YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
አቶ #ሚሊዮን ዛሬ በ|#ሀዋሳ ከተማ ከወጣቶች ጋር በተወያዩበት ወቅት ነው።


"ለሚቀጥሉት 10 አመታት የሀዋሳን ከተማ እንዲያገለግል ታስቦ የተዘጋጀው መሪ እቅድ (Master Plan) በከተማው ዙሪያ በሚኖሩ አርሶ አደሮች ጥያቄ መሰረት ለጊዜው እንዲቆም መደረጉን የደቡብ ክልል ፕሬዝደንት አቶ ሚሊዮን ማቲዮስ ተናገሩ"

©zeki
@YeneTube @Fikerassefa
ግምቱ ወደ 28 #ሚሊዮን የሚጠጋ ብር በስድስት ኩንታል ተሞልቶ ከአዲስ አበባ ወደ #ሚዛን ተፈሪ ሲጓዝ በካፋ ዞን የጨና ወረዳ ነዋሪዎች በቁጥጥር ስር ዋለ

ገንዘቡ ለምን አላማና በማን እንደሚጓጓዝ እስካሁን #በፖሊስ ምርመራ እየተደረገበት መሆኑን ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡

📌የምንመለስበት ይሆናል ❗️
©MOHAMMED NURE ENDRIES
@YeneTube @Fikerassefa
የአፊኒ ባህላዊ ስነ ስርዓት!!

"በሀገሪቱ የተጀመረውን ለውጥ ለማስቀጠል የወጣቱ ሚና ከፍተኛ መሆን አለበት" – የሲዳማ ብሄር የሀገር ሽማግሌዎች
.

በኢትጵያ የተጀመረውን ለውጥ ለማስቀጠል የወጣቱ ሚና ከፍተኛ መሆን እንዳለበት የሲዳማ ብሄር የሀገር ሽማግሌዎች አሳሰቡ፡፡ በብሄሩ አመታዊው የአፊኒ ባህላዊ ስነ ስርአት በሶሬሳ ጉዱማሌ በሃዋሳ በዛሬው ዕለት ተካሂዷል፡፡

ሲዳማ ከሌሎች ህዝቦች ጋር ተዋዶ እና ተፍቅሮ በአንድነት የመኖር እሴቱን ጠብቆ የኖረ ነው ያሉት የሀገር ሽማግሌዎች ወጣቱም ይህን አኩሪ ባህል ሊጠብቀውና ማንኛውም ጥያቄዎችን በሰላማዊ መንገድ ሊያቀርብ እንደሚገባ ገልፀዋል።

በውይይቱ ላይ የተገኙት የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ #ሚሊዮን_ማቲዎስ በበኩላቸው የሲዳማ ብሄር በአቃፊነቱ እንጂ በጥላቻ አይታወቅም ስለዚህም ከሁሉም ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ጋር በአንድነት ለመኖር የዘመናት ባህሉ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።

ወጣቱም የአባቶቹን ምክር በመስማት ሊተገብር ይገባል ያሉ ሲሆን ይህ መሰል ባህላዊ ስርአት ሌሎችም እንደተሞክሮ ሊጋሩት እንደሚገባ ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል።

የውይይቱ ተሳታፊ ወጣቶችም የሀገር ሽማግሌዎችን ምክርና ተግሳፅ በስርአቱ መሰረት በመቀበል ለሀገራዊ ለውጡ የሚጠበቅባቸውን እንደሚወጡ fbc ገልፀዋል።

በወጣቱ ስም በሃዋሳም ሆነ በዞኑ የሚነሱ የሰላም መደፍረሶችን በመከላከል ህግና ስርአት እንዲከበር የበኩላችንን እንወጣለን ብለዋል ተሳታፊዎቹ፡፡

ክልል የመሆን ጥያቄ እና ሙሰኞችን የማጋለጥ ሂደት በሰላማዊ መንገድ እንደሚታገሉ ተናግረዋል።

በአፊኒ ስርአት የሀገር ሽማግሌዎችና ወጣቶቹ በወቅታዊ የፀጥታ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት ካደረጉ በኋላ ቃል በመግባት አጠናቀዋል።

ምንጭ፦ fbc
@Yenetube @Fikerassefa
አሜሪካ እና የአውሮፓ ኅብረት ሀገራት የሰብዓዊ ዕርዳታ እና ልማት አመራሮች በቀጣዩ ሳምንት በትግራዩ ጦርነት ላይ ሊመክሩ እንደሆነ ሮይተርስ ዘግቧል፡፡ የስብሰባው ዐላማ በትግራይ ባለው የሰብዓዊ ቀውስ እና ሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ዙሪያ የጋራ መግባባት ለመፍጠር እና በተመድ ማዕቀፍ ውስጥ በአስቸኳይ ሰብዓዊ ዕርዳታ ላይ ወሳኝ ርምጃዎች እንዲወሰዱ ለማድረግ ነው፡፡ የቡድን-7 ሀገሮችም በሰኔ ወር የመጀመሪያ ቀናት በኢትዮጵያው ቀውስ ላይ እንደሚመክሩ ተሰምቷል፡፡

አሜሪካ እና የአውሮፓ ኅብረት የልማት አጋሮች ዛሬ በአዲስ አበባ ባደረጉት ስብሰባ ለትግራይ ክልል ተረጅዎች 500 #ሚሊዮን_ዶላር እንደሚለግሱ አውሮፓ ኅብረት በትዊተር ገጹ አስታውቋል፡፡ በትግራይ ክልል ሁሉም ወገኖች ግጭት እንዲያቆሙ፣ የሰብዓዊ ዕርዳታ ሥርጭትን እንዳያሰናክሉ እና ጋዜጠኞች በክልሉ ተንቀሳቅሰው እንዲዘግቡ እንዲፈቅዱ ሀገራቱ በስብሰባቸው በጋራ ጠይቀዋል፡፡ በክልሉ አስከፊ ርሃብ እንዳይከሰት መንግሥት አስቸኳይ ርምጃዎችን እንዲወስድም አሳስበዋል፡፡

[Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa