YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
አሜሪካ እና የአውሮፓ ኅብረት ሀገራት የሰብዓዊ ዕርዳታ እና ልማት አመራሮች በቀጣዩ ሳምንት በትግራዩ ጦርነት ላይ ሊመክሩ እንደሆነ ሮይተርስ ዘግቧል፡፡ የስብሰባው ዐላማ በትግራይ ባለው የሰብዓዊ ቀውስ እና ሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ዙሪያ የጋራ መግባባት ለመፍጠር እና በተመድ ማዕቀፍ ውስጥ በአስቸኳይ ሰብዓዊ ዕርዳታ ላይ ወሳኝ ርምጃዎች እንዲወሰዱ ለማድረግ ነው፡፡ የቡድን-7 ሀገሮችም በሰኔ ወር የመጀመሪያ ቀናት በኢትዮጵያው ቀውስ ላይ እንደሚመክሩ ተሰምቷል፡፡

አሜሪካ እና የአውሮፓ ኅብረት የልማት አጋሮች ዛሬ በአዲስ አበባ ባደረጉት ስብሰባ ለትግራይ ክልል ተረጅዎች 500 #ሚሊዮን_ዶላር እንደሚለግሱ አውሮፓ ኅብረት በትዊተር ገጹ አስታውቋል፡፡ በትግራይ ክልል ሁሉም ወገኖች ግጭት እንዲያቆሙ፣ የሰብዓዊ ዕርዳታ ሥርጭትን እንዳያሰናክሉ እና ጋዜጠኞች በክልሉ ተንቀሳቅሰው እንዲዘግቡ እንዲፈቅዱ ሀገራቱ በስብሰባቸው በጋራ ጠይቀዋል፡፡ በክልሉ አስከፊ ርሃብ እንዳይከሰት መንግሥት አስቸኳይ ርምጃዎችን እንዲወስድም አሳስበዋል፡፡

[Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa