ጉባኤው በወይብላ ቅድስት ማሪያም ቤተክርስቲያን ላይ የተፈጸመውን አስነዋሪ ድርጊት አወገዘ!
በጥምቀት በዓል ላይ በቡራዩ ከተማ አስተዳደር ወይብላ ቅድስት ማሪያም ቤተክርስቲያን ላይ የተፈጸመውን አስነዋሪ ድርጊት እንደሚያወግዝ የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አስታወቀ።
ጉባኤው በጥምቀት በዓል ላይ በቡራዩ ከተማ አስተዳደር የተፈጸመውን ሕገወጥ ድርጊት በመቃዎም መግለጫ አወጥቷል።
በመግለጫው ሃይማኖቶች የትኅትና፣ የሰላምና የአንድነት፣ የፍቅርና መከባበር መሰረቶች ናቸው ብሏል።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተ ክርስቲያን ለዘመናት የሰላም መሰረት ሆና ዘልቃለች ያለው የጉባኤው መግለጫ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሃይማኖትን ሽፋን አድርገው ግጭት ለመፍጠር የሚንቀሳቀሱ ኃይሎችን አጥብቀን እንቃዎማለን ነው ያለው።
ጥር 12 በቡራዩ ከተማ አስተዳደር በሕግ ማስከበር ሽፋን በቤተክርስቲያኗ ላይ የተቃጣው ድርጊት ፍጹም ሕገ ወጥ ነው ያለው መግለጫው መንግሥት አጥፊዎችን ተከታትሎ ለሕግ እንዲያቀርብም ጠይቋል።
መንግሥት የሃይማኖትን እና የዜጎችን ሰላም እና ደኅንነት የማስጠበቅ ኃላፊነቱን እንዲወጣ የጠየቀው የጉባኤው መግለጫ የሕይዎት፣ የአካል እና የመንፈስ ስብራት በደረሰባቸው ወገኖች የተሰማንን ጥልቅ ሐዘንም በተሰበረ ልብ እንገልፃለን ነው ያለው።
መንግሥት ቀድሞ ባወጣው መግለጫ በተፈጠረው ክስተት፣ በደረሰው የሞትና ከባድ የአካል ጉዳት እንዳዘነ አስቀድሞ ጉዳዩን አጣርቶ አጥፊዎችን ለሕግ እንደሚያቀርብ አሳውቋል።
@YeneTube @FikerAssefa

"በሶማሌ ክልል በተከሰተው ድርቅ 1.4 ሚሊዮን ሕዝብ ለመርዳት ርብርብ እየተደረገ ነው”፦ የክልሉ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ቢሮ
በሶማሌ ክልል በድርቁ ምክንያት በሰዎች ላይ የከፋ ጉዳት እንዳይደርስ እንዲሁም ሰዎች በድርቁ ምክንያት ለረሃብ እንዳይጋለጡ በተሠራው ቅንጅታዊ ተግባር አንድ ነጥብ አራት ሚሊዮን ሕዝብ ለመርዳት ርብርብ እየተደረገ መሆኑን የክልሉ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አብዱልፈታህ አህመድ አስታወቁ።
አቶ አብዱልፈታህ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንዳስታወቁት፤ በሶማሌ ክልል ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተከሰተው ድርቅ ሰዎችን ከቦታ ቦታ እያፈናቀለ እንስሳትን ደግሞ እየገደለ ነው።
ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ከ235 ሺ 700 በላይ እንስሳት በዚህ ድርቅ ምክንያት ሕይወታቸው አልፏል።
በክልሉ 2 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሕዝብ ደግሞ ከዚህ ጋር በተያያዘ ለከፋ ጉዳት ተጋልጧል ብለዋል።
የክልሉ መንግሥት ችግሩን ለመቋቋም ከተለያዩ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ካልሆኑ ድርጅቶችና ተቋማት ጋር በቅንጅት በመሆን በርካታ ተግባራትን እያከናወነ ሲሆን በዚህም ለእንስሳቱ የሚውሉ የተለያዩ የመኖ ዓይነቶችን በማሰባሰብ ከ19 ወረዳዎች በላይ ማዳረሱን አብራርተዋል።
በተለይ የግብርና ሚኒስቴርና የክልሉ እንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ በጋራ በመሆን በአብዛኛው የአካባቢው ማህበረሰብ የአርብቶ አደር እንደመሆኑ ማህበረሰቡ በእንስሳት ላይ በሚደርሰው ጉዳት ቀጥተኛ ተጋላጭ እንዳይሆን የእንስሳት ሀብቱ ሕይወት እንዳያልፍ የመታደግ ሥራ እያከናወነ መሆኑን ጠቅሰዋል።
[EBC]

አገራዊ ለውጡን ተከትሎ የአየር ኃይሉን ዝግጁነትና ብቃት የሚያጎለብቱ የለውጥ ተግባራት መከናወናቸውን የአየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ ገለጹ፡፡
የአየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ፤ አየር ኃይላችን የታጠቀው መሳሪያና ቴክኖሎጂ ዒላማውን ለይቶ የሚመታ በመሆኑ ሠላማዊ ዜጎች የጥቃት ሰለባ ሊሆኑ አይችሉም ሲሉም ተናግረዋል፡፡
አሸባሪው ህወሃት "የኢትዮጵያ አየር ኃይል ሠላማዊ ዜጎች ላይ ጥቃት እየፈጸመ ነው" ሲል የሚያቀርበውን ውንጀላ ከእውነት የራቀ ነው ብለውታል።
በቅርቡ በአገር አቀፍ ደረጃ በተካሄደ ደማቅ መርሃ-ግብር በኢትዮጵያ ላይ የተቃጣውን የህልውና አደጋ በመመከት የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ የመከላከያ ሠራዊት አባላት እውቅናና ሽልማት መበርከቱ ይታወሳል።
በመርሃ ግብሩ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትርና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ዶክተር አቢይ አህመድ የላቀ አመራርነት ላስመዘገቡ የጦር መኮንኖች የ'አድዋ ጀግና ሜዳይ' የሸለሙ ሲሆን ከእነዚህም መካከል የአየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ አንዱ ናቸው፡፡
ሌተናል ጄኔራል ይልማ ከጦር መኮንንነት በተጨማሪ ምርጥ አብራሪ መሆናቸውም በሽልማት መርሃ ግብሩ ላይ ተገልጿል።
ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ፤ አገራዊ ለውጡን ተከትሎ የአየር ኃይሉን ዝግጁነትና ብቃት የሚያጎለብቱ የለውጥ ተግባራት መከናወናቸውን ነው የተናገሩት፡፡
ይህም አየር ኃይሉ በኢትዮጵያ ላይ የተቃጣውን የህልውና አደጋ በብቃት በመመከት ረገድ የሚጠበቅበትን ሚና እንዲያበረክት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርጓል ብለዋል፡፡
አየር ኃይሉ በኢትዮጵያ የአየር ክልል ከየትኛውም ወገን የሚቃጣን ጥቃት ለመመከትና አጸፋዊ እርምጃ ለመውሰድ በሙሉ ቁመና ላይ እንደሚገኝም ተናግረዋል፡፡
አየር ኃይሉ ሕዝባዊ መሰረት ያለውና በጠንካራ ስነ ምግባር የተገነባ በመሆኑ የትኛውም አይነት ኦፕሬሽኖች ሠላማዊ ዜጎች ላይ ጥቃት እንዳይደርስ ታሳቢ ያደረጉ መሆናቸውን ነው ያስረዱት፡፡
የአየር ኃይሉ ከለውጡ በፊት ኢትዮጵያን በሚመጥንና ኢትዮጵያዊያንን በሚመስል መልኩ የተገነባ እንዳልነበረ፤ በአንድ አካባቢ ሰዎች ታጥሮ ለአንድ ፓርቲ ህልውና ሲሰራ እንደቆየም አንስተዋል።
ከአገራዊ ለውጡ በኋላ በአጭር ጊዜ ለታላቅ አገር የሚመጥንና የሁሉም ኢትዮጵያዊያን የሆነ ተቋም መገንባት መቻሉን መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ለዋና መስሪያ ቤት ባለ 36 ወለል ህንፃ ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ የማስቀመጥ ሥነ-ስርዓት ተካሄደ፡፡
በመርሃ ግብሩ ላይ የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ፣ የኢትዮጵያ ኤልክትሪክ አገልግሎት ስራ አመራር ቢርድ ሰብሳቢ ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያን ጨምሮ ሌሎች የከፍተኛ የመንግስት ስራ ኃላፊዎች፣ የተቋሙ ከፍተኛ አመራሮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
@YeneTube @FikerAssefa
በመርሃ ግብሩ ላይ የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ፣ የኢትዮጵያ ኤልክትሪክ አገልግሎት ስራ አመራር ቢርድ ሰብሳቢ ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያን ጨምሮ ሌሎች የከፍተኛ የመንግስት ስራ ኃላፊዎች፣ የተቋሙ ከፍተኛ አመራሮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
@YeneTube @FikerAssefa
የሱዳን ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ጄኔራል መሀመድ ሀምዳን ዳጋሎ አዲስ አበባ ገቡ!
የሱዳን ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ጄኔራል መሀመድ ሀምዳን ዳጋሎ አዲስ አበባ ገቡ። አዲስ አበባ ሲገቡም የመከላከያ ሚንስትሩ ዶ/ር አብርሀም በላይ እና የብሔራዊ ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ተመስገን ጥሩነህ አቀባበል እንዳደረጉላቸው ኢቢሲ ዘግቧል።

አሜሪካ የቻይና አየር መንገዶች ላይ የበረራ እገዳ ጣለች!
የአሜሪካ መንግስት እንዳስታወቀው እገዳው ከፊታችን ጥር 22 እስከ መጋቢት 20 ድረስ የሚቆይ ሲሆን፤ አጠቃላይ 44 በረራዎች እንዲቋረጡ የሚያደርግ ነው።
በክልከላው በተለይም አራት የቻይና አየር መንገዶች ማለትም ዢመን፣ ኤር ቻይና፣ ቻይና ሰሳውዘርን እና ኢስተርን የተባሉ አየር መንገዶች የሚጎዱ መሆኑ ታውቋል።
የቻይና ባሳለፍነው ወር 20 የዩናትድ አየር መንገድ፣ 10 የአሜሪካን አየር መንገድ፣ እና 14 የዴልታ አየር መንገድ በረራዎችን ከኮሮና ጋር በተያየዘ ማገዷ የሚታወስ ሲሆን፤ የአሜሪካ ውሳኔም ለቻይና እርምጃ አጸፋ መሆኑ ተነግሯል።
[Alain]

በአዲስ አበባ ነገ ለሚካሄደው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ውድድር የሚዘጉ መንገዶችን ፖሊስ ይፋ አደረገ፡፡
ዘንድሮ ለ21ኛ ጊዜ በሚደረገው ውድድር የሃገሪቱን ጥሪ ተቀብለው ወደ ኢትዮጵያ የመጡ ዳያስፖራዎች፣ የውጭ ሀገራት ዜጎች እንዲሁም በርከታ ተሳታፊዎች ይታደሙበታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ውድድሩ የሚጠበቅበትን ዓላማ እንዲያሳካና በሰላም እንዲጠናቀቅ በፌዴራልና በከተማ ደረጃ የተዋቀረው የፀጥታና ደህንነት ግብረ ኃይል አስፈላጊውን ዝግጅት አጠናቆ ወደ ስራ መግባቱን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
በዕለቱ መነሻውን መስቀል አደባባይ በማድረግ የሚጀመረው ወድድር በአዲስ አበባ ስታዲዮም፣ ሜክሲኮ አደባባይ፣ በልደታ ቤተክርስቲያን በማድረግ ፣ በዛጉዌ ህንፃ በመታጠፍ-በጌጃ ሰፈር ፣ጎማ ቁጠባ በፍል ውሃ በማድረግ በካዛንቺስ ፣ በኡራኤል ቤተክርስቲያን ወደ ባንቢስ በመታጠፍ መድረሻውን መስቀል አደባባይ ያደርጋል፡፡በመሆኑም የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይኖር እና አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን መጠቀም እንዲችሉ ለተሸከርካሪ ዝግ የሆኑ መንገዶች እንደሚኖሩ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
በዚህም መሰረት ፦
ኮቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ደንበል ህንፃ ማሳለጫ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ፣ የቀድሞ አራተኛ ክፍለ ጦር፤ ከቡልጋሪያ ማዞሪያ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኬኬ ህንፃ ወይም ጨርቆስ ማዞሪያ፤ ከአራት ኪሎ ወደ መስቀል አደባበይ የሚወስደው መንገድ ቅዱስ ገብርኤል መሳለሚያ፤ ከሳር ቤቶች አደባባይ ወደ ሜክሲኮ ለሚመጡ አፍሪካ ህብረት አደባባይ፤ ከካርል አደባባይ ወደ ከፍተኛ ፍ/ቤት የሚወስደው መንገድ ልደታ ፀበል፤ ከጦር-ኃይሎች ወደ ሚክሲኮ ለሚመጡ ኮካ መገንጠያ
እንዲሁም ከሜክሲኮ ልደታ ኮንደሚኒዬም መብራት፤ከመርካቶ በጎማ ተራ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ ለሚመጡ በርበሬ በረንዳ፤ ከተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን በጎማ ቁጠባ የሚወስደው መንገድ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የኋላ በር (ሼልድሬንስ)፤ ከቸርቸር ጎዳና ወደ አምባሳደር ፣ ከሜክሲኮ እና ለገሃር ለሚመጡ አገር አስተዳደር/ኢምግሬሽን/ መብራት ፤ ከአዋሬ ወደ ካዛንቺስ ለሚመጡ ሴቶች አደባባይ- ከመገናኛ ወደ 22 ለሚመጡ ዘሪሁን ህንፃ፤ መድሃኔዓለም የሚመጡ አትላስ ሆቴል አካባቢ
ከጠዋቱ 11፡30 ሰዓት ጀምሮ ውድድሩ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ለተሽከርካሪ ዝግ ሲሆኑ በተጨማሪም አሽከርካሪዎች የውድሩሩ ተሳታፊዎች ወደ ሚያልፉባቸው መንገዶች ተሽከርካሪ ይዞ መውጣት በጥብቅ የተከለከለ መሆኑ ተገልጿል፡፡
በዚህም አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙና ለፀጥታ አካላት ተባባሪ እንዲሆኑ እና አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥም ሆነ ለፖሊስ መረጃ ለመስጠት 011-1-11-01 11 እና በ991 ነፃ የስልክ ቁጥሮች መጠቀም እንደሚቻል የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳውቋል፡፡

ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተላለፈ መልዕክት
የተከበራችሁ ውድ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ፤ የጥምቀት በዓል በሀገራችን ብሎም በአዲስ አበባ ከተማ በድምቀት ከሚክበሩ በዓላት መካከል በናፍቆት የሚጠበቅ ነው:: በዓሉ በሀገራችን የኦርቶዶክስ ተውዋህዶ ቤተክርስትያን ለዓለም ያበረከተችው ድንቅ ቅርስ ሲሆን ለእኛ ለኢትዮጵያዋን ደግሞ የኩራታችን ምንጭ ጭምር ነው::
በዘንድሮ የከተራ ፣ የጥምቀትና የቃና ዘገሊላ በአላት ላይ የሀገራቸውን ጥሪ ተቀብለው ወደ ኢትዮጵያ የመጡ ትውልደ ኢትዩጵያውን ፣ ዲያስፖራዎች እና የኢትዮጵያ ወዳጆች እንዲሁም በርከታ ቁጥር ያለው የእምነቱ ተከታዮች ታድመውበታል፡፡
የጥምቀት በዓል የበዓሉን ትውፍታዊ ገፅታውን ጠብቆ በሰላምና በፍቅር: በድምቀትና በአብሮነት መንፈስ በማክበር በአዲስ አበባ በአስራ አንዱም ክፍለ ከተሞች 266 ታቦታት ከመንበራቸው በመዉጣት በ72 ልዩ ልዩ የጥምቀተ ባህር ስፈራዎች አድረው በሰላም ወደ መንበራቸው እንዲመለሱ ተደርጓል፡፡
በዓላት በመጡ ቁጥር ድብቅ ፍላጎታቸውን ለማሳካት የሚፈልጉ ሃይሎች በኢትዮጵያ ሰላም የለም ለማስባልና የአሸባሪውን ቡድን ተቀጥላ ፍላጎቶች ለማስፈፀም፤ በህዝብ የተመረጠን መንግስት በአመፅና ግርግር ለማውረድ ፤ በህዝቦች መሃከል ጥርጣሬና ግጭት ለመፍጠር፤ ብሎም ህዝባዊ በአሉን ወደለየለት ትርምስ ለመክተት፤ ህዝብን የሚሸብሩ ድርጊቶችን ለመፈፀም አቅደው ቢንቀሳቀሱም ሀገሩን እምነቱንና ባህሉን አክባሪ የሆነው ህዝባችን ባደረገው ርብርብ በዓሉ ጠላት በተመኘው ልክ ሳይሆን በሰላም ተጀምሮ በሰላም ተጠናቋል::
ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ በአራዳ ክ/ከተማ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አጠገብ ፀብ አጫሪና አሳፋሪ ድርጊት እንዲሁም ከባህረ ጥምቀቱ ወደ ደብሯ በመመለስ ላይ በነበረችው በወይ ብላ ማርያም ታቦት በቡራዩ ከተማ አዋስኝ አካባቢ የገጠማት መስተጓጎል እና ከዚሁ ጋር በተያያዘ በተፈጠረው አለመግባባት ህይወታቸውን ላጡና ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖቻችን የከተማ አስተዳደሩ ጥልቅ ሀዘን ተሰምቶታል፡፡
በዚህ ረገድ እንደ መንግስት የመንግስት አካላት ጥፋት የሆነውን ለይተን እርምጃ መውሰድ የጀመርን ሲሆን በቀረውም አጥፊዎች ላይ እርምጃ በመውሰድ ሃላፊነታችንን የምንወጣ መሆኑን ማሳወቅ እንወዳለን፡፡
ከተማችን እንደወትሮዋ ሁሉ በከተማዋ ውስጥ የሚካሄዱ ሃይማኖታዊ ባህላዊ የተለያዩ ክብረ በዓላትና ኩነቶች በድምቀት በሰላም በአብሮነት መንፈስ እንዲካሄዱ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እጅና ጏንት ሆኖ መስራቱን ይቀጥላል:;
በከተማችን የጥምቀት በዓል በድምቀትና በስላም እንዲከበር ምዕመኑ መላው የከተማችን ነዋሪወችና የጸጥታ ሃይሎች ላደረጋችሁት ጥረት ለከፈላችሁት ዋጋና ላስያችሁት ጨዋነት የከተማ አስተዳደሩ የላቀ ምስጋነውን ያቀርባል:: ይህንኑ በቅርቡ በሚጠበቀው በእፍሪካ መሪወች ጉባኤ በሰላም ውብና ጽዱ በሆነ አካባቢ እና በማራኪ አቀባበልና አገልግሎት የበለጠ እንዲትዘጋጁ አደራ እንላለን::
በመጨረሻም ህዝብ እያደረገ ላለው ጠንካራ ድጋፍ እና በአላቱ በሰላም እንዲጠናቀቁ ኃላፊነታቸውን በብቃት ለተወጡ ሁሉ የላቀ ምስጋናችንን እናቀርባለን!!
የከተማችንን ሰላም በማረጋገጥ የጀመርነውን የኢትዮጵን ትንሳኤ የማረጋገጥ ተግባር አጠናክረን እንቀጥላለን!!
ጥር 14/2014 ዓ.ም
አዲስ አበባ

❤1
21ኛው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ነው በሴቶች አትሌት ያለም ዘርፍ የኋላው፣በወንዶች ደግሞ አትሌት ገመቹ ዲዳ አሸናፊ ሆነዋል።
25 ሺህ ሯጮች የሚሳተፉበት 21ኛው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በመዲናችን በደማቅ ሁኔታ እየተካሄደ ነው።የ21ኛው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የተለያዩ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ፣ ታዋቂ ኢትዮጵያውያን አትሌቶችና ከጎረቤት አገሮች የመጡ አትሌቶች እና የሩጫው ተሳታፊዎች ተገኝተዋዋል።
በተካሄደው የአትሌቶች ሩጫ በሴቶች አትሌት ያለም ዘርፍ የኋላው 1ኛ ስትወጣ ግርማዊት ገ/እግዚአብሔር 2ኛ ፣መልክናት ውዱ 3ኛ ውድድሯን አጠናቃለች።
በወንዶች ደግሞ አትሌት ገመቹ ዲዳ 1ኛ ሲወጣ ፣አትሌት ጌታነህ ሞላ 2ኛ፣ አትሌት ቦኪ ድሪባ 3ኛ ደረጃን አግኝቷል።ሩጫው እየተካሄደ ያለው “መጸዳዳት በሽንት ቤት” በሚል መሪ ቃል ነው።ህዳር 5 ቀን 2014 ዓ.ም ሊካሄድ የነበረውን የ2014 ቶታል ኢነርጂስ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ፥ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መሰረት ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙ ይታወሳል።
Via FBC

የክልል መለያ ከተሽከርካሪዎች ሰሌዳ ላይ እንዲነሳ የሚያደርግ ረቂቅ አዋጅ ለፓርላማ ተመራ!
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሐሙስ ጥር 12 ቀን 2014 ዓ.ም. ባካሄደው አራተኛ መደበኛ ስብሰባው፣ የክልል መለያ በተሽከርካሪዎች ሰሌዳ ላይ እንዲነሳ የሚያደርግ ረቂቅ አዋጅ ለፓርላማ መራ፡፡ምክር ቤቱ የተወያየበት ረቂቅ አዋጅ ከተሽከርካሪ መለያ፣ መመርመርያና መመዝገቢያ አዋጅ ጋር በአባሪነት ተያይዞ ያለውን ሰንጠረዥ ይሽራል፡፡
በዚህ ረቂቅ አዋጅ የሚሻረው ሰንጠረዥ የተሽከርካሪ መለያ ቁጥር ሰሌዳ ዓይነቶችና ምልክቶችን በዝርዝር የደነገገ ሲሆን፣ እንደ ተሸከርካሪዎቹ አገልግሎት የሚኖራቸውን ቀለምና መለያ አስቀምጧል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ሰንጠረዡ እንደ አአ፣ ኦሮ፣ አማ፣ ደሕ እና ሌሎች አሥራ ሁለት የክልልና ከተማ አስተዳደሮችን የሚወክሉ ምህፃረ ቃሎችን ዘርዝሮ፣ ተሽከርካሪዎቹ እንደ ተመዘገቡበት ክልል ወይም የከተማ አስተዳደር ሰሌዳቸው እንዲሠፍር ያዛል፡፡
የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አሁን ያዘጋጀው የመንገድ ትራንስፖርት አዋጅ፣ ይኼንን አሠራር በማስቀረት ወጥነት ያለው ብሔራዊ የተሽከርካሪ ሰሌዳ አሠራር ለመዘርጋት አልሟል፡፡በሚኒስቴሩ የሕግ አማካሪ አቶ አበጀ ማሞ ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ ለተወካዮች ምክር ቤት የተመራው ረቂቅ አዋጅ ከፀደቀ በኋላ የክልል መለያ የያዙ የተሽከርካሪ ሰሌዳዎች ተግባራዊ የሚሆኑት አዲስ ብሔራዊ ሰሌዳ ይፋ እስኪደረግ ብቻ ነው፡፡
እንደ አማካሪው ገለጻ፣ ኢትዮጵያ ባለፈው ዓመት የፈረመችው እ.ኤ.አ. የ1968 ‹‹የቬዬና የመንገድ ትራፊክ ኮንቬንሽን››፣ ፈራሚ አገሮች ብሔራዊ ደረጃን የያዘ መለያ በአገሮች ውስጥ ለሚገኙ ተሽከርካሪዎች እንዲሰጡ ያዛል፡፡ ይሁንና የተሽከርካሪ መለያ፣ መመርመርያና መመዝገቢያ አዋጅ ላይ የተቀመጠው አሠራር ክልሎች የየራሳቸውን መለያ የያዘ ሰሌዳ እንዲሰጡ እንጂ፣ ወጥነት ያለው አገር አቀፍ የተሽከርካሪ ሰሌዳ ተግባራዊ እንዲደረግ አይፈቅድም፡፡ ‹‹ተሽከርካሪ ዓለም አቀፍ ቁስ ነው፣ አንድ መኪና ከዚህ ተነስቶ ኬንያም ሆነ ሱዳን ሲሄድ የአገሮቹ መንግሥት ግራ ሊጋቡ አይገባም፤›› ያሉት አቶ አበጀ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ በቅርቡ ተግባራዊ የሚደረገው የሰሌዳ ዓይነት የሚገልጸው ተሽከርካሪነታቸውን ብቻ እንደሚሆን አስረድተዋል፡፡
https://www.ethiopianreporter.com/article/24452
Via Reporter

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይና የሱዳኑ ጄኔራል መሀመድ ዳጋሎ ተወያዩ!
የሱዳን ሉኣላዊ የሽግግር ምክር ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ሌተናል ጄኔራል መሀመድ ሀምዳን ዳጋሎ (ሄመቲ) በኢትዮጵያ ጉብኝታቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጋር መወያየታቸው ተገለፀ፡፡
ሌተናል ጄኔራሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ የኢትዮጵያ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ እና የአገር መከላከያ ሚኒስትሩን አብርሃም በላይ (ዶ/ር) አግኝተዋል፡፡
የሱዳን የዜና ኤጀንሲ (ሱና) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይና ሌተናል ጄኔራሉ በሁለቱ አገራት የሁለትዮሽ ግንኙነትና የጋራ ጥቅሞች (ፍላጎቶች) ዙሪያ መወያየታቸውን ዘግቧል፡፡
ኢትዮጵያና ሱዳን ከታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብና ከድንበር ጉዳይ ጋር የተያያዘ ከፍ ያለ የጋራ አጀንዳ እንዳላቸው የሚታወቅ ነው፡፡
በመከላከያ ሚኒስቴር ዋናው መስሪያ ቤት ምሽቱን በተደረገው ውይይታቸው የሁለቱን አገራት ወንድማማች ሕዝቦች ፍላጎት ለማሳካትና ለማላቅ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል ተብሏል፡፡
ሌተናል ጄኔራሉ ‹‹አዲስ አበባን በመጎብኘቴ እና የዚህችን ውብ አገር መሪዎች በወንድማማችነት መንፈስ በማግኘቴ ደስተኛ ነኝ። ይህም የሁለቱን አገራት ግንኙነት ጥልቀት እና ጥንካሬ ያረጋግጣል›› ማለታቸውም ተዘግቧል፡፡
የጦር መኮንኑ ከአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማህመት ጋር ‹‹በሱዳን አስጨናቂ ሁኔታዎች ዙሪያ›› ትናንት በአዲስ አበባ መወያየታቸው ኮሚሽነሩ መግለፃቸው ይታወሳል፡፡
Via Walta

YeneTube
የክልል መለያ ከተሽከርካሪዎች ሰሌዳ ላይ እንዲነሳ የሚያደርግ ረቂቅ አዋጅ ለፓርላማ ተመራ! የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሐሙስ ጥር 12 ቀን 2014 ዓ.ም. ባካሄደው አራተኛ መደበኛ ስብሰባው፣ የክልል መለያ በተሽከርካሪዎች ሰሌዳ ላይ እንዲነሳ የሚያደርግ ረቂቅ አዋጅ ለፓርላማ መራ፡፡ምክር ቤቱ የተወያየበት ረቂቅ አዋጅ ከተሽከርካሪ መለያ፣ መመርመርያና መመዝገቢያ አዋጅ ጋር በአባሪነት ተያይዞ ያለውን ሰንጠረዥ…
የክልል መለያን የያዙ ሰሌዳዎችን የሚያስቀር ረቂቅ አዋጅ ለፓርላማ እንደተመራ የሚገልጽ ዘገባ ዛሬ ረፋድ ላይ ከሪፖርተር ጋዜጣ አጋርተናችሁ ነበር።
ነገር ግን ዜናው የተሳሳተ መሆን የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡
በመግለጫውም ፥ በቅርቡ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የመንገድ ትራንስፖርት ረቂቅ አዋጅ ላይ አስፈላጊውን ግብዓቶች በማካተት እንዲፀድቅ ወደ ህዝብ ተወካዮች ም/ቤት መምራቱን አስታውሷል፡፡
ሆኖም ግን ከረቂቅ አዋጁ ይዘት ውጭ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች የክልል መለያ ከተሽከርካሪዎች ሰሌዳ ላይ እንዲነሳ የሚያደርግ ረቂቅ አዋጅ ለፓርላማ መመራቱን የሚገልጽ ዜና እየተዘገበ ስለመሆኑ አረጋግጠናል ብሏል ሚኒስቴሩ ፡፡
“በመጀመሪያ መረጃዉ የተሳሳተና ከረቂቅ አዋጁ ይዘት ውጭ መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን” ሲልም ገልጿል፡፡
በመቀጠልም ፥ “በቀድሞ አዋጁ የነበረዉ የተወሰኑ ክልሎችን ታርጋ ዝርዝር የያዘ አባሪ በዚህ ረቂቅ አዋጅ የቀረው መንግስት ተጨማሪ ክልሎች ሲወጡ በየጊዜዉ በአዋጁን ማሻሻል ሳያስፈልገዉ ተግባራዊ ለማድረግ እንዲችል ታስቦ መሆኑ ታውቆ የክልል መለያ ሰሌዳን ከተሸከርካሪዎች ላይ የማንሳት የረቂቅ አዋጁ ሀሳብና ይዘት አካል እንዳልሆን ሊታወቅ ይገባል” ሲልም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አስታውቋል፡፡
ረቂቅ አዋጁ የመንገድ ትራንስፖርትን አስመልክቶ የፌዴራሉንና የክልል አስፈጻሚ አካላት የተሰጣቸውን ሥልጣንና ተግባር በማያሻማ ሁኔታ የሚያስቀምጥ ከመሆኑም በላይ ለሀገራችን ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ዕድገት የመንገድ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚያበረክተውን አስተዋጽኦ የበለጠ ለማጎልበት ዘርፉ አስተማማኝ፣ የተቀናጀ፣ ዘመናዊና ደኅንነቱ የተረጋገጠ ሆኖ እንዲራመድ የሚያስችል እንደሆነና በቅርቡም ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ቀርቦ ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር ሰፊ ውይይት ተደርጎና አስፈላጊዉ ማሻሻያ ተደርጎበት እንደሚጸድቅ ከትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል፡፡

Free Online Courses with Free Certificates 😳
To Get the links join our Telegram channel 👇🏾
https://tttttt.me/+qtDDnplBq9UzZGRk

🇺🇸🇺🇸🇺🇸🇺🇸🇺🇸🇺🇸 🇨🇦🇨🇦🇨🇦🇨🇦🇨🇦
በአሜሪካ ና ካናዳ በስኮላርሺፕ የመማር ዕድል!
ያለ ቅድመ ክፍያ ለመመዝገብ ቴሌግራም ቦት ላይ አፕላይ ያድርጉ! 👇
@marakischolarshipbot
አድራሻ: ቦሌ ጌቱ የንግድ ማዕከል 1ኛ ፎቅ ቁጥር 102
ስልክ: 0960612222
ለበለጠ መረጃ @marakiconsultant
ቴሌግራም ቻናል👇
@marakiconsultancy

በሀገር መከላከያ የሰባተኛ ዕዝ ጀብድ ለፈፀሙ የሠራዊቱ አመራሮችና መኮንኖች እውቅና ሰጠ
በኢፌዴሪ የአገር መከላከያ ሠራዊት የሰባተኛ ዕዝ ጀብድ ለፈፀሙ የሠራዊት አመራሮችና መኮንኖች ሽልማትና ዕውቅና ሰጠ።
በዕውቅና እና ሽልማት አሰጣጥ ሥነስርዓቱ ላይ የዕዙ ከፍተኛ አመራሮች፣ የሃይማኖት አባቶችና ነዋሪዎች ተገኝተዋል።
የዕዙ ከፍተኛ አመራሮች በሥነ ሥርዓቱ ላይ እንዳሉት፤ ጀብድ የፈጸሙ የሠራዊት አባላትን ማበረታት ለቀጣይ ተልዕኮ ያዘጋጃል።
በዕዙ ምርጥ አዋጊ፣ ተዋጊና አገልግሎ ሰጭ የሠራዊት አባላትና አመራሮች ዕውቅና እና ሽልማት መስጠቱ የሀገር ኩራት መሆኑንም ገልጸዋል።
የሀገር መከላከያ ሠራዊት ከአባቶቹ የተረከበውን የሀገር ነፃነት ለማስከበር የሚከፍለው መስዋዕትነት በሀገር ደረጃ ከፍተኛ ክብር ያለው መሆኑን የሚያረጋግጥ ብለዋል።
ከፍተኛ አመራሮቹ እንዳሉት፤ አሸባሪው ህወሓት ከውጭ ጠላቶች ጋር በማበር ኢትዮጵያን ለማፍረስ የያዘው ግብ በጀግኖች ልጆቿ መስዋዕትነት በመክሸፉ ሀገር ተከብራ እንድትኖር አድርጓል።
በሽብር ቡድኑ ላይ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች በወሰዱበት እርምጃም ግፍና በደል ይፈፀምባቸው የነበሩ ዜጎችን ነፃ ማውጣት ተችሏል ብለዋል።
በሥነሥርዓቱ ላይ "ትጥቃችንን ሳናላላ ኢትዮጵያን በጀግንነት እንጠብቃለን!"፤ "በተሰጠን ሽልማት ሳንኩራራ የላቀ ስራ ለመፈፀም ሁሌም እንተጋለን"! የሚሉና ሌሎች ተያየዥ መልዕክቶች ተላልፈዋል።
በህዳር ወር 2014 ዓ.ም መጀመሪያ የተመሰረተው ዕዙ አሸባሪው ህወሓትን ለመደምሰስ በተካሄዱ አውደ ውጊያዎች አኩሪ ተጋድሎ መፈጸሙ በሥነሥርዓቱ ላይ ተገልጿል።
Via:- ኢዜአ
@Yenetube @Fikerassefa

ዜጎቿ ኢትዮጵያን ለቀው እንዲወጡ ስትወተውት የነበረችው አሜሪካ አሁንም ዩክሬንን ለቀው እንዲወጡ አሳሰበች!
ዜጎቿ ኢትዮጵያን ለቀው እንዲወጡ ስትወተውት የነበረችው አሜሪካ አሁንም ወደ ሩሲያ ከመጓዝ እንዲቆጠቡ አሳሰበች፡፡ዋሽንግተን ዩክሬን ኪቭ የሚገኙ ዲፕሎማቶቿ እና ቤተሰቦቻቸው ሃገሪቱን ለቀው እንዲወጡም አሳስባለች፡፡ሩሲያ ዩክሬንን ልትወር እንደምትችል በማሳሰብም በምስራቅ አውሮፓ የሚገኙ ዜጎቿ ለቀው በቶሎ ስለ መውጣት እንዲያስቡም አስጠንቅቃለች፡፡
Via Alain

ከባሕር ዳር ወደ ሰቆጣ ሲጓዝ በነበረ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶብስ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ20 ሰዎች ሕይወት አልፏል፡፡
ለግዳጅ ከባሕር ዳር መነሻውን ያደረገው የሕዝብ ማመለሻ አውቶብስ በደረሰበት አደጋ ሰዎች ህይወታቸው ሲያልፍ፣ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው እንዳሉም ታውቋል፡፡
የደረሰውን የትራክ አደጋ በተመለከተ ከአሚኮ ጋር ቆይታ ያደረጉት የድሃና ወረዳ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት የመንገድ ትራፊክ ደኅንነት ክፍል ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ሲሳይ አበራው ለግዳጅ ከባሕር ዳር የወጣው የሕዝብ ማመላለሻ አውቶብስ በመንገድ ላይ ያገኛቸውን ሰዎች ጭኖ ሲጓዝ አደጋው እንደደረሰ ነው የተናገሩት፡፡ አደጋው የደረሰው መለያ ቁጥሩ 11300፣ የጎን ቁጥሩ 2527 የሆነ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶብስ መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡
ጉዳቱ የደረሰው ከአምደወርቅ ወጣ ብሎ አቦ መገጠንያ መንገድ በምትባል ሥፍራ እንደሆነም ገልጸዋል፡፡ በግምት 200 ሜትር ከሚሆን ገደል ውስጥ መግባቱንም ተናግረዋል፡፡ በደረሰው አደጋም 20 ሰዎች ህይወታቸው ሲያልፍ 6 ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን ነው የተናገሩት፡፡ ከአደጋው ከተረፉ ሰዎች ጋር ቆይታ እንዳደረጉ የተናገሩት ኃላፊው ከእብናት ወደ አምደ ወርቅ ሲጓዝ ብዙ ሰው እንደነበርና ከአምደወርቅ ሲያልፉ ግን ሰው ያልነበረባቸው ወንበሮች እንደነበሩ ነግረውኛል ነው ያሉት፡፡ ለአደጋው ምክንያት ፍጥነት እና የመንገዱ መጎዳት ሳይሆን እንዳልቀረም ተናግረዋል፡፡ ጉዳቱ ከፍተኛ መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡
Via AMC

ሁለተኛው ዙር የ12ኛ ክፍል ፈተና ከመጪው ጥር 24 እስከ ጥር 27 ይሰጣል!
የሁለተኛው ዙር የ12ኛ ክፍል ፈተና ከመጪው ጥር 24 እስከ ጥር 27 እንደሚሰጥ ተገለፀ።የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እንዲሁም የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት በትምህርት ሥርዓቱ ላይ ያደረሰው ተፅእኖ ከፍተኛ መሆኑ ይታወቃል።በተለይም ወረርሽኙ ወደአገር ከገባ በኃላ እና በትግራይ ክልል ጦርነት ከተነሳ በኃላ የዓመቱ መርሀግብር በእጅጉ ተናግቷል።
ከጥቂት ወራት በፊት ብሄራዊ ፈተና የወሰዱ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች እስካሁን ውጤት ያልተነገራቸው ሲሆን በዚህም ያለትምህርት ወራትን ለማሳለፍ ተገደዋል።እስካሁን የፈተናው ውጤት ይፋ የሚደረግበትም ቀን አልታወቀም።
በአማራ፣ በኦሮሚያ እና በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የተለያዩ ዞኖችና ወረዳዎች በፀጥታ ምክንያት የ12ኛ ክፍል ፈተና መውሰድ ያልቻሉ ተማሪዎች ከመጪው ጥር 24 እስከ ጥር 27 ቀን 2014 ለፈተና ይቀመጣሉ ተብሏል።
በትግራይ ክልል ፈተና መቀመጥ የነበረባቸው ተማሪዎች በጦርነት ምክንያት ላለፉት ዓመታት በአግባቡ ለፈተና መቀመጥ አልቻሉም።በአጠቃላይም 58 ሺህ 936 ተማሪዎች ፈተናውን ይወስዳሉ ተብሎ ይገመታል።
✍Addis Maleda