YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በአዲስ አበባ እፎይታ የገበያ ማዕከል ትላንት ምሽት የተነሳው የእሳት ቃጠሎ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገለፀ!

ትላንት ከምሽቱ 2:20 አካባቢ በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 10 እፎይታ የገበያ ማዕከል ሱቆች ላይ የተነሳው የእሳት ቃጠሎ አደጋ በቁጥጥር ስር መዋሉን የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ አስታወቁ።የእሳቱን ለማጥፋት የእሳት አደጋ መከላከያ፣ ፖሊሶች እና የአካባቢው ነዋሪዎች ባደረጉትርብርብ በቁጥጥር ስር መዋሉንም ነው ምክትል ከንቲባዋ በማህበራዊ ገፃቸው የገለፁት።
ጠቅላላ የተቃጠሉ የሱቆች ቁጥርና የደረሰው የጉዳት መጠን እየተጣራ ሲሆን፤ ሙሉ መረጃውን እንደደረሰ ይፋ እንደሚፈረግም ተገልጿል።

አደጋው በቁጥጥር ስር ቢውልም፤ የእሳት ቃጠሎ ትላንት ከሰዓት በኋላ ብቻ በአዲስ አበባ የደረሰ ሁለተኛ አደጋ በመሆኑ እና እሳቱ በተነሳ ጊዜ ዘረፋም ስለነበረ ጠንከር ያለ የምርምራ ስራ ተጀምሯል ብለዋል ም/ከንቲባዋ። ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች ለጋራ ሰላም ሲባል ምንም አይነት መረጃ ያለው ግለሰብ ለህግ አስከባሪ እና ለፖሊስ መረጃውን እንዲሰጥ ጠይቀዋል።
ሁሉም የከተማዋ አመራር እና ነዋሪዎች መሰል አደጋዎች ዳግም እንዳይከሰቱ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉም ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አሳስበዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
ባለፉት ስድስት ወራት 125 አዳዲስ ከተሞች የኤሌክትሪክ ሐይል ማግኘታቸው ተገለጸ!

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ባልተዳረሰባቸው የሃገሪቱ አካባቢዎች ፍትሃዊ ተደራሽነትና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የተለያዩ ዘርፈ ብዙ ሥራዎች እያከናወነ እንደሚገኝ አስታውቋል።በዚህም ተቋሙ ባለፉት ስድስት ወራት 161 አዳዲስ ከተሞች ኤሌክትሪክ እንዲያኙ ለማድረግ ታቅዶ 125ቱ  የኤሌክትሪክ ሃይል አግኝተዋል።በመልሶ ግንባታ ሥራ ደግሞ 10 አቅዶ 10 ከተሞችን ማገናኘት ችሏል፡፡በአዲስና በመልሶ ግንባታ ሥራዎች 171 የገጠር ከተሞችና መንደሮች የኤሌክትሪክ ኃይል እንዲያገኙ ለማድረግ አቅዶ 135ቱን ማሳካቱንም ነው ተቋሙ የገለጸው

ከዚህ ባለፈም ባለፉት ስድስት ወራት የገጠር ከተሞችና መንደሮችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ 1 ሺህ 35 ነጥብ 15 ኪሎ ሜትር የመካከለኛ መስመር ዝርጋታ ለማከናወን ተቋሙ አቅዶ 1 ሺህ 439 ነጥብ 67 ኪሎ ሜትር  በመዝርጋት ከዕቅድ በላይ አፈፃፀም አሳይቷል።በተጨማሪም 749 ነጥብ 93 ኪሎ ሜትር  የዝቅተኛ መስመር ዝርጋታ ለማከናወን አቅዶ 1 ሺህ 439 ነጥብ 9 ኪሎ ሜትር መዘርጋት መቻሉን ገልጿል፡፡

እንዲሁም በተለያዩ የገጠር ከተሞችና መንደሮችን 427 የትራንስፎርመር ተከላ ለማከናወን ታቅዶ 314 ያህሉ ተከናውኗልም ነው ያለው፡፡ተጠቃሚነትን ከማሳደግ አኳያ በ2013 የመጀመሪያው መንፈቅ ዓመት 142 ሺህ 11 አዳዲስ ደንበኞች የኤሌክትሪክ አገልግሎት እንዲያገኙም መደረጉንም ነው ተቋሙ ያስታወቀው።በቀጣይም ከዋናው የኃይል ቋት የሚርቁ 25 የገጠር ከተሞችና መንደሮች በሚኒ ግሪድ የሶላር ፕሮጀክት ተጠቃሚ ለማድረግ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራም እንደሚገኝ ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎትን ጠቅሶ የዘገበው ፋብኮ ነው።

@YeneTube @FikerAssefa
የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ባለስልጣን አሁን ካለው ተጨማሪ የባለ ሁለት እግር ሞተር ፈቃድ የመስጠት ፍላጎት እንደሌለው ተናገረ፡፡

በ2011 አዲስ መመሪያ መዘጋጀቱን ተከትሎ በአሁኑ ሰዓት 3600 የሚደርሱ ሞተሮች ፈቃድ ተሰጥቷቸው እየሰሩ ሲሆን ይህ ቁጥር ለከተማው ለጊዜው በቂ ነው ብሏል፡፡

የትራንስፖርት ባለስልጣን በከተማው የትራንስፖርት አገልግሎት ዙሪያ በመከረበት መድረክ ላይ ተገኝተን እንደሰማነው አሁንም አልፎ አልፎ በሞተር ሳይክሎች በከተማዋ ዝርፊያ እየተፈፀመ ነው፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ ለቁጥጥር ያስቸገረና የተደራጀ ዝርፊያና ስርቆት በሞተር ሳይክሎች መፈፀም መብዛቱን ተከትሎ ሞተር ሳይክሎች ሙሉ በሙሉ ከከተማው እንዲወጡ ተደርጎ ነበር፡፡

ቆይቶ ሞተር ሳይክሎቹ በማህበር ሆነው ቀለም አስቀብተው የጂ.ፒ.ኤስ መቆጣጠሪያ ተገጥሞላቸውና ዩኒፎርም መልበስ ግዴታ እንዲሆን ተደርጎ ለ3600ዎቹ ዳግም ፈቃድ ተሰጥቷል፡፡

በፊት ከነበሩት 15,000 ገደማ የሞተር ሳይክሎች ውስጥ ከ11,000 በላይ የሚሆኑት ፈቃድ ቢጠይቁም ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ አሁን በስራ ላይ ያሉትን በወጉ ሥርዓት የማስያዝና የመቆጣጠር እንጂ አዲስ ፈቃድ የመስጠት ፍላጎት እንደሌለኝ እወቁት ብሏል፡፡

Via:- Sheger FM
@Yenetube @Fikerassefa
አንቶኒዮ ጉተሬዝ የምያንማርን መሪ ኦንግ ሳንሱካይ መታሰርን አወገዙ

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት(ተመድ) ዋና ጸኃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ የምያንማር መሪ ኦንግ ሳን ሱ ካይንና ሌሎች የፖለቲካ መሪዎች በምያንማር የፓርላማ መክፈቻ ዋዜማ ላይ መታሰራቸውን አወገዘ፡፡

ጉተሬዝ የሀገሪቱ ህግ አውጭ፣ አስፈጻሚና የፍርድቤት ስልጣን ወደ ወታደር መተላለፉ እንደሚያሳስባቸው ገልጸዋል፡፡ የምያንማር ወታደር መፈንቅለ መንግስት በማካሄድ ኦንግ ሳን ሱ ካይን አስሯል፤ለአንድ አመት የሚቆይ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጇል፡፡

Via:- Alian
@YeneTube @Fikerassefa
የኤሌክትሪክ ቆጣሪ እናስገባለን በሚል ሰበብ ህገወጥ ድርጊት የሚፈፅሙ ግለሰቦች ስላሉ ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ተቋሙ አሳሰበ!

የኤሌክትሪክ ቆጣሪ እናስገባለን በሚል ሰበብ ህገወጥ ድርጊት የሚፈፅሙ ግለሰቦች ስላሉ ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አሳሰበ፡፡ከኤሌክትሪክ አገልግሎት ጋር ተያይዞ ለሚቀርቡ ሌሎች ማንኛውም ጥያቄዎች ምላሽ የሚሰጠውም ይህ ተቋም ሳለ ከህጋዊ አሰራር ውጭ የተቋሙ ሠራተኛ በመምሰል እኩይ ዓላማ ያነገቡ ግለሰቦች የኤሌክትሪክ ቆጣሪ እናስገባለን በሚል በህገ-ወጥ መንገድ ከህብረተሰቡ ገንዘብ የሚቀበሉ ግለሰቦች መኖራቸውን ተቋሙ በደረሰው ጥቆማና ባደረገው ማጣራት ማረጋገጡን ነው የገለጸው፡፡

ለአብነትም ነዋሪነቷ በአዲስ አበባ ከተማ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 የሆነች አንዲት ግለሰብ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የማያውቀው ነገር ግን "ከተቋሙ ነው የመጣነው ቆጣሪ እናስገባልሻለን" ብለው በማታለል ገንዘብ ተቀብለዋት ህጋዊ ያልሆነ የኤሌክትሪክ ቆጣሪ ገጥመውላታል፡፡

ግለሰቧ ለእነዚህ ሰዎች በሐሰተኛ እሴት ታክስ ደረሰኝ 12 ሺህ ብር የከፈለቻቸው ቢሆንም ድርጊቱ ከተቋሙ እውቅና ውጪ እንደነበር ነው የተጠቀሰው፡፡ በመጨረሻም በተደረገው ማጣራት የተገጠመው ቆጣሪ ህገወጥና ትክክለኛውን የአሰራር ስርዓት ተከትሎ የተፈፀመ አለመሆኑን ተደርሶበት የተገጠመላት ቆጣሪ አገልግሎት እንዳይሰጥ መደረጉንም ነው የተገለጸው፡፡ህብረተሰቡ እንደነዚህ አይነት መሰል እኩይ ድርጊቶች ሊያጋጥመው ስለሚችል አስፈላጊ ጥንቃቄ እንዲወስድ ተቋሙ በአንፅንኦት አሳስቧል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የፌዴራል መንግሥት ተቋማት በሥራቸው የሚገኙ ሠራተኞችን ሀብትና ንብረት እስከ ጥር 20 ቀን 2013 ዓ.ም. ድረስ መዝግበው እንዲያጠናቅቁ በተሰጠው የጊዜ ገደብ መሠረት ግዴታቸውን የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤትን ጨምሮ 197 የፌዴራል መንግሥት ተቋማት ላይ አስተዳደራዊና ሕጋዊ ዕርምጃ እንደሚወስድ፣ የፌዴራል የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን አስታወቋል።

[Reporter]
@YeneTube @FikerAssefa
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን በተለያዩ ወረዳዎች በነበረው የጸጥታ ችግር ተፈናቅለው በተለያዩ መጠለያ ጣቢያ ውስጥ ያሉትን ዜጎች መልሶ ለማቋቋምና ለመደገፍ  የሚያስችል ከ14 ሚሊዩን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን  በክልሉ የተፈናቀሉ ዜጎችን ለመደገፍ  የተቋቋመው የገቢ አሰባሰብ አብይ ኮሚቴ አስታውቋል።

የቤኒንሻጉል ጉሙዝ ክልል የግብርና እና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ እንዳስታወቀው ገቢው የተሰበሰበው በክልል ደረጃ ካሉት ተቋማት እንዲሁም ከዞንና ወረዳ  ደረጃ ካሉት መስሪያ ቤቶች ነው።ከዚህ ቀድም ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለክልሉ ተፈናቃዩች የተላከው ድጋፍ  በአሶሳ ዞን ሆሞሻ በተባለ  ወረዳ ተራግፎ የነበረና በቶሎ ተፈናቃዩች  አልደረሰም የሚል ቅሬታም ሲቀርብ የቆየ ሲሆን ከትናንት ጅምሮ ወደ ስፋራ ማጓጓዝ መጀመሩንም ገልጿል።

[DW]
@YeneTube @FikerAssefa
የዋሪት የውሀ ማጣሪያ ከ15% ልዩ ቅናሽ ጋር

ሰብስቤ www.sebsibie.com በመግባት መገበየት ይችላሉ።

ሰብስቤ ሁሉንም ሰብስቦ በአንድ ላይ የያዘ የግብይት ድረገፅ

ከ3,200 በላይ ዕቃዎች

@SebsibieEthiopia
www.sebsibie.com

📞 0953707070

Dedicated online shopping platform
🖼 ለጓደኛ፣ ለወዳጅ ዘመድ፣ ለሙሽሮች እና ለተመራቂዎች ለየት ያለ ስጦታ መስጠት ይፈልጋሉ?
#join
👇👇👇👇
@giftsoflovee
@giftsoflovee
👆👆👆👆
📱+251914839754
📱+251936871620
#ኣድራሻችን፡ 4 ኪሎ: ቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ህንፃ
#በአሰላ ከተማ ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የድጋፍ ሰልፍ እየተከናወነ ይገኛል!!

"ዶክተር አብይን ለመደገፍ የምንሳሳለት ነፍስም ሆነ ሀብት የለም!" የሚል መፈክር በሰልፉ ላይ ታይቷል።

አሰላ
@Yenetube @Fikerassefa
ከመተከል የሸሹ ታጣቂዎች በሆሮ ጉድሩ ወለጋ ንጹሐንን እየገደሉ መሆኑ ተጠቆመ

በኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን ከመተከል ሸሽተው የገቡ ታጣቂዎች በየእለቱ በንጹሐን ዜጎች ላይ የግድያና የንብረት ዘረፋ ተግባር እየፈጸሙ መሆኑን የአካባቢው ኗሪዎች ለአዲስ #ማለዳ አረጋገጡ።

ተጨማሪ ለማንበብ 👇

https://buff.ly/3oC96Cz
@Yenetube @Fikerassefa
ብርጋዴር ጄነራል መአሾ ሀጎስ ስዩም የተመድ የደቡብ ሱዳን ሰላም ማስከበር ተልእኮ አዛዥ ሆኑ!

በኢትዮጵያ አየር ኃይል ውስጥ ለ25 ዓመታት ያገለገሉት ብርጋዴር ጄነራል መአሾ ሀጎስ ስዩም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የደቡብ ሱዳን ሰላም ማስከበር ተልእኮ አዛዥ ሆነው ተሰየሙ።

ብርጋዴየር ጄነራል መአሾ በተመድ የላይቤሪያ እንዲሁም ዳርፉር ሰላም አስከባሪ ኃይል ውስጥ ማገልገላቸውም ታውቋል።

አዲሱን ሹመት ከጥር 04 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ እንደተሰጣቸውም በተመድ መረጃ ላይ ተገልጿል።

[Walta]
@YeneTube @FikerAssefa
የከፍተኛ ትምህርት አግባብነት እና ጥራት ኤጀንሲ ከግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ባለፈ በመንሥስት ዩኒቨርሲቲዎችም ክትትልና ቁጥጥር የማድረግ ውጥን እንዳለው ተነገረ፡፡

ይህን ሥራ ከመቼ እንደሚጀምር ባይጠቀስም፣ የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትም እንደግል ተቋማቱ ሁሉ ለሚያስተምሩት ትምህርት የዕውቅና ፈቃድ ሊያገኙ ይገባል ተብሏል፡፡

በዚሁ መሠረት ዩኒቨርሲቲዎች የሚያስተምሩባቸው ፕሮግራሞች አግባብነትና ብቃት እንዲገመገም ለከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ እንዲያቀርቡ መታዘዛቸውን ተሰምቷል፡፡

ይህን የተናገሩት የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትሩ ዶ/ር ሳሙኤል ኡርካቶ ከግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ባለቤቶችና የሥራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት ባደረጉበት ወቅት ነው፡፡

በዚሁ ጊዜ ሚኒስትሩ ባደረጉት ንግግር የግሉ ዘርፍ ትምህርትን ለዜጎች ለማዳረስ ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል ብለዋል፡፡ይሁን እንጂ ከአሁን ወዲያ የመንግሥትም ሆኑ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፊታቸውን ወደ ትምህርት ጥራት ማዞር ይጠበቅባቸዋል ሲሉ ተሰምቷል፡፡

ዶ/ር ሳሙኤል አሁን ለሚታየው የትምህርት ጥራት ችግር መንስኤ ያሏቸውን 4 ነጥቦች ዘርዝረዋል፡፡

እነዚህም የመምህራን ጥራት ችግር፣ ሥርዓተ ትምህርትን ወቅቱን ጠብቆ አለመከለስ፣ መሠረተ ልማት ሳይሟላ ትምህርት መስጠት እና ወቅቱን ያላማከለ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች ናቸው፡፡

ስለሆነም የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር እነዚህን በማሻሻል ጥራት ያለው ትምህርት እንዲሰጥ ከተቋማት ጋር መመካከር አስፈልጎታል ብለዋል ዶ/ር ሳሙኤል ኡርካቶ፡፡

ተመሳሳይ ውይይቶች በተከታታይ እንደሚካሄዱም ተናግረዋል፡፡በምክክር መድረኩ ላይ የሳይንስ ፖሊሲና ስትራቴጂ ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ያለው ሚናና ዲጂታል ክህሎት እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ወቅታዊ አቋም ላይ ያተኮሩ ጽሑፎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

በኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት 51 የመንግሥት ዩኒቨርስቲዎችና 278 የሚደርሱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አሉ፡፡

[Sheger FM]
@YeneTube @FikerAssefa
በማይካድራ ጭፍጨፋ የተገለጸው የሟቾች ቁጥር የተጋነነ መሆኑን ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ አስታወቀ!

በሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ በምትገኘው የማይካድራ ከተማ ጥቅምት 30 ቀን 2013 ዓ.ም. በንፁኃን ዜጎች ላይ በተካሄደው ጭፍጨፋ በተለያዩ አካላት የተገለጸው ቁጥር፣ የተጋነነ ነው ሲል የፌዴራል ዋና ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ አስታወቀ፡፡

ከጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ በትግራይ ክልል በተካሄደው የሕግ ማስከበር ዘመቻ የነበረውን አጠቃላይ ሁኔታ እንዲያጠና ከፌዴራል ፖሊስ፣ ከጠቅላይ ዓቃቤ ሕግና ከአገር መከላከያ ሚኒስቴር የተውጣጣው ግብረ ኃይል የመጀመርያ የሆነውን ባለ 90 ገጽ ሪፖርት ይፋ አድርጓል፡፡

ዘገባው የሪፖርተር ነው ተጨማሪ ለማንበብ: https://bit.ly/3raOiUe

@YeneTube @FikerAssefa
መድሃኒትን ለተላመደ ለቲቢ በሽታ ከዚህ በፊት ከ18 እስከ 24 ወራት ይሰጥ የነበረው የህክምና አገልግሎት ከ9 እስከ 12 ወራት በሚሰጥ መድሐኒት መተካቱን ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ህክምናው ከዚህ ቀደም በመርፌና በሚዋጥ መድሃኒት መልክ ሲሰጥ እንደነበር የሚታወስ ሲሆን አሁን በሚዋጥ መድሃኒት መተካቱ ነው የተጠቀሰው፡፡

በዛሬው ዕለት መድሐኒቱን የተላመደ የቲቢ በሽታ ህክምና ለሚከታተሉ ታካሚዎች በአጭር ጊዜ አገልግሎት ማግኘት የሚያስችል የማስጀመሪያ ስነ- ስርዓት ተካሄዷል፡፡

በዚሁ ወቅት የበሽታ መከላከልና መቆጣጠር ምክትል ዳይሬክተርና የብሔራዊ ቲቢ መከላከል ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ ታዬ ለታ መድሃኒቱን የተላመደ የቲቢ በሽታ በማህበረሰቡ ዘንድ እየፈጠረ ያለው ተጽዕኖ ከባድ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የጤና ሚኒስቴር የበሽታውን አሳሳቢነት በመመልከትና ትኩረት በመስጠት ስርጭቱ እንዳይስፋፋ በመከላከልና በበሽታው ለተያዙ ህሙማን ተገቢውን የህክምና አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
የፖለቲካ ፓርቲዎች እጩ ተመራጮችን የድጋፍ ፊርማ እንዲያሰባስቡ የሚያስገድደው ሕግ እንዲሻር ተወሰነ፡፡

ውሳኔውን ያሳለፈው የሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ሲሆን፤ የፖለቲካ ፓርቲ ተመራጭ እጩዎች የድጋፍ ፊርማ ማሰባሰብን የሚያስገድደው በፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ስነ ምግባር አዋጅ አንቀጽ 32፤ ንዑስ አንቀፅ 2 መሠረት በ6ኛው አገራዊ ምርጫ ተፈፃሚ እንዳይሆን የሚል ነው፡፡

በዚህ መሠረት የፖለቲካ ፓርቲ እጩዎች ለአገራዊ ምርጫ 10,000 ለክልል ደግሞ 4000 የድጋፍ ፊርማ እንዲያሰባስቡ የሚያስገድደው አሠራር ለመጪው ምርጫ ብቻ እንዲቀር ተደርጓል፡፡

በሌላ በኩል፤ ለግል ተወዳዳሪዎች የድጋፍ ፊርማ ማሰባሰብን የሚያስገድደው ድንጋጌ ተሻሽሏል፡፡በዚህም መሠረት፤ የግል የምርጫ ተወዳዳሪ 5000 የድጋፍ ፊርማ ማሰባሰብ እንዳለበት በሕጉ የተደነገገ ሲሆን፤ በማሻሻያው በግማሽ እንዲቀንስ ተደርጓል፡፡

በሌላ በኩል፤ የግል ተወዳዳሪ አካል ጉዳተኛ ከሆነ 3000 የድጋፍ ፊርማ ማሰባሰብ ይጠበቅበት የነበረው 1,500 ብቻ እንዲሆን በማሻሻያው ተካትቷል፡፡

የተጠቀሱት ማሻሻያዎች ለ6ኛ አገራዊ ምርጫ ብቻ ተግባራዊ የሚሆኑ ናቸው፡፡የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 9ኛ መደበኛ ስብሰባ የሥነ-ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽንን እንደገና ለማቋቋም የቀረበለትን ረቂቅ አዋጅና በሌሎች አጀንዳዎችም ላይ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡

Via Sheger FM
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ንዝረት ህክምና ዳግም መሰጠት ተጀመረ።

በአማኑኤል የአዕምሮ ጤና ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የኤሌክትሪክ ንዝረት ህክምና ዳግም መስጠት መጀመሩን ተናግሯል።በሆስፒታሉ የአዕምሮ ህክምና ስፔሻሊስት ዶክተር ዮናስ ላቀው የኤሌክትሪክ ንዝረት ህክምናው መጀመሩን ለኢትዮ ኤፍ ኤም አረጋግጠው ከባድ የድብርት ህመም ላለባቸው ተደጋጋሚ ራስን የማጥፋት ሀሳብ ላላቸው ሰዎችና አልበላም አልጠጣም አልናገርም ለሚሉ ሰዎች የኤሌክትሪክ ሀይል በመልቀቅ አንጎላቸውን የምናነቃበት ህክምና ነው ብለዋል።የኤሌክትሪክ ንዝረት ህክምና በኢትዮጵያ በተለይም በአማኑኤል የአዕምሮ ጤና ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከተጀመረ ወደ 20 አመት እንደሚጠጋ ይነገራል።

በአማኑኤል ሆስፒታል ብቻ የሚገኘው ህክምናው ከመላው የኢትዮጵያ አካባቢዎች የሚመጡ ታካሚዎችን እንደሚያስተናግድም ተሰምቷል።ህክምናውን ለማድረግ የሚሰጥ ማደንዘዣ ከኮቪድ ወረርሽኝ ጋር ላይሄድ ይችላል በሚል አገልግሎቱ ተቋርጦ እንደነበረ የነገሩን ዶክተር ዮናስ ላቀው አሁን ላይ ግን የኤሌክትሪክ ህክምና ክፍሉም ጽዳትና እድሳት ተደርጎለት ዳግም ስራ ጀምሯል ብለዋል።ከኮቪድ ወረርሽኝ ጋር ተያይዞም ታካሚዎች ሲመጡ ቅድሚያ የኮቪድ ምርመራ ተደርጎላቸው ህክምናውን ያገኛሉ ሲሉ ተናግረዋል።

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
የንግድ እና ኢንደስትሪ ሚኒስቴር ለነዳጅ ኩባንያዎች የሚያቀርበውን ነዳጅ የዱቤ ሽያጭ እንደሚያቆም አስታወቀ፡፡

አሁን ባለው አሰራር በአገሪቱ ብቸኛ ነዳጅ አስገቢ የሆነው የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ለ 36 የነዳጅ ኩባንያዎች ነዳጅ በአንድ ወር ዱቤ እያቀረበ ይገኛል፡፡ሆኖም ካፒታል ከነዳጅ ድርጅት ምንጮች ያገኘችው መረጃ እንደሚያመለክተው ምርቱን ምናልባት ኩሁለት ወራት በኋላ በአዲስ አሰራር ማለትም በጥሬ ገንዘብ እንደሚያቀርብ ተነግሯቸዋል፡፡ስለጉዳዩ ካፒታል ያናገረቻቸው አቶ ታደሰ ሃይለማርያም፣ የነዳጅ አቅራቢ ድርጅቱ ዋና ስራ አስፈጻሚ፣ አዲሱ አሰራር የሳቸውን ተቋም የማይመለከት ይልቁንም ከታሪፍ እና የነዳጅ ንግድ ጋር በተያያዘ ሃላፊነት ያለበት በንግድ እና ኢንደስትሪ ሚኒስቴር የሚከናወን ነው ብለዋል፡፡

መንግስት ምርቱን በቀጥታ ክፍያ ለማድረግ የወሰነበት አንደኛው ምክንያት አንዳንድ የነዳጅ ድርጅቶች በዱቤ ለወሰዱት ምርት በወቅት ሂሳብ ያለማወራረድ አዝማሚያ በማሳየታቸው እና ብሩን ለማስመለስ አታካች ወደ ሆነ ተጨማሪ የስራ ጫና መፍጠራቸው ነው፡፡አቶ ታደሰም ይህንኑ ሃሳብ ይጋራሉ፡፡ለካፒታል እንዳሉት በተለይ በቅርብ አመታት የመጡት የነዳጅ ኩባንያዎች እዳን በወቅቱ የመክፈል ችግር ይታይባቸዋል፡፡እስከ 13 የሚጠጉ ዋና ዋና እና በርካታውን የገበያ ድርሻ የያዙት ኩባንያዎች እዳቸውን በወቅቱ ይከፍላሉ ያሉት አቶ ታደሰ አዲሱ አሰራር ተግባራዊ መሆን ድርጅታቸውን የፋይናንስ አቅም የተረጋጋ ከማድረግ ባለፈ ሂሳብ ለማስመለስ ያለውን ውጣ ውረድ ያቀለዋል ብለዋል፡፡

ምንጮች ለካፒታል እደተናገሩት አዲሱ አሰራር ተግባራዊ መደረግ በሚጀምርበት የመጀመሪያዎቹ ጊዜያት ኩባንያዎች የተወሰነውን የገንዘብ መጠን በጥሬ ገንዘብ ቀሪውን በባንክ ዋስትና በማስያዝ ምርቱን ያገኛሉ በሂደት ግን ሙሉ ለሙሉ በጥሬ ገንዘብ ክፍያ የሚደረግ ይሆናል፡፡አዲሱ አሰራር ኩባንያዎቹ ገንዘብ እንደ ብድር እና የአገልግሎት ክፍያ (ለእንደ ባንክ ዋስትና ያሉ) ፈፅመው የሚያመጡት እንደሚሆን ታሳቢ ተደርጎ በተወሰነ መልኩ የሚኖርባቸውን ተጨማሪ ወጪ ለመሸፈን የታሪፍ ለውጥ ሊኖር እንደሚችል በባለሞያዎች ተገምቷል፡፡ምንጮች አዲሱ አሰራር ምናልባት በቀጣዩ ሚያዝያ ወር ወደ የመጀመሪያው የትግበራ ምእራፍ እንደሚሸጋገር ገምተዋል፡፡

Via Capital
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከሁለት አመታት በፊት መተግበር የጀመረው የታሪፍ ማስተካከያ ተቋሙ ብድር ማግኘት እዲያስችል አድርጎታል አሉ፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የታሪፍ ማስተካከያው ለአገልግሎት ጥራት፣ እድሳት እና አዳዲስ ማሰፋፊያ ፕሮጀክቶች ስራ በከፍተኛ ሁኔታ እያገዘኝ ነው አለ፡፡ለሁለት አመት በአራት ምእራፎች መተግበር የጀመረው የታሪፍ ማስተካከያ አገልግሎት ሰጪው በቂ የፋይናንስ አቅም እዲፈጠርለት ማድረጉን አስታውቋል፡፡የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሽፈራው ተሊላ ለካፒታል እንደተናገሩት ቀደም ባሉት ጊዜያት የነበረው ታሪፍ ተቋሙን ከስራ ማስኬጃ ስራ ባለፈ የማያላውስ ሁኔታ ውስጥ ከቶት ነበር ብለው፤ ሆኖም ከታህሳስ 2011 ዓ/ም ወዲህ መተግበር የጀመረው የታሪፍ ማሻሻያ ተቋሙን በርካታ ስራዎችን ማከናወን የሚያስችል አቅም ፈጥሮለታል ብለዋል፡፡ቀደም ሲል በነበረብን የገንዘብ ችግር አበዳሪዎች ገንዘብ ሊያቀርቡልን ፍላጎት አልነበራቸውም በዚህም የመብራት መቆራረጥ እና ሌሎች ተያያዥ የአገልግሎት ማሻሻያዎችን እና እድሳቶችን ለማድረግ ተቸግረን ነበር ብለው፤ “ከታሪፍ ለውጡ ወዲህ የፋይናንስ ቁመናችን በመሻሻሉ ብድሮችን ማግኘት እና ፕሮጀክቶችን ማስተዳደር ጀምረናል፣” ሲሉ አክለዋል አቶ ሽፈራው፡፡

[Capital]
@YeneTube @FikerAssefa
በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በህጋዊነት የተመዘገቡ ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ መወዳደሪያ ምልክቶቻቸውን መውሰዳቸውን ቦርዱ አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 6ተኛው አገር አቀፍ ምርጫን ለማከናወን በጊዜ ሰሌዳው ላይ ካስቀመጣቸው ተግባራት መካከል አንደኛው የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ምልክቶቻቸውን የሚመርጡበት/ የሚያስገቡበት መርሃ ግብር ነው።

በጊዜ ሰሌዳው መሰረት ከጥር 13 ቀን እስከ ጥር 24 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ፓርቲዎች ምልክት የሚያስገቡበት እና ቦርዱ አጣርቶ የሚያፀድቅበት እንደሆነ ይታወሳል።

በዚህም መሰረት ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ መወዳደሪያ ምልክቶቻቸውን የመረጡ ሲሆን በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ፀድቋል። በዚህም መሰረት የፖለቲካ ፓርቲዎቹ እና ምልክቶቻቸው የሚከተሉት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ገልጿል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa