ኢትዮ ቴሌኮም ገመድ አልባ የብሮድባንድ ኢንተርኔት አገልግሎት ለመኖሪያ ቤት አቀረበ!
ኢትዮ ቴሌኮም ገመድ አልባ 4ጂ ብሮድባንድ ፈጣን የኢንተርኔት አገልግሎት ለመኖሮያ ቤቶች ማቅረቡን አስታወቀ።የድርጅቱ ሥራ አስፈፃሚ ወይዘሪት ፍሬህይወት ታምሩ በሰጡት መግለጫ፤ የአሁኑ አገልግሎት ከዚህ በፊት በገመድ (ፋይበርና ኮፐር) ሲሰጥ የቆየውን አግልግሎት ፈጣን በሆነና በተሻለ ጥራት ገመድ አልባ በሆነ መልኩ አግልግሎት መስጠት የሚያስችል ነው ብለዋል።
እንደ ዋና ሥራ አስፈፃሚዋ ማብራሪያ፤ አገልግሎቱ ደንበኞች በመኖርያ አካባቢያቸው አልያም በመረጡት ስፍራ 4ጂ የሞባይል ኔትዎርክን በከፍተኛ ፍጥነት የኢንተርኔት አገልግሎት ማግኘት የሚያስችል አማራጭ ነው።ይህ አገልግሎት በተለይም የፋይባር እነ ኮፐር ገመዶች በማይደርሱባቸው የመኖሪያ አካባቢዎች ተመራጭ መሀኑን ወ/ት ፍሬህይወት ገልጸዋል።ኢትዮ ቴሌኮም በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ ተገድቦ የነበረውን ድርጅቱ ባደረገው የማስፋፊያ ተግባር የ4ጂ አገልግሎትን 136 ከተሞች አግልግሎት ተጠቃሚ መሆን መቻላቸውን ወይዘሪት ፍሬህይወት ገልፀዋል።
Via EPA
@YeneTube @FikerAssefa

ደራርቱ ቱሉ በአትሌቶች የሽልማነት ሥነ-ሥርዓት ላይ ሰላም እንዲወርድ ተማጸነች!
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝደንት ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ ትናንት ረቡዕ መጋቢት 14/2014 ዓ.ም ቤልግሬድ ውስጥ በተካሄደው የአትሌቲክስ ውድድር ላይ ለተሳተፉ አትሌቶች በተከናወነ የሽልማት ሥነ-ሥርዓት ላይ የፌደራል መንግሥት እና የትግራይ ኃይሎች ሰላም እንዲያወርዱ ጠየቀች።ደራርቱ ቱሉ በ18ኛው የዓለም ቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ ተሳትፈው ኢትዮጵያ የውድድሩ የበላይ ሆና እንድታሸነፍ በማድረግ አስደናቂ ድል ተጎናጽፈው ለተመለሱት የአትሌቲክስ ቡድኑ አባላት በተደገረው የሽልማት ሥነ-ሥርዓት ላይ ጦርነት እንዲያቆም ተማጽናለች።
"ትግራይ ትናንም ኢትዮጵያ ናት።ዛሬም ኢትዮጵያ ናት። ነገም ኢትዮጵያ ናት።እባካችሁ መሪዎቻችን፤ እባካችሁ፤ ተጠቅማችሁ ሳይሆን ተጎድታችሁ ኢትዮጵያን አንድ አድርጓት። ይህን ከፈጣሪ ጋር ትችላለሁ" ስትል ደራርቱ ጥሪ አቅርባለች።ኮማንደር ደራርቱ ስሜታዊ ሆና እያነባች ባደረገችው በዚህ ንግግር "የትግራይ እናቶች እና አባቶች፤ እናቶቻችን እና አባቶቻችን ናቸው። በእርግጠኝነት ደግሞ ነገ ሌላ ቀን ነው። ኢትዮጵያ ታርቃ አንድ ሆና ትቆማለች" ብላለች።
[BBC]

በከረዩ የሚችሌ ገዳ የጅላ አባላት ላይ በተፈጸመው ግድያ ዙሪያ በምርመራ ሂደቱ ላይ ጫና እየተደረገ ነዉ ሲል ኢሰመኮ አስታወቀ!
በከረዩ የሚችሌ ገዳ የጅላ አባላት ላይ በመንግሥት የታጠቁ ሀይሎች በተፈጸመው ግድያ ዙሪያ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን እየተደረገ ያለዉን የምርመራ ሂደት ተመልክቻለሁ ብሏል።በሂደቱ የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ቢሮ ፣ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ፣ የምሥራቅ ሸዋ ዞን ፖሊስ መምሪያ ፣ ግድያውን ለመመርመር የተዋቀረውን የምርመራ ቡድን እንዲሁም የከረዩ ማኅበረሰብ የሀገር ሽማግሌዎችን አነጋግሬያለሁ ሲል ኮሚሽኑ ባወጣው መግለጫ ጠቅሷል፡፡
በዚህም መሰረት በአንድ በኩል የተፈጸመውን ግድያ ለመመርመር ከኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ እና ከክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የተውጣጣ መርማሪ ቡድን ተቋቁሞ ሥራ የጀመረ መሆኑን ኢሰመኮ አስታውቋል፡፡ ሆኖም በአካባቢው ማኅበረሰብ በግድያው ላይ ተሳትፎ ያላቸው መሆኑን የተጠቆሙ ፣ አልያም በድርጊቱ ዋነኛ ፈጻሚ ናቸው ተብለው የተጠረጠሩ ሰዎች ገና በቁጥጥር ስር ያልዋሉ ወይም ምርመራ እየተደረገባቸው አለመሆኑን ምክንያታዊ አሳማኝ ሁኔታዎችን ኮሚሽኑ ተመልክቻለሁ ብሏል።
ከእነዚህ ተጠርጣሪዎች ውስጥ የተለያዩ የመንግሥት የሥራ ኃላፊነት ቦታዎች ላይ የሚገኙ ጭምር ያሉ በመሆናቸው በምርመራ ሂደቱ ላይ ጫና እያደረሱ መሆናቸውን ወይም ለሂደቱ አስፈላጊ ድጋፍ ማድረግ የሚገባቸው የፀጥታ እና የአስተዳዳር አካላትም ሥራው በሚፈለገው ፍጥነት ምርመራዉ እንዲጠናቀቅ በቂ ትብብር እያደረጉ እንዳልሆነ ተዓማኒ የመረጃ ምንጮች ደርሰዉኛል ብሏል፡፡ በተጨማሪም የምርመራ ሂደቱን በተመለከተ ፣ በቁጥጥር ስር የዋሉ ተጠርጣሪዎች በሕግ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ፍርድ ቤት ያልቀረቡ መሆኑን ኮሚሽኑ ያወጣውን መግለጫ ብስራት ሬድዮ ተመልክቷል፡፡
ኮሚሽኑ መንግሥት በሕዝቡ ላይ የተፈጠረውን ቅሬታ በእርቅ እንዲፈታ ጥረት ማድረጉ ተገቢ ቢሆንም የእርቅ ሂደቱ የወንጀል ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት ሊያስቀር ስለማይችል የሕግ ተጠያቂነት ሂደቱ ሊደናቀፍ አይገባም ሲል ገልጿል፡፡ የክልሉ መንግሥት ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ እያከናወናቸው ያሉ ሥራዎች አበረታች መሆናቸው ኮሚሽኑ ገልጾ ይህን መሰል ሂደቶች በአካባቢው ማኅበረሰብ የሕግ ተጠያቂነትን ለመተካት አልያም ለማስቀረት የሚደረግ መሆኑን የሚያመላክት ቅሬታ ካለ ከጥቅሙ ይልቅ አሉታዊ ተጽዕኖው ሊያመዝን ስለሚችል ከፍተኛ ጥንቃቄ ይሻዋል ሲል ባወጣው መግለጫ ጠቅሷል ።
[ዳጉ ጆርናል]

የኢትዮጵያ መንግስት ለሰብዓዊነት ሲባል ግጭት ለማቆም ሰለመወሰኑ የወጣ መግለጫ
የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ክልል ለሚገኙ የሰብዓዊ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦቱ የተሳለጠ እንዲሆን የተለያዩ እርምጃዎችን በመውሰድ ላይ ይገኛል። በዚህም መሰረት የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ እርዳታ የአየር በረራዎች ቁጥር እንዲጨምር እንዲሁም ለእርዳታ አቅራቢ ድርጅቶች የነዳጅ እና የጥሬ ገንዘብ የሚቀርብበትን ስርዓት የተሳለጠ እንዲሆን ተደርጓል። ከዚህ ጋር በተያያዘም የአለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ፣ የአለም ጤና ድርጅት እና የአውሮፓ ህብረት የሰብዓዊ እርዳታዎችን ማደረስ እንዲችሉ የአየር በረራ ተመቻችቷል።ከዚህ በተጨማሪም የኢትዮጵያ መንግስት በአብአላ-መቀሌ የየብስ ትራንስፖርት መስመር በኩል የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት መድረስ እንዲችል አስፈላጊውን ሁሉ እያደረገ ይገኛል።
ይሁን እንጂ በአሁኑ ወቅት በሺዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ክልል ነዋሪዎች የሰብዓዊ እርዳታን ፍለጋ ወደአጎራባች ክልሎች እየተጓዙ መሆኑ እየተስተዋለ ነው። በዚህም በትግራይ አጎራባች ክልሎች የሚኖሩ ዜጎች ከትግራይ ክልል የሚመጡ የሰብዓዊ እርዳታ ፈላጊ ዜጎችን ተቀብሎ በማስተናገድ እያሳዩ ያለው በጎ ተግባር በህዝቦች መካከል ያለውን የወንድማማችነት እና የአንድነት መንፈስ የሚያሳይ ነው። መንግስት እነዚህ ዜጎች የሰብዓዊ እርዳታው ከቀያቸው ሳፈናቀሉ ባሉበት እንዲርሳቸው ቢደረግ እንግልታቸውን እንድሚቀንስ በጽኑ ያምናል። በመሆኑም መንግስት በከፍተኛ ችግር ውስጥ የሚገኙ ዜጎቹን ችግር በአፋጣኝ የመፍታት ኃላፊነቱ ከምንም ነገር በላይ ቅድሚያ የሚሰጠው መሆኑን በመረዳት የአስቸኳይ የሰብዓዊ አቅርቦቶች ወደትግራይ ክልል በበቂ ሁኔታ መድረስ የሚችሉበትን ሁኔታ ለማሳካት የተቻለውን ሁሉ ጥረቶች ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኑን ለመግለጽ ይወዳል።
በዚህም መሠረት በከፍተኛ ችግር ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን ህይወት ለመታደግ እና የዜጎችን እንግልት ለመቀነስ ይቻል ዘንድ ከተለመደው የተለዩ እርምጃዎችን መውሰድ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ መንግስት ይህ ውሳኔ ከወጣበት ሰዓት ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ ለሰብዓዊነት ሲባል ግጭት የማቆም ውሳኔ አስተላልፏል። በዚህ አጋጣሚ መንግስት ዓለም ዓቀፉ የለጋሾች ማህበረሰብ እያቀረበ ያለውን ድጋፍ እና እርዳታ በከፍተኛ መጠን እንዲጨምር ጥሪ ያቀረባል።
የሰብዓዊ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦቱ በተሳለጠ ሁኔታ መድረስ እንዲችል ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተባብሮ ለመስራት ያለውን ቁርጠኝነት በድጋሚ ያረጋግጣል። ይህ የመንግስት ጥረት እና ቁርጠኝነት የሰብዓዊ ሁኔታውን በማሻሻል ረገድ የሚኖረው ስኬት የሚረጋገጠው በሌላኛው ወገን የሚገኘው አካል በተመሳሳይ ለዚህ አላማ በሚኖረው ቁርጠኝነት ልክ መሆኑን መንግስት ያምናል። ይህ በመንግስት በኩል የተላለፈው ውሳኔ አላማው የአስቸኳይ የሰብዓዊ ድጋፍ በነጻነት ተጓጉዞ ለእርዳታ ፈላጊ ዜጎች ለመድረስ እንዲችል ነው። በመሆኑም ለሰብኣዊነት ግጭት የማቆም ውሳኔ የተፈለገውን ውጤት ማምጣት እንዲችል መንግስት በትግራይ ክልል የሚገኙ አማጺያን ከማንኛውም የጥቃት እንቅስቃሴ እንዲታቀቡ እና ን በጉልበት ከያዟቸው የአጎራባች ክልል አካባቢዎችእንዲወጡ ይጠይቃል።የኢትዮጵያ መንግስት ይህ ለሰብኣዊነት ግጭት የማቆም ውሳኔ በሰሜን ኢትዮጵያ ያለውን የሰብዓዊ ሁኔታ በእጅጉ ሊያሻሽል እንደሚችል ብሎም በቀጣይ ያለተጨማሪ ደም መፋሰስ ለግጭቱ መፍትሔ ሊያመጣ እንደሚችል ተስፋ ያደርጋል።
የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

በአዲስ አበባ በህገ-ወጥ መንገድ ተከማችተው የተገኙ በርካታ የመኪና መለዋወጫና ንብረቶች ተያዙ!
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በተለያዩ የንግድ ሱቆችና በግለሰቦች መኖሪያ ቤቶች በተደረገ ብርበራ በህገ-ወጥ መንገድ ተከማችተው የተገኙ በርካታ ላፕቶፖች፣ ሞባይል ስልኮችና የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች ከ18 ተጠርጣሪዎች ጋር በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ፖሊስ ገለፀ ።
በተለምዶ ሱማሌ ተራና አሜሪካን ግቢ እየተባሉ በሚጠሩት አካባቢዎች በሚገኙ የንግድ ሱቆችና መኖሪያ ቤቶች ላይ የክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ ባደረገው ጥናትና በህዝብ ጥቆማ መነሻነት ንብረቶቹ ተይዘዋል።

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ለሶማሌ ክልል 30 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ!
ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ለሶማሌ ክልል ያደረገውን የ30 ሚሊዮን ብር ድጋፍ የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጀማል አህመድ በጅግጅጋ በመገኝት አስረክበዋል።
የሶማሌ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ በበኩላቸው፣ ድርቅ በክልሉ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን ገልፀው ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ይህንን ድጋፍ ማድረጉ ትልቅ እርምጃና የአጋርነት ማሳያ ነው ብለዋል።
የክልሉ መንግስት ድርቁ ያደረሰውን ጉዳት ለመቀልበስ በሚያደርገው እንቅስቃሴም ኢንቨስትመንት ግሩፑ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።
ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ድገፍ ከመስጠት ባለፈ በክልሎች በተለያዩ የኢንቨስትመንት መስኮች እንደሚሰማራ ዋና ስራ አስፈፃሚው አቶ ጀማል አህመድ መናገራቸውን የክልሉ መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ዘገባ ያመለክታል።

የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ዲና ሙፍቲ ኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጣ አምና ትግራይ ክልል ውስጥ የዓለማቀፉን ድንበር የለሹ ሐኪሞች ቡድን ሦስት ሠራተኞች የገደሉት የመንግሥት ወታደሮች ናቸው በማለት በቅርቡ የሠራው ዘገባ "መሠረተ ቢስ ነው" ሲሉ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አጣጥለውታል። ዲና ጋዜጣው ዘገባውን ያተመው ተጨማሪ እና ጥልቅ ምርመራ ሳያደርግ እና በኃይል ተገደው ሊመሰክሩ የሚችሉ በአማጺው ሕወሃት ቁጥጥር ስር ያሉ ምርኮኛ ወታደሮችን በማነጋገር ነው በማለት ተችተዋል።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
ህወሓት የሰብዓዊ እርዳታ ትግራይ የሚደርስ ከሆነ ግጭት ለማቆም እስማማለሁ አለ!
ከፌደራል መንግሥቱ ጋር ላለፉት 16 ወራት ግጭት ውስጥ የቆየው ህወሓት የሰብዓዊ እርዳታ ትግራይ የሚደርስ ከሆነ ግጭት ለማቆም እንደሚስማማ ገለጸ።ህወሓት ይህን ያለው ትናንት ሐሙስ መጋቢት 15/2014 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ የፌደራሉ መንግሥት በትግራይ ክልል ሰብዓዊ እርዳታ በተቀላጠፈ ሁኔታ እንዲደርስ ለማስቻል ግጭት ለማቆም መወሰኑን ካስታወቀ በኋላ ነው።
የፌደራሉ መንግሥት ከዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው የተከሰተውን ሰብአዊ ቀውስ "በእጅጉ ሊያሻሽል" ስለሚችል እና "በቀጣይ ያለተጨማሪ ደም መፋሰስ ለግጭቱ መፍትሔ ሊያመጣ እንደሚችል" ተስፋ በማድረግ መሆኑን ገልጿል።መንግሥት ይህ ውሳኔ የሚፈለገውን ውጤት እንዲያመጣ "በትግራይ ክልል የሚገኙ አማጺያን ከማንኛውም ጥቃት እንዲታቀቡና በኃይል ከያዟቸው የአጎራባች ክልል አካባቢዎች እንዲወጡ" ጠይቋል።
ይህን ተከትሎ ህወሓት ባወጣው መግለጫ ላይ በበቂ መጠን እና ተቀባይነት ባለው ጊዜ ሰብዓዊ እርዳታ ወደ ትግራይ የሚደርስ ከሆነ ጥሪውን እንደሚቀበል ገልጿል።በትግራይ ካለው የሰብዓዊ እርዳታ ፍላጎት ጋር ተመጣጣኝ የሆነ እና ተቀባይነት ባለው ጊዜ የሰብዓዊ እርዳታው የሚደርስ ከሆነ "የትግራይ መንግሥት ግጭት ለማቆም ቁርጠኛ ነው" ብሏል።

የመኖርያ ቤት ኪራይ ዋጋ ጭማሪን እና ተከራዮችን ማስወጣትን ለመገደብ የወጣው ደንብ ለሚቀጥሉት ሶስት ወራት መራዘሙን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዛሬ አሳውቋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የዜጎችን ጥያቄና አገራዊ ሁኔታን ከግምት ውስጥ በማስገባት ከዚህ በፊት የመኖርያ ቤት ተከራዮችን ለማስለቀቅና የመኖሪያ ቤት ኪራይ ጭማሪ ለመገደብ ደንብ ማውጣቱን አስታውሷል።ደንቡ ላለፉት ሶስት ወራት እንዲራዘምም ተደርጎ እንደነበር ገልጿል።
አሁንም ዜጎችን ከተለያዩ ጫናዎች ለመከላከል ሲባል ይህ ደንብ ለሚቀጥሉት ሶስት ወራት እንዲራዘም የከተማው አስተዳደር መወሰኑን አሳውቋል።ስለሆነም በዚሁ መሰረት በሚቀጥሉት ሶስት ወራት ተከራዮችን ማስለቀቅና እና የቤት ኪራይ የዋጋ ጭማሪ ማድረግ የተከለከለ መሆኑን ተገልጿል።

የጉጂ አባ ገዳ መኖሪያ ቤታቸው ላይ 'ኦነግ ሸኔ' ጥቃት መፈጸሙን ተናገሩ!
የኦሮሞ አባ ገዳዎች ሕብረት ሰብሳቢ እና የጉጂ አባ ገዳ የሆኑት ጂሎ ማንዶ ታጣቂዎች በመኖሪያ ቤታቸው ላይ ጥቃት መፈጸማቸውን ለቢቢሲ ተናገሩ።አባ ገዳ ጂሎ ከትናንት በስቲያ ረቡዕ ዕለት መጋቢት 14/2014 ዓ.ም. ከእኩለ ሌሊት በኋላ በቤታቸው ላይ ለተፈጸመው ጥቃት እራሱን የኦሮሞ ነጻነት ጦር ብሎ የሚጠራውን እና መንግሥት ሸኔ የሚለውን ታጣቂ ቡድን ተጠያቂ አድርገዋል።የታጣቂ ቡድኑ ቃል አቀባይ ግን ታጣቂዎቻቸው 'የተባለውን ጥቃት አልፈጸሙም' ሲሉ አስተባብለዋል።አባ ገዳው ጥቃት በተፈጸመበት ዕለት በመኖሪያ ቤታቸው ባለመኖራቸው ከጥቃቱ መትረፋቸውንና በንብረት ላይ ከደረሰው ውጪ በሰው ላይ ጉዳት አለመድረሱን ገልጸዋል።
"በቁጥር ስንት ሆነው እንደመጡ ባላውቅም በአራት ሞተር ሳይክሎች መጥተው ቤቱ ላይ ተኩስ ከፈቱ። በርካታ ጥይት ተኩሰው ቤት ሰባብረው፣ ቤት ውስጥ የነበረ አንድ ኩንታል ቡና በትነው ሄዱ እንጂ ሰው እና ከብት ምንም አልሆነም" በማለት የነበረውን ሁኔታ አባ ገዳ ጂሎ ያስረዳሉ።አባ ገዳው ታጣዊዎች ትጥቅ ፈትተው የሰላም አማራጭን እንዲከተሉ ጥሪ ማስተላለፋቸው የጥቃቱ ዒላማ እንዲሆኑ እንዳደረጋቸው ያምናሉ።"እነርሱ መጀመሪያም ቂም ይዘውብኝ ነበር። እየደወሉ፤ 'የኦሮሞ ነጻነት ጦር በሰላም ግቡ እያልክ የምትቀሰቅሰው አንተ ነህ' ሲሉኝ ቆይተዋል" በማለት አባ ገዳው ይናገራሉ።
"እየደወሉ '600 የሚሆን ሠራዊት አስገብተህ (ትጥቅ አስፈትተህ) መሳሪያቸውን ወርሰሃል፤ ያን መሳሪያ እስክታመጣ በሕይወትህ ፍረድ' ይሉኛል" ሲሉ ጂሎ ማንዶ ከታጣቂዎቹ ይደርስባቸው ስለነበረው ዛቻ ያስረዳሉ።እራሱን የኦሮሞ ነጻነት ጦር ብሎ የሚጠራው ታጣቂ ቡድን ቃል አቀባይ የሆነው ኦዳ ተርቢ፤ የኦሮሞ ነጻነት ጦር አባ ገዳዎችን እና የገዳ ሥርዓትን እንደሚያከብር ገልጸው፤ "በከረዩ አባ ገዳዎች ላይ የተፈጸመውን እና የመንግሥት (የዐቢይ) ጦር ለሥርዓቱ ያለውን ንቀት ከግምት በማስገባት ይህ የተፈጸመው በእነርሱ (በመንግሥት ጦር) ሊሆን ይችላል" ብለዋል።ከዚህ ቀደም የጉጂ እና የቦረና አባ ገዳዎች 'ኦነግ ሸኔ' የኦሮሞ ጠላት ነው በማለት ማወጃቸው ይታወሳል።ታጣቂዎች ትጥቅ እንዲፈቱም ጥሪ አስተላልፈዋል።
Via BBC

👍1
ብሪታኒያ የኢትዮጵያ መንግሥት ለሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ላልተወሰነ ጊዜ በሰብዓዊነት ላይ የተመሠረተ የተናጥል ተኩስ አቁም ማድረጉን እና ያልተገደበ የሰብዓዊ ዕርዳታ ለትግራይ እንዲገባ ሁኔታዎችን ማመቻቸቱን በአድናቆት እንደምትመለከተው ገልጻለች።
ብሪታኒያ አዲስ አበባ በሚገኘው ኢምባሲዋ በኩል ባወጣችው መግለጫ፣ ሕወሃት ተመሳሳይ ርምጃ እንዲወስድ ጥሪ አድርጋለች። ሕወሃት ዘግየት ብሎ ለተኩስ አቁም ዝግጁ መሆኑን ገልጧል።
@Yenetube @Fikerassefa

የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዜሌንስኪ የአውሮፓ ህብረት አገራቸውን በአባልነት እንዲቀበላት ጠየቁ፡፡
ዜሌንስኪ ጥያቄውን ያቀረቡት ትናንት ሌሊት በቪዲዮ ሊንክ (ምስለ ጉባኤ) መላ ለአውሮፓ ህብረት ምክር ቤት ባስተላለፉት መልዕክት እንደሆነ ሜይል ኦን ላየን ፅፏል፡፡ጦርነቱ እንደቀጠለ ሲሆን ሩሲያ ድኔፕሮ ወደ ተባለው የዩክሬይን 4ኛው ትልቅ ከተማ ሁለት ከፍተኛ ሚሳየሎን መተኮሷ ተሰምቷል፡፡የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ)ን ልዩ የመሪዎች ጉባኤ መጠናቀቅ ተከትሎ ሩሲያ በዩክሬን ጅምላ ጨራሽ መሳሪያ የምትጠቀም ከሆነ ለምላሹ ዝግጁ ነን ብለዋል፡፡
ይሁንና ባይደን ምላሻቸውን በምን ዓይነት ሁኔታ ተግባራዊ እንደሚያደርጉት የታወቀ ነገር የለም፡፡የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በጦርነቱ መጀመሪያ በዩክሬኑ ጦርነት ጣልቃ የሚገባ ካለ ውርድ ከራሴ ሲሉ ማስጠንቀቃቸው ይታወቃል፡፡

በባሌ ዞን በሚገኙ አካባቢዎች የተቋረጠውን የኤሌክትሪክ ኃይል የመጠገን ሥራ እየተከናወነ ነው!
በባሌ ዞን በሚገኙት የሮቤ፣ ጎባ፣ ጋሠራ፣ አጋርፋ፣ ሲናና፣ ዲንሾ እና አካባቢያቸው ከትናንት በስቲያ አንስቶ የተቋረጠውን የኤሌክትሪክ ኃይል የመጠገን ሥራ እየተከናወነ ነው።
በዞኑ የኤሌክትሪክ መቋረጥ ያጋጠመው ከመልካ ዋከና የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ወደ ሮቤ የሚሄደው መስመር በዲንሾ አካባቢ ተቆርጦ በመውደቁና የማከፋፈያ ጣቢያውን የከረንት ትራንስፎርመር በማቃጠሉ ነው።በኃይል ማከፋፈያው ላይ ያጋጠመውን ብልሽት በመጠገን አገልግሎቱን እስከምሽት ድረስ ለማስቀጠል ርብርብ እየተደረገ ነው።

የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ይፋዊ ስራ የማስጀመሪያ ፕግራም አካሄደ::
የዋዜማ ሪፖርተር እንደዘገበው በፕሮገራሙ ከተለያዩ የሃይማቶት ተቋማት የተውጣጡ የሃይማት አባቶችና የተለያዩ ብሄር ብሄረሰቦችን ይወክላሉ የተባሉ የአገር ሽማግዎች የጸሎትና ምርቃት ስነ ስርዓት አከናውነዋል፡፡
ኮሚሽኑ በፓርላማ ከተቋቋመ ጀምሮ ቢሮውን በማድረጀት ላይ መሆኑን፣ በቀጣይ ሶስት አመታት የሚፈጽማቸውንና በአዋጅ የተሰጡትን 12 ዋና ዋና ሃለፊነቶች የሚያስፈጽምበት ደንብና መመሪያ እያዘጋጀ ስለመሆኑ እንዲሁም ከሚዲያ ጋር ሊኖር ስለሚችል ግንኙነት የሚረዳ የሚዲያ ስተራቴጅ ዝግጅት ላይና ሌሎች ስራዎችን እያከናወነ መሆኑንና ዋና ኮሚሽነር ዶ.ር መስፍን አርአያ ተናግረዋል፡፡ኮሚሸነሩ በተያዘው በጀት አመት ቀጣይ ጥቂት ወራት ውስጥ የተጀመሩ ጥቂት ስራዎችን በማጠናቀቅ ለቅድመ ውይይት ስራ እንደሚዘጋጅ ዋና ኮሚሽነሩ ተናግረዋል፡፡
[ዋዜማ ራዲዮ]

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከህብረተሰቡ የተለያዩ ቅሬታዎችንና ጥቆማዎችን የሚቀበልበት የስልክ ቁጥሮችን ይፋ አድርጓል፡፡
ከተማ አስተዳደሩ ከህብረተሰቡ ጋር ውይይቶችን ሲያካሂድ መቆየቱ ይታወሳል፡፡
በውይይቶቹም በርካታ ጠቃሚ ሃሳቦችንና ግብአቶችን ማሰባሰብ መቻሉን ከከንቲባ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡
ሆኖም አሁንም ህብረተሰቡን ለማዳመጥ ተጨማሪ አማራጮችን መዘርጋት አስፈላጊ በመሆኑ ማንኛውም ሰው ካለበት ሆኖ ጥቆማዎችን መስጠት የሚችልበት የስልክ ቁጥሮችን አስተዳደሩ ይፋ አድርጓል፡፡
በዚህም መሰረት ህብረተሰቡ ማንኛውንም ቅሬታና ጥቆማዎችን በነፃነት የሚሰጥባቸው የጥቆማ መስጫ የስልክ ቁጥሮችን ይፋ አድርጓል፡፡
በዚህም መሰረት!
አጭር ቁጥር ፡- 👉 9977
የሞባይል ስልኮች
👉 09-00640830
👉 09-00640789
አስፈላጊ የሰነድ መረጃዎችን በቴሌግራም ለማያያዝ እና ለአጭር መልእክቶች( text messages) የሞባይል ቁጥሮችን መጠቀም እንደሚቻል ተገልጿል።

ከመጪው ማክሰኞ ጀምሮ በሳዑዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን ወደ አገራቸው የመመለስ ስራ እንደሚጀመር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ብርቱካን አያኖ በሰጡት መግለጫ ፥ በሳዑዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንን ወደ አገራቸው ለመመለስ ሲካሄድ የቆየው የቅድመ ዝግጅት ስራ ተጠናቋል፡፡
16 ተቋማትን ያካተተ ብሔራዊ ኮሚቴ ተቋቁሞ ወደ ስራ መግባቱን አንስተው ፥ በዚህም ከመጪው ማክሰኞ ጀምሮ በአስቸጋሪ ሁኔታ ያሉ ዜጎችን ወደ አገራቸው የመመለስ ስራ ይጀመራል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
በሳዑዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ያሉ ከ102 ሺህ በላይ የሚሆኑ ዜጎችን በአጭር ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ ግብ ተቀምጦ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች በመስራት ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡