YeneTube
በባሌ ዞን በሚገኙ አካባቢዎች የተቋረጠውን የኤሌክትሪክ ኃይል የመጠገን ሥራ እየተከናወነ ነው! በባሌ ዞን በሚገኙት የሮቤ፣ ጎባ፣ ጋሠራ፣ አጋርፋ፣ ሲናና፣ ዲንሾ እና አካባቢያቸው ከትናንት በስቲያ አንስቶ የተቋረጠውን የኤሌክትሪክ ኃይል የመጠገን ሥራ እየተከናወነ ነው። በዞኑ የኤሌክትሪክ መቋረጥ ያጋጠመው ከመልካ ዋከና የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ወደ ሮቤ የሚሄደው መስመር በዲንሾ አካባቢ ተቆርጦ በመውደቁና…
#Update
በባሌ ዞን በሚገኙ አካባቢዎች የተቋረጠውን የኤሌክትሪክ ኃይል የመጠገን ሥራ ከቀኑ 11:36 ላይ ተጠናቋል፣ ከመልካዋከና ሮቤ ያለው መስመር ዳግም እንዲገናኝ በመደረጉ አካባቢዎቹም ኃይል አግኝተዋል።
Via EEPCo
@YeneTube @FikerAssefa

https://tttttt.me/sabinaadvisor
የስራ ጉዞ ወደ # Europe
#Schengen_visa
👉 የሚሰራበት አገር - geneva, Swaziland
👉 የስራው አይነት :- accounting
👉 የስራ ቀናት - 6 ቀናት/ week
👉 የወር ደሞዝ - €10000_13000 and more
👉 ፆታ - አይጠይቅም
👉 ዕድሜ - 25እስከ 45
👉 መኖሪያ ቤት - በነፃ
👉 ፕሮሰሱ የሚፈጀው ግዜ ከ 2 - 3 ወር ነው
#10 persons
#Requirements
👉 Passport
👉photo
👉Degree documents
👉Work experience
Contact:
@Sabinavisa
+251118683939
0936363639
0936363680
የስራ ጉዞ ወደ # Europe
#Schengen_visa
👉 የሚሰራበት አገር - geneva, Swaziland
👉 የስራው አይነት :- accounting
👉 የስራ ቀናት - 6 ቀናት/ week
👉 የወር ደሞዝ - €10000_13000 and more
👉 ፆታ - አይጠይቅም
👉 ዕድሜ - 25እስከ 45
👉 መኖሪያ ቤት - በነፃ
👉 ፕሮሰሱ የሚፈጀው ግዜ ከ 2 - 3 ወር ነው
#10 persons
#Requirements
👉 Passport
👉photo
👉Degree documents
👉Work experience
Contact:
@Sabinavisa
+251118683939
0936363639
0936363680
የተመድ ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ የኢትዮጵያ መንግሥት በትግራይ ክልል እንደ ባንክ፣ ኤሌክትሪክ እና ቴሌኮምንኬሽን ያሉ መሠረታዊ የመንግሥት አገልግሎቶችን ባስቸኳይ እንደገና እንዲጀምር በቃል አቀባያቸው ስቲፋኒ ዱጃሪክ በኩል ባወጡት መግለጫ ጠይቀዋል። ጉተሬዝ ሁሉም ወገኖች ሰብዓዊ ዕርዳታ ሳይስተጓጎል ወደ ትግራይ እንዲገባ እንዲያመቻቹም አሳስበዋል። ሁሉም ወገኖች አሁን የወሰኑትን በሰብዓዊነት ላይ የተመሠረት ግጭት የማቆም ውሳኔ ወደ ዘላቂ የተኩስ አቁም ስምምነት ማሸጋገር እንዳለባቸው ጉተሬዝ ጨምረው አሳስበዋል።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
ኦፌኮ 2ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው!
የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረንስ (ኦፌኮ) 2ኛ መደበኛ ጉባኤውን በዛሬው ዕለት እያካሄደ ይገኛል።ጉባኤው ለ2 ቀናት የሚቆይ ሲሆን ከተለያዩ የኦሮሚያ ዞኖች የተውጣጡ የፓርቲው አባላትና ኃላፊዎች ተገኝተውበታል።በጉባኤው በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ውይይት ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።
[EBC]

በብላቴ ማእከል በ2 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ለሚገነባ አውሮፕላን ማረፊያ መሠረተ ድንጋይ ተቀመጠ።
በብላቴ የልዩ ዘመቻዎች ማሰልጠኛ ማእከል ለሚገነባው አውሮፕላን ማረፊያ የመሠረት ድንጋይ ያስቀመጡት የመከላከያ ሚኒስትር ዶክተር አብርሃም በላይ፣ የኢፌድሪ ጦር ኀይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ቩም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላና የደቡብ ክልል ርእስ መሥተዳድር ርስቱ ይርዳው ናቸው።
እንደ ኢዜአ ዘገባ የአውሮፕላን ማረፊያው ግንባታ የ75 ኪሎ ሜትር የውስጥ ለውስጥ አስፓልት መንገድን ያካተተ ነው።ከመሠረት ድንጋይ ማስቀመጥ ሥነ ሥርዐቱ ጎን ለጎን የልዩ ዘመቻዎች ኀይልና የሪፐብሊካን ጥበቃ ኀይል በዓል ሥነ ሥርዓት እየተካሄደ ነው።በበዓሉ ለኮማንዶ፣ አየር ወለድ ልዩ ኀይል፣ ጸረ ሽብርና ባሕር ጠለቅ ክፍሎች የሜዳይ ሽልማት እንደሚሰጥ የወጣው መርኃግብር አመላክቷል።

ባለፉት ስድስት ወራት በባቢሌ ዝሆኖች መጠለያ ጣቢያ በሰዎችና በዝሆኖች መካከል በተፈጠረ ግጭት 11 ዝሆኖችና 4 ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ።
የሶማሌ እና የኦሮሚያ ክልል የሚያዋስነው የባቢሌ የዝሆኖች መጠለያ ጣቢያ ከተጋረጠበት አደጋ ማዳን በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ውይይት እየተካሄደ ነው።ዩኒቨርሲቲው ከኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ባለስልጣን ጋር በመተባበር ባዘጋጀወው በዚህ መድረክ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።በመድረኩ ባለፉት ስድስት ወራት በመጠለያ ጣቢያው በዝሆኖችና በሰዎች መካከል በተፈጠረ ግጭት 11 ዝሆኖችና 4 ሰዎች መገደላቸው ተገልጿል።
ህገወጥ ሰፈራ፣ ደን ጭፍጨፋና፣ የጎሳዎች ግጭትና የእርሻ መስፋፋት ለዝሆኖችና ለሰዎች ግጭት መንስኤ መሆኑም ነው የተጠቆመው።ከዚህ በተጨማሪ መጤ አረሞች እና ያልተጠኑ የኢንቨስትመንት ፍቃዶች በተጨማሪነት ለዝሆኑ ቁጥር መመናመን እንደምክንያት እንደቀረበ የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የምርምር ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ተስፋዬ ለማ ተናግረዋል።የባቢሌ የዝሆኖች መጠለያ በ1963 ዓ.ም ሲቋቋም 600 ይደርስ የነበረው የዝሆኖች ቁጥር አሁን ላይ 300 መድረሱ በመድረኩ ተጠቁሟል።
[FBC]

በአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ መሠረት የደመወዝ ቦርድ ተቋቁሞ ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል ባለመወሰኑ ተቀጣሪዎች በሚስተዋለው የኑሮ ውድነት በእጅጉ እየተፈተኑ መሆኑን የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን አስታወቀ::
የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት አቶ ካሣሁን ፎሎ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በአገሪቱ ላይ እየተስተዋለ ያለው የኑሮ ውድነት ተቀጣሪዎች ላይ ከፍተኛ ጫና ፈጥሯል:: በአሠሪና ሠራተኛ አዋጁ መሠረት የደመወዝ ቦርድ ተቋቁሞ ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል ባለመወሰኑ በተለይ ዝቅተኛ ደመወዝ የሚያገኙ ሠራተኞች አሳሳቢ ሁኔታ ላይ መሆናቸውን ጠቁመዋል::
ከሁለት ዓመት በፊት በወጣው የአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ መሠረት የደመወዝ ቦርድ ይቋቋማል እንደሚል አስታውሰው፤ ይህ የደመወዝ ቦርድ በየዓመቱ ኑሮ ውድነቱን እያየ ዝቅተኛ የደመወዝ ወለልን የመወሰን ሥልጣን እንዳለው አስረድተዋል::
መነሻ የደመወዝ ወለል ባለመኖሩ አሰሪዎች በፈለጉት ዋጋ ሠራተኞችን ይቀጥራሉ ያሉት ፕሬዚዳንቱ፤ በዚህም የተነሳ ከሰባት መቶ ብር ጀምሮ ተቀጥሮ የሚሠራ ሠራተኛ አለ:: ደመወዛቸው አምስት ሊትር ዘይት እንኳ መግዛት የማይችል በመሆኑ ምሳ ይዘው ወደ ሥራ መሄድ እንኳን የማይችሉ ሠራተኞች መኖራቸውን አስገንዝበዋል::
ፌዴሬሽኑ በአገር አቀፍ ደረጃ ዝቅተኛው የደመወዝ ወለል ስንት ይሁን የሚል ጥናት በማጠናቀቅ ላይ መሆኑን አስታውቀው፤ የምንጠብቀው የቦርዱን መቋቋም ስለሆነ መንግሥት የሠራተኞችን ችግር በውል ተገንዝቦ በተለያዩ ምክንያቶች የዘገየው የደመወዝ ቦርድ ተቋቁሞ ዝቅተኛው የደመወዝ መነሻ የሚስተካከልበት መንገድ መፍጠር አለበት ብለዋል::
በተጨማሪም አንዳንድ ድርጅቶች በዶላር እጥረትና ተያያዥ ችግሮች ምክንያት ሥራ በአግባቡ መሥራት አልቻልንም በሚል ሠራተኛ የመቀነስ ሁኔታ እየተስተዋለ መሆኑን የጠቆሙት አቶ ካሣሁን፤ በኑሮ ውድነት ከመፈተን ባለፈ ሥራቸውን የማጣት ስጋት የተደቀነባቸው ሠራተኞችም በርካታ ናቸው:: በመሆኑም መንግሥት ሠራተኞቻቸውን ይዘው ላሉ ድርጅቶች ብድር በማመቻቸትና አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ ሠራተኛ እንዳይቀንሱ ማድረግ እንዳለበት ተናግረዋል::
በሰሜኑ የአገራችን ክፍል በተደረገው ጦርነት ምክንያት ድርጅታቸው ወድሞ ሥራቸውን መቀጠል ያልቻሉ ሠራተኞች መኖራቸውን አስታውሰዋል:: መንግሥት ለእነዚህ ድርጅቶች አስፈላጊውን እገዛ አድርጎ ወደ ሥራ የሚመለሱበትን ሁኔታ መፍጠር ቢቻል የብዙዎችን ሸክም ሊያቃልል እንደሚችልም ጠቁመዋል::
የሠራተኛ ማኅበራት ሠራተኞች ከሸማቾችና አምራቾች በቀጥታ የሚገዙበትን እድል ለመፍጠር እየሠሩ ነው ያሉት ፕሬዚዳንቱ፤ ለችግሩ ዘላቂ መፍትሔ እንዲቀመጥ ከመንግሥት ጋር ውይይት የማድረግ ሃሳብ መኖሩን ተናግረዋል::
መንግሥት በሕገ ወጥ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ በመውሰድና ዘይት ከውጭ በማስገባት የዋጋ ንረቱን በጊዜያዊነት ለማረጋጋት የጀመረውን ጥረት አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ጠይቀዋል:: ችግሩን በዘላቂነት ለመቅረፍ ግን ቦርዱን አቋቁሞ ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል ማስቀመጥ ጊዜ ሊሰጠው እንደማይገባ ጠቁመዋል::
[Addis Zemen/EPA]

የብረታ ብረት አምራች ኢንዱስትሪዎች የምርት መጠን ከ20 ወደ 10 በመቶ ዝቅ ማለቱ ተገለጸ
በኢትዮጵያ የሚገኙ ብርታ ብረት አምራች ኢንዱስትሪዎች የምርት መጠን ከ20 ወደ 10 በመቶ ዝቅ ማለቱን የብረታ ብረት ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ገለጸ።
የምርት መጠኑ ከ20 ወደ 10 በመቶና ከዛ በታች ዝቅ ማለቱን የብረታ ብረት ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ፊጤ በቀለ ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል። የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተሩ ምርቱን 20 በመቶ ማምረት ከፍተኛ ነበር ያሉ ሲሆን፣ አሁን ግን እየተመረተ ያለው ከ10 በመቶ በታች መሆኑን አስረድተዋል።
ብረታ ብረት ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት በዓመት ከ11 ሚሊዮን ቶን በላይ የሚሆኑ ምርቶችን የማምረት አቅም ስላለው 385 ቢሊዮን ብር ማግኘት ይቻል ነበር ያሉት ፊጤ፣ አሁን ግን በግማሽ ዓመት እንኳ እየተመረተ ያለው 20 ቢሊዮን ብር የሚያስገኝ ምርት ብቻ ነው ብለዋል።
@Yenetube @Fikerassefa

ምክር ቤቱ በዛሬው ዕለት ባካሄደው 6ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ!
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 6ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል፡፡
1. ምክር ቤቱ በቅድሚያ የተወያየው በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ረቂቅ ፖሊሲ ላይ ነው፡፡ በ2004 ዓ.ም ትኩረቱን በመካከለኛና ትላልቅ የማምረቻና አገልግሎት መስጫ ተቋማት ቴክኖሎጂን መጠቀም፣ መቅዳትና ማላመድን መሠረት ያደረገ የሳይንስ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ፖሊሲ በማውጣት የተለያዩ ጥረቶች ሲደረጉ ቆይተዋል፡፡
በፖሊሲው አፈጻጸም ሂደት የተገኙ ውጤቶች ቢኖሩም መሰረታዊ ለውጥ ከማምጣት አንፃር ስኬታማ እንዳልነበር ከተደረጉ ጥናቶች መረዳት ተችሏል፡፡
በመሆኑም ለአገር ውስጥ የቴክኖሎጂ ልማት ልዩ ትኩረት የሚሰጥ፤ የኢንተርፕራይዞችን የቴክኖሎጂ አቅም በማሳደግ ከምርታማነታቸው ጋር ያላቸው ትስስር የሚያጠናክር፤ ለፈጠራ ስራ /Innovation/ ትኩረት የሚሰጥ ፖሊሲ በማስፈለጉ፣ ከግብርና እና ከማኑፋክቸሪንግ በተጨማሪ ቱሪዝም፣ ማዕድን እና አይሲቲ ለአገራዊ ብልጽግና መሰረት ተደርገው በመወሰዳቸው በቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን እንዲታገዙ ማድረግ የሚገባ በመሆኑ፣ በአጠቃላይ ለአዳዲስ ለውጦች እና ፍላጎቶች ምላሽ መስጠት የሚችል እና የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ልማትን የሚያፋጥን ሁሉአቀፍ ፖሊሲ ማዘጋጀት አስፈላጊ እንደሆነ ታምኖበታል ረቂቅ ፖሊሲ ተዘጋጅቶ ለምክር ቤቱ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በረቂቅ ፖሊሲው ላይ በጥልቀት ተወያይቶ ግብዓቶች በማጽደቅ ስራ ላይ እንዲውል ወስኗል፡፡
2. ምክር ቤቱ በመቀጠል የተወያየው የ11 የአስፈጻሚ ተቋማትን አደረጃጀት፣ ስልጣንና ተግባር ለመወሰን በቀረቡ ረቂቅ ደንቦች ላይ ሲሆን በፌደራል መንግስት አስፈጻሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 1263/2014 መሰረት፡-
• የኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ባለስልጣን፣
• የኢትዮጵያ የስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት፣
• የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን፣
• የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን፣
• የኢትዮጵያ ደን ልማትን ሥልጣን፣
• የእንስሳት ልማት ኢንስቲትዩት፣
• የእንስሳት ጤና ኢንስቲትዩት፣
• የአምራች ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት፣
• የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ኢንስቲትዩት፣
• የማዕድን ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት እና
• የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት
አደረጃጀት፣ ስልጣንና ተግባር ለመወሰን በቀረቡ ረቂቅ ደንቦች ላይ ተወያይቶ ግብዓቶችን በማከል ያጸደቀ ሲሆን ደንቦቹ በነጋሪት ጋዜጣ ታትመው ከወጡበት ቀን ጀምሮ ስራ ላይ እንዲውሉ ምክር ቤቱ መወሰኑን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
To participate in the giveaway: 1. Follow @back2school_eth account on Instagram. 2. Put #backtoschoolafricaexpo and “to register call on +251 97 408 2036
+251 97 408 2037
in your TikTok video caption.
+251 97 408 2037
in your TikTok video caption.
ተቃዋሚው የአፋር ሕዝብ ነጻነት ፓርቲ የትግራይ ክልል ታጣቂዎች ባስቸኳይ ከአፋር ክልል እንዲወጡ እና መከላከያ ሠራዊት በክልሉ እንዲሰማራ ዛሬ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው መግለጫ ጠይቋል። ፓርቲው ፌደራል መንግሥቱ ከሃላፊነት በመሸሽ ከትግራይ ኃይሎች ጋር ግንኙነት ሰላም ለመፍጠር የአፋር ሕዝብ እንቅፋት እንደሆነበት አድርጎ አቅርቧል በማለት ከሷል። ፌደራል መንግሥቱ እና ሕወሃት ተኩስ ለማቆም የደረሱበትን ውሳኔ በበጎ እንደሚያየው የገለጠው ፓርቲው፣ ሆኖም ውሳኔው የአፋር በርካታ አካባቢዎች በሕወሃት ቁጥጥር ስር ያሉ መሆናቸውን፣ የአፋርን ሰብዓዊ ቀውስ፣ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን፣ የሕዝቡን ጥቅሞች እና ስጋቶች ከግምት ያላስገባ በመሆኑ ውሳኔውን በጥርጣሬ እንደሚያየው ጠቁሟል። የአፋር ሕዝብ መገለል ከፌደራል መንግሥቱ ጋር ግጭት ውስጥ እንዳያስገባው ስጋት እንዳለውም ፓርቲው አስጠንቅቋል።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
👍1
የኢትዮጵያ መንግሥት በኦሮሚያ ክልል ከሚንቀሳቀሰው እና ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ጦር ብሎ ከሚጠራው ቡድን ጋር እርቅ እንዲያወርድ የኦሮሞ ፌድራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) ሊቀ-መንበር ጥሪ አቀረቡ።
ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ይኸን ጥሪ ያቀረቡት ዛሬ የኦፌኮ ሁለተኛ አጠቃላይ ጉባኤ በአዲስ አበባ መካሔድ ሲጀምር ነው።ፕሮፌሰር መረራ በጉባኤው መክፈቻ ባደረጉት ንግግር የኢትዮጵያ መንግሥት ከአንድ አመት በላይ በትግራይ ከተዋጋው ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ ጋር ግጭት ለማቆም መወሰኑን አስታውሰው በኦሮሚያም ባለሥልጣናቱ "ሸኔ" ከሚሉት ታጣቂ ጋር እርቅ ሊያወርድ እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል።
በሰሜን ኢትዮጵያ የተካሄደውን ጦርነት ኦፌኮ ከጅማሮው መቃወሙን ያስታወሱት መረራ አሁንም መንግስት በትግራይ ብቻ ሳይሆን ኦሮሚያን ጨምሮ ግጭቶች ባሉባቸው አካባቢዎች ልዩነቶችን በእርቅ በመቋጨት ለህዝብ ሰላም እንዲሰጥ ጠይቀዋል "ማንም ያሸንፍ ፤ ጫካ ያሉት የኦሮሞ ልጆችም ያሸንፉ ፣ ሌሎችም ያሸንፉ ነገርግን የኦሮሞን ሕዝብ ትልቅ ዋጋ ያስከፍላል" ያሉት የኦፌኮ ሊቀ-መንበር "በኦሮሞ አምላክ ይሁንባችሁ። የቻላችሁ ሰዎች አስቡበት ብላችሁ ንገሯቸው።የኦሮሞን ህዝብ አጥፍታችሁ አትጥፉ፤ ይህ ጨወታ አያዋጣንም።በመላ የኦሮሚያ ዱር ላሉት ያቺኑ ለህወሃቶች የሰጣችኋትን ዕድል ለእነርሱም ስጡ" የሚል ጥሪ አቅርበዋል።
ፕሮፌሰር መረራ በንግግራቸው ከኦፌኮ 206 ጽህፈት ቤቶች 203ቱን በመዝጋት እና አመራርና አባላትን በማሰር መንግስት ከምርጫ ተሳትፎ ፓርቲያቸውን እንደገፋ ጠቅሰው ተችተዋል።ዛሬ እና ነገ በሚካሄደው ጠቅላላ ጉባኤው ኦፌኮ የአመራር ሹም ሽር ያደርጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ዶይቼ ቬለ ዘግቧል።በፓርቲው ጠቅላላ ጉባኤው ከአንድ ዓመት ከመንፈቅ የእስር ቆይታ በኋላ ባለፈው ታህሳስ መጨረሻ የተፈቱት አቶ ጃዋር መሃመድን ጨምሮ የፓርቲው አመራሮች ታድመዋል።
[DW]

የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረንስ (ኦፌኮ) ፕሮፌሰር መረራ ጉዲናን በድጋሚ የፓርቲው ሊቀመንበር አድርጎ መምረጡን ገለጸ፡፡
ፓርቲው 2ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው፡፡ፓርቲው በዚሁ ጉባዔው ከፕሮፌሰር መረራ ጉዲና በተጨማሪ፥ አቶ በቀለ ገርባን የኦፌኮ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር አድርጎ መርጧል፡፡እንዲሁም አቶ ጀዋር መሀመድን ምክትል ሊቀመንበር አድርጎ መምረጡ ተገልጿል፡፡በተጨማሪም ፓርቲው እያካሄደ ባለው መደበኛ ጉባኤው አቶ ጀዋር መሀመድን ጨምሮ 17 የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላትን መርጧል።ትናንት መካሄድ የጀመረው የኦፌኮ ጉባኤ ዛሬም የቀጠለ ሲሆን፥ የተለያዩ ውሳኔዎችን ያስተላልፋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተጠቁሟል፡፡

ኢትዮ ኤሌክትሪክ ወደ ፕሪምየር ሊጉ አድጓል!
ኢትዮ ኤሌክትሪክ አንድ ጨዋታ እየቀረዉ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ማደጉን አረጋግጧል።
Via Hatrick Sport
@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮ ኤሌክትሪክ አንድ ጨዋታ እየቀረዉ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ማደጉን አረጋግጧል።
Via Hatrick Sport
@YeneTube @FikerAssefa
የጂቡቲ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኦማር ጉሌህ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ።
ፕሬዚዳንቱ ቦሌ ዓለም ዐቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ጠቅላይ ሚኒስተር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።ለፕሬዝዳንቱ ክብር 7 ጊዜ መድፍ ተተኩሷል።
ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኦማር ጉሌህ በቆይታቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጋር የሁለቱን አገራት ትብብር ወደላቀ ደረጃ የሚያደርስ ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።ኢትዮጵያና ጂቡቲ ረጅም ዘመናትን ያስቆጠረ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ያላቸው አገራት ናቸው።
@YeneTube @FikerAssefa
ፕሬዚዳንቱ ቦሌ ዓለም ዐቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ጠቅላይ ሚኒስተር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።ለፕሬዝዳንቱ ክብር 7 ጊዜ መድፍ ተተኩሷል።
ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኦማር ጉሌህ በቆይታቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጋር የሁለቱን አገራት ትብብር ወደላቀ ደረጃ የሚያደርስ ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።ኢትዮጵያና ጂቡቲ ረጅም ዘመናትን ያስቆጠረ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ያላቸው አገራት ናቸው።
@YeneTube @FikerAssefa
https://tttttt.me/sabinaadvisor
የስራ ጉዞ ወደ # Europe
#Schengen_visa
👉 የሚሰራበት አገር - geneva, Swaziland
👉 የስራው አይነት :- accounting
👉 የስራ ቀናት - 6 ቀናት/ week
👉 የወር ደሞዝ - €10000_13000 and more
👉 ፆታ - አይጠይቅም
👉 ዕድሜ - 25እስከ 45
👉 መኖሪያ ቤት - በነፃ
👉 ፕሮሰሱ የሚፈጀው ግዜ ከ 2 - 3 ወር ነው
#10 persons
#Requirements
👉 Passport
👉photo
👉Degree documents
👉Work experience
Contact:
@Sabinavisa
+251118683939
0936363639
0936363680
የስራ ጉዞ ወደ # Europe
#Schengen_visa
👉 የሚሰራበት አገር - geneva, Swaziland
👉 የስራው አይነት :- accounting
👉 የስራ ቀናት - 6 ቀናት/ week
👉 የወር ደሞዝ - €10000_13000 and more
👉 ፆታ - አይጠይቅም
👉 ዕድሜ - 25እስከ 45
👉 መኖሪያ ቤት - በነፃ
👉 ፕሮሰሱ የሚፈጀው ግዜ ከ 2 - 3 ወር ነው
#10 persons
#Requirements
👉 Passport
👉photo
👉Degree documents
👉Work experience
Contact:
@Sabinavisa
+251118683939
0936363639
0936363680
Forwarded from Teklu Tilahun - ተክሉ ጥላሁን
#ወደ_ሀብት_ጉዞ
አዲስ መጽሐፍ በገበያ ላይ
ቲንክ ኤንድ ግሮው ሪች በሚለውና #አስበህ_ሐብታም_ሁን በሚል በተተረጎመው መጽሐፉ የምናውቀው የናፖሊዮን ሂል አዲስ መጽሐፍ በገበያ ላይ።
#ወደ_ሀብት_ጉዞ
ይህ ወደ ሀብት ጉዞ የተሰኘው መጽሐፍ እያንዳንዱን ሕልማችንንና ዓላማችንን ለማሳካት ያግዘናል፡፡
ብልፅግና በገንዘብና ዝና ብቻ የተገደበ ትርጉም እንደሌለው ያሳየናል፡፡ እውነተኛ ባለጸጋ ለመሆን በሁሉም የሕይወት ዘርፎች መበልፀግ ያስፈልጋል- በአካል፣ በመንፈስ፣ በገንዘብ፡፡
ለዚህም ደግሞ ከ25 ሺ በላይ ሰዎች የውድቀት ምክንያት፣ ከ500 በላይ ስኬታማ ሰዎች ምስጢርና የሀያ አምስት አመታት የምርምር ውጤት... ወደ #ሀብት_ጉዞ መጽሐፍን ፈጥሯል።
ከ60 ሚሊየን ኮፒ በላይ ከተሸጠው አስበህ ሀብታም ሁን መጽሐፍ ቀጥሎ ከፍተኛ ሽያጭን የተቀዳጀ መጽሐፍ።
እነሆ በሁሉም መልክ ወደ ሀብት ጉዞ!!
የናፖሊዮን ሂልን መጽሐፍ ይዞ!!!
በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ያገኙታል።
*
ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram-
https://tttttt.me/teklu_tilahun

ተዋናይ ዊል ስሚዝ ኦስካርስ በተሰኘው የፊልም ጥበብ የሽልማት መድረክ የሚስቱን ስም አንስቶ ያብጠለጠለውን ታዋቂውን ኮሜዲያን ክሪስ ሮክን በጥፊ ተማታ።
ክሪስ ሮክ፤ የዊል ስሚዝ ሚስት ጄዳ ፒንኬት ስሚዝን የፀጉር ቁርጥ በቀልድ ወረፍ ካደረገ በኋላ ነው ይህ የተከሰተው።ዊል ስሚዝ ከመቀመጫው በመነሳት ወደ መድረኩ አቅንቶ ክሪስ ሮክን በጥፊ አጋጭቶ ሲመለስ ብዙዎች ጉዳዩ ቀልድ ነው ብለው አስበው ነበር።ነገር ግን ወደ ወንበሩ ከተመለሰ በኋላ "የሚስቴን ስም በ. . . አፍህ አታንሳ" ብሎ ሲጮህ ነው ብዙዎች ተዋናዩ ማምረሩን የተረዱት።
ስሚዝ ከዚህ ብዙዎችን ካስበረገገ ድርጊት በኋላ የኦስካር ሽልማቱን ሲያነሳ ለድርጊቴ ይቅርታ በሉኝ ብሏል።"አካዳሚውን [ኦስካር ሸላሚው ኮሚቴ] እንዲሁም ለሽልማት የታጩ የተውኔት አጋሮቼን ይቅርታ መጠየቅ እሻለሁ" ሲል ተማፅኗል።
ዊል ስሚዝ፤ ኪንግ ሪቻርድ በተሰኘው ፊልም ላይ የቴኒስ ከዋክብቱን ቬነስና ሰሪና ዊሊያምስ አባት ሆኖ በመተወኑ ነው በሕይወቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ለስም የከበደውን የኦስካር ሽልማት ያገኘው።"ጥበብ የሕይወት ቅጂ ናት።ልክ እንደ ተወንኩት ሪቻርል ዊሊያምስ የእብደት ሥራ ሠርቻለሁ። ነገር ግን ፍቅር የእብድ ሥራ እንድትሠሩ ያደርጋችኋል።"
ባለቤቱ ፒንኬት ስሚዝ ከዚህ በፊት የፀጉር መነቀል የሚያስከትል አለፔሲያ የተሰኘ በሽታ እንዳለባት ተናግራ ነበር።የዊል ስሚዝ ጥፊ ሰላባ የሆነው ክሪስ ሮክ በሁኔታው እጅግ ተደናግጦ "በቴሌቪዥን ታሪክ እጅግ አስደናቂውን ክስተት ታድመናል" ሲል ተደምጧል።
Via BBC