር፣ የህገ መንግስት እና የስያሜ ለውጦችን እንደሚያደርግ የሚጠበቀው የነባሩ የደቡብ ክልል የወደፊት አደረጃጀት ሁኔታ በዚህ ጉባኤ ላይ እንደማይነሳ የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተሯ ገልጸዋል።

አዲሱ የ“ደቡብ ኢትዮጵያ” ክልል የኢፌዴሪ 12ኛ ክልል ሆኖ እንዲደራጅ የፌዴሬሽን ምክር ቤት በሙሉ ድምጽ የወሰነው፤ ከአንድ ወር በፊት ሰኔ መጨረሻ ላይ ባካሄደው መደበኛ ጉባኤ ላይ ነበር። ይህ ውሳኔ በተላለፈበት ወቅት የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር “ነባሩ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ክልል አዲስ ለተመሰረተው ክልል በአፋጣኝ የስልጣን ርክክብ እንዲያደርግ አቅጣጫ ተቀምጧል” ማለታቸው ይታወሳል።

የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ ይህን ቢሉም የደቡብ ክልል የስልጣን ርክክቡን ለማድረግ ከፌዴሬሽን ምክር ቤት ጉባኤ በኋላ አንድ ወር ፈጅቶበታል። በኢትዮጵያ ካሉ ክልሎች የዚህን ዓመት ማጠቃለያ መደበኛ ጉባኤ ለማካሄድ የመጨረሻ የሆነው የደቡብ ክልል፤ እስከ መጪው እሁድ ሐምሌ 30 በሚቆየው ስብሰባው ከስልጣን ርክክብ በተጨማሪ የክልሉን አስፈጻሚ አካላት የ2015 ሪፖርት ይገመግማል ተብሏል።የክልሉ ፍርድ ቤቶች እና የኦዲተር መስሪያ ቤት ሪፖርትም በምክር ቤቱ ጉባኤ ላይ እንደሚቀርብ ተገልጿል።

Via Ethiopia Insider
@YeneTube @FikerAssefa
👍1
ከአማራ ክልል ወደ አዲስ አበባ ሲጓዙ የነበሩ ስልሳ ሦስት ሰዎች በሸኔ ታጣቂዎች መታገታቸው ተገለጸ!

በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ኩዩ ወረዳ ልዩ ሥሙ ቱሉ ሚልኪ በተባለ አካባቢ ሰኞ ሐምሌ 24/2015 በሸኔ ታጣቂ ቡድን ስልሳ ሦስት ሰዎች ታፍነው መወሰዳቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።

የደጀን ከተማ ሰላም እና ጸጥታ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አንዳርጌ ዘውዴ፤ ድርጊቱ የተፈጸመው 65 ሰዎችን አሳፍሮ ከባህር ዳር ከተማ በመነሳት ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ በነበረ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ላይ መሆኑን ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።

የታጣቂ ቡድኑ አባላት እገታውን የፈጸሙት ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ገደማ መሆኑን እንዲሁም አቅመ ደካማ ከሆኑ አንዲት ባልቴት እና አንድ ሽማግሌ በስተቀር ሹፌሩን እና ረዳቱን ጨምሮ በአጠቃላይ 63 ሰዎችን አግተው መውሰዳቸውን በአካባቢው የነበሩ የዓይን እማኞች ተናግረዋል።

Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
👍1
የመቐለ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎቹን መቀበል ጀመረ!

የመቐለ ዩኒቨርስቲ በ2013 ዓ.ም ተመራቂ ለነበሩ የመጀመርያ ዲግሪ መደበኛ ተማሪዎች፣ የድህረ ምረቃ ተማሪዎች ፣ የተከታታይ ትምህርትና የማታ ተማሪዎች እንዲሁም የህክምና ትምህርት ክፍል ተማሪዎች ሐምሌ 26 እና 27/2015 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲው በአካል በመገኘት ምዝገባ እንዲያደርጉ ባሳሰበዉ መሰረት በዛሬዉ እለት ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርስቲዉ መግባት መጀመራቸው ተዘግቧል።ተማሪዎቹ ከሶስት አመታት በኋላ ነዉ ወደ ዩኒቨርስቲው የተመለሱት።

ዩኒቨርስቲው በተመሳሳይ ተመራቂ ላልሆኑ የመጀመርያ ዲግሪ መደበኛ ተማሪዎች ምዝገባ መስከረም 04 እና 05/2016 ዓ.ም የሚከናወን መሆኑን የዩኒቨርሲቲው ሬጂስትራር ጽ/ቤት ማሳወቁ ይታወሳል።

@YeneTube @FikerAssefa
በታጣቂዎች እና በመንግሥት ኃይሎች ግጭት በላሊበላ በረራ መስተጓጎሉ ተነገረ!

በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ላሊበለ ከተማ ዙሪያ በመንግሥት ኃይሎች እና በታጣቂዎች መካከል ግጭት መካሄዱን ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናገሩ::በዚህም ሳቢያ ቢቢሲ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች ማክሰኞ እኩለ ቀን ላይ አካባቢ ማረፍ የነበረበት አውሮፕላን መዳረሻውን ለመቀየር ተገዷል ብለዋል።

የታሪካዊቷ ላሊበላ ከተማ ነዋሪዎች እንዳሉት ማክሰኞ ሐምሌ 25/2015 ዓ.ም. ከከተማዋ በቅርብ ርቀት ላይ ባሉ አካባቢዎች በአገር መከላከያ ሠራዊት እና በታጣቂዎች መካከል የነበረውን ግጭት “ከባድ” ሲሉ ገልጸውታል።ቢቢሲ በከተማዋ ከሚገኙ ምንጭ ለመረዳት እንደቻለው ማክሰኞ ጠዋት የመጀመሪያው አውሮፕላን ከአዲስ አበባ ተነስቶ ላሊበላ አርፏል። ከላሊበላም ወደ አዲስ አበባ መንገደኞችን አሳፍሮ ተመልሷል።

ነገር ግን እኩለ ቀን 6፡50 ላይ ማረፍ የነበረበት አውሮፕላን በከተማዋ ዙሪያ በተፈጠረው ችግር ምክንያት ማረፍ ባለመቻሉ ተመልሷል ብለዋል።ቢቢሲ ያነጋገረው ሌላኛው ነዋሪ በትናንትናው ዕለት ከእኩለ ቀን በፊት የላሊበላ ሹምሸሃ አውሮፕላን ማረፊያ በፋኖ ታጣቂዎች ሥር ገብቶ እንደነበር ገልጿል።

ነዋሪው ተጨማሪ የአገር መከላከያ ሠራዊት አባላት በአውሮፕላን ወደ ላሊበላ እየመጡ ነው የሚል መረጃ ከተናፈሰ በኋላ የፋኖ ታጣቂዎች አየር ማረፊያውን ስለመቆጣጠራቸው ሰምቻለሁ ብለዋል።ቢቢሲ በላሊበላ አየር ማረፊያ ስላጋጠመው ክስተት ከተጨማሪ ገለልተኛ ወገን ማጣራት አልቻለም።በላሊበላ አየር ማረፊያ ስለተከሰተው ሁኔታ ከኢትዮጵያ ኤርፖርቶች ድርጅት እና ከአየር መንገድ መረጃ ለማግኘት ቢቢሲ ያደረግነው ጥረት እስካሁን አልሰመረም።

ነዋሪዎች የላሊበላ አየር ማረፊያ እራሳቸውን ፋኖ ብለው በሚጠሩ ታጣቂዎች ቁጥጥር ሥር ይገኛል ይበሉ እንጂ አየር መንገዱ ነገ ወደ ላሊበላ ለሚደረጉ በረራዎች ቲኬቶችን በድረ-ገጹ አማካይነት እየሸጠ ነው።ታጣቂዎች ከላሊበላ ከተማ 25 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘውን የላሊበላ ሹምሸሃ አየር ማረፊያ እካባቢ ሲይዙ በሰው እና በንብረት ላይ የደረሰ ጉዳት ስለመኖሩ የተባል ነገር የለም።

ለደኅንነታቸው ሲባል ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈቀዱ ነዋሪ ላሊበላ ከተማ ውስጥ ማክሰኞም ሆነ ዛሬ ረቡዕ ንጋት ላይ ምንም አይነት የተለየ እንቅስቃሴ እንደሌለ ገልጸው፤ በጋሸና እና በሰቆጣ አቅጣጫዎች ግን የተኩስ ድምጽ ይሰማል ብለዋል።በረራ ያስተጓጎለው ግጭት የተሰማው በአገር መከላከያ ሠራዊት እና እራሳቸውን ፋኖ ብለው በሚጠሩ ታጣቂዎች መካከል የሚከሰተው ግጭት እተስፋፋ በመጣበት ወቅት ነው።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
1👍1
ብሔራዊ ባንክ ገዥ አቶ ማሞ ምህረቱ ከአሜሪካ ግምጃ ቤት ምክትል ረዳት ፀሐፊ ጋር ተወያዩ!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ አቶ ማሞ ምህረቱ ከአሜሪካ ግምጃ ቤት ምክትል ረዳት ፀሐፊ ኤሪክ ሜየር ጋር በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ማሻሻያ መርሐ-ግብር ላይ ተወያዩ።

በውይይቱም ብሔራዊ ባንክ ገዥ አቶ ማሞ ምህረቱ የአሜሪካ ግምጃ ቤት በኢትዮጵያ እድገትን ለማፋጠንና የኢኮኖሚ መረጋጋት እንዲመጣ እየተወጣ ላለው ገንቢ ሚና ምስጋና ማቅረባቸውን ባንኩ በማህበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
የመዲናዋ ነዋሪዎች የቤት ጣሪያና ግድግዳ ግብር ክፍያቸውን እስከ ነሐሴ 30 እንዲያጠናቅቁ ማሳሰቢያ ተሠጠ!

የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የመዲናዋ ነዋሪዎች የቤት ጣሪያና ግድግዳ ግብር ክፍያቸውን እስከ ነሐሴ 30 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ እንዲያጠናቅቁ አሳሰበ።የአዲስ አበባ ከተማ ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ አደም ኑሪ ፥ በቤት ወይም በከተማ ቦታ ኪራይና የቤት ግብር አዋጅ መሰረት የጣሪያና ግድግዳ የግብር ክፍያ ሲተገበር መቆየቱን ጠቅሰዋል።

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት አዲስ የገበያ ጥናት በማድረግ በሚያዝያ ወር ላይ ወቅታዊ የማድረግ ስራ መሰራቱን አስታውሰዋል።በዚህም መሰረት እንዲከፍሉ ይጠበቅባቸው የነበሩ ሰዎች እስካሁንም በመክፈል ላይ መሆናቸውን ገልጸው ፥ ከሚጠበቀው አንጻር በርካቶች ገና ናቸው ብለዋል።

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa