በፓኪስታን በሁለት ባቡሮች መካከል በተፈጠረ ግጭት ቢያንስ የ 25 ሰዎች ህይወት አለፈ
በደቡባዊ ፓኪስታን ሁለት የመንገደኛ ባቡሮች መካከል በተፈጠረ ግጭት ቢያንስ የ 25 መንገደኞች ህይወት አልፏል፡፡
አደጋው የደረሰበት ስፍራ የአካባቢው ነዋሪዎች በነብስ አድን ስራ ላይ መሰማራታቸው ተሰምቷል፡፡
ግጭቱ እንዴት ሊያጋጥም እንደቻለ የተናገረ መረጃ የለም፡፡ ሆኖም ግን የባቡሩ አደጋ በተደጋጋሚ በፓኪስታን የሚያጋጥም ሲሆን እድሜ ጠገብ የባቡር መንገድ መኖሩና ደካማ የጥገና ስርዓት ለአደጋዎቹ መንስኤ ናቸው፡፡
#ዳጉ_ጆርናል
@Yenetube @Fikerassefa

የመንገድ ትራፊክ ደኅንነት ትምህርት በአንደኛ ደረጃ ሥርዓተ ትምህርት ውስጥ ተካተተ
የአዲስ አበባ ከተማ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ ከትምህርት ሚንስቴር ጋር በመተባበር የመንገድ ትራፊክ ደኅንነት ትምህርት በአንደኛ ደረጃ (ከ1ኛ-8ኛ ክፍል) ሥርዓተ ትምህርት ውስጥ እንዲካተት ማድረጉን አስታውቋል፡፡
ኤጀንሲው የመንገድ ትራፊክ ደኅንነት ትምህርት በአንደኛ ደረጃ (ከ1ኛ-8ኛ ክፍል) ሥርዓተ ትምህርት እንዲካተት ከትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች ጋር በመወያየት ከ1ኛ እስከ 8ኛ ክፍል በሥርዓተ-ትምህርት መካተት የሚገባቸውን ነጥቦች የያዘ ሰነድ አዘጋጅቷል፡፡
ኤጀንሲው የመንገድ ደህንነት ትምህርት በስርዓተ ትምህርት ተካቶ እንዲሰጥ ለረዥም ጊዜ ባደረገው ጥረት እና ክትትል በአንደኛ ደረጃ ሥርዓተ ትምህርት በሶሻል ሳይንስ (Social Studies) 7ኛ እና 8ኛ ክፍሎች፣ በእንግሊዘኛ ቋንቋ ከ1-8ኛ ክፍሎች፣ በአካባቢ ሳይንስ ከ1-6ኛ ክፍሎች እና በአፍ መፍቻ ቋንቋ ከ1-8ኛ ክፍሎች እንዲካተቱ መደረጉን ገልጿል፡፡
የመንገድ ትራፊክ ደኅንነት በትምህርት ካሪኩለም ውስጥ መካተቱ የመንገድ ትራፊክ ህጎች እና ደንቦችን በአግባቡ አውቆ ተግባራዊ በማድረግ ኃላፊነቱን እና ግዴታውን በአግባቡ የሚወጣ ዜጋ በመፍጠር በኢትዮጵያ እየደረሰ ያለውን የትራፊክ ግጭት አደጋዎች ለመቀነስ ጉልህ ሚና እንዳለው ከኤጀንሲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የደቡብ ክልል ምክር ቤት አቶ እርስቱ ይርዳን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አድርጎ ሾመ
ስድስተኛ ዙር መስራች ጉባኤውን እያካሄደ የሚገኘው የደቡብ ብሄሮች፣ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል መንግስት አቶ እስርቱ ይርዳን ርዕሰ መስተዳድር አድርጎ ስለመምረጡ ብስራት ራዲዮ ከክልሉ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን የማህበራዊ ትስስር ገፅ ተመልክቷል።
ምክር ቤቱ የ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ አሸናፊ ፓርቲ ከሆነው ብልጽግና ለሹመት በእጩነት የቀረቡለትን አቶ እርስቱ ይርዳን በሙሉ ድምጽ ርዕሰ መስተዳድር አድርጎ ሾሟል።
አቶ እርስቱ በምክር ቤቱ ፊት ቃለ መሃላ ከፈጸሙ በሗላ የክልሉን እጩ የካቢኔ አባላት ለምክር ቤቱ አቅርበው ያስጸድቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።
Via :- #ዳጉ_ጆርናል

በአፍሪካ ህብረት ጉባኤ እየተፈጸመ ስላለዉ መፈንቅለ መንግስት መሪዎች ቅሬታ አሰሙ
ባለፈው አንድ አመት አምስት ወታደራዊ የመንግስት ግልበጣ በአፍሪካ መፈጸሙን ተከትሎ የመፈንቅለ መንግስት ማዕበል ሲሉ በአፍሪካ ህብረት ጉባኤ የተገኙ መሪዎች ቅሬታቸዉን አሰምተዋል፡፡የምርጫ መስፋፋት እና ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር መኖር በአፍሪካ የመፈንቅለ መንግስት ቁጥር እንዲቀንስ አድርጎ እንደነበር አይዘነጋም፡፡
የጦር ሰራዊት ሀይል በቅርቡ ስልጣን ከተቆጣጠረባቸው ሀገራት መካከል ሁለቱ ቡርኪናፋሶ እና ማሊ አማፂያንን ለመቆጣጠር ሲታገሉ ቆይተዋል።ባለፈው ሳምንት በጊኒ ቢሳው የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ተካሂዶ የነበረ ሲሆን የጊኒ ቢሳዉ ፕሬዚዳንት የአደንዛዥ ዕፅ አዘዋዋሪዎች ቡድኖች ለመንግስት ግልበጣዉ ሙከራ ተጠያቂ አድርገዋል።
በምዕራብ አፍሪካ ሀገራት የተካሄደው መፈንቅለ መንግሥት በበርካታ ሰዎች ተቀባይነት ቢያገኝም፣ በጥቅምት አጋማሽ በሱዳን የተካሄደው ወታደራዊ የመንግስት ግልበጣ ግን የሲቪል አገዛዝ ይመለስ በሚሉ በርካታ የጎዳና ላይ ተቃውሞዎችን አስከትሏል። በዚህም የተነሳ ርህራሄ በሌለው ሃይል ከ70 በላይ ሰልፈኞች ተገድለዋል፡፡
በ አዲስ አበባ በተካሄደዉ የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ የተገኙት እያንዳንዱ መሪ “በማያሻማ መልኩ የታየውን የመንግስት ለውጥ ኢ-ህገ መንግስታዊ በማለት ማውገዛቸውን” የአፍሪካ ህብረት የሰላም እና የፀጥታው ምክር ቤት መሪ ባንኮሌ አዴዮ ተናግረዋል፡፡ ወታደራዊ መንግስታትን አንታገስም ሲሉ አክለዋል፡፡
ወታደራዊዉን የመንግስት ግልበጣ ተከትሎ ቡርኪናፋሶ፣ጊኒ፣ማሊ እና ሱዳን ከአፍሪካ ህብረት አባልነት መታገዳቸዉ ይታወሳል፡፡

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አነሳ
አዋጁ 63 ተቃውሞ እና 21 ድምፀ ተአቅቦ ቀርቦበታል !!
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ በአገሪቱ ተጥሎ የቆየውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አነስቷል፡፡
ምክር ቤቱ በስብሰባው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲነሳ በቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ላይ ከተወያየ በኋላ በ63 ተቃውሞ በ21 ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ እንዲነሳ ወስኗል፡፡
ይህን ውሳኔ ተከትሎ፤ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርድ ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም ጋር ተያይዞ ያላጠናቀቃቸው ጅምር ሥራዎች ካሉ ይህ ውሳኔ ከተላለፈበት ከዛሬ ጀምሮ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ አጠናቆ ለሚመለከተው አካል ሪፖርት እንዲያደርግ መወሰኑን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል፡፡
በተመሳሳይ የፍትህ አካላት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም ጋር ተያይዞ የጀመሯቸውን ጉዳዮች በመደበኛው የፍትህ አሰሰጣጥ ሥርዓት እንዲያጠናቅቁም ምክር ቤቱ ወስኗል።

ሩሲያ በዩክሬን ላይ አሁንም ጥቃት ልትፈጽም ትችላለች ሲሉ ባይደን ተናገሩ
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን እንደተናገሩት ሩስያ በዩክሬን ላይ አሁንም ጥቃት ልትፈጽም እንደምትችል በመግለጽ ሊደርስ የሚችለዉ ሰብዓዊ ኪሳራ እጅግ ግዙፍ ነዉ ሲሉ አስታዉቀዋል፡፡በአገር አቀፍ ደረጃ በቴሌቪዥን በተላለፈው የፕሬዝዳንቱ መልዕክት ዩናይትድ ስቴትስ ለእንደዚህ ዓይነቱ እርምጃ ቆራጥ ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ መሆኗን ተናግረዋል ።
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ሩሲያ ከዩክሬን ጋር በሚያዋስናት ድንበር 150,000 ወታደሮችን አስፍራለች ሲሉ ገልጸዋል፡፡የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር በበኩሉ አንዳንድ ሃይሎች አካባቢዉን ለቀዉ መውጣታቸውን ቢያሳዉቅም ባይደን ግን ይህ አልተረጋገጠም ሲሉ ተናግረዋል፡፡ባይደን የሩሲያ ጦር መልቀቅ ጥሩ ነበር ነገርግን እስካሁን አላረጋገጥንም ሲሉ አክለዋል፡፡
ባይደን ይህንን መልዕክት ያስተላለፉት የሩስያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የሞስኮ የጸጥታ ስጋት ትኩረት ሊሰጠው እና በቁም ነገር መታየት እንዳለበት ከተናገሩ ከሰዓታት በኋላ ነው።ፑቲን በተደጋጋሚ ዩክሬንን ለመዉረር አቅደዋል መባሉን ያስተባብላሉ፡፡ ፣ ሩሲያ በአውሮጳ ምድር ሌላ ጦርነት ሀገራቸዉ እንደማትፈልግ ቢናገሩም ከህዳር ወር ጀምሮ ያለዉ ውጥረት ግን እየጨመረ ይገኛል፡፡

በጉጂ ዞን ከ450 ኩንታል በላይ እህል በኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች መዘረፉ ተነገረ
በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን በዘጠኝ ወረዳዎች በተከሰተዉ ድርቅ ምክንያት ከተለያዩ ቦታዎች ድጋፎች እየተደረጉ ቢሆንም ለእርዳታ የሚላከዉን የረድኤት ድጋፍ በኦነግ ሸኔ ምክንያት ለሚገባቸዉ ሰዎች መድረስ እንዳልተቻለ ተጠቁሟል፡፡ከተለያዩ አካላት የሚላከዉ ድጋፍ እስከ አዶላ ከተማ ብቻ እየደረሰ ሲሆን ከዛ መልስ ባሉ አካባቢዎች በመንገድ መዘጋት የተነሳ ማስተላለፍ እንዳልተቻለ እንዲሁም ለማለፍ ቢሞከርም በሽበርተኛዉ ቡድን ታጣቂዎች የረድኤት ድጋፉ እንደሚዘረፍ ተገልጿል ፡፡
በቅርቡ ወደ ዞኑ ድጋፍ የተደረገ ከ450 ኩንታል በላይ የተለያዩ እህሎችን የያዘ አሽከርካሪ በሸብርተኛው ሸኔ መወሰዱን የዞኑ መንግስት ኮሚኒኬሽን ሀላፊ አቶ ዮሀንስ ወርቁ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡በአጠቃላይ በአሁኑ ሰዓት በዞኑ 561 ሺ 565 ሰዎች መደበኛ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው የተገለጸ ሲሆን እርዳታ ካልተደረገላቸው የከፋ ጉዳት እንደሚገጥማቸው ይፋ ተደርጓል፡፡
ከጸጥታዉ ችግር አሳሳቢነት የተነሳ በፍጥነት መፍትሄ የሚያሻ ጉዳይ መሆኑን ሲሉአቶ ዮሀንስ ወርቁ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናረዋል፡፡

በመንግሥት በኩል ለሰላም የሚደረጉ ጥረቶች ቢጠናከሩም ህወሓት የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ አለመሆኑን አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናገሩ
በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል የተከሰተዉን ቀዉስ በሚመለከት ለሰላም የሚደረጉ ጥረቶች አሁንም እንደቀጠሉ ናቸዉ። በቅርቡ መንግስት ለሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት አመቺነት ያደረገዉን የተኩስ አቁም ዉሳኔ ለዚህ አንድ ማሳያ ነዉ ያሉት አምባሳደሩ መንግስት ዘላቂ የሰላም ሁኔታ ለመፍጠር ጥረት እያደረገ ቢሆንም ፤ ህወሓት የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ አለመሆኑን ገልጸዋል።
አምባሳደሩ በመግለጫቸዉ ከህወሓት ጋር እየተደረገ ያለ ድርድር አለ ባይሉም በመንግስት በኩል እየተደረጉ ያሉ ጥረቶችን ለአለማቀፍ ተቋማት እና መንግስታት ገለጻ እንደተደረገላቸዉና እዉቅና እየሰጡት መሆኑንም አንስተዋል። የሰብዓዊ አቅርቦቱም አስቸኳይ የምግብ ድጋፍ እና መድሀኒትን ጨምሮ አየደረሰ ነዉም ብለዋል።
ብስራት ራዲዮ ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ አደጋ ስራ አመራር ኮሚሽንን ዋቢ አድርጎ ከ 1.8 ቢሊዮን ብር በላይ ወደ ትግራይ መላኩንም መዘገቡ ይታወሳል ።
ሆኖም የህወሓት ታጣቂ ሀይሎች በቅርቡ በኤርትራ ላይ የፈጸሙትን ጥቃት ጨምሮ ለሰላም የሚደረጉ ጥረቶች ላይ የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ አይደለም ሲሉ የዉጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናግረዋል።
አያይዘዉም በየትኛዉም አካል ሰላም ለመፍጠር የሚመጡ ወገኖችንም ኢትዮጵያ እንደምትቀበል አስታዉቀዋል።
Via:- #ዳጉ_ጆርናል

በአዲስ አበባ በትላንትናው እለት በደረሰ የእሳት አደጋ የአንድ ሰዉ ህይወት አለፈ
በአዲስ አበባ ከተማ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ልዩ ቦታዉ ፋሲል ፋርማስ ጀርባ በደረሰ የእሳት አደጋ የአንድ ሰዉ ህይወት ሲያልፍ በሶስት ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።
አደጋው የደረሰው ከረፋዱ 4 ሰዓት ከ19 ደቂቃ ላይ በሁለት መኖሪያ ቤቶች ላይ ሲሆን በአደጋው በሰው ላይ ከደረሰው ጉዳት በተጨማሪ 300 ሺህ ብር የተገመተ ንብረት መውደሙን የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ በተለይ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል።
የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ባደረጉት ርብርብ አደጋዉ ከዚህ የከፋ ጉዳት እንዳያደርስ ማድረግ የተቻለ ሲሆን በዚህ ሂደት ከአምስት ሚሊየን ብር የተገመተ ንብረት ማዳን ተችሏል።
ህይወቱ ያለፈዉ የ40 ዓመት ጎልማሳ ሲሆን የእሳት አደጋዉ በተከሰተበት ወቅት በቆጥ ላይ አልጋ ላይ ተኝቶ ነበረ። በሌላ በኩል ቀላል ጉዳት የደረሰባቸዉ ሶስት ሰዎች በእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አምቡላንስ የመጀመሪያ ህክምና ተደርጎላቸዋል።

በሱዳን በጎሳ ግጭት የተነሳ የሟቾች ቁጥር 65 ደረሰ
በሱዳን ብሉ ናይል ግዛት ለቀናት በዘለቀው የጎሳ ግጭት የሞቱት ሰዎች ቁጥር ቢያንስ 65 መድረሱን የግዛቱ የጤና ኃላፊ አስታዉቀዋል። በደቡባዊ የሀገሪቱ ክፍል በሃውሳ እና በቢርታ ብሄረሰቦች መካከል በነበረው ግጭት ከተግደሉት ሰዎች በተጨማሪ 150 የሚጠጉ ሰዎች መቁሰላቸውን ገማል ናስር አል ሰይድ በትላንትናዉ እለት ተናግረዋል።
ከሟቾቹ መካከል አብዛኞቹ በጥይት የተመቱ እና በስለት የተወጉ ወጣቶች እንዳሉበት ተነግሯል፡፡በብሉ ናይል የሚገኙ ሆስፒታሎች የተራቀቁ መሳሪያዎች እና የህይወት አድን መድኃኒት እጥረት ስላለባቸዉ በዋና ከተማዋ ካርቱም የሚገኙ ባለስልጣናት 15 ክፉኛ የተጎዱ ሰዎችን በአየር መጓጓዣ በማንሳት እንዲረዷቸው አል ሰይድ አሳስበዋል።
ቅዳሜ ዕለት ባለሥልጣናቱ የሟቾች ቁጥር ቢያንስ 31 መሆኑን ተናግረዋል ።በአካባቢው መረጋጋት ለማምጣት ባለስልጣናት ወታደራዊ ፈጣን ድጋፍ ሰጭ ሃይሎችን አሰማርተዋል። እንዲሁም ግጭቱ በተከሰተባቸው የግዛቱ ዋና ከተማ ሮዝሬስ እና አል-ዳማዚን ከተሞች ከቅዳሜ ምሽት ጀምሮ የሰዓት እላፊ ገደብ ተጥሏል፡፡
የብሉ ናይል ገዥ አህመድ አል ኦምዳ ለአንድ ወር ማንኛውንም ስብሰባ ወይም ሰልፍ የሚከለክል ትእዛዝ አስተላልፈዋል።

ትኩረት ለሻሸመኔ
በሻሸመኔ ከተማ አቦስቶ ተብሎ በሚጠራው እና ሚካኤል ቤተክርስቲያን አካባቢ አለመረጋጋት መኖሩን #ዳጉ_ጆርናል በሻሸመኔ ከተማ ነዋሪዎች አረጋግጧል።
እንደ ነዋሪዎቹ ገለጻ አለመረጋጋት ያለ ሲሆን በቅዱስ ሲኖዶስ የተወገዘዉ ቡድን ወደ ቤተክርስቲያኑ ለመግባት ሙከራ በሚያደርግበት ወቅት ወጣቶች በመከላከላቸዉ ነዉ ብለዋል።
Via:- ዳጉ ጆርናል

ኤም ፔሳ በኢትዮጵያ 2 ሚሊዮን የሚሆኑ ደምበኞች እንደሚኖሩኝ ጠብቃለሁ አለ
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በኤም ፔሳ ( M-pesa ) አገልግሎቱ በሞባይል የሚደረግ የገንዘብ ዝዉዉርን ለማከናወን ፈቃድ ከተሰጠዉ በኋላ እስከ ቀጣዩ አመት መጋቢት ወር ድረስ 2 ሚሊዮን ደምበኞች እንደሚያፈራ የሳፋሪኮም ፋይናንስ ኦፊሰር ዲሊፕ ፓል መናገራቸውን ዘ ኢስት አፍሪካን (The East African) ጽፏል።
ፋይናንስ ኦፊሰሩ ከኢትዮ ቴሌኮም ብርቱ ፉክክር እንደሚገጥማቸዉ የገለጹ ሲሆን ፤ የኤም ፔሳ አገልግሎትን እስከ መስከረም መጠናቀቂያ ድረስ በኢትዮጵያ ለማስተዋወቅ እቅድ መያዙንም ነዉ የተናገሩት።
በተጨማሪም እስከ ቀጣዩ አመት መጋቢት ወር ድረስ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ደምበኞች 10 ሚሊዮን እንደሚደርስ ግምታቸዉን አስቀምጠዋል። ብስራት ራዲዮ በቅርቡ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ሶስት ሚሊዮን የደምበኞች ቁጥር ላይ መድረሱን መዘገቡ ይታወሳል።
የፋይናንስ ኦፊሰሩ ኢትዮ ቴሌኮም በቴሌብር የሞባይል ገንዘብ ዝዉዉር በኩል ቴክኖሎጂዉን ለህዝቡ በማሳወቅ እያደረገ ያለዉ አስተዋጽኦ እና እየታየ ያለዉ መነቃቃት ፤ ኤም ፔሳ ወደ ሀገር ዉሰጥ ሲገባ ስራዉን እንደሚያቀልለት ተናግረዋል።

👍2
በደላንታ ወረዳ ማዕድን በማዉጣት ላይ የነበሩ ከ 20 በላይ የሆኑ ወጣቶች ባጋጠማቸው አደጋ በፍርስራሽ ዉስጥ ተዉጠዋል ተባለ
በደላንታ ወረዳ 018 ቀበሌ ልዩ ስሙ ቆቅ ዉሃ ተብሎ በሚጠራዉ አካባቢ በባህላዊ መንገድ የኦፓል ማዕድንን በማዉጣት ስራ ላይ የነበሩ ወጣቶች ሀሙስ ከሌሊቱ 6 ሰዓት ገደማ ላይ ባጋጠማቸዉ የመሬት መደርመስ አደጋ በፍርስራሽ ዉስጥ ተዉጠዉ እንደሚገኙ የደላንታ ወረዳ ማዕድን ልማት ጽ/ት ቤት ሀላፊ አ/ቶ ተስፋ ሰማሁ ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።
እስከ 200 ሜትር ጥልቀት ድረስ የተቆፈረዉ ጉድዷድ ወጣቶቹ በድንገት በስራ ላይ በነበሩበት ወቅት በመደርመሱ በፍርስራሽ ዉስጥ ሊዋጡ መቻላቸዉን ነግረዉናል። ቁጥራቸዉ በዉል የማይታወቁ ወጣቶች አደጋዉ ያጋጠማቸዉ ሲሆን ከቤተሰቦቻቸው በመጣ ሪፖርት መሰረት ግን ከ 20 በላይ እንደሆኑ ለማወቅ ተችሏል ብለዋል።
ወጣቶቹ በህይወት ስለመኖራቸዉ የሚታወቅ ነገር የለም ያሉት ሃላፊዉ ከአርብ ንጋት ጀምሮ ቁፋሮ እየረከናወነ መሆኑን ለብስራት ተናግረዋል።
ገደሉ ጥልቅ በመሆኑ በዘመናዊ ማሽነሪዎች የታገዘ ቁፋሮን ለማከናወን አልተቻለም ያሉን አቶ ተስፋ ህብረተሰቡን በማስተባበር በሰዉ ሀይል የነፍስ አድን ስራዉ እየተከናወነ መሆኑን አክለዋል። እስከአሁን ድረስም 25 ሜትር ጥልቀት አካባቢ ቁፋሮ በሰዉ ሀይል መከወኑን ተናግረዋል። የአካባቢው ነዋሪዎች በነፍስ አድን ስራ ላይ ላሉ ሰዎች ምግብ በማቅረብ ድጋፍ እያደረጉ እንደሆነም አክለዋል።
ከ 2004 ዓ.ም ጀምሮ በአካባቢው የኦፓል ማዕድንን የማዉጣት ስራ የተጀመረ ሲሆን ወጣቶች በባህላዊ መንገድ ማዕድኑን ሲያወጡ ቆይተዋል። ብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ከዚህ ቀደም ፤ በወረዳው የኦፓል ማዕድን በስፋት የሚገኝ መሆኑን እና ከ5 ሺ በላይ ወጣቶች በዘረፉ ተሰማርተው የዕለት ከዕለት ህይወታቸውን እየገፉበት እንደሚገኙ ዘገባ ሰርቷል፡፡ ወረዳው ሀብቱን በአግባቡ ለመጠቀም ዘመናዊ መሳሪያ ባለመኖሩ በወጣቶች በግምት እየተቆፈረ እንደሚገኝ የደላንታ ወረዳ ማዕድን ልማት ጽ/ቤት አስታውቆ ነበር።
በበረከት ሞገስ

👍22😭10❤2
ተዋናይ ጌታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ
በኢትዮጵያ የፊልም ኢንዱስትሪ ከ60በላይ ፊልሞች ላይ የተሳተፈው ተዋናይ ጌታቸው እጅጉ ( ባቡጅ) ትናንት ምሽት ከዚህ አለም በሞት መለየቱ ተሰምቷል። ለቤተሠቡና ለአድናቂዎቹ መፅናናትን ይሰጥ ዘንድ ተመኘን ።
#ዳጉ_ጆርናል
@yenetube @Fikerassefa

😭149👍18❤9
ሩሲያ ከድምጽ ፍጥነት አሥር እጥፍ የበለጠ የሚጓዝ ሚሳኤል እንዳላት አስታወቀች
የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን አዲሱ የሞስኮ ሙከራ የተደረገበት ባሊስቲክ ሚሳኤል አስር እጥፍ ከድምፅ ፍጥነት እንዳለው በሰከንድ 3 ኪ.ሜ እንደሚጓዝ አስታውቀዋል።
ፍጥነት አስፈላጊ ነው ምክንያቱም ሚሳኤል በፈጠነ ቁጥር ኢላማውን የጠበቀ ይሆናል። ኢላማውን ለመምታት በፈጠነ መጠን የመከላከያ ሰራዊት ምላሽ የሚሰጥበት ጊዜ ይቀንሳል በማለት አክለዋል። በእርግጥ እንደዚህ አይነት ሚሳኤሎች አደጋዎችን እንዳያስከትሉ ለመከላከል የሚቻል ሲሆን ነገር ግን ፍጥነቱ እየጨመረ በሄደ መጠን የመከላከል ስራውን የበለጠ እያከበደው ይሄዳል። ለዚህም ነው ፕሬዚዳንት ፑቲን ይህን አዲስ አይነት ሚሳኤል በማወጅ ፍጥነት ላይ አፅንዖት ሰጥተው የተናገሩት። የዩናይትድ ስቴትስ ባለስልጣናት ይህንን አዲስ የሙከራ ስርዓት ቀድሞውኑ እንደሚያውቁት እና ዩክሬን እና አጋሮቿን ለማዘጋጀት ሲሉ ገለፃ እንዳደረጉ አስታውቀዋል።
ይህ መጠነ ሰፊ ግጭት ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ሩሲያ ወደ 12 ሺ የሚጠጉ ሚሳኤሎች በዩክሬን ግዛቶች ላይ አወንጭፋለች። ከእነዚህ ውስጥ 80 በመቶ የሚሆኑት በዩክሬን አየር ስርዓት ተጠልፈዋል። ነገር ግን እነዚህ ፈጣን የባለስቲክ ሚሳኤሎች ከአየር መቃወሚያ እና ከሌሎች የመከላከያ ስርዓቶች ውጪ ለማድረግ የታሰቡ ናቸው።ሩሲያ በዩክሬን ላይ ትናንት ሀሙስ ባደረሰችው የባለስቲክ ሚሳኤል ጥቃት ምክንያት የሰሜን አትላንትቲክ ጦር ቃልኪዳን ኔቶ እና ዩክሬን አስቸኳይ ውይይት በሚቀጥለው ሳምንት በብራስልስ እንደሚያደርጉ ይጠበቃል። የናቶ-ዩክሬን ምክር ቤት ስብሰባ ማክሰኞ የሚካሄድ ሲሆን የኪየቭን የእንሰብሰብ ጥያቄ ተከትሎ እንደሚደረግ የፈረንሳዩ የዜና ወኪል አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ያነጋገራቸው ባለስልጣናት ገልጸዋል።
እ.ኤ.አ. በሀምሌ 2023 የተመሰረተው ምክር ቤት በኔቶ አባላት እና በዩክሬን መካከል የጋራ አካል ነው። ወታደራዊ ህብረትን ለመቀላቀል ፍላጎት ያለው - እንዲሁም የጦርነት ቀውስ ሲያጋጥን የምክክር አማራጭ ሆኖ ይሠራል ።የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ሩሲያ ትናንት በዲኒፕሮ አዲስ የባላስቲክ ሚሳኤል መጠቀሟ የጦርነቱን ከባድነክ ያሳያል ብለዋል። "ዛሬ በዩክሬን ላይ የባሊስቲክ ሚሳኤል መጠቀሟ ሩሲያ ለሰላም ምንም ፍላጎት እንደሌላት ተጨማሪ ማረጋገጫ ነው" ሲሉ ዘለንስኪ በሰጡት መግለጫ ላይ ተናግረዋል። ጥቃቱ የሩስያ መሪ ቭላድሚር ፑቲን ጦርነቱን ለማባባስ የወሰዱት "ሁለተኛ እርምጃ" ነው ሲሉ ዘለንስኪ ገልፀዋል።
ዘለንስኪ አክለው ፑቲን "ከቻይና፣ ብራዚል፣ የአውሮፓ ሀገራት፣ አሜሪካ እና ሌሎች የሚደረጉ የሰላም ጥሪዎችን ችላ በማለት" ከአንድ ሺህ ቀናት በፊት የተጀመረውን ግጭት ለማራዘም ሁሉንም ነገር እያደረጉ ነው ብለዋል። "አለም የአፀፋ ምላሽ መስጠት አለበት" ፤ "በሩሲያ ድርጊት ላይ ጠንካራ ምላሽ አለመስጠት እንዲህ አይነት ባህሪ ተቀባይነት ያለው እንዲመስል መልእክት ያስተላልፋል" በማለት ተናግረዋል። ሩሲያ በኃይል ብቻ ወደ እውነተኛ ሰላም መገደድ አለባት ፤ ይህ ካልሆነ ግን ማለቂያ የሌላቸው የሩሲያ ጥቃቶች ፣ ዛቻዎች እና አለመረጋጋት በዩክሬን ላይ ብቻ ሳይሆን በሌሎች ላይም የሚከተል ነው ሲሉ ገልፀዋል።

👍54❤7⚡5👎2👀1
የጣርያና ግድግዳ ግብር ሕገ ወጥ ነው ተባለ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የጣሪያ ግድግዳ/የንብረት ግብር ብሎ ከከተማዋ ነዋሪ እየሰበበሰበ ያለው ግብር ሕገ ወጥ ነው በሚል የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሳኔ ሰጠ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የጣሪያ ግድግዳ/የንብረት ግብር ብሎ ከከተማዋ ነዋሪ እየሰበበሰበ ያለው ግብር "ሕገ ወጥ መኾኑን" በመግለጽ እናት ፓርቲ ክስ መመሥረቱን አስታዉሶ ክሱን የተመለከተው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ዛሬ ጥር 9 ቀን 2017 ዓ.ም. ባስቻለው ችሎት የንብረት ግብር ማሻሻያ ጥናት ተብሎ ሚያዝያ 3 ቀን 2015 ዓ.ም. የወጣውና "ለግብሩ መሰብሰብ መሠረት የሆነው መመሪያ ተፈጻሚነት ሊኖረው አይገባም" ተብሎ መመሪያው እንዲሻር በሙሉ ድምጽ ወስኖልኛል ሲል እናት ፓርቲ በማህበራዊ ገፁ አስታውቋል::

👍202😁18❤14🔥5⚡1
ባለቤቱን ገድሎ ስጋዋን ከትፎ መጸዳጃ ቤት ዉስጥ የከተተዉ ተከሳሽ በሞት እንዲቀጣ ተወሰነበት
ፀሃዬ ቦጋለ በየነ የተባለ ተከሳሽ ከነሐሴ 27 ቀን 2014 ዓ.ም በግምት ከቀኑ 5፡00 እስከ ነሐሴ 28 ቀን 2014 ዓ.ም ከምሽቱ 12፡30 ድረስ ባለው ጊዜ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 አርሴማ ፀበል አከባቢ ባለቤቱ የነበረችውን ሟች ወንበር ላይ ተቀምጣ እያለ ሳታየው ከኋላዋ በመምጣት በሊጥ ማዳመጫ ዱላ ማጅራትዋን በመምታት ህይወቷ እንዲጠፋ አድርጓል መባሉን ዳጉ ጆርናል ከፍትሕ ሚኒስቴር ሰምቷል።
ግለሰቡ ባለቤቱን እራሷን እንድትስት ካደረገ በኋላ እዛው ትቷት ከቤት ወጥቶ በመሄድና ከተወሰነ ሰዓታት በኋላ ተመልሶ በመምጣት ሟች እራሷን ስታ ከወደቀችበት መሬት ለመሬት በመጎተት እቤት ውስጥ ወደሚገኘው መታጠቢያ ቤት በማስገባት አንድ እግሯን ከዳሌዋ ጀምሮ በመቁረጥና ሙሉ የእግሯን ስጋ አጥንቷ ባዶ እስኪሆን ድረስ መልምሎ በማውጣት ስጋዋን አድቅቆ በመክተፍና በመቆራረጥ መጸዳጃ ቤት ውስጥ ጨምሯል።
ወንጀለኛዉ የቆረጠውን እግሯን ለሁለት በመስበርና በፌስታል በመቋጠር ፀጉሯን በመቀስ በመቁረጥ ቀሪ አስከሬንዋ ላይ ጨርቅና የተለያየ መዘፍዘፊያ በመጫን እዛው መታጠቢያ ቤት ውስጥ በማስቀመጥ እስከ ነሃሴ 30/2014 ዓ.ም ድረስ ምንም እንዳልተፈጠረ እቤት ውስጥ እያደረ ከቆየ በኋላ ከጷግሜ 1/2014 ዓ.ም ጀምሮ እስከ መስከረም 16/2015 ዓ.ም ድረስ ቤቱን ዘግቶ ተሰዉሮ ነበር ብሏል።
በዚህም ምክያንት በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምርመራ ተጣርቶ በፍትህ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ በሴቶችና ህጻናት ላይ ሚፈፀሙ ወንጀሎች ዐቃቤ ሕግ ዳይሬክቶሬት በወ/ሕ/አ539/1/ሀ/ መሰረት በፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ የሰው ግድያና ከባድ ውንብድና ወንጀል ችሎት ክስ ቀርቦበት ክርክር ሲደረግ ቆይቷል፡፡
በክርክሩ ሒደትም የዐቃቤ ሕግ ማስረጃ ከተሰማ በኋላ ተከሳሽ እንዲከላከል ብይን ቢሰጥም የመከላከያ ማስረጃ አቅርቦ የቀረበበትን ክስ ሊከላከል ባለመቻሉ ፍ/ቤቱ በተከሳሽ ላይ የጥፋተኛነት ፍርድ በመስጠት በዕድሜ ልክ ፅኑ እስራት እንዲቀጣ የወሰነ የነበረ ቢሆንም ዐቃቤ ሕግ ባቀረበው ይግባኝ መሰረት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የወሰነውን የእድሜ ልክ ጽኑ እስራት ውሳኔ በመሻር ተከሳሹ በሞት እንዲቀጣ ወስኖበታል፡፡

😭67👍40❤10
አየር መንገዱ የሀገር ውስጥ ተርሚናል አገልግሎቱ ለጊዜው መቋረጡን ገለፀ!!
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሀገር ውስጥ ተርሚናል አገልግሎቱ ለጊዜው መቋረጡን አስታውቋል፡፡
በዚህም የሀገር ውስጥ መንገደኞች በዓለም አቀፍ መንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናል በኩል እንዲስተናገዱ አየር መንገዱ አሳስቧል፡፡
አየር መንገዱ ጉዳዩን አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ፤ ዛሬ ከቀኑ 6:30 በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የሀገር ውስጥ መንገደኞች ማስተናገጃ ሕንፃ ውስጥ ወደ በረራ ይዞ መግባት ከሚከለከሉ ቁሳቁሶች መካከል ከመንገደኞች የሚሰበሰብ የሲጋራ መለኮሻ (ላይተር) ጊዜያዊ የማስቀመጫ ስፍራ ውስጥ ጭስ በመከሰቱ ለመንገደኞች ደህንነት ሲባል ሕንፃው ለጊዜው አገልግሎት አቋርጧል ብሏል፡፡

👍50❤2😁2
ለ2ኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀርቧል
ዛሬ ለ2ኛ ጊዜ ፍርድ ቤት የቀረበው ድምፃዊ አንዱዓለም ፖሊስ አንዳንድ ምርመራ ውጤቶች ስላልደረሱልኝ ተጨማሪ ቀናት ይሰጠኝ ባለው መሰረት ተጨማሪ 12 ቀን ተፈቅዶለታል።
የድምፃዊ አንዱዓለም ጠበቃ በበኩሉ የዋስ መብት ይፈቀድለት ብሎ ቢጠይቅም
ፖሊስ ማስረጃዎችን ያጠፋብኛል መፈቀድ የለበትም በማለቱ ሳይፈቀድ ቀርቷል።
መጋቢት 29 ቀን 2017 ዓም ቀጠሮ ተሰርቷል።

👍38👎3❤2😭2
የሱዳን ጦር የካርቱምን አየር ማረፊያ መቆጣጠሩን አስታወቀ
የሱዳን ጦር ሃይል (SAF) እኤአ ከሚያዝያ 2023 አጋማሽ ጀምሮ በፓራሚትሪ ፈጣን ድጋፍ ሰጪ ሃይሎች (RSF) ተይዞ የነበረውን የካርቱም አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ መቆጣጠሩን የካርቱም አካባቢ ወታደራዊ ምንጮች ገለፁ።

👍14❤5