YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.87K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የኢሚግሬሽንና የዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተርና ሌሎች ሁለት ም/ዳይሬክተሮች ከስልጣናቸው ተነሱ።

የኢሚግሬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ ብሩህተስፋ ሙልጌታን ጨምሮ ሌሎች ሁለት ም/ዳይሬክተሮች ከስልጣን መነሳታቸውን ዋዜማ ዘግባለች።

@YeneTube @FikerAssefa
👍1
YeneTube
የኢሚግሬሽንና የዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተርና ሌሎች ሁለት ም/ዳይሬክተሮች ከስልጣናቸው ተነሱ። የኢሚግሬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ ብሩህተስፋ ሙልጌታን ጨምሮ ሌሎች ሁለት ም/ዳይሬክተሮች ከስልጣን መነሳታቸውን ዋዜማ ዘግባለች። @YeneTube @FikerAssefa
በተያያዘ ዜና ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሹመዋል።

አዲሷ ተሿሚ ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት ከዚህ ቀደም የቱሪዝም ሚንስትር ዲዔታ ፣ በውጪ ጉዳይ ሚር የዲያስፖራ አገልግሎትና በውጪ ሀገር በዲፕሎማቲክ ሚስዮን ውስጥ ይሰሩ እንደነበር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

@YeneTube @FikerAssefa
371ሺህ የቀድሞ ታጣቂዎችን መልሶ ለማቋቋም ዝግጅት እየተደረገ ነው!

371ሺህ የሚደርሱ የቀድሞ ታጣቂዎችን መልሶ የማቋቋም ሥራ ለመሥራት ዝግጅት እየተደረገ እንደሆነ ብሔራዊ ተሐድሶ ኮሚሽን ገለጸ፡፡

የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አምባሳደር ተሾመ ቶጋ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በሰሜኑ ጦርነት እንዲሁም በሌሎች አካባቢዎች የፖለቲካ ዓላማቸውን በትጥቅ ለማስፈጸም ተደራጅተው ሲንቀሳቀሱ የነበሩና በአሁኑ ጊዜ ወደ ሰላማዊ ትግል ለመግባት የወሰኑ 371 ሺ የሚደርሱ የቀድሞ ተዋጊዎችን በአንድ ቦታ የማሰባሰብ እና መልሶ የማቋቋም ሥራዎችን ለመሥራት ዝግጅት እየተደረገ ነው፡፡

(ኢ ፕ ድ)
@YeneTube @FikerAssefa
👍1
በ2015 በጀት ዓመት ከቡና የወጪ ንግድ ከአንድ ነጥብ ሦስት ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሳሕለማርያም ገብረመድህን ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በ2015 በጀት ዓመት 360 ሺህ 144 ቶን ቡና በላይ በመላክ አንድ ነጥብ 8 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ 240 ሺህ 369 ቶን በላይ ቡና በመላክ ከአንድ ነጥብ 3 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ማግኘት ተችሏል፡፡ ይህም የዕቅዱን 67 በመቶ ማሳካት ተችሏል፡፡

በበጀት ዓመቱ የተላከው ቡና መዳረሻ ሀገራት መካከልም ሳዑዲ ዓረቢያ በመጠን 48 ሺህ 413 ነጥብ 39 ቶን ሲሆን በገቢ 224 ነጥብ 84 ሚሊዮን ዶላር፣ ጀርመን በመጠን 36 ሺህ 065 ነጥብ 71 ቶን ቡና፤ በገቢ ደግሞ 173 ነጥብ 47 ሚሊዮን ዶላር፣ አሜሪካ በመጠን 21ሺህ 020 ነጥብ 86 ቶን፣ በገቢ 150 ነጥብ 47 ሚሊዮን ዶላር ድርሻ ኖሯቸው ከ1ኛ እስከ 3ኛ ደረጃን መያዛቸውን ጠቅሰዋል፡፡

አቶ ሳሕለማርያም ወደ ውጪ ከተላከው የቡና ምርት የተገኘው ገቢ ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር እጅግ መጠነኛ ቅናሽ እንዳለው ገልጸው፤ ከዓለም አቀፍ የቡና ዋጋ መቀነስ፣ ከነበሩት ሌሎች ፈታኝ ሁኔታዎች አንጻር ሲታይ በእጅጉ የሚበረታታ ውጤት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በተለይ በበጀት ዓመቱ ቡና ላኪዎች በተለያዩ ኤግዚቢሽኖች ላይ በመሳተፍ የሀገሪቱን ቡና የማስተዋወቅ ሥራ ሠርተዋል፡፡ በዚህም 141 ቡና ላኪዎችን እንዲሳተፉ በማመቻቸት 47 ሺህ 424 ቶን ቡና ከገዥዎች ጋር ኮንትራት በመግባት 76 ሚሊዮን 500 ሺህ ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የውጭ ምንዛሪ ገቢ መገኘቱን ገልጸዋል፡፡

Via EPA
@YeneTube @FikerAssefa
“የጋምቤላ ክልል የጸጥታ ኹኔታ የመንግሥትን ተጨማሪ ትኩረት የሚሻ ነው” ኢሰመኮ

በጋምቤላ ክልል ያለው የጸጥታ ሁኔታ በነዋሪዎች ላይ ያደረሰው ከፍተኛ ጉዳት እና የሰብአዊ መብቶች ጥሰት፤ የመንግሥትን ተጨማሪ ትኩረት የሚሻ ነው ሲል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አሳሰበ።ኮሚሽኑ ከግንቦት ወር 2015 ጀምሮ በተለያዩ የጋምቤላ ክልል አካባቢዎች ሲከሰቱ የቆዩ የትጥቅ ግጭቶችን፣ የታጠቁ ቡድኖች ጥቃቶችንና አጠቃላይ የጸጥታ ችግሮችን እና በዚህ ሳቢያ የሚደርሱ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን እየተከታተለ እንደሚገኝ አስታውቋል።

በተለይም ከግንቦት ወር 2015 ጀምሮ በክልሉ ላለው የጸጥታ ችግር መነሻ፣ በኢታንግ ልዩ ወረዳ በተወሰኑ ነዋሪዎች መካከል የተነሳ አለመግባባት መሆኑ ማረጋገጡን የገለጸ ሲሆን፤ ይሄው አለመግባባት በፍጥነት ወደ ብሔርን መሠረት ያደረገ ውጥረት እንደተሸጋገረ ነዋሪዎች ነግረውኛል ብሏል።ይህንን ተከትሎም የተለያየ ብሔር ታጠቂ ቡድኖች በኢታንግ ልዩ ወረዳ፣ ጋምቤላ ወረዳ፣ ጎግ ወረዳ፣ በጋምቤላ ከተማ ብሔር ብሔረሰቦች ተብሎ በሚጠራው አካባቢ እና በከተማው በሚገኙ ሌሎች ሰፈሮች ላይ ጥቃት መፈጸማቸውን ገልጿል፡፡ በዚህም ምክንያት በርካታ ሲቪል ሰዎች እንደተገደሉ፣ የአካል ጉዳት፣ መፈናቀል እና ንብረት ውድመት መድረሱን አስታውቋል።

በጸጥታው ችግር ምክንያት ገና ወደ አካባቢዎቹ በአካል ደርሶ ምርመራ ለማድረግ አለመቻሉን የገለጸው ኮሚሽኑ፤ ነገር ግን ነዋሪዎች በአንዳንድ አካባቢዎች ያሉ መንደሮች ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ መውደማቸውን ነዋሪዎች ገልጸውልኛል ብሏል።በክልሉ በተደጋጋሚ ከጎረቤት አገር ደቡብ ሱዳን በሚመጡ ታጣቂ ቡድኖች በሚደርሱ ጥቃቶች እንዲሁም፤ አልፎ አልፎ በክልሉ በሚኖሩ ብሔሮች መካከል በሚከሰቱ ግጭቶች ሳቢያ ከፍተኛ ጉዳት የሚደርስ መሆኑም በመግለጽ፤ ክልሉ ወደ 350 ሺሕ የሚጠጉ የደቡብ ሱዳን ስደተኞችን በስምንት የተለያዩ ካምፖች እንደሚያስተናግድም አስታውሷል።

ከኹለት ወራት በላይ ለዘለቀው የጋምቤላ ክልል የጸጥታ ችግር እና በክልሉ ልዩ ልዩ አካባቢዎች በመድረስ ላይ ያሉ ግጭቶች ተሳታፊዎችን በተመለከተ ተጎጂዎችም ሆነ የክልሉ የጸጥታ እና የአስተዳደር ኃላፊዎች፤ የተለያዩ ብሔር ታጣቂ ቡድኖችን በኃላፊነት እንደሚጠቅሱም ኢሰመኮ ገልጿል።በአንዳንድ አካባቢዎች የክልሉ ኑዌር ብሔረሰብ ታጣቂዎች፣ በሌላ አካባቢ የአኝዋ ብሔረሰብ ታጣቂዎች፣ እንዲሁም ከጎረቤት አገር ደቡብ ሱዳን የመጡ ታጣቂዎች እና በአንዳንድ የስደተኛ ካምፖች ውስጥ እንደሚኖሩ የተገለጸ ሰዎች ጭምር በግጭቶቹ ተሳታፊ መሆናቸውን ኮሚሽኑ አመላክቷል፡፡

“እነዚህ ጥቃቶች እና ግጭቶች በአብዛኛው ብሔር ናቸው” ያለው ኮሚሽኑ፤ “በሌላ በኩል ግጭት የሚደርስባቸውን አካባቢዎች ያለ የብሔር ልዩነት ኹሉንም ነዋሪዎች አካባቢውን ሸሽቶ ለመፈናቀል፣ ለንብረት ውድመት እና ለሌሎች የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ያጋለጠ” መሆኑን ጠቁሟል።

የክልሉ መንግሥት ከሐምሌ 12/2015 ጀምሮ ላልተወሰኑ ቀናት ተግባራዊ የሚሆን ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት እስከ ጠዋት 12፡00 ሰዓት የሚዘልቅ እና በኹሉም የክልሉ አካባቢዎች ተፈጻሚ የሚሆን የሰዓት እላፊ ገደብ፣ እንዲሁም ከተመደቡ የጸጥታ አካላት ውጪ መሣሪያ ይዞ የመንቀሳቀስ ገደብ መጣሉ ይታወሳል።ከዚህ በተጨማሪም የፌዴራል ፖሊስና የአገር መከላከያ ሰራዊት የተውጣጣ ኃይል ከክልሉ የጸጥታ ኃይሎች በተጨማሪ መሰማራቱን የገለጸው ኢሰመኮ፤ ይህም የክልሉን ጸጥታ ኹኔታ በተወሰነ መልኩ እንዳረጋጋውና በጋምቤላ ከተማ ተቋርጦ የነበረው መደበኛ እንቅስቃሴ እንዲጀመር ማስቻሉን ገልጿል።

ሆኖም በክልሉ የተጣለው የሰዓት እላፊ ገደብ አፈጻጸም ነዋሪዎችን ለተጨማሪ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች እንዳይዳርግ መከላከልን ጨምሮ፣ በክልሉ በተለያየ ወቅት የሚያገረሹ እና ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመሩ ነዋሪዎችን ለከፍተኛ ጉዳት የዳረጉ ጥቃቶችን እና ግጭቶችን በዘላቂነት ለማስቆም ተጨማሪ ትኩረት እና ክትትል ማድረግ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አሳስቧል።ስለሆነም በክልሉ የተሰማራውን ከፌዴራል እና ከክልሉ የጸጥታ አካላት የተውጣጣ ኃይል ማጠናከር እና አስፈላጊውን ድጋፍ ከመስጠት ተግባር ጎን ለጎን፤ ተጠያቂነት ማረጋገጥ፣ በደረሰው ግጭት ሳቢያ አካባቢውን ለቀው ለሸሹ ነዋሪዎች አስፈላጊውን ሰብአዊ ድጋፍ ማድረስ፣ በግጭቱ የተነሳ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ተገቢውን የሕክምና አገልግሎት እንዲያገኙ ሁኔታዎችን ማመቻቸት እንደሚገባም ገልጿል።

እንዲሁም ለረጅም ዓመታት እና በየጊዜው ወደ ግጭት ለሚያመራው በተቀባይ ማኅበረሰብ እና በስደተኞች መካከል ላለው የላላ ግንኙነት ዘላቂ መፍትሔ ማፈላለግ እንደሚያስፈልግም ኮሚሽኑ አሳስቧል::

@YeneTube@FikerAssefa
ትዊተር አርማውን ከምናውቃት ወፍ ወደ ‘ኤክስ’ ምልክት ሊቀይር መሆኑን ኢላን መስክ ገለጠ!

የትዊተር ባለቤት ኢላን መስክ የትዊተር ‘ሎጎ’ ከተለመደው የወፍ ምልክት ወደ ‘ኤክስ’ [X] ሊቀይር መሆኑን ገልጧል።የቢዝነስ አርማውን ወደ ኤክስ ኮርፕ የቀየረው መስክ “እንደውም ይህን ሊሆን የሚገባው ቀድሞ ነበር” ብሏል።

ዘገባዎች እንደሚጠቁሙት ቢሊየነሩ ልክ እንደ ቻይናው ዊቻት ኤክስ የተባለ “ሁሉን ያካተተ” መተግበሪያ የመሥራት ሐሳብ አለው።የትዊተር አርማ የሆነችው ወፍ እንደምትቀየር እሑድ ዕለት ያሳወቀው መስክ “በቃ ሁላችንም የትዊተር አርማን ቻው የምንልበት ጊዜ ተቃርቧል። ቀስ በቀስ ደግሞ ሁሉንም ወፎች” ብሏል።

የዛኑ ዕለት አዲስ ጊዜያዊ አርማ ይፋ እንደሚደረግም ያሳወቀው መስክ የእንግሊዝኛ ኤክስ ፊደል ምልክት ያለበት አርማ ለጥፏል።የትዊተር ሥራ አስፈፃሚ ሊንዳ ያካሪኖ በትዊተር ገፃቸው አርማ መቀየሩ አስደሳችና አዲስ ጅማሮ ነው ብላለች።በእስያ ሃገራት ለምሳሌ በሕንድ ፔይቲኤም፤ በኢንዶኔዥያ ደግሞ ጎጄክ የሚባሉ መተግበሪያዎች ሁሉን አቀፍና በርካቶች የሚጠቀሙባቸው ናቸው።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔ 17 ቢሊዮን ብር ዓመታዊ በጀት አጸደቀ!

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔ ለ2016 በጀት ዓመት የሚሆን 17 ቢሊዮን ብር በጀት አጸደቀ። የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ካጸደቀው በጀት ውስጥ 74 በመቶው የሚሸፈነው የፌደራል መንግስት ለትግራይ ክልል ከሚያስተላልፈው የድጋፍ በጀት ነው።

የትግራይ ክልል የሰሜኑ ጦርነት ከተነሳ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ በመደበኛ ሁኔታ በጀት ያጸደቀው፤ ባለፈው ሳምንት አርብ ሐምሌ 14፤ 2015 እንደሆነ የክልሉ ፕላን ኮሚሽን ኮሚሽነር ወ/ሮ ሀንሳ ተክላይ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል። ለክልሉ መንግስት የሚመደበው በጀት ከዚህ ቀደም ይጸድቅ የነበረው በትግራይ ክልል ምክር ቤት ነበር።

የ2016 በጀት በጊዜያዊ አስተዳደሩ ካቢኔ የጸደቀው የትግራይ ክልል ምክር ቤት ህግ የማውጣት ስልጣኑን ለክልሉ ስራ አስፈጻሚ አካል በመስጠቱ መሆኑን ኮሚሽነሯ አስረድተዋል።  የክልሉ ካቢኔ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ባደረገው ስብሰባ፤ ለ2016 በጀት ዓመት 17 ቢሊዮን ብር በጀት ማጽደቁን የጊዜያዊ አስተዳደሩ ካቢኔ አባል የሆኑት ወ/ሮ ሀንሳ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።

ይህ በጀት የሰሜኑ ጦርነት ከመቀስቀሱ አስቀድሞ ለ2013 በጀት ዓመት ጸድቆ ከነበረው “ከ18 ቢሊዮን ብር በላይ” ጋር ሲነጻጸር ቅናሽ ማሳየቱን ጠቁመዋል። የአሁኑ በጀት በ2012 በክልሉ ምክር ቤት ከጸደቀው በጀት ጋር ሲነጻጸር ያለው ልዩነት የ300 ሺህ ብር ገደማ ብቻ ነው።

Via Ethiopia Insider
@YeneTube @FikerAssefa
👎1
🔥🔥አስቸኳይ ክፍት የስራ ቅጥር💥💥

🔴በሁሉም ስራ ዘርፎች ሰራተኞችን በብዛት እንፈልጋለን። 
🔥ቀጥታ ወደ ስራ ቦታ እንልካለን።

📞 ስልክ:- 09 78 88 18 19
                 09 77 64 18 19

💥ጉዳይ አስፈፃሚ/smart phone ያለው/
      🔹የት/ደረጃ:10
      🔹የስራ ልምድ: 0አመት ጀምሮ
      🔹ደሞዝ:5000+ የቀን አበል
💥ካሸር አሰልጥኖ
      🔹የት/ት ደረጃ= 12/ዲፕሎማ
      🔹ልምድ= 0 አመት
      🔹ደሞዝ= 5,500
💥ባርማን/ባሬስታ
      🔹የት/ት ደረጃ= መፃፍ ማንበብ
      🔹ልምድ= ያለው
      🔹ደሞዝ=በስምምነት
💥ሪሴፕሽን ለገስት ሀውስ/ለሆቴሎች
     🔹የት/ደረጃ:10ኛ- ከዚያ በላይ
     🔹የስራ ልምድ: 0 አመት ጀምሮ    
     🔹ደሞዝ፡ 4,500
💥ቤቲንግ ቤት ካሸር (በፈረቃ)
     🔹የት/ት ደረጃ= 10ኛ በላይ
     🔹የስራ ልምድ=0
     🔹ደሞዝ=5000
💥 ሼፍ/ዋና እና ረዳት/
     🔹የት/ት ደረጃ= 10ኛ በላይ
     🔹የስራ ልምድ=ያለው
     🔹ደሞዝ=6000-10,000

ለበለጠ መረጃ
🏘አድራሻ: አ.አ 22 ጎላጎል ሲደርሱ ወደ ቦሌ በሚወስደው መንገድ ወረድ ብለው  ሎተስ ህንፃ ግራውንድ ላይ ቢ.ቁ 006

👇👇https://tttttt.me/JobsAtHewan
በጉራጌ ዞን በታጠቁ ኃይሎች በተፈጸመ ጥቃት ስድስት ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ!

በደቡብ ክልል ጉራጌ ዞን በምስራቅ መስቃን ወረዳ፤ ሐሙስ ሐምሌ 13/2015 እና ዕሁድ ሐምሌ 16/2015 የታጠቁ ኃይሎች በፈጸሙት ጥቃት ስድስት ሰዎች መገደላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል።በወረዳው በቼ እና ዲዳ በተባሉ የቀበሌ ከተሞች፤ ምሽት 3 ሰዓት ላይ ጥቃቱ እንደተሰነዘረ እና ግድያዎች እንደተፈጸሙ ምንጮች ከስፍራው ለአዲስ ማለዳ አስታውቀዋል፡፡

ታጣቂዎቹ ጥቃቱን ካደረሱ በኋላ ከአካባቢው መሰወራቸው የተገለጸ ሲሆን፤ እስካሁን በቁጥጥር ሥር የዋለ አካል አለመኖሩ ተጠቅሷል።በተጠቀሰው ምሽት ላይ ሦሰት ሰዓት አካባቢ በቼ ቀበሌ ውስጥ በተሰነዘረ ጥቃት ሦስት ሰዎች መገደላቸው የታወቀ ሲሆን፤ በተመሳሳይ ዕሁድ ሐምሌ 17/2015 ምሽት ኹለት ሰዓት ገደማ አንድ አባውራ ከነባለቤታቸው እና ጎረቤታቸው ከሆኑ ግለሰብ ጋር መገደላቸውን አዲሰ ማለዳ ያገኘችው መረጃ ያመላክታል።

በመስቃንና ማረቆ ብሔረሰብ መካከል ባለው የቆየ አለመግባባት በተደጋጋሚ የሚፈጸም ማንነት ተኮር ጥቃት መኖሩ የተገለጸ ሲሆን፤ በአሁኑ ወቅትም ለአካባቢው ማህበረሰብ በነጻነት መንቀሳቀስ አስቸጋሪ መሆኑ ተመላክቷል።እንደ ነዋሪዎች ገለጻ፤ በአካባቢው ባለው የሰላም እጦት ሳቢያ አብዛኛውየመንግሥት ሠራተኞች ለደኅንነታቸው በመስጋት በሥራ ገበታቸው ላይ እንደማይገኙ እና ብዙ የመንግሥት መስሪያ ቤቶች ዝግ መሆናቸውን ብሎም የተከፈቱትም አገልግሎት እየሰጡ አለመሆኑን ተነግሯል።

የጉራጌ ዞን ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ጠጄ መሀመድ ከሐሙስ ሐምሌ 13/2015 እስከ ሐምሌ 17/2015 ድረስ ስድስት ሰዎች መገደላቸውን ሪፖርት እንደደረሳቸው ጠቅሰው፤ “በቂ የጸጥታ አካላት ወደቦታው ልከናል” ሲሉ ገልጸዋል፡፡ ኃላፊው አክለውም፤ ግድያውን በሚመለከት ማንነትን መሰረት ያደረገ ነው ወይም አይደለም? የሚለውን ጉዳይ በሚመለከት በመጣራት ላይ የሚገኝ ሲሆን፤ በጊዜው ይፋ እንደሚደረግም አስታውቀዋል።

በዞኑ ኹለቱ ወረዳዎች መካከል ዓመታትን ያስቆጠረው ግጭት ዕልባት ሳያገኝ የቀጠለ ሲሆን፤ በተደጋጋሚ ሰላም ሚኒስቴርን ጨምሮ በርካታ አካላት ለችግሩ ዕልባት ለመስጠት ሙከራ ሲያደርጉ መቆየታቸው ይታወሳል። በዚህም መሰረት ከአራት ዓመታት በፊት ሰላም ሚኒስቴር ከወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመሆን ሰፊ ሥራዎችን ይሰራ እንደነበር ነገር ግን ይህ ነው የሚባል ለውጥ ማምጣት ባለመቻሉ ችግሮች ተባብሰው መቀጠላቸውን ለማወቅ ተችሏል።

Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
😭1
በአንዳንድ የአማራ፣ አፋርና ትግራይ አካባቢዎች ያልፈነዳ የጦርነት ቅሪት እጅግ አሳሳቢ መሆኑ ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ገለፀ።

ኮሚቴው ይህን ያለው እ.ኤ.አ ከጥር እስከ ሰኔ 2023 በኢትዮጵያ የነበረው እንቅስቃሴ አስመልክቶ ሐምሌ 15 ቀን 2015 ዓ.ም በ8 ገፅ ቀንብቦ ባወጣው ሪፖርት ነው፡፡በሪፖርቱ እንደተመላከተው የጦርነት ቀጣና በነበሩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ያለፈነዱ ፈንጂዎች በአካባቢው ለሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች በተለይም ለህፃናት አስጊ ሁኖ መቆየቱን ገልጿል፡፡

ምንም እንኳን ከሰላም ስምምነቱ በኃላ የሰብዓዊ እርዳታዎችን ለማቅረብ ምቹ ሁኔታዎች በአንፃራዊነት ቢመቻቹም አሁንም ድረስ ግን በመላ አገሪቱ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ሰብዓዊ መብታቸው እየተጣሰ በመሆኑ ከፍተኛ ጥበቃና እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ተመላክቷል።

ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ጋር በጋራ በመሆን በአማራ፣ አፋር፣ ኦሮሚያ፣ ሶማሌና ትግራይ በሚገኙና ለችግር ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ለመድረስ እየሰራ መሆኑን ኮሚቴው ገልፆል፡፡

የንፁህ መጠጥ ውሃ፣ አስፈላጊ የሚባሉ የሰብዓዊ እርዳታዎችን እንዲሁም የህክምና እርዳታዎች ሲያደርግ መቆየቱን የገለፀው ሪፖርቱ በተለይ በትግራይ ክልል የነፍሰ ጡርና የሚያጠቡ እናቶችና ህፃናት አመጋገብ ሁኔታ አሳሳቢ እየሆነ በመምጣቱ ህይወትን ለመታደግ አፋጣኝ ርምጃ እንድንወስድ አድርጎናል ብሏል፡፡

ባለፉት ጊዜያትም ኮሚቴው 1 ሺህ 156 የተጠፋፉ ሰዎችን ከቤተሰቦቻቸው ጋር ማገናኘቱን፣ 14 ሺህ 933 ለሚሆኑት ውሃ አቅርቦት ማድረሱን፣ 116 ሺህ 730 ለሚሆኑት አስፈላጊ የቤት ቁሳቁሶች ማቅረቡንና ለ76 የጤና ተቋማት በመደበኛነት መደገፉን አስታውቋል፡፡

[Asham]
@YeneTube @FikerAssefa
🔥🔥አስቸኳይ ክፍት የስራ ቅጥር💥💥

🔴በሁሉም ስራ ዘርፎች ሰራተኞችን በብዛት እንፈልጋለን። 
🔥ቀጥታ ወደ ስራ ቦታ እንልካለን።

📞 ስልክ:- 09 78 88 18 19
                 09 77 64 18 19

💥ጉዳይ አስፈፃሚ/smart phone ያለው/
      🔹የት/ደረጃ:10
      🔹የስራ ልምድ: 0አመት ጀምሮ
      🔹ደሞዝ:5000+ የቀን አበል
💥ካሸር አሰልጥኖ
      🔹የት/ት ደረጃ= 12/ዲፕሎማ
      🔹ልምድ= 0 አመት
      🔹ደሞዝ= 5,500
💥ባርማን/ባሬስታ
      🔹የት/ት ደረጃ= መፃፍ ማንበብ
      🔹ልምድ= ያለው
      🔹ደሞዝ=በስምምነት
💥ሪሴፕሽን ለገስት ሀውስ/ለሆቴሎች
     🔹የት/ደረጃ:10ኛ- ከዚያ በላይ
     🔹የስራ ልምድ: 0 አመት ጀምሮ    
     🔹ደሞዝ፡ 4,500
💥ቤቲንግ ቤት ካሸር (በፈረቃ)
     🔹የት/ት ደረጃ= 10ኛ በላይ
     🔹የስራ ልምድ=0
     🔹ደሞዝ=5000
💥 ሼፍ/ዋና እና ረዳት/
     🔹የት/ት ደረጃ= 10ኛ በላይ
     🔹የስራ ልምድ=ያለው
     🔹ደሞዝ=6000-10,000

ለበለጠ መረጃ
🏘አድራሻ: አ.አ 22 ጎላጎል ሲደርሱ ወደ ቦሌ በሚወስደው መንገድ ወረድ ብለው  ሎተስ ህንፃ ግራውንድ ላይ ቢ.ቁ 006

👇👇https://tttttt.me/JobsAtHewan
የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና መሰጠት ጀመረ!

የ2015 ዓ.ም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና መሰጠት ጀምሯል።

በዛሬው ዕለት የ12ኛ ክፍል የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች ፈተናቸውን እየወሰዱ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የማህበራዊ ሳይንስ ፈተና ከሐምሌ 19 እስከ 21 ቀን 2015 ዓ.ም እንደሚሰጥ ታውቃል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በዐማራ እና አፋር ክልሎች በሳምንት ውስጥ ሦስት የረድኤት ሠራተኞች እንደተገደሉ ተገለጸ!

ባለፈው የአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ፣ በአፋር እና ዐማራ ክልሎች፣ ሦስት የረድኤት ሠራተኞች እንደተገደሉ፣ የኢትዮጵያ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ገለጸ።

ከሦስቱ ሠራተኞች፣ ሁለቱ በአፋር አንዱ ደግሞ በዐማራ ክልል እንደተገደሉ የተናሩት የምክር ቤቱ ዋና ዲሬክተር ኄኖክ መለሰ፣ ከሰሜኑ ጦርነት በኋላ፣ በቁጥር 40 የሚደርሱ የሰብአዊ ድጋፍ ሠራተኞች መገደላቸውን ተናግረዋል፡፡

ግድያ የተፈጸመባቸው ሠራተኞች ይሠሩባቸው የነበሩትን ተቋማት ከመግለጽ የተቆጠቡት አቶ ኄኖክ፣ ለረድኤት ሠራተኞች ጥበቃ እና ከለላ እንዲደረግ ጠይቀዋል፡፡

Via VoA
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ተመልካቾቹን በየወሩ 10 ብር ሊያስከፍል መሆኑ ተሰማ፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሐምሌ 19 ቀን 2015 ዓ.ም ባወጣው አጭር መግለጫ እንዳመለከተው ‹‹ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ከሰኔ ወር ጀምሮ የቴሌቪዥን አገልግሎት ክፍያ በየወሩ 10 ብር ከወርሃዊ ኤሌከትሪክ ፍጆታ ቢል ጋር ተዳምሮ እንዲዘጋጅ መደረጉን ›› ይፋ አድርጓል፡፡

መግለጫው ‹‹ ከ50 ኪሎ ዋት ስዓት በላይ የኤሌክትሪክ ሃይል ›› የሚጠቀሙ ደንበኞቹን ‹‹ በሙሉ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቲቪ) በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት አዋጅ ቁጥር 1278/2015 ዓ.ም በተሰጠው ስልጣን መሰረት አመታዊ የቴሌቪዥን አገልግሎት ክፍያ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የፍጆታ ሂሳብ ክፍያ ቢል ጋር እንዲሰበስብ መወሰኑን ›› አስታውሷል፡፡

በዚህም ‹‹ የኤሌክትሪክ ፍጆታና የቴሌቪዥን አገልግሎት ክፍያ ›› በጋራ እንዲሚፈፀም አገልግሎቱ አመልክቷል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
👍1
የአለም ባንክ ግሩፕ ፕሬዝዳንት አጃይ ባንጋ በሚቀጥለው ሳምንት ወደ አዲስ አበባ እንደሚመጡ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር አስታውቋል።

ፕሬዝዳንቱ ሐምሌ 25 ቀን 2015 ዓ.ም አዲስ አበባ ይገባሉ የተባለ ሲሆን ከኢትዮጵያ ከፍተኛ መሪዎች ጋር እንደሚመክሩም ተገልጿል።

@YeneTube @FikerAssefa
ነገ በሚጀመረው ሁለተኛዉ የሩሲያ እና የአፍሪቃ ሃገራት የመሪዎች ጉባኤ ለመገኘት የተለያዩ የአፍሪቃ ሃገራት መሪዎች ሩሲያ እየገቡ ነው።

የአፍሪቃ ሩሲያ መሪዎች ጉባኤ በተያዘለት የጊዜ ቀጠሮ መሠረት ከነገ ጀምሮ በቅዱስ ፒተርስበርግ ከተማ ለሁለት ቀናት እንደሚካሄድ ተገልጿል። የሩሲያ ባለሥልጣናት እንዳሉት የአፍሪቃ ሃገራት መሪዎች በጉባኤዉ ላይ እንዳይከፈሉ ምዕራባዉያን መንግሥታት ከፍተኛ ግፊት ሲያደርጉ ነበር። የኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስትር በትዊተር ገጻቸው ይፋ እንዳደረጉት በስብሰባው ላይ ለመገኘት ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቅ ከቀትር በፊት ዛሬ ወደ ሩሲያ ተጉዘዋል።

የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድም ሩሲያ ከገቡት የአፍሪቃ ሃገራት መሪዎች አንዱ ናቸው። የሩሲያ ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ከጉባኤው አስቀድሞ ከኢትዮጵያ እና ከግብጽ መሪዎች ጋር እንደሚነጋገሩ ተጠቁሞ ነበር።ፑቲን ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጋር ባደረጉት ውይይትም የሩሲያ ኢትዮጵያ ግንኙነት 125 ዓመታትን እንዳስቆጠረ በማስታወስ ከአፍሪቃ ቀዳሚዋ የሞስኮ አጋር እንደሆነች ተናግረዋል።

ምንም እንኳን የተቀዛቀዘ ቢመስልም አሁንም የሁለቱ ሃገራት የንግድ ትስስር 56 በመቶ መድረሱን መግለጻቸው ተዘግቧል።ሩሲያ የዩክሬን እህል ለዓለም ገበያ እንዳይቀርብ ያደናፈውን ውሳኔዋን በማስመልከት ከአፍሪቃ ሃገራት መሪዎች ጋር እንደምትወያይ ዘገባዎች ያመለክታሉ።

[DW]
@YeneTube @FikerAssefa
የአዲስ አበባ አስተዳደር ለመኖሪያ ቤት ግንባታ በአጋርነት ለመስራት የመረጣቸው የግል ሪል ስቴት አልሚዎች ከግማሽ ትሪሊዮን ብር በላይ በኾነ ወጪ የመኖሪያ ቤቶች ግንባታ ሊጀምሩ መኾኑን ሪፖርተር ዘግቧል።

አስተዳደሩ በቀረጸው 70/30 የመንግሥትና የግል አጋርነት የቤት ግንባታ መርሃ ግብር እንዲሳተፉ የመረጣቸው 68 ሪል ስቴት አልሚዎች ናቸው። መኖሪያ ቤቶቹን ለመገንባት ከተመረጡት መካከል፣ ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ፣ ፍሊንትስቶን ሆምስና ጊፍት ሪል ስቴት እንደሚገኙበት ዘገባው ጠቅሷል። የከተማ አስተዳደሩ ድርሻ ከሊዝ ነጻ የኾነ የመኖሪያ ቤት መገንቢያ መሬት ማቅረብ ሲኾን፣ አልሚዎቹ ደሞ ቤቶቹን ገንብተው ማጠናቀቅና 30 በመቶውን ለከተማ አስተዳደሩ ማስረከብ መኾኑን ዘገባው አመልክቷል።

@YeneTube @FikerAssefa
የአማራ ክልል የሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፊ እና የርዕሰ መስተዳድሩ የጸጥታ አማካሪ ከስልጣናቸው ተነሱ!

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ይልቃል ከፋለ የጸጥታ ጉዳዮች አማካሪያቸውን እና የክልሉን ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፊን ከስልጣናቸው አነሱ። ዶ/ር ይልቃል የጸጥታ ጉዳዮች አማካሪያቸውን ከኃላፊነት ያነሱት የተሰጣቸውን “ተግባር እና ኃላፊነት በአግባቡ አልተወጡም” በሚል ነው።

ዶ/ር ይልቃል ሁለቱን ኃላፊዎች ከስልጣናቸው ያነሱት ከትላንት በስቲያ ሰኞ ሐምሌ 17፤ 2015 በጻፉት ደብዳቤ ነው። በአማራ ክልል ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ በምክትል ኃላፊነት ደረጃ የርዕሰ መስተዳድሩ የጸጥታ ጉዳዮች አማካሪ አቶ ከፋለ እሱባለው እና የቢሮው ምክትል ኃላፊ ኮማንደር መንገሻ አውራሪስ፤ ውሳኔውን የሚገልጽ ደብዳቤ እንደደረሳቸው ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” አረጋግጠዋል።

ከሰኞ ዕለት ጀምሮ ከአማካሪነታቸው የተነሱት አቶ ከፋለ፤ በዚህ የኃላፊነት ቦታ ለአምስት ዓመት ገደማ ቆይተዋል። አቶ ከፋለ ይህንን ኃላፊነት ያገኙት በቀድሞው የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የአመራርነት ጊዜ ሲሆን፤ የአሁኑን ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ይልቃልን ጨምሮ ባለፉት ዓመታት ክልሉን የመሩትን አምስት ርዕሰ መስተዳድሮች በአማካሪነት አገልግለዋል።

Via Ethiopia Insider
@YeneTube @FikerAssefa
ጠ/ሚ ዓብይና ፕሬዝዳንት ፑቲን የአቶሚክ ኢነርጂ ትብብር ፍኖተ ካርተ እንደሚፈራረሙ ገለጹ!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) እና የራሺያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የአቶሚክ ኢነርጂን ጠቅም ላይ ለማዋል የትብብር ፍኖተ ካርታ እንደሚፈራረሙ አስታወቁ።በጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ የተመራ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን በሁለተኛው የአፍሪካ ራሺያ የጋር ጉባዔ ለመሳተፍ ዛሬ በራሺያዋ ሴንት ፒተርስበርግ ከተማ የገባ ሲሆን ልዑካን ቡድኑ ከራሺያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቱን ጋር በመገናኘት በሁለቱ አገራት ትብብርና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትና ላይ መክሯል።

ነገ ከሚጀመረው የራሺያ አፍሪካ የጋራ ጉባኤ ግን ለጎንም ኢትዮጵያና ራሺያ 15 የሚደርሱ የሁለትዮሽ የትብብር ስምምነቶችን እንደሚፈራረሙ ፕሬዝዳንት ፑቲን ለኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ገልጸውላቸዋል።የትብብር ስምምነት ከሚደረግባቸው ጉዳዮች መካከል አንዱ ፣ ኢትዮጵያ ከአቶሚክ ኃይል ኤሌክትሪክ ለማመንጨትና ለመጠቀም የሚያስችላት የትብብር ፍኖተ ካርታ እንደሆነ ፕሬዝዳንት ፑቲን ገልጸዋል።ከዚህም በተጨማሪ ሁለቱ ሀገራት በሳይበር ደህንነት እና በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መስክ ለመተባበር ስምምነት እንደሚፈራረሙ ታውቋል።

"በራሺያ ቆይታዎ ወቅት የትብብር ስምምነት የምናደርግባቸውን የሰነዶች ፓኬጅ አዘጋጅተናል፤ ከነዚህም መካከል የመረጃ ደህንነት ስምምነት ፣ በአየር ትራፊክ ፣ በኢንፎርሜሽን እና የግንኙነት ቴክኖሎጂዎች መስክ የመግባቢያ ሰነድ ፣ የአቶሚክ ኢነርጂን ለመጠቀም የሚያስችል የትብብር ፍኖተ ካርታ ፣ በጉምሩክ አገልግሎቶች ፕሮቶኮል እና ሌሎች" ሲሉ ፑቲን ለጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ ተናግርዋል።ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ በበኩላቸው ከኢትዮጵያና ራሺያ የሁለትዮሽ ትብብር በተጨማሪ በተለያዩ ዓለም አቀፍ አጀንዳዎች እንደሚነጋገሩ አስታውቀዋል።

Via Reporter
@YeneTube @FikerAssefa
👍1
🔥🔥አስቸኳይ ክፍት የስራ ቅጥር💥💥

🔴በሁሉም ስራ ዘርፎች ሰራተኞችን በብዛት እንፈልጋለን። 
🔥ቀጥታ ወደ ስራ ቦታ እንልካለን።

📞 ስልክ:- 09 78 88 18 19
                 09 77 64 18 19

💥ጉዳይ አስፈፃሚ/smart phone ያለው/
      🔹የት/ደረጃ:10
      🔹የስራ ልምድ: 0አመት ጀምሮ
      🔹ደሞዝ:5000+ የቀን አበል
💥ካሸር አሰልጥኖ
      🔹የት/ት ደረጃ= 12/ዲፕሎማ
      🔹ልምድ= 0 አመት
      🔹ደሞዝ= 5,500
💥ባርማን/ባሬስታ
      🔹የት/ት ደረጃ= መፃፍ ማንበብ
      🔹ልምድ= ያለው
      🔹ደሞዝ=በስምምነት
💥ሪሴፕሽን ለገስት ሀውስ/ለሆቴሎች
     🔹የት/ደረጃ:10ኛ- ከዚያ በላይ
     🔹የስራ ልምድ: 0 አመት ጀምሮ    
     🔹ደሞዝ፡ 4,500
💥ቤቲንግ ቤት ካሸር (በፈረቃ)
     🔹የት/ት ደረጃ= 10ኛ በላይ
     🔹የስራ ልምድ=0
     🔹ደሞዝ=5000
💥 ሼፍ/ዋና እና ረዳት/
     🔹የት/ት ደረጃ= 10ኛ በላይ
     🔹የስራ ልምድ=ያለው
     🔹ደሞዝ=6000-10,000

ለበለጠ መረጃ
🏘አድራሻ: አ.አ 22 ጎላጎል ሲደርሱ ወደ ቦሌ በሚወስደው መንገድ ወረድ ብለው  ሎተስ ህንፃ ግራውንድ ላይ ቢ.ቁ 006

👇👇https://tttttt.me/JobsAtHewan