YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#በአሰላ ከተማ ሰሞኑን ተፈጥሮ የነበረው አለመግባባት በእርቅ #መፈታቱ ተገለፀ።

በአሰላ ከተማ ባሳለፍነው ሳምንት ከሀይማኖት ጋር በተያያዘ ተፈጥሮ የነበረው አለመግባባት ነው በዛሬው እለት በእረቅ የተፈታው።

በዚህ ተግባር ላይ ተሳትፈው የነበሩ አካላትም በሀግ ቁጥጥር የዋሉ ሲሆን፥ ችግሩም በዛሬው እለት በተደረገ ውይይት በእረቅ መፈታቱን የኦዲፒ ማእከላዊ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

በዛሬው እለተ የአሰላ ከተማ ወጣቶች ተወካዮች፣ አባ ገዳዎች፣ የሀይማኖት አባቶች እና ሌሎች የህብረተሰቡ ተወካዮችን እንዲሁም የአሰላ ከተማ ከንቲባ ወይዘሮ ዘይነባ አደም በተገኙበት ውይይት ተደርጓል።

በውይይቱ ላይም የአርሲ ዩኒቨርሲቲ የአካባቢው ማህበረሰብ አብሮነትን የሚያሳይ ጥናታዊ ጽሁፍ አቅርቦ ውየይት ተደርጎበታል።

በመካከላቸው አለመግባባት ተፈጥሮ የነበሩ አካላትም ይህ ችግር እንዲፈጠር ያደረጉትን በማጋለጥ በዛሬው የውይይት መድረክ ላይ እርቅ መፈፀማቸው ተነግሯል።
©fbc
@yenetube @mycase27
25 #ስለታማ መሳሪያዎችን ይዞ ሲንቀሳቀስ የነበረው ግለሰብ #በአሰላ ከተማ ተያዘ።

16 ሳንጃ እና 9 ጩቤ ይዞ የተገኘው ይህ ግለሰብ በቁጥጥር ስር የዋለው ትላንት ከቀኑ 6 ሰዓት አካባቢ በአሰላ መናኸሪያ ውስጥ መሆኑን #ሰምተናል

መረጃውን የነገሩን የአርሲ ዞን ፖሊስ ኢንስፔክተር #አበበ ወልዴ ነዋሪዎች አጠራጣሪ ነገሮች ስትመለከቱ ለፖሊስ በአፋጣኝ ጥቆማ ስጡ ብለዋል፡፡

©Sheger fm
@yenetube @mycase27
#በአሰላ ከተማ ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የድጋፍ ሰልፍ እየተከናወነ ይገኛል!!

"ዶክተር አብይን ለመደገፍ የምንሳሳለት ነፍስም ሆነ ሀብት የለም!" የሚል መፈክር በሰልፉ ላይ ታይቷል።

አሰላ
@Yenetube @Fikerassefa