YeneTube
117K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ 💦በሠላም አደረሳችሁ 2014ዓ.ም

የሻረግ ቅመማ-ቅመም 👌

#ምርቶቻችንን :-
👉 በሸዋ ሾፒንግ
👉 በክዊንስ
👉 በሎሚያድ
👉 በጋራ ማርት
👉 በልዊስ(ባምቢስ)
👉 በዴይሊ ሚኒማርት እና በሌሎች ሱፐር ማርኬቶች ያገኙናል።

#ጥራት እና ዋጋ ቅናሽ መለያችን ነው !!
🎁🎁ውብ እና ማራኪ እንጨት ላይ የ ተቀረጹ ስጦታዎች ለ ሚወዱዋቸው ያበርክቱ
👉wooden Post Cards
👉wooden Note Books
👉wooden Gift Boxes
📞☎️0982933211 @Ephrem7
📞☎️0940597823 @beity3
👋👋Join us at👇👇
t.me/EphaAdverts
🎁🎁🎁🎁🎁🎁🎁🎁🎁
#ታደሰ ስዩም የተፈቀደለት የሂሳብ አዋቂ

ጊዜዎን ቆጥበው
ሰራተኛ ወጣብኝ ሳይሉ በስራው ብዙ አመት ልምድ ባላቸው ሙያተኞች ጊዜው ባፈራቸው እውቅ ሳፍትዌሮች እና በተመጣጣኝ ዋጋ አጠቃላይ የድርጅቶን ሒሳብ መያዝ ይፈልጋለሁ?

እንግድያውስ ድርጅታችን እርስዎን ለማገልገል በሩን ክፍት አድርጎ ይጠብቃል::
እኛ ስለ ሒሳብዎ, እርስዎ ስለ ድርጅትዎ ብቻ ይጨነቁ

አድራሻ መገናኛ 22 ከጎላጎል በስተቀኝ የሚገኘው ሕንጻ 4ኛ ፎቅ የቤት ቁጥር 279/4/8 እንዲሁም በስልክ ቁጥር +251904591215/ +251900310388 +251902475483 ያገኙናል::
🇺🇸🇺🇸🇺🇸🇺🇸🇺🇸🇺🇸 🇨🇦🇨🇦🇨🇦🇨🇦🇨🇦
በአሜሪካካናዳ በስኮላርሺፕ የመማር ዕድል!

ያለ ቅድመ ክፍያ ለመመዝገብ ቴሌግራም ቦት ላይ አፕላይ ያድርጉ! 👇
@marakischolarshipbot


አድራሻ: ቦሌ ጌቱ የንግድ ማዕከል 1ኛ ፎቅ ቁጥር 102

ስልክ: 0960612222

ለበለጠ መረጃ @marakiconsultant

ቴሌግራም ቻናል👇
@marakiconsultancy
💥  የባንዲራ ፎጣ  🇪🇹 🇪🇹

📌Size 2m×2.2m

📌 ዋጋ :- 1200

📌free delivery

አድራሻ:-መገናኛ ዲያስፖራ አደባባይ

ብዛት ለሚወስዱ ቅናሽ እናደርጋለን

📞 0912732493

ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
     @gebeyaadis
የሱዳን ጦር አዛዥ በሀገሪቱ ተቃውሞ ቢቀጥልም አዳዲስ ሚኒስትሮችን ሾሙ!

የሱዳን ወታደራዊ አዛዥ ጄኔራል አብደልፈታህ አል ቡርሃን ለመሰረተዉ አዲስ መንግስት 15 ሚኒስትሮችን መሾሙን አስታወቀ፡፡|እርምጃው በወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ስልጣኑን ከተቆጣጠረ ከሶስት ወራት በኋላ ሲሆን ይህም በምርጫ ሊደረግ የታቀደውን ሽግግር ውድቅ ያደረገ መሆኑን ማሳያ ነዉ ተብሏል፡፡

መፈንቅለ መንግስቱ ከተጀመረ ወዲህ ከ70 በላይ ሰልፈኞች በጸጥታ ሃይሎች የተገደሉበት ከፍተኛ ተቃውሞ ተካሂዷል።ዘጋቢዎች እንደሚሉት አዲስ መንግስት መሰየሙ ወታደራዊ ቡድኑን ሙሉ በሙሉ ስልጣኑን እንዲለቅ የሚፈልጉ ተቃዋሚዎች ዉሳኔዉ የሚያስከፋ ሆኗል፡፡

ቀደም ሲል በሱዳን የሚገኙ ዳኞች ተቃውሞውን በሃይል ለማፈን በሚል የተፈጸሙ ወንጀሎችን እንዲመረምር ጠይቀው ወታደራዊ መሪዎች መከላከያ በሌላቸው ተቃዋሚዎች ላይ አሰቃቂ ጥሰቶችን ፈፅመዋል ሲሉ ከሰዋል።ዩናይትድ ስቴትስ ብጥብጥ እስካልቆመ እና በሲቪል የሚመራ መንግስት እስካልተመለሰ ድረስ ለሱዳን የኢኮኖሚ ድጋፏን እንደማትቀጥል ገልጻለች።

[Bisrat FM]
@YeneTube @FikerAssefa
በጋምቤላ ክልል ከደቡብ ሱዳን የሚነሱ የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት የ8 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 5 ሰዎች ከባድ እና ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል!

በጋምቤላ ክልል ከደቡብ ሱዳን የሚነሱ የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች ድንበር አቋርጠው በመግባት ጥቃት ማድረሳቸውንና በጥቃቱም የ8 ሠዎች ህይወት ሲያልፍ በ5 ሠዎች ላይ ደግሞ ከባድና ቀላል ጉዳት መድረሱን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቡላ ኡቦንግ እንዳሉት፤ በጋምቤላ በዚህ ሰዓት በጋ ስለሆነ እና ክልሉን ከደቡብ ሱዳን ጋር የሚያጋራው ድንበር ሰፊና ክፍት ስለሆነ የታጣቂዎች የመግባትና የመውጣት አዝማሚያ አለ ብለዋል።

በዚህም የሙርሌ ታጣቂዎች ትናትና ድንበር አቋርጠው በመግባት በኑዌር ዞን አኮቦ ወረዳ በካንካን ቀበሌ ድንገተኛ ተኩስ በመክፈት የ8 ሠዎች ህይወት ወዲያው ሲያልፍ 5 ሠዎች ላይ ከባድና ቀላል ጉዳት መድረሱን አመልክተዋል።

ኮሚሽነር አቡላ አክለውም ክልሉ በአሁኑ ሰዓት ልዩ ኃይሉንና ሚሊሻ በመጠቀም ሰላምና ፀጥታ የማስከበር ስራውን እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

የአካባቢው ማህበረሰብ የታጣቂ ቡድኑን እንቅስቃሴ ነቅቶ በመጠበቅ ለመንግሥት ተገቢውን ጥቆማ ማድረግ እንደሚኖርበት የጠቆሙት ኮሚሽነሩ በደረሰው ጉዳት ማዘናቸውን ገልጸዋል።

የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች ከዓመታት በፊት፤ በኑዌር ዞን እና አኙዋ ዞኖች ገብተው በርካታ ሕፃናት አፍነው ሲወስዱ፣ ከ170 በላይ ሰዎች ደግሞ ሕይወታቸውን ማጣታቸው ይታወሳል።

በወቅቱ ከ2ሺህ በላይ ከብቶች መውሰዳቸውንም ኮሚሽነሩ ጨምረው አስታውሰዋል።በወቅቱ የኢፌድሪ መከላከያ ሠራዊት ወደ ደቡብ ሱዳን በመግባትና ታጣቂዎቹ የሚኖሩበት አካባቢ ላይ ጥቃት በመፈፀም፣ ታፍነው ከተወሰዱት ሕፃናት መካከል ከ100 ሕፃናት በላይ ወደ ቤተሰቦቻቸው መመለሳቸውን ማስረዳታቸውን የጋምቤላ ክልል ፕሬስ ሴክሬተሪያት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

@YeneTube @FikerAssefa
በአብየ ግዛት የሚገኘውን የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ኃይል የመተካቱ ሂደት በቀጣይ ወር እንደሚጀምር ተመድ አስታወቀ!

በአብየ ሚገኘውን የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ሃይል የተመተካቱ ሂደት በቀጣይ ወር እንደሚጀመር የተባበሩት መንግስታት ድርጅት(ተመድ) የሰላም ማስከበር ዘመቻ ኃላፊ ጅን ፔሬ ላክሮክስ አስታወቁ፡፡ሱዳን በአብየ ያለው የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ጦር እንዲወጣ ጥያቄ አቅርባ የነበረ ሲሆን፤ ጥያቄዋም በተመድ ተቀባይነት ማግኘቱ ይታወሳል፡፡ሱዳን የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ጦር ይወጣ ያለችው በኢትዮጵያ እና ሱዳን መካከል በድንበር ጉዳይ አለመግባባት ውስጥ መግባታቸውን ተከትሎ ነው፡፡

ኃላፊዋ ላክሮክስ ይህን ያሉት ከሱዳን ሉአላዊ የሽግግር ም/ቤት ፕሬዝዳንት አብዱል ፈታህ አልቡርሃን ጋር ባደረጉት የስልክ ወይይት ነው ተብሏል፡፡የሽግግር ም/ቤቱ እንደገለጸው አልቡርሃን ከተመድ ኃላፊ ጋር ያደረጉት ውይይት የተመድ ኢንትሪም ሴኩሪቲ ፎርስ ፎረ አብየ ውስጥ ያሉት የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ወታደሮችን በሱዳን መንግስት በተጠየቀው መሰረት ለመተካት የመከረ ነበር፡፡

በስልክ ወይይቱ ወቅት ላክሮክስ የመተካቱና የመተካቱ ስራ በፈረንጆቹ ቀጣይ የካቲት ወር እንደሚጀመርና እስከ ፈረንጆቹ መጋቢት 2022 እንደሚገጥል ማረጋገጣቸው ተዘግቧል ሲል አል አይን በድህረ ገጹ አስነብቧል፡፡የተመድ የጸጥታው ም/ቤት ሰላም አስከባሪ ወደ አብየ ግዛት የሰላም አስካሪ የላከው፤ በነዳጅ በበለጸገችው አብየ ግዛት የሱዳንና የደበብ ሱዳን ጦሮች መፋጠጣቸውን ተከትሎ ነበር፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
እንደምን አደራችሁ!!! ቀንዎን ሲያቅዱ ለ #EtNationaldialogue ኮሚሽን ኮሚሽነርነት እጩ መምረጡን እንዳይዘነጉ!!
#Update

ቅዱስ ፓትርያርኩ ህክምናቸውን ጨርሰው ወደ ጽርሐ መንበረ ፓትርያርክ ተመለሱ።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በሆስፒታል ሲደረግላቸው የነበረውን ህክምና ጨርሰው በሙሉ ጤንነት ወደ ጽርሐ መንበረ ፓትርያርክ በሰላም ተመልሰዋል።

መረጃውን ከኢኦተቤ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ ነው ያገኘነው።

Via Fidel post
@Yenetube @Fikerassefa
መንግስት አሁን የያዘውን የበላይነት እንዳስጠበቀ ወደ ንግግር የሚወስዱ መንገዶችን መከተል ይገባዋል ሲል የኢትዮጵያ ሶሻል ዲሞክራቲክ ፓርቲ አሳሰበ፡፡

የሕወሓት ቡድን አሁንም የመስፋፋት ሙከራ የሚያደርግ ከሆነ መንግስት ባለበት ሊያከስመው እንደሚገባ እና ወደ ንግግር የሚወስዱ አማራጮችን መከተል እንደሚኖርበት የተናገሩት የፓርቲው ፕሬዝዳንት በየነ ጴጥሮስ(ፕ/ር) ናቸው፡፡

ፕሬዝዳንቱ በአለም ታሪክ በጦርነት ተጀምሮ በጦርነት መፍትሔ ያገኘ ጉዳይ የለም መንግስትም ይህን ከግምት በማስገባት ወደ ድርድር የሚያደርሱ መንገዶችን መከተል ይገባዋል ብለዋል፡፡

የሕወሓት ቡድንም ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን በማክበር አሁን እየተከተለ ያለውን መንገድ በማቆምና ትጥቁን በማውረድ ወደ ምክክር መምጣት እንዳለበት ገልፀዋል፡፡

አክለውም ሊደረግ በታሰበው ብሔራዊ ምክክር ላይ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሚናቸው የጎላ መሆኑን በመገንዘብ የብሔራዊ ምክክሩን መንፈስ ከወዲሁ በማቀንቀን አላማውን እንዲመታ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

[አሐዱ]
@YeneTube @FikerAssefa
1
በአዲስ አበባ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ እና በቡራዩ አዋሳኝ ወይ ብላ ማርያም ቤተ ክርስቲያን አካባቢ በተፈጠረው ችግር በሰዎች ላይ ሞትና ከባድ ጉዳት መድረሱ መንግስት አስታወቀ፡፡

በዓሉ በተገቢው መንገድ ባለመከበሩ፣ እንዲሁም በደረሰው የሰው ሕይወት መጥፋትና የአካል ጉዳት መንግሥት የተሰማውን ጥልቅ ኀዘን የገለጸ ሲሆን በስፍራው የተፈጠረውን ክስተት በማጣራት ለድርጊቱ ተጠያቂ የሆኑ አካላትን ለሕግ እንደሚያቀርብ አስታውቋል፡፡

በዓሉ የኢትዮጵያውያንን መፋቀር፣ ኅብረ ብሔራዊ አንድነትና ሰላም በሚገልጽ መንገድ እንዳይከበር የተለያዩ አካላት የሸረቧቸውን ሤራዎች ሕዝቡና የጸጥታ አካላት ተናብበውና ተቀናጅተው አክሽፈውታል ሲል የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት።

ኢትዮጵያ የምታስተናግዳቸው ታላላቅ ዓለም አቀፋዊ ክንውኖች ከፊታችን አሉ። እነዚህ ክንውኖች እንዳይሳኩ የኢትዮጵያን ገጽታ ማበላሸት የፈለጉ አካላት የጥምቀትን በዓል በመረበሽ ተልኳቸውን ለማሳካት ሞክረው ነበር ነገር ግን አልተሳካላቸውም ሲል ነው ያስታወቀው፡፡ኢትዮጵያ በዓለም ደምቃ እንድትታይ ከሚያደርጓት በዓላት መካከል አንዱ የሆነው የጥምቀት በዓል በመላ ሀገሪቱ በደማቅ ሁኔታ ተከብሮ ማለፉንም ገልጻል፡፡

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
አጤ ምኒልክ በዓድዋ ጦርነት የተዋጉበት ጎራዴ ከአሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ ተመለሰ።

አጤ ምኒልክ በዓድዋ ጦርነት ላይ የተዋጉበት ጎራዴ ከአሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ ተመለሰ።በወቅቱ ከጎራዴው ጋር ተዘርፎ የነበረው መስቀልም እንዲሁ ተመልሷል።

በተጨማሪም ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ የተላላኳቸው ደብዳቤዎች፣ ፎቶግራፎች፣ ፖስት ካርዶችና የጽሑፍ እና የምስል ቅርሶች ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ አስመላሽ ብሔራዊ ኮሚቴ ቅርሶቹን ለቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን አስረክቧል።

የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው ወደ ሀገር የተመለሱትን ቅርሶች ጠብቆ የማቆየት ኃላፊነትን ተቀብለናል ብለዋል። ቅርሶቹ በታሪክም የሚነገረውን የኢትዮጵያን ቀደምትነትና ኃያልነት በተግባር የሚያሳዩ መሆናቸውንም ተናግረዋል።

ኢትዮጵያን በተለያየ መንገድ ለማጠልሸት ለሚጣጣሩ አካላት ምላሽ የሚሰጡም ናቸው ብለዋል።ቅርሶቹን ጠብቆና ተንከባክቦ ከማስቀመጥ ባሻገር በቀጣይ የማስተዋወቅ ሥራው እንደሚቀጥል መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።በርክክብ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር ፕሬዚዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴን ጨምሮ የማኅበሩ አባላትና እንግዶች ተገኝተዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
🎁💝 የኔ ስጦታ
YeneSetota Gift Shop and Events 🎁💝

የሃገራችን የመጀመሪያው የኦንላይን የስጦታ እቃዎች መሸጫ።

👉 ለፍቅረኛዎ
👉 ለባለቤትዎ
👉 ለልጆችዎ
👉 ለእርስዎ
👉 ለጓደኞችዎ
👉 ለድርጅትዎ በብዛት

🚚 አሁኑኑ ይዘዙን ቤትዎ በር ድረስ በነፃ እናደርስሎታለን 🛵

የቴሌግራም ቻናላችንን በመጠቀም ይሸምቱ
@yene_setota

ለቅናሽ ዋጋ እና ለተለያዩ ጥቅማ ጥቅሞች አፕሊኬሽናችንን ከPlay store በማውረድ ይጠቀሙ (only 3MB)
📱 www.yenesetota.com/android_app.php

ዌብሳይታችንን ይጎብኙ
🌐 www.yenesetota.com

ቲክቶክ/TikTok
📷 https://tiktok.com/@yenesetota

🛍 ሱቃችንን መተዉ ይጎብኙ
አድራሻ: ከ 22 ወደ ቦሌ መድሃኒአለም (ኤድና ሞል) በሚወስደዉ መንገድ ፀጋ የገበያ ማዕከል አጠገብ ያለው ህንፃ 1ኛ ፎቅ።

📞 ለበለጠ መረጃ በ
098898-6302 ወይም በ093333-2325
ይደውሉ።
😁1
ሐይማኖትን እና ሐይማኖታዊ በዓላትን የግጭት መነሻ ከማድረግ እንዲቆጠብ እና ትናንት በወይብላ ማርያም ቤተ ክርስቲያን በኦርቶዶክስ ሐይማኖት በዓለ ጥምቀት አከባበር ላይ ጸጥታ ኃይሎች ላጠፉት የሰው ሕይወት ይቅርታ እንዲጠይቅ ኢዜማ ዛሬ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባሰራጨው መግለጫ አሳስቧል።

የኦሮሚያ ክልል ጸጥታ ኃይሎች በምዕመናን ላይ በወሰዱት የኃይል ርምጃ የሞት እና መቁሰል አደጋ እንደደረሰ የገለጸው ኢዜማ፣ ችግሩ የተፈጠረው የሰንደቅ ዓላማ ቀለማትን የያዙ ምዕመናን ታቦት አጅበው ወደ ቤተ ክርስቲያኒቷ እንዳይገቡ በመከልከላቸው እንደሆነ ገልጧል። ኢዜማ አክሎም፣ በመንግሥት እና ጸጥታ መዋቅሮች ውስጥ የሚገኙ እና ሐይማኖታዊ ግጭት ለማስነሳት የሚጥሩ ኃይሎች እንዳሉ እና ሆኖም እነሱን የሚቆጣጠር የፖለቲካ እመራር አለመኖሩን ጠቅሷል።

በተያያዘ፣ እናት ፓርቲ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በዚሁ ሐይማኖታዊ ስነ ሥርዓት ላይ ለጠፋው ሕይወት ይፋዊ ማብራሪያ እንዲሰጥ እና ይቅርታ እንዲጠይቅ፣ ለምዕመኑ የሞራል ካሳ እንዲከፍል እና ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ የታሰሩ ምዕመናንን እንዲፈታ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው መግለጫ ጠይቋል።

Wazema
@YeneTube @FikerAssefa
በአማራ ክልል ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ሰዎች ያለምክንያት እየታሰሩ ነው ሲሉ የከሚሴ ከተማና አካባቢው አንዳንድ ነዋሪዎች አመለከቱ፡፡

ለደህንነታቸው ስማቸው እንዳይገለፅና ድምፃቸውም እንዳይቀረፅ ያስጠነቀቁት አስተያየት ሰጪዎች ምክንያቱ በማይታወቅ ሁኔታ ሰዎች በፖሊስ እየተያዙ እየታሰሩ ነው ብለዋል፡፡የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር የሰላምና ፀጥታ ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ አቶ አብዲ እንደሪስ ያለምክንያት የታሰረ ሰው የለም፣ በቅርቡ ከነበረው የህወሓት ወረራ ጋር ግንኙነት ነበራቸው የተባሉ ተጠርጣሪዎች መያዛቸውን ግን አረጋግጠዋል፡፡

የማጣራት ሥራው የተለየ የህብረተሰብ ክፍል ላይ ያነጣጠረ አይደለም ያሉት አቶ አብዲ እስሩ “የሐይማኖት አባቶችን ያነጣጠረ ነው” የሚለውን ስምታ አይቀበሉም። ምን ያህል ሰዎች በቁጥጥር ስር እንደዋሉ ለመናገር ፈቃደኛ ያልሆኑት አቶ አብዲ ህብረተሰቡ ከአሉባልታ ወሬ ይቆጠብ ሲሉም መክረዋል፡፡

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ 💦በሠላም አደረሳችሁ 2014ዓ.ም

የሻረግ ቅመማ-ቅመም 👌

#ምርቶቻችንን :-
👉 በሸዋ ሾፒንግ
👉 በክዊንስ
👉 በሎሚያድ
👉 በጋራ ማርት
👉 በልዊስ(ባምቢስ)
👉 በዴይሊ ሚኒማርት እና በሌሎች ሱፐር ማርኬቶች ያገኙናል።

#ጥራት እና ዋጋ ቅናሽ መለያችን ነው !!
🎁🎁ውብ እና ማራኪ እንጨት ላይ የ ተቀረጹ ስጦታዎች ለ ሚወዱዋቸው ያበርክቱ
👉wooden Post Cards
👉wooden Note Books
👉wooden Gift Boxes
📞☎️0982933211 @Ephrem7
📞☎️0940597823 @beity3
👋👋Join us at👇👇
t.me/EphaAdverts
🎁🎁🎁🎁🎁🎁🎁🎁🎁
🇺🇸🇺🇸🇺🇸🇺🇸🇺🇸🇺🇸 🇨🇦🇨🇦🇨🇦🇨🇦🇨🇦
በአሜሪካካናዳ በስኮላርሺፕ የመማር ዕድል!

ያለ ቅድመ ክፍያ ለመመዝገብ ቴሌግራም ቦት ላይ አፕላይ ያድርጉ! 👇
@marakischolarshipbot


አድራሻ: ቦሌ ጌቱ የንግድ ማዕከል 1ኛ ፎቅ ቁጥር 102

ስልክ: 0960612222

ለበለጠ መረጃ @marakiconsultant

ቴሌግራም ቻናል👇
@marakiconsultancy
ለተለያዩ የስራ እድሎች, ስኮላርሺ ፕሮግራሞች, ስልጠና እና የህይወት ክህሎቶችን ለማግኝት አዋቂን ይቀላቀሉ!

Join our Telegram👇

https://tttttt.me/+qtDDnplBq9UzZGRk