በአንዳንድ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የትምህርት ጥራት መጓደል አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴርና የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ ገለጹ፡፡
ተቋማቱ ይህንን ያሉት ከግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር በትምህርት ጥራት ላይ ተወያይተዋል።
በውይይቱ እንደተመላከተው ተቋማቱ ባለፉት ዓመታት በቁጥር ደረጃ ቢጨምሩም፤ ጥራትና አግባብነት ላይ ውስንነት ይታይባቸዋል።
ከከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት አጀንሲ የተገኘው መረጃ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ቁጥር 278 መድረሱን ያሳያል።
የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አንዱዓለም አድማሴ እንደተናገሩት በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚሰጠው ትምህርት የጥራት መጓደል አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል።
“አንዳንድ ተቋማት ከ10ኛ ክፍል ላቋረጡ ተማሪዎች ዲግሪ ይሰጣሉ፤ ማንበብና መጻፍ የማይችሉ ሰዎችም እንዲሁ ወረቀት እየወሰዱ ነው” ብለዋል ዋና ዳይሬክተሩ።
መቁረጫ ነጥብ ሳያሟሉ ትምህርታቸውን የሚከታተሉ መኖራቸው መረጋገጡን ያነሱት ዶክተር አንዱዓለም እውቅና ሳይሰጣቸው እንደሚያስተምሩና ከተፈቀደው ተማሪ ቁጥር በላይ እንደሚመዘግቡም ተናግረዋል።
ችግሮች እርምጃ በመውሰድ ብቻ ስለማይፈቱ ተቀራርቦ በመስራትና በመደጋገፍ ለማስተካከል መስራት ይገባል ብለዋል።
ዶክተር አንዱዓለም ተቋማቱ ከሕገወጥ እንቅስቃሴ ተቆጥበው ወደ ትክክለኛው መስመር መግባት እንደሚኖርባቸው አስገንዝበዋል።
ከዚህ በኋላ እውቅና የሚሰጣቸው ተቋማት ተመዝነው የጥራት መስፈርት የሚያሟሉበት ስርዓት እንደሚዘረጋ አስታውቀዋል።
Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa

የሩሲያ ሴናተር ነገ ኢትዮጵያ ይገባሉ!
የሩስያ ፌዴሬሽን ሴናተር አንድሬ ኤ ክሊሞቭ ለሶስት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት ነገ አዲስ አበባ ይገባሉ፡፡ የከፍተኛ ሴናተሩ ጉብኝትም ሩሲያ ከኢትዮጵያ እና ከሌሎች የአፍሪካ አገራት ጋር የፖለቲካ ትብብርን ለማጠናከር የሚረዳ ነው፡፡የሴናተሩ ጉብኝት ከኢትዮጵያ ጋር ብቻ ሳይሆን ከሌሎች የአፍሪካ መንግስታት የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ጠንካራ ግንኙነት ለመፍጠር የሚያስችል መድረክ የሚፈጥር መሆኑን በኢትዮጵያ የሩሲያ ኤንበሲ አስታውቋል። ኢትዮጵያ እና ሩሲያ ባለፉት ጥቂት ዓመታት በተለያዩ ደረጃዎች ከፍተኛ የሆነ የፖለቲካ ግንኙነት እንዳላቸውም ኤንባሲው ገልጿል፡፡የሴናተሩ ጉብኝት ዓላማም በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር የታሰበ እንደሆነ ኢምባሲው ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት አስታውቋል፡፡

ከዩኒቨርሲቲ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚደረግ የተማሪዎች ዝውውር በጊዜያዊነት ታገደ!
የተማሪዎች ከመንግሥት ዩኒቨርሲቲ ወደ ሌላ ዩኒቨርሲቲ የሚያደርጉት ዝውውር በጊዜያዊነት መታገዱን የሳይንስ እና ከፍተኛ የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።ዝውውሩ በጊዜያዊነት የተቋረጠው የየዩኒቨርሲቲዎቹ አከዳሚክ ካላንዳር በመዛባቱ እንደሆነ የሳይንስና ከፍተኛ የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ሳሙኤል በተለይ ለኢቲቪ ተናግረዋል።ሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርት አሰጣጥ እኩል እንዳልነበረ የገለጹት አቶ ደሳለኝ፣ በኮቪድ-19 ስርጭት ምክንያት ዩኒቨርሲቲዎች ባለፈው ዓመት የተቆራረጠ ትምህርት ሲሰጡ ነበር ብለዋል።ከሁለት ዓመታት በፊት በዩኒቨርሲቲዎች ይከሰቱ በነበሩ አለመረጋጋቶች ከተቋም ተቋም የአከዳሚክ ካላንዳር እንዲዛባ ማድረጋቸውንም ነው የተናገሩት።
በእነዚህ ክስተቶች ምክንያት ዩኒቨርሲቲዎች ዘንድሮ ተማሪዎችን ያስመረቁበት እና የጠሩበት ጊዜ የተለመደውን መደበኛ የአዳሚክ ካላንደር እንዳዛባ ገልጸዋል።ይህን ለማስተካካል ሲባል የተማሪዎች ከዩኒቨርሲቲ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚያደርጉት ዝውውር በጊዜያዊነት ታግዷል ተብሏል።ይሁን እንጂ ተማሪዎች ከፍተኛ ችግር ካጋጠማቸው ለአብነትም የቤተሰብ፣ ማኅበራዊ፣ የጤና ችግር ካጋጠማቸው እና አስገዳጅ ሁኔታ ካለ በሸኚው እና በተቀባዩ ተቋም ተማሪውን ማስተናገድ የሚችልበት ሁኔታ ካለ ዝውውሩ ሊፈቀድ እንደሚችል ተጠቁሟል።
እያንዳንዱ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም የተዛባውን የራሱን የአካዳሚክ ካላንደር ለማስተካከል እና ወደ መደበኛ ትምህርት ለመግባት ጥረት እያደረገ መሆኑንም አቶ ደሳለኝ ገልጸዋል።አንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች ኮርስ ጀምረዋል፤ እንዳንዶቹ ኮርስ ጨርሰዋል፤ አንዳንዶቹ ደግሞ አልጀመሩም ያሉት ኃላፊው፣ ተማሪዎች የሚወሰዱትን ኮርስ በትክክል ማጠናቃቀቻውን ማረጋገጥ እንደሚገባ ገልጸዋል።እንደ አቶ ደሳለኝ ገለጻ፣ አሁን የወጣው ጊዜያዊው የዝውውር መመሪያ ዩኒቨርሲቲዎች የትምህርት አቀባበል ካላንደር ሥርዓት እስከሚይዝ ድረስ ላልተወሰነ ጊዜ ይቆያል።
[EBC]

አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ለ2ኛ ዙር ዝግጅት 28 ተጫዋቶችን ጠሩ!
ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾች የካቲት 1 ቀን 2013 ዓ.ም ጽህፈት ቤት ሪፖርት እንዲያደርጉ ተብሏል፡፡ ብሔራዊ ቡድኑ ከየካቲት 1 እስከ 6 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ልምምድ እንደሚያደርግ ተገልጿል፡፡
@YeneTube @FikerAssefa
ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾች የካቲት 1 ቀን 2013 ዓ.ም ጽህፈት ቤት ሪፖርት እንዲያደርጉ ተብሏል፡፡ ብሔራዊ ቡድኑ ከየካቲት 1 እስከ 6 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ልምምድ እንደሚያደርግ ተገልጿል፡፡
@YeneTube @FikerAssefa
ባለፉት ስድስት ወራት በአዲስ አበባ ከተማ 110 የእሳት አደጋዎች መድረሳቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
በአደጋውም የአምስት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ከ157 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን ነው ኮሚሽኑ የገለጸው፡፡ ከደረሱት አደጋዎች መካከል 24ቱ በንግድ ተቋማትና በልዩ ልዩ ድርጅቶች የደረሱ ናቸው ተብሏል፡፡የኤሌክትሪክ መስመሮችን በአግባቡ አለመዘርጋት እና የኤሌክትሪክ ኃይልን በጥንቃቄ አለመጠቀም፣ በቀላሉ በእሳት ሊቀጣጠሉ የሚችሉ ቁሳቁሶችንና ተቀጣጣይ ነገሮች እሳት በቀላሉ በሚያገኛቸው ቦታዎች ማስቀመጥ፣ የቡታጋዝ እንዲሁም የሲሊንደር ፍንዳታዎች የቃጠሎው መንስኤ መሆናቸውን በፎረንሲክ ምርመራ መረጋገጡን ኮሚሽኑ ገልጿል፡፡
የአብዛኞቹ የአደጋዎች መንስኤዎች በቸልተኝነት ያጋጠሙ መሆኑን በተለይ ደግሞ ለልዩ ልዩ ጉዳዮች ሻማ ለኮሶ መርሳት እንዲሁም ሰዎች በኤሌክትሪክ ኃይል የሚሰሩ መሳሪያዎችን ሲጠቀሙ ቆይተው በድንገት የኤሌክትሪክ ኃይል ሲቋረጥ ሳያጠፉ ባሉበት ጥሎ በመሄድ የኤሌክትሪ ኃይል ሲመጣ እቃዎቹ ግለው የእሳት አደጋ እንዲከሰት ምክንያት እንደሆኑ በምርመራው ውጤት ተረጋግጧል፡፡
በቅርቡ በኮልፌ እፎይታ የገበያ ማእከል እና በጉለሌ የዕፅዋት ማእከልም የእሳት አደጋ ማጋጠሙ ይታወቃል፡፡የንግድ ማእከሉ የአደጋ መንስኤ እየተጠራ እንደሆነና በጉለሌ የዕፅዋት ማእከል የደረሰውን አደጋን በተመለከተ ዛፍ ቆርጦ ለማስጫን ጨረታ ያሸነፈው ግለሰብ ስራውን እንዲሰሩለት የቀጠራቸው ሰራተኞች ምግብ ለማዘጋጀት ባቀጣጠሉት እሳት አደጋው መድረሱን በታክቲክ ምርመራ መረጋገጡን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
[AMN]

አብን ለዶ/ር አብይ ድጋፍ በኦሮሚያ ክልል በተካሄደው ሰልፍ ስሜ ከሽብርተኛ ድርጅቶች ጋር በአመራሮች ተጠቅሷል ሲል የኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲን ከሰሰ፡፡
ፓርቲው በዛሬው እለት በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል ከተሞች ዶ/ር አብይን ለመደገፍ ፅንፈኞችን ለማውገዝ በሚል በተጠራ ሰልፍ ላይ በሰበታ ከተማ ከንቲባና በከተማዋ የብልፅግና ፓርቲ ኃላፊ የአብንን ስም የዘር ፍጅት ላይ ከተሰማሩ የኦሮሞ ሽብርተኛ ቡድን ጋር በማጣመር ፈርጀውናል ለዚህም ይቅርታ ሊጠየቅ ይገባል ብሏል፡፡

#ንጉስ_ሀበሻ የተባሉ የዩቲዩብ ቻናል የዩቲዩብ ቻናሉን ቀድመው ሰብስክራይብ ላደረጉ 60 ሰዎች የካርድ ስጦታ እሰጣለው ብሏል። ካርዱን ተቀብለናል እኛ ነን የምንልክላችሁ።
1) መስፈርት ሰብስክራይብ ማድረጎን የሚገልፅ Screenshot መላክ ብቻ ነው።
2) Screenshot @Negushabesha ላይ ይላኩ
ይጫወቱ ያሸንፉ!!
GO Subscriber ⬇️
https://youtube.com/channel/UCQWeCEGxtGhXSX3Aug6pk4g?sub_comfirmation=1

ለአሸናፊዎች ሽልማት መላክ ተጀምራል !

በማይካድራ ሳምሪ በተሰኙ የተደራጁ ወጣቶች የተፈጸመው የጅምላ ጭፍጨፋ ቦኮሀራም ናይጄሪያ ላይ በተመሳሳይ ወር ከፈፀመው ወንጀል የበለጠ እንደሆነ ኢንተርፖል አስታወቀ።
ዓለም አቀፉ የፖሊስ ትብብር ተቋም ኢንተርፖል በፈረንጆቹ የዘመን አቆጣጠር በወርሃ ህዳር 2020 ዓ.ም በመላው ዓለም የተፈፀሙ 10 አስከፊ የሽብር ጥቃት አስመልክቶ ሪፖርቱን አውጥቷል።
እንደዚህ ሪፖርት ከሆነ በህወሃት ቡድን አደራጅነት ማይካድራ ላይ የተፈፀመው የጅምላ ግድያ ቦኮሃራምና ሌሎች የሽብር ቡድኖች በተለያዩ ሀገራት ከፈፀሟቸው አሰቃቂ ጭፍጨፋዎች በመብለጥ በርካታ ንፁሃን ሰዎች ህይወታቸውን ያጡበት ኢሰብዓዊ ድርጊት ነው፡፡
የህወሃት ቡድን አስታጥቆ እንዳሰማራቸው በተገለጸው ሳምሪ የተሰኙ የወጣቶች የጥቃት ቡድን በማይካድራ በፈፀሙት ማንነትን መሰረት ያደረገ የጅምላ ጭፍጨፋ 600 ንፁሃን ዜጎች መገደላቸውን በኢንተርፖል የሽብር ወንጀል መከላከል ዳይሬክቶሬት ያወጣው መረጃ ያሳያል።
ከሶስት ወራት በፊት በህዳር ወር ላይ ብቻ በተፈፀሙ የሽብር ወንጀሎች አፍሪካ ቀዳሚ ስፍራ ላይ መቀመጧን የጠቀሰው የኢንተርፖል መረጃ ንፁሃን ላይ ባነጣጠሩ የጅምላ ግድያ ወንጀሎች በርካታ ህይወት መቀጠፉን አስገንዝቧል።
የሽብር ቡድኖቹ ከሰብዓዊ ፍጡር በማይጠበቅ መልኩ ጭካኔ የተሞላባቸውን የጅምላ ጭፍጨፋዎች መፈፃማቸው የተገለፀ ሲሆን ከአፍሪካ በመቀጠል ደቡባዊ የእስያ አካባቢና ምስራቃዊ የሜዲትራኒያን ቀጠና የዚህ ሽብር ወንጀል ሰለባ መሆናቸው ተጠቁሟል።
ባለፈው የፈረንጆች ዓመት ወርሃ ህዳር ላይ ብቻ በተፈፀሙና በርካቶች በአሰቃቂ ሁኔታ ህይወታቸውን ባጡባቸው የሽብር ወንጀል ድርጊቶች ላይ ትኩረቱን ያደረገው የኢንተርፖል መረጃ በኢትዮጵያ ማይካድራ ላይ የተፈፀመው የጅምላ ጭፍጨፋና ናይጄሪያ ውስጥ ሜይጉዱሩ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ቦኮሃራም ያካሄደው ግድያ በሰብዓዊነት ላይ ከተፈፀሙ ከባድ የሽብር ወንጀሎች ቀዳሚ ተርታ ላይ መሰለፋቸውን ያሳያል።
የተለያዩ ኢሰብዓዊ ዓላማዎችን ይዘው የሚንቀሳቀሱ የሽብር ቡድኖች በንፁሃን ላይ የሚፈፅሟቸው ግድያዎች አሳሳቢ መሆናቸው በመረጃው ተጠቅሷል።
ከሶስት ወራት በፊት የንፁሃንን ህይወት የቀጠፉ የሽብር ወንጀሎች ከተፈፀሙባቸው ሀገራት መካከል ኢትዮጵያን፣ ናይጄሪያን፣ ሞዛምቢክን፣ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎን፣ ሶማሊያን፣ ቡርኪናፋሶንና ቻድን የያዘችውን አፍሪካን በቀዳሚነት ጠቅሷል።
ከሌሎች የአለም ክፍሎች ደግሞ ከደቡብ እስያ አፍጋኒስታን፣ ከምስራቅ ሜዲትራኒያን ሶሪያን እንዲሁም ኢንዶኔዥያንና ኦስትሪያን አካቷል።
የሽብር ቡድኖቹ በእነዚህ ሀገራት በፈፀሟቸው አሰቃቂ የጅምላ ግድያዎች እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በህዳር ወር 2020 ዓ.ም ብቻ አንድ ሺ የሚጠጉ ንፁሃን ዜጎች መገደላቸውን ኢንተርፖል ያወጣው መረጃ ይጠቁማል።
ኢንተርፖል ያሰባሰበው የመረጃው ግኝት እንደሚያሳየው መንግስታዊ ባልሆኑ ታጣቂ ቡድኖች ከተፈፀሙ ጥቃቶች አራቱና በከፍተኛ ሁኔታ የንፁሃንን ህይወት የቀጠፉ የሽብርተኝነት ወንጀሎች በአፍሪካ፣ በደቡብ እስያ (በዋናነት በአፍጋኒስታን) በባህረ ሰላጤ አካባቢ ሀገራት በዋነኝነት በየመንና በምስራቅ ሚዲትራኒያን (በሶሪያ) የተፈፀሙ መሆናቸውንም አመላክቷል።
በኢትዮጵያ ሳምሪ የተሰኙ የህወሃት ቡድን ያደራጃቸው ሃይሎች ማይካድራ ላይ የፈፀሙትና በናይጄሪያ ቦኮሀራም የተፈፀሙት ኢ-ሰብአዊ ጭፍጨፋዎች ከሁሉም የከፋ እልቂት የተመዘገበባቸው የሽብር ወንጀሎች መሆናቸውን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኢንተርፖል የላከለትን መረጃ ዋቢ አድርጎ አድርሶናል፡፡
Via Ethio FM
@Yenetube @Fikerassefa

ኢትዮጵያ ያለ አሳሪ ስምምነት ሕዳሴ ግድብን ውሃ እንዳትሞላ የሱዳን ውሃ ሚንስትር አሲር አባስ እንዳስጠነቀቁ የሱዳኑ ዜና ወኪል ሱና ዘግቧል፡፡ ኢትዮጵያ በመጭው ሐምሌ የግድቡ ሁለተኛ ዙር ውሃ ሙሌት በተናጥል ካከናወነች፣ የታችኛው ተፋሰስ ሀገሮች ሕዝቦች ደኅንነት አደጋ ላይ ይወድቃል ሲሉ አስጠንቅቀዋል አባስ፡፡ ሚንስትሩ ማስጠንቀቂያውን የሰጡት ከአውሮፓ ኅብረት ከፍተኛ ሃላፊዎች ጋር ትናንት በተወያዩበት ወቅት ነው፡፡
@yenetube @Fikerassefa
@yenetube @Fikerassefa
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 477 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ13 ሰዎች ህይወት ደግሞ አልፋል
ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 5,605 የላቦራቶሪ ናሙና ምርመራ 477 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን የጤና ሚኒሰቴር አስታውቋል ።
በአጠቃላይ እስካሁን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 138,861 ደርሷል።
በሌላ በኩል 838 ሰዎች ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ እስካሁን ድረስ 123,806 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

337 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሃገራቸው ተመልሰዋል።
ዛሬ ወደ አገር የተመለሱትን ዜጎች ሁሉም ወንዶች ሲሆኑ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄኔራል ተወካይ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው ለተመላሾቹ አቀባበል አድርገዋል።