YeneTube
117K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እና ባለቤታቸው ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው እንዲሁም የኦሮሚያ ክልል ፕሬዜዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ፤ የክብር ዶክተር አሊ ቢራ ህክምና በሚከታተልበት አዳማ ጄነራል ሆስፒታል በመገኘት ጠይቀዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
ኢያስጴድ ተስፋዬ ከእስር መፈታቱ ተሰማ!

የኡቡንቱ ቴሌቪዥን ተባባሪ መስራች እና ዋና አዘጋጅ የሆነው ኢያስጴድ ተስፋየ ከ43 ቀናት እስር በኋላ መፈታቱ ተሰማ።

ኢያስጴድ በተለምዶ ሶስተኛ ተብሎ በሚጠራው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ለ 43 ቀናት ፍርድ ቤት ሳይቀርብ ብሎም ምንም አይነት ክስ ሳይመሰረትበት መቆየቱም ተገልጿል።

[@AddisZeybe]
@YeneTube @FikerAssefa
እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ 💦በሠላም አደረሳችሁ 2014ዓ.ም

የሻረግ ቅመማ-ቅመም 👌

#ምርቶቻችንን :-
👉 በሸዋ ሾፒንግ
👉 በክዊንስ
👉 በሎሚያድ
👉 በጋራ ማርት
👉 በልዊስ(ባምቢስ)
👉 በዴይሊ ሚኒማርት እና በሌሎች ሱፐር ማርኬቶች ያገኙናል።

#ጥራት እና ዋጋ ቅናሽ መለያችን ነው !!
Forwarded from YeneTube
🎁🎁ውብ እና ማራኪ እንጨት ላይ የ ተቀረጹ ስጦታዎች ለ ሚወዱዋቸው ያበርክቱ
👉wooden Post Cards
👉wooden Note Books
👉wooden Gift Boxes
📞☎️0982933211 @Ephrem7
📞☎️0940597823 @beity3
👋👋Join us at👇👇
t.me/EphaAdverts
🎁🎁🎁🎁🎁🎁🎁🎁🎁
Forwarded from YeneTube
#ታደሰ ስዩም የተፈቀደለት የሂሳብ አዋቂ

ጊዜዎን ቆጥበው
ሰራተኛ ወጣብኝ ሳይሉ በስራው ብዙ አመት ልምድ ባላቸው ሙያተኞች ጊዜው ባፈራቸው እውቅ ሳፍትዌሮች እና በተመጣጣኝ ዋጋ አጠቃላይ የድርጅቶን ሒሳብ መያዝ ይፈልጋለሁ?

እንግድያውስ ድርጅታችን እርስዎን ለማገልገል በሩን ክፍት አድርጎ ይጠብቃል::
እኛ ስለ ሒሳብዎ, እርስዎ ስለ ድርጅትዎ ብቻ ይጨነቁ

አድራሻ መገናኛ 22 ከጎላጎል በስተቀኝ የሚገኘው ሕንጻ 4ኛ ፎቅ የቤት ቁጥር 279/4/8 እንዲሁም በስልክ ቁጥር +251904591215/ +251900310388 +251902475483 ያገኙናል::
Forwarded from YeneTube
🇺🇸🇺🇸🇺🇸🇺🇸🇺🇸🇺🇸 🇨🇦🇨🇦🇨🇦🇨🇦🇨🇦
በአሜሪካካናዳ በስኮላርሺፕ የመማር ዕድል!

ያለ ቅድመ ክፍያ ለመመዝገብ ቴሌግራም ቦት ላይ አፕላይ ያድርጉ! 👇
@marakischolarshipbot


አድራሻ: ቦሌ ጌቱ የንግድ ማዕከል 1ኛ ፎቅ ቁጥር 102

ስልክ: 0960612222

ለበለጠ መረጃ @marakiconsultant

ቴሌግራም ቻናል👇
@marakiconsultancy
Forwarded from YeneTube
💥  የባንዲራ ፎጣ  🇪🇹 🇪🇹

📌Size 2m×2.2m

📌 ዋጋ :- 1200

📌free delivery

አድራሻ:-መገናኛ ዲያስፖራ አደባባይ

ብዛት ለሚወስዱ ቅናሽ እናደርጋለን

📞 0912732493

ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
     @gebeyaadis
አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ኢትዮጵያ ለሰላም ያሳየችውን አስደናቂ ጥረት አወደሱ!

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ኢትዮጵያ ሰላም ለማስፈን አስደናቂ ጥረቶችን ማድረጓን አወድሰዋል፡፡
የኢትዮጵ መንግስት " ሰላም ለማስፈን አስደናቂ ጥረት" አድርጓል ያሉት ዋና ፀሀፊው " ለተፈጠሩ ግጭቶች ፖለቲካዊና ዲፕሎማሲዊ መፍትሔ ለማበጀት አሁን ብሩህ ተስፋና ዕድል አለ " ነው ያሉት፡፡

ጉቴሬዝ ይህን ያሉት ከአፍሪካ ህብረቱ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልእክተኛው አሊሴጉን አባሳንጆ ጋር በተወያዩበት ወቅት ነው፡፡

ምንጭ፡ ቢቢሲ
@Yenetube @Fikerassefa
የስሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ "ከሰባት ወራት በኋላ የመጀመሪዎቹን የውጭ ጎብኝዎች ተቀብለን በማስተናገዳችን ደስ ብሎናል" በማለት ገልጧል።

Simien Mountains National Park Office

Via :- Fidel post
@Yenetube @Fikerassefa
ፋኦ፤ በኢትዮጵያ፣ ኬንያና ሶማሊያ ከ25 ሚሊየን በላይ ህዝቦች በድርቅ ሳቢያ ለምግብ እጥረት ተጋልጠዋል አለ!

የዓለም ምግብ እና ግብርና ድርጅት ፋኦ በአፍሪካ ቀንድ የገጠመውን የድርቅ ጉዳት እና የረሃብን አደጋ ለመቀነስ የገንዘብ ድጋፍ እንደሚያደርግ ባወጣው መግለጫ አስታውቃል።

እንደ ድርጅቱ መግለጫ ከሆነ በአፍሪካ ቀንድ ድርቅ ያጋጠመው ለተከታታይ ሶስት ዓመታ ዝናብ ባለመዝነቡ ሲሆን በተለይም በሶማሊያ፣ ኬንያ እና ኢትዮጵያ ያሉ አርብቶ አደሮችን እና በእርሻ ስራ በሚተዳደሩ አርሶ አደሮች ላይ ምግብ እጥረት እንዲያጋጥማቸው አድርጓል።

በዚህም መሰረት በሶስቱ ሀገራት ያሉ ከ25 ሚሊየን በላይ ህዝቦች በቀጣዮቹ ጥቂት ወራት ውስጥ አስቸኳይ የምግብ ድጋ እንደሚያስፈልጋቸው ፋኦ በቅድመ ማስጠንቀቂያ ሪፖርቱ አስታውቋል።

[Alain]
@YeneTube @FikerAssefa
ሠራዊቱ የሚለካው በግዳጅ አፈፃፀሙ እንጂ በብሔሩ አይደለም- ጀነራል አበባው ታደሰ

የመከላከያ ሰራዊት ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀነራል አበባው ታደሰ የኢትዮጵያ ሠራዊት የሚለካው በሥራው ስኬት እና በግዳጅ አፈፃፀሙ እንጂ በብሔሩ እንዳልሆነ ገልፀዋል።

ከዚህ በፊት በነበረው የብሔር ተኮር የሠራዊት ግንባታ ዋጋ የከፈለው እራሱ ሠራዊቱ ነው ያሉት ጀነራል አበባው ኢትዮጵያዊነትን የተላበሰ እና በሙያው ብቁ የሆነ ሠራዊት እየተገነባ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

በቅርቡ የተካሄደው ወታደራዊ የማዕረግ እና የሜዳልያ ሽልማት በግዳጅ አፈፃፀም ላይ የተመሰረተ፣ በየደረጃው ላሉ እዞች ማዕረግ የተሰጠበት፣ የሠራዊቱ አመራሮችን የሚመጥን እና የሠራዊቱን ሞራል የገነባ እንደነበር ገልፀዋል።

በመጀመሪያው ምዕራፍ ከአሸባሪው ሕወሓት ጋር የገጠመው የኢትዮጵያ ሠራዊት ከጠላት የሰው ኃይል ቁጥር እና ትጥቅ ያነሰ ነገር ግን ኢትዮጵያዊነትን ስንቁ ያደረገ እንደነበርም አብራርተዋል።

ጦርነቱ ሲጀመር ከ250 ሺሕ በላይ የታጠቀ የአሸባሪው ሕወሓትን ኃይል ከነተጨማሪ ጀሌዎቹ ከ44 ሺሕ ባልበለጠ ሠራዊት መግጠሙንም ጀነራል አበባው ከኢቲቪ ጋር በነበራቸው ቆይታ አስታውሰዋል።

ከአሸባሪው ሕወሓት ጋር እየተደረገ ያለው ጦርነት አልተጠናቀቀም ያሉት ጀነራል አበባው ሠራዊቱ የምዕራፍ አንዱን ጦርነት አጠናቅቆ ለቀጣይ ግዳጅ እየተዘጋጀ መሆኑን ገልፀዋል።

አሸባሪው የሕወሓት ቡድን አሁንም ትንኮሳውን እንዳላቋረጠ የገለጹት ጀነራሉ አበባው አሸባሪውን ቡድን ተቆጣጥሯቸው ከነበሩ አካባቢዎች በማስወጣት የተገኘው ድል ሕዝባዊ ድል እንደሆነና የጠላትን የማድረግ አቅም ያዳከመ እና ከፍተኛ የሰው ኃይል እና የንብረት ኪሳራ ያደረሰ መሆኑን አመልክተዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
"ዜግነቴን መቀየር ብፈልግ እኔ በግልጽ እናገር ነበር፣ የቀየርኩት ዜግነት የለም፣ ለመቀየረም ምክንያት የለኝም፣ ኢትዮጵያዊ ነኝ"--- አትሌት ሙክታር እድሪስ

“4-3-3 ስፖርት በኢትዮጵያ” የሚል ስያሜ ያለውና ከ128 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት የፌስቡክ ገጽ “ኢትዮጵያን በአለም እና በኦሎምፒክ መድረክ ላይ በ5 እና 10 ሺህ ሜትር ወክሎ በመወዳደር በተደጋጋሚ ለሀገራችን የወርቅ መሰል ውጤቶችን ሲያስመዘግብ የነበረው ከደቡብ ክልል ስልጤ ዞን የተገኘው አትሌት ሙክታር እድሪስ ዜግነቱን ወደ ቱርክ ቀይሯል። ምን እየተሰራ ይሆን?” የሚል መልዕክት አጋርቶ ነበር።

ገጹ መልዕክቱን ከሰዐታት በኃላ ቢያጠፋውም መረጃው በስፋት መሰራጨቱን ተመልክተናል።

ኢትዮጵያ ቼክ ጉዳዩን ለማጣራት አትሌት ሙክታር እድሪስን ያነጋገረ ሲሆን የተሰራጨው መረጃ ሀሠተኛ መሆኑን አስታውቋል። “እንደዚህ አይነት ሀሠተኛ መረጃ ለምን ማሰራጨት እንደፈለጉ አልገባኝም፣ ዜግነቴን መቀየር ብፈልግ እኔ በግልጽ እናገር ነበር፣ የቀየርኩት ዜግነት የለም፣ ለመቀየረም ምክን ያት የለኝም፣ ኢትዮጵያዊ ነኝ። አሁን ያለሁትም ኢትዮጵያ ውስጥ ነው” በማለት ለኢትዮጵያ ቼክ አስረድቷል።

አትሌት ሙክታር እድሪስ በአለም ሻምፒዮና ለሁለት ተከታታይ ጊዜ በ5 ሺህ ሜትር ለሀገሩ የወርቅ ሜዳሊያ ማስገኘቱ ይታወቃል።

Via Ethiopia Check
@YeneTube @FikerAssefa
በኦሮሚያ ክልል ባለፉት ስድስት ወራት በደረሱ የትራፊክ አደጋዎች የ775 ሰዎች ህይወት አልፏል!

በኦሮሚያ ክልል በስድስት ወራት ውስጥ 2,007 የትራፊክ አደጋዎች መከሰቱን የክልሉ የትራፊክ ቁጥጥር እና ክትትል ክፍል ሀላፊ ኢንስፔክተር ስለሺ ገመቹ በተለይ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

በደረሰው አደጋ የ775 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ፣በ326 ሰዎች ላይ ከባድ እንዲሁም በ206 ሰዎች ላይ ደግሞ ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል።ባለፉት ስድስት ወራት በደረሰው የትራፊክ አደጋ በክልሉ ከ179 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ወድሟል፡፡

ከፍተኛ አደጋዎች ከተመዘገባበቸው ውስጥ ሰሜን ሸዋ ፣ምዕራብ ሀረርጌ ፣ምስራቅ አርሲ እና ቄለም ወለጋ ዞኖች ተጠቃሽ ናቸው፡፡በተጨማሪም በሱሉልታ፣ሰበታ፣ ሻሸመኔ፣ዱከም እና አዳማ ከተሞች ከፍተኛ የትራፊክ አደጋ ተመዝግቧል።

በ2014 ዓ.ም የደረሰው የትራፊክ አደጋ ካለፈው 2013 ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የአደጋው መጠን በ68 ቀንሷል። አብዛኛው የሞት አደጋ የደረሰው በቀኑ ጊዜ መሆኑን ኢንስፔክተር ሰለሺ ገመቹ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

[Bisrat FM]
@YeneTube @FikerAssefa
ኢራን የዘመናዊ የጦር መሳሪያ ግንባታ ጥበቤን ለጎረቤቶቼ እና ለወዳጆቼ ለማጋራት ተሰናድቻለሁ አለች፡፡

ፋርሳዊቱ አገር የታላላቅ ጦር መሳሪያዎች ጥበቧን ለወዳጆቿ እና ለጎረቤቶቿ ለማጋራት መሰናዳቷን የተናገሩት የወታደራዊ ትብብር ምክትል ኃላፊው ሐቢቦላህ ሳያሪ እንደሆኑ ስፑትኒክ ፅፏል፡፡

ኢራን በአሁኑ ወቅት በተለያዩ እቀባዎች እና ክልከላዎች ውስጥ ብትሆን ወታደራዊ ኢንዱስትሪዋ ታላቅ እርምጃ እያሳየ መሆኑ በመረጃው ተጠቅሷል፡፡

የተለያዩ አገር በቀል ክሩዝ እና ባልስቲክ ሚሳየሎችን ሰርታ እያወጣች ነው፡፡ተደጋጋሚ ሙከራዎችንም ታደርጋለች፡፡

የኢራንን የታላላቅ ጦር መሳሪያዎች ግንባታ በሥጋት ዓይኖች የሚያዩት ምዕራባውያን ኃያላን በዓይነ ቁራኛ እየተከታተሏት መሆኑ ይነገራል፡፡በአሁኑ ወቅትም በኒኩሊየር ነክ ጉዳይ በኦስትሪያ ቬየና ቀጥተኛ ያልሆነ ንግግር እያደረጉ ነው፡፡

Sheger
@YeneTube @FikerAssefa
🎁💝 የኔ ስጦታ
YeneSetota Gift Shop and Events 🎁💝

የሃገራችን የመጀመሪያው የኦንላይን የስጦታ እቃዎች መሸጫ።

👉 ለፍቅረኛዎ
👉 ለባለቤትዎ
👉 ለልጆችዎ
👉 ለእርስዎ
👉 ለጓደኞችዎ
👉 ለድርጅትዎ በብዛት

🚚 አሁኑኑ ይዘዙን ቤትዎ በር ድረስ በነፃ እናደርስሎታለን 🛵

የቴሌግራም ቻናላችንን በመጠቀም ይሸምቱ
@yene_setota

ለቅናሽ ዋጋ እና ለተለያዩ ጥቅማ ጥቅሞች አፕሊኬሽናችንን ከPlay store በማውረድ ይጠቀሙ (only 3MB)
📱 www.yenesetota.com/android_app.php

ዌብሳይታችንን ይጎብኙ
🌐 www.yenesetota.com

ቲክቶክ/TikTok
📷 https://tiktok.com/@yenesetota

🛍 ሱቃችንን መተዉ ይጎብኙ
አድራሻ: ከ 22 ወደ ቦሌ መድሃኒአለም (ኤድና ሞል) በሚወስደዉ መንገድ ፀጋ የገበያ ማዕከል አጠገብ ያለው ህንፃ 1ኛ ፎቅ።

📞 ለበለጠ መረጃ በ
098898-6302 ወይም በ093333-2325
ይደውሉ።
ከሰባት ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገነባው የንግድ ባንክ ሕንፃ ተጠናቀቀ

በርዝማኔውና በአገሪቱ የሕንፃ ግንባታ ታሪክ ከፍተኛ ወጪ የወጣበት፣ እንዲሁም በዘመናዊ ጥበብ የታነፀው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሕንፃ ግንባታ በመጠናቀቁ በይፋ ሊመረቅ ነው፡፡

ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በምሥራቅ አፍሪካ ረዥሙ በመሆን የሚጠቀሰው የባንኩ ሕንፃ በይፋ የሚመረቀው ከአንድ ሳምንት በኋላ ነው፡፡

Via - The Reporter
@Yenetube @Fikerassefa
ኢራን፣ ሩሲያ እና ቻይና የጋራ የባህር ኃይል ልምምድ ሊጀምሩ ነው

የኢራን፣ የሩስያ እና የቻይና ባህር ሃይሎች በህንድ ውቅያኖስ ላይ ሰፊ የጋራ ወታደራዊ ልምምድ ነገ ሊጀምሩ ነው፡፡

“ማሬን ሴኩሪቲ ቤልት 2022” የተሰኘው የሀገራቱ የባህር ሃይል ልምምድ ዓላማ የአለም አቀፍ የባህር ንግድ ደህንነትን ለማጠናከር፣ ንግድን ለማስፋፋት፣ የባህር ላይ ሽብርተኝነትን እና የባህር ላይ ወንበዴዎችን ለመዋጋት እንዲሁም በታክቲካል ስራዎች ላይ ልምድ ለመለዋወጥ ታሳቢ ያደረገ መሆኑን የኢራን መንግስት ቴሌቪዥን ዘግቧል።

ልምምዱ በህንድ ውቅያኖስ ሰሜናዊ ክፍል በ17ሺህ ስኩዌር ኪሎ ሜትር ቦታ ላይ እንደሚካሄድ ዘገባው አስታውሷል።

የመጀመሪያው “ማሬን ሴኩሪቲ ቤልት 2019” ከተካሄደ በኋላ ይህ ሦስተኛው ወታደራዊ ልምምድ መሆኑን አናዶሉ ኤጀንሲ ዘግቧል፡፡

Via :- FBC
@Yenetube @Fikerassefa
አገራዊ የምክክር ሂደቱ እንዲሳካ ሁሉም ዜጋ ሃላፊነቱን በአግባቡ መወጣት አለበት – ምሁራን


ጠንካራና ቅቡልነት ያለው ሀገረ መንግስትን በመገንባት ሂደት ሚናው ከፍተኛ በሆነውና

በቅርቡ እንደሚካሄድ በሚጠበቀው ሀገራዊ የምክክር መድረክ ሁሉም ዜጋ ሃላፊነቱን በአግባቡ መወጣት አለበት ሲሉ ምሁራን ተናገሩ ፡፡
ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉ የታሪክ እና የህግ ምሁራን የዕጩ ኮሚሽነሮችን ጥቆማ ከመስጠት ጀምሮ ያሉ አጋጣሚዎችን በአግባቡ በመጠቀም በቀጣይ ሂደቶች ሁሉ ንቁ ተሳትፎ ማድረግ ይገባል ብለዋል፡፡

በኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ የታሪክና የህግ መምህር እንዲሁም ተመራማሪው ዶክተር አልማው ክፍሌ÷ አካታችነት፣ ጠንካራ ተቋማዊ አሰራርን እውን ማድረግ እና ለኮሚሽኑ የገቢ ምንጭን በግልጽ ማስቀመጥን የመሰሉ መሰረታዊ ጉዳዮች ትኩረት ሊሰጣቸው እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡
ስለ ሂደቱ ለህዝብ መረጃ ለመስጠት የሚታስችል የኮሙኒኬሽን አሰራርና ሌሎች ዓለም አቀፍ ተሞክሮዎችን መተግበር እንደሚገባም ዶክተር አልማው ክፍሌ አብራርተዋል ፡፡
የታሪክና ባህል ተመራማሪ ተባባሪ ፕሮፌሰር አህመድ ዘከሪያ እና በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የህግ መምህር የሆኑት አቶ ሃይሉ ነጋ እንዳሉት÷ ዜጎች በሀገር ጉዳይ ላይ በጋራ ይቆሙ ዘንድ ከፍ ያለ ሚና እንዳለው ለሚታመንበት ኮሚሽንና እና የምክክር ሂደቱን የሚያስተናብሩ ባለድርሻዎችን ወደ ፊት ለማምጣት በሚከወኑ ስራዎች በቂ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል፡፡
ዓለም አቀፍ ተሞክሮዎችን ለራስ በሚበጅ መልኩ መጠቀምንም ምሁራኑ እንደ ምክረ ሀሳብ አስቀምጠዋል፡፡

Via :- FBC
@Yenetube @Fikerassefa
👍1
የድሬደዋ አስተዳደር ድጋፍ አፋር ክልል በጦርነት ለተጎዱ ሦስት የጤና ተቋማት

የድሬደዋ አስተዳደር በአፋር ክልል በጦርነቱ የተጎዱ ሦስት ጤና ተቋማትን መሰረታዊ አገልግሎት ማስጀመር የሚያስችል የህክምና ቁሳቁሶችን ወደ አፋር ልኳል። የድሬደዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሀር እና የጤና ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ለምለም በዛብህ ከ3.5 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያላቸው የተለያዩ የህክምና ቁሳቁሶችን ወደ አፋር ክልል ልከዋል።

የመስተዳድሩ ጤና ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ለምለም በዛብህ መስተዳድሩ በአፋር ክልል በጦርነቱ ከተጎዱ የጤና ተቋማት ሦስቱን መልሶ የማደራጀት ኃላፊነት መውሰዱን ጠቅሰው ለዚህም አስፈላጊ ቁሳቁሶችን ካሉት የመንግስት ህክምና ተቋማት እና ከግል ከማሰባሰብ በተጨማሪ ቀሪዎቹን በግዥ በማሟላት መሰረታዊ የጤና አገልግሎት ሥራ ለማስጀመር የሚረዱ ግብዓቶችን ወደ ክልሉ መላኩን ተናግረዋል።

የአስተዳደሩ ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር በበኩላቸው መስተዳድሩ ጦርነቱ በአፋር ክልል ኅብረተሰብ ላይ ያደረሰውን ዘርፈ ብዙ ጉዳት ተከትሎ የተለያዩ ድጋፎች መደረጋቸውን ጠቅሰው መደጋገፉ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል። በመስተዳድሩ ጤና ጽ/ቤት የሚገኙ ባለሞያዎች የህክምና ቁሳቁሶችን ወደ አፋር ክልል በዛሬው ዕለት ይዘው ተንቀሳቅሰዋል።

Via:- DW
@Yenetube @Fikerassefa
በሶማሌ ክልል በተከሰተው ድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ የማሰራጨት ስራ እየተሰራ ነው

በሶማሌ ክልል በተከሰተው ድርቅ ምክንያት ለተጎዱ ወገኖች የተደረገውን ድጋፍ ወደ ህብረተሰቡ የማሰራጨት ስራ እየተከናወነ መሆኑ ተገለፀ፡፡

በክልሉ በተከሰተው ድርቅ ሳቢያ በርካታ አርብቶ አደሮች ድጋፍ ይሻሉ ነው የተባለው፡፡

የተለያዩ ክልሎች በድርቁ ለተጎዱ ዜጎች በዓይነትና በጥሬ ገንዘብ ድጋፍ እያደረጉ እንደሚገኙ የክልሉ አደጋ ስጋትና ስራ አመራር ቢሮ ገልጿል።

የቢሮው ምክትል ሃላፊ አቶ ሳዲቅ አብዱልቃድር እንደተናገሩት ÷ በዛሬው እለት 20 ሺህ ኩንታል ምግብና ምግብ ነክ ድጋፍ ወደ ህብረተሰቡ የማሰራጨት ስራ ተጀምሯል፡፡

ይህም ዘይት፣ ሩዝ፣ ዱቄትና ሌሎች ሰብአዊ ድጋፎችን ያካተተ ሲሆን÷ ለ36 ወረዳዎች የሚዳረስና ለአንድ ወር የሚሆን ቀለብ መሆኑን ተናግረዋል።

በሶማሌ ክልል በተከሰተው ድርቅ ከ230 ሺህ በላይ እንስሳት ህይወት ሲያልፍ÷ ከ2 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ አርብቶ አደሮች ድጋፍ እንደሚሹ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡

Via FBC
@Yenetube @Fikerassefa