YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በአዲስ አበባ በዛሬው እለት በደረሱ ሁለት የእሳት አደጋዎች ከ3.5 ሚሊየን ብር በላይ የተገመተ ንብረት ወደመ!

የመጀመሪያው የእሳት አደጋ በአዲስ አበባ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ልዩ ቦታው መሻለኪያ ቄስ ሰፈር ዛሬ ረፋድ ላይ ደርሷል።መሿለኪያ ቄስ ሰፈር በደረሰው የእሳት አደጋ 3 ሚሊየን አምስት መቶ ሺ ብር የሚያወጣ ንብረት መውደሙን የአዲስ አበባ እሳትና ድንገተኛ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቃል፡፡የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ከፌደራል ፓሊስ፣አዲስ አበባ ፓሊስ እና ከህብረተሰቡ ጋር በመሆን እሳቱን መቆጣጠር የቻለ ሲሆን 30 ሚሊየን ብር የሚያወጣ ንብረት ከውድመት መታደግ መቻሉን በኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ቡድን መሪ አቶ ጉልላት ጌታነህ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል።

አደጋው በሱቆች እና በመኖሪያ ቤት ላይ ውድመት ያደረሰ ሲሆን መነሻ ምክንያቱ ግን በውል አልታወቀም፡፡አደጋውን በቁጥጥር ስር ለማዋል 2 ሰዓት ከ15 ደቂቃ ወስዷል። 109 የእሳት አደጋ ሰራተኞች 24 ተሽከርካሪዎች እና 145 ሺ ሊትር ውሀ ጥቅም ላይ ውሏል፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ የደረሰው ሁለተኛው የእሳት አደጋ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ልዩ ቦታው 93 ቁጥር ማዞሪያ ነው፡፡አደጋው የተነሳው በተለኮሰ ሻማ ምክንያት እንደሆነ ሲገለፅ 50ሺ ብር የሚያወጣ ንብረት ማውደሙን አቶ ጉልላት ጨምረው ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል።የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ባለሙያዎች ባደረጉት ርብርብ 2 ሚሊየን ብር የሚያወጣ ንብረት በእሳት እንዳይወድም ማድርግ ችለዋል፡፡

Via Bisrat FM
@YeneTube @FikerAssefa
የህውሓት አባላት በቁጥጥር ስር ዋሉ፤ እርምጃም ተወሰደባቸው ሲል የመከላከያ ሰራዊት ገለጸ።

የመከላከያ ሀይል ሰምሪት መምሪያ ኃላፊ ብ/ጄኔራል ተስፋዬ አያሌው እንዳረጋገጡት አቶ ተክወይኒ አሰፋ፣ ዶክተር ሰለሞን ኪዳኔ፣ አቶ ገ/መድህን ተወልደ፣ አቶ ወ/ጊዮርጊስ ደስታ፣ አምባሳደር አባዲ ዘሞ፣ ወ/ሮ ቅዱሳን ነጋ፣ አቶ ቴድሮስ ሃጎስ፣ ወ/ሮ ምህረት ተክላይ፣ አቶ አብርሃም አደም መሃመድ በቁጥጥር ስር ውለዋል።አቶ ሴኮ ቱሬ ጌታቸው፣ አቶ ዘርአይ አስገዶም፣ አቶ አበበ ገ/መድህን፣ አቶ ዳንኤል አሰፋ ደግሞ እርምጃ የተወሰደባቸው ናቸው።

(ምንጭ፦ የመከላከያ ሰራዊት)
@YeneTube @FikerAssefa
በሊባኖስ ይኖሩ የነበሩ 91 ዜጎች ወደ ሃገራቸው ተመለሱ።

በሊባኖስ ያለሰነድ ይኖሩ የነበሩ 91 ዜጎችን ቆንስላ ጽህፈት ቤት ጉዳያቸውን ተከታትሎ በሊባኖስ መንግስት በኩል ካስፈጸመ በኋላ ዛሬ ወደ ሃገራቸው በሰላም እንዲመለሱ መደረጉን ከሊባኖስ ቆንስላ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

@YeneTube @FikerAssefa
ኢሎን መስክ የአለም ባለፀጋው ሰው ሆነ!

የቴስላ እና ስፔስ ኤክስ ባለቤት የሆነው ኢሎን መስክ የአለማችን ሀብታሙ ሰው መሆን እንደቻለ ቢቢሲ አስነብቧል። ኢሎን በሀብት የአንደኝነቱን ደረጃ የተቆናጠጠው የአማዞኑን ጄፍ ቤዞስ ከትናንት ጀምሮ በመብለጥ ነው። በአሁኑ ሰዓት የኢሎን አጠቃላይ ሃብት 185 ቢሊየን ዶላር ደርሷል ተብሏል። ለዚህም ያገዘው የኤሌክትሪክ መኪና አምራች ኩባንያው ቴስላ ድርሻው በትናንትናው እለት ከፍተኛ እድገት በማሳየቱ ነው ተብሏል። የቴስላ አጠቃላይ ዋጋ 700 ቢሊየን ዶላር የሚገመት ሲሆን አቻ የመኪና አምራቾች ማለትም ቶዮታ፣ ቮልስዋገን፣ ሃዩንዳይ፣ ጂ ኤም እና ፎርድ ዋጋቸው ተደምሮ የሱን አያህልም።ኢሎን የአለም ባለጠጋው ሰው ከተባለ በኋላ በትዊተር ገፁ 'እንግዳ ነገር' ያለ ሲሆን 'አሁንም ወደ ስራ' የሚል ጽሑፍ አስከትሏል።

@YeneTube @FikerAssefa
በምክር ቤቱ ሕንፃ ጠባቂዎች ላይ ምርመራ እንዲደረግ ተጠይቋል!

ከትላንት በስቲያ የዩናይትድ ስቴትስ ሕግ አውጭዎች ምክር ቤት ሕንጻን በመውረር፣ የተፈጸመውን ድርጊት አስመልከቶ በምክር ቤቱ ሕንጻ ጠባቂ ፖሊሶችና ሕግ አሰከባሪዎች ላይ ምርመራ እንዲደረግ የምክር ቤት አባላት ጠይቀዋል፡፡ሕግ አውጭዎቹ የምክር ቤት አባላት የትናንቱን ሁከት በመቆጣጠር ከፍተኛ ተጋድሎ ይደረጉትን የፖሊስና ሕግ አስከባሪ አካላት አድናቆታቸውን ቢገልጹም ቀድሞውኑም ቢሆን እንዲህ ያለ ነገር እንዴት ሊከሰት እንደቻለ ምርመራ እንዲደረግ ጠይቀዋል፡፡

በተለይም በአዲሱ ሕግ አውጭ ምክር ቤት የምክር ቤቱን ሕንጻና አስተዳደር በጀት ኮሚቴ የሚመሩት ሁለቱ ዴሞክራቶች ፣ድርጊቱን በዝርዝር የሚያመላክቱ ብዙ ቪዲዮች እንዳሉ በመግለጽ “አንዳንዶቹ ጀግንነትን የሚያሳዩ ቢሆንም አንዳንዶቹ ግን አሳሳቢ ናቸው፡፡” ብለዋል፡፡ስለዚህ ሙሉ ምርመራ ተደርጎ የምክር ቤቱ ህንፃ በዚያ ፍጥነት እንዴት ሆኖ ሊወረር እንደቻለ የጥበቃውና የደህንነቱ ሁኔታ እንደገና ሊመረመር ይገባዋል ብለዋል፡፡

“የፕሬዘዳንቱን መሰረት ቢስ ቅሰቀሳ ሰምተው ቀደም ሲል ለተቃውሞ አመጽ የተዘጋጁ ሰዎች መኖራቸው እየታወቀ ለምን በቂ ዝግጅት አልተደረገም?” የሚሉ ጥያቄዎችም የምክር ቤት አባላቱ አንስተዋል፡፡የምክር ቤት አባል የሆኑት ኢላን ኦማር “ለብሄራዊ ደህንነት ጥበቃ በቢሊዮን ዶላሮች እናወጣለን፡፡በዛሬው እለት በአገሪቱ ምክር ቤት ላይ ህገ ወጥ ነውጠኞች ያደጉትን ወረራ ግን ማስቆም አልቻልንም፡፡ ይህ ተቀባይነት የለውም!” ብለዋል፡፡የዩናይትድ ስቴት ምክር ቤት በዓመት ወደ 460 ሚሊዮን በጀት የሚመደብለት ሲሆን ከ2ሺ 300 በላይ ሲቪል ሠራተኞችም እንዳሉት ተነግሯል፡፡

[VoA]
@YeneTube @FikerAssefa
በአንኮበር ወረዳ ጎረጎ ዙሪያ ቀበሌ ከፍተኛ የመሬት መንሸራተት ተከስቷል፡፡

በቀበሌው በርበሬ ውሃ ጎጥ በተባለ ቦታ በተከሰተው የመሬት መንሸራተት ከ32 በላይ አርሶ አደሮች የእርሻ መሬት በከፍተኛ ሁኔታ ተጎድቷል፡፡የጉዳቱን መጠን ለማየትና መፍትሔ ለመስጠት በወረዳው ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ኃላፊና ምክትል አስተዳዳሪ አቶ አዲሱ አስጨናቂ የተመራ የልዑካን ቡድን በቦታው ላይ ታኅሳስ 28/2013 ዓ.ም ተገኝቶ ቅኝትና ውይይት አድርጓል፡፡

በውይይቱም አርሶ አደሮቹ በተፈጠረው ነገር ክፉኛ ማዘናቸውን ገልጸው፣ ችግሩ መሬታቸውን ብቻ ሳይሆን ለሕይወታቸውም በሰቀቀን ተኝተን እየተነሳን ሲሆን አንድ ቀን በዚህች ጎጥ አሳዛኝ ክስተት ሳይፈጠር መንግሥት ለጊዜው ልጆቻችንንና ከብቶቻችንን የምናሰፍርበት ቦታ እንዲሰጠን ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

የወረዳው ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ኃላፊና ምክትል አስተዳዳሪ አቶ አዲሱ አስጨናቂና ባልደረቦቻቸው በሰጡት ምላሽ ችግሩ በወረዳው አቅም የሚፈታ አይደለም ተጨማሪ ጥናትም ይጠይቃል በጊዜያዊነት ግን ከቦታው ተነስታችሁ ወደ ሌላ አካባቢ እንድትሰፍሩ ቦታ እናመቻቻለን፤ ቦታውም እስኪመቻች በአፋጣኝ ለቃችሁ በአቅራቢያ ወዳሉ ከተሞች ቤት ተከራይታቸሁ ልጆቻችሁን ከጥፋት ታደጉ፣ ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ከሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ጋር እንነጋገራለን ማለታቸውን የወረዳው ኮሙኒኬሽን ቢሮ ዘግቧል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የክሪፕቶ ከረንሲ ዋጋ ከ1 ትሪሊየን ዶላር መብለጡ ተነገረ!

ክሪፕቶ ከረንሲ ባሳለፍነው አስር አመታት አለም እንደ አዲስ የተዋወቀችው የመገበያያ አይነት ነው። ከክሪፕቶ መገበያያ አይነቶች ትልቅ ዋጋ ያለው ደግሞ ቢትኮይን ነው። የቢትኮይን ዋጋ በተለያዩ ጊዜያት ከፍና ዝቅ እያለ የቆየ ቢሆንም ትናንት(ሐሙስ) ከሰዓት የ1 ቢትኮይን ዋጋ 39,000 የአሜሪካን ዶላር በመድረስ የምን ጊዜም ከፍተኛ ዋጋውን አስመዝግቧል። ይህንንም ተከትሎ የቢትኮይንና መሰል የክሪፕቶ መገበያያዎች ድምር ዋጋ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ 1.05 ትሪሊዮን ዶላር ደርሷል። ከዚህ ውስጥ ቢትኮይን የአንበሳውን ድርሻ የሚወስድ ሲሆን 69 በመቶ የሚሆነው የተያዘው በዚሁ ገንዘብ አይነት ነው። ከሱ በመቀጠል ኢቴሪየምና ቢትኮይን ካሽ በረዥም ርቀት ይከተሉታል።መረጃውን ያገኘነው ከኮይን ማርኬት ካፕ ድረገፅ ነው።

@YeneTube @FikerAssefa
የመንግስት ባለስልጣናት አርአያ አለመሆን ለኮሮና ቫይረስ ስርጭት መባባስ አስተዋጾ እያደረገ ነው ተባለ!

በኢትዮጵያ በርካታ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎችና ባለስልጣናት የኮሮና ቫይረስ መከላከያ መመሪያ የሚባሉትን አፍና አፍንጫን መሸፈንን ጨምሮ ርቀትን በመጠበቅ ረገድ አርአያ መሆን እንደተሳናቸው የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።በፌደራልና በክልል ደረጃ የሚገኙ የስራ ሀላፊዎች በመገናኛ ብዙሃን ላይ ሲቀርቡ እንኳን እነዚህን መመሪያዎች በተደጋጋሚ እንደሚጥሱ በጤና ሚኒስቴር የኮቪድ 19 ግብረ ሀይል ሀላፊ ዶ/ር ሊሻን አድማሱ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል።

መመሪያዎቹን በማክበር ባለስልጣናቱ ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ ዶ/ር ሊሻን ጥሪ አቅርበዋል።የኮሮና ቫይረስ በከፍተኛ ፍጥነት በኢትዮጲያ መሰራጨቱ የቀጠለ ሲሆን ከሚመረመሩ ሰዎች መካከል አሁንም 10 በመቶ ያህሉ በቫይረሱ መጠቃታቸውን ማረጋገጥ ተችሏል።የትምህርት ቤቶች በድጋሚ መከፈት ለቫይረሱ መስፋፋት አስተዋጾ እያደረገ ይገኛል።

[Bisrat FM]
@YeneTube @FikerAssefa
የሱዳን ሉዓላዊ የሽግግር ም/ቤት ም/ሊቀመንበር ኤርትራ ገብተዋል!

የሱዳን ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት ምክትል ሊቀመንበር መሐመድ ሃምዳን ዳጋሎ አስመራ መግባታቸውን የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ሚኒስትሩ አቶ የማነ ገብረመስቀል በትዊተር ገጻቸው እንዳሉት በመሐመድ ሃምዳን ዳጋሎ የተመራ ልዑክ አባላት ዛሬ አስመራ ገብተው ከፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር እየተወያዩ ነው፡፡አቶ የማነ ጉብኝቱ የኤርትራና የሱዳን የሁለትዮሽ ግንኙነት ዙሪያ በከፍተኛ የሀገራቱ ባለሥልጣናት መካከል የሚደረገው ምክክር አካል ነው ብለዋል።

[Al ain]
@YeneTube @FikerAssefa
በትግራይ ክልል ባሉ ክለቦች ሲጫወቱ ለነበሩ ተጫዋቾች የተፈቀደው ልዩ የዝውውር ጊዜ ተራዘመ!

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በትግራይ ክልል ባሉ ክለቦች ሲጫወቱ ለነበሩ ተጫዋቾች የፈቀደው ልዩ የዝውውር ጊዜ እስከ ጥር 3 ቀን 2013 ተራዝሟል።ዝውውሩ በክልሉ በነበረው ሰላም የማስከበር ሥራ ምክንያት በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ የነበሩ መሆኑን ታሳቢ በማድረግ ከታኅሣሥ 26-30 ቀን 2013 ዓ.ም ለአምስት የሥራ ቀናት የተፈቀደ ነበር።ፌዴሬሽኑ ባወጣው መረጃ የማራዘሚያ ቀናት የተሰጠው ታኅሣሥ 29 የገና በዓል በመሆኑ የተነሣ መሆኑን አሳውቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
በገና እለት የሁለት ሰዎችን ህይወት በማጥፋት የተሰወረው ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ዋለ!

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ደብረ ብርሃን ከተማ ቀበሌ 06 ያሬድ ጁስ ቤት ውስጥ ታህሳስ 29 ቀን 2013 ዓ.ም ከምሽቱ 3፡30 አካባቢ ለጊዜው ምክንያቱ ባልታወቀ መንስኤ የሁለት ሰዎችን ህይወት የቀጠፈውና ሌሎች ሁለት ሰዎችን በማቁሰል ተሰውሮ የነበረው ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገለጸ፡፡በደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር 3ኛ ፖሊስ ጣቢያ የታክቲክ ወንጀል ምርመራ ክፍል ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ደረጀ ነጋ እንደገለፁት ፣ ተጠርጣሪው አንድ የዩኒቨርሲቲ ተማሪ እና አንድ አስተናጋጅ ገድሎ እንዲሁም ሌሎች ሁለት ሰዎችን አቁስሎ ተሰውሮ ነበር፡፡ይሁን እንጅ የወጋገን ባንክ ጥበቃ ሰራተኛ የሆነው ተጠርጣሪ በፖሊስ ክትትል ከተደበቀበት ቦታ አንድ ክላሽንኮቭ ጠብመንጃ ከ18 ጥይት ጋር እንደያዘ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራው እየተጣራ ይገኛል ብለዋል፡፡ሁለቱ ተጎጂዎች ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

Via Bisrat FM
@YeneTube @FikerAssefa
በጅማ ከተማ በደረሰ የእሳት አደጋ 6 ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት መውደሙን ፖሊስ አስታወቀ።

የከተማው ፖሊስ መምሪያ የወረዳ ሁለት ጽህፈት ቤት ዋና አዛዥ ኮማንደር ካሊድ አባ ተማም ለኢዜአ እንደገለጹት አደጋው የደረሰው ዛሬ ንጋት አካባቢ 11 ሰዓት ከ30 ደቂቃ ላይ ነው።በከተማው በቦቾ ቦሬ ቀበሌ መናኸሪያ አካባቢ በሚገኝ አንድ የእንጨት ስራ ወጤቶች ማምረቻና መሸጫ የግል ድርጅት ላይ አደጋው መድረሱን ተናግረዋል።በአደጋው በድርጅቱ ተመርተው ለገበያ የተዘጋጁ ዘመናዊ የእንጨት ስራ ውጤቶች ሙሉ ለሙሉ መውደማቸውን አመልክተዋል።“የወደመው ንብረት 6 ሚሊዮን ብር ግምት አለው” ያሉት ኮማንደር ካሊድ በአደጋው በሰዎች ላይ የደረሰ ጉዳት አለመኖሩን ተናግረዋል።በአካባቢው ነዋሪዎች፣ በጸጥታ አካላትና በእሳት አደጋ መከላከያ ሰራተኞች ትብብር በተደረገ ጥረት ቃጠሎው ወደ ሌሎች የንግድ ተቋማት ሳይዛመት በቁጥጥር ስር መዋሉን ተናግረዋል።
እንደ ኮማንደር ካሊድ ገለጻ የአደጋው መንስኤ እየተጣራ ነው።

Via ENA
@YeneTube @FikerAssefa
ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የድንበር ውዝግብ በሰላም መፍታት እንዳለባት የደቡብ ሱዳኑ ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር ማያርዲት ጠየቁ!

ፕሬዚዳንት ኪር የሱዳን ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት አባል የሆኑትን ቼምስ አል ዲን ካባሽ እና ተጠባባቂ የሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦመር ጋማር ኢልዲንን በጁባ አነጋግረዋል፡፡ ተጠባባቂ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በኢትዮ ሱዳን ድንበር ከሰሞኑ የተፈጠረውን ሁኔታ ለፕሬዚዳንት ኪር ገልጸዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ኪር ካርቱምና አዲስ አበባ የድንበር እሰጥ አገባውን በድርድርና በሰላማዊ መንገድ ብቻ መፍታት እንዳለባቸው ጁባ ለተገኙት የሱዳን ባለሥልጣናት መግለጻቸውን ሱዳን ትሪቡን ዘግቧል፡፡

[Al-ain]
@YeneTube @FikerAssefa
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 94ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

#PMOEthiopia
@YeneTube @FikerAssefa
በ66 ቁልፎች ወንጀል የሰራው ግለሰብ እስራት ተፈረደበት!

በጅማ ከተማ ሸቤ ሶምቦ ወረዳ 66 ቁልፎችን አመሳስሎ በመቅረፅ በዝርፊያ በወንጀል የተሰማራ ግለሰብ በሁለት ዓመት እስራት መቀጣቱን የወረዳው ፍርድቤት አስታውቋል፡፡

ግለሰቡ በወረዳው የሚገኙ ዘጠኝ የመንግስት መስሪያቤቶችን አመሳስሎ በሰራው ቁልፍ እየከፈፈተ ሲዘርፍ እንደነበር የሸቤ ሶምቦ ወረዳ ኮሚኒውኬሽን ለአዲስ ዘይቤ አሳውቋል፡፡

የወንጀሉ ኢላማ የነበሩ መስሪያ ቤቶችም፡ የወረዳው ትምህርት ጽ/ቤት፣ ኮሚኒውኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት፣ ቴክኒክና ሙያ ጽ/ቤት፣ የሥራ እድል ፈጠራ ጽ/ቤት፣ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት፣ ስፖርት ጽ/ቤት፣ አፈጉባኤ ጽ/ቤት፣ መሬት ጥበቃ ጽ/ቤትና ሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ጽ/ቤት መሆናቸውን አክሏል፡፡

[@addiszeybe]
@YeneTube @FikerAssefa
ሰበር ዜና!

የህወሓት መሪ የሆኑት አቶ ስብሃት ነጋ በቁጥጥር ስር ዋሉ።

የህወሓት መሪ ስብሃት ነጋን ጨምሮ ሌሎች የቡድኑ አመራሮች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የሀገር መከላከያ ሰራዊት ገለፀ።

በዚሁ መሠረት በቁጥጥር ስር የዋሉት፣

1. የጁንታው ቁንጮ አመራር አቶ ስብሐት ነጋ

2. ሌተናል ኮሎኔል ፀአዱ ሪች- የስብሐት ነጋ ባለቤት እና ቀደም ሲል በጦር ኃይሎች ሆስፒታል ሐኪም የነበረች በኋላም በጡረታ የተገለለች

3. ኮሎኔል ክንፈ ታደሰ-ከመከላከያ የከዳ

4. ኮሎኔል የማነ ካህሣይ-ከመከላከያ የከዳ

5. አስገደ ገ/ክርስቶስ-ከመሀል ሀገር ተጉዞ ቡድኑን የተቀላቀለ እና ለጊዜው ሓላፊነቱ ያልታወቀ ግለሰብ በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን፣

6. የሜጀር ጀነራል ኃየሎም አርአያ ባለቤት የነበረች እና ኑሮዋን በአሜሪካ አድርጋ የቆየች በኋላም ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ወደ ህወሓት ተቀላቅላ የነበረችው ወ/ሮ አልጋነሽ መለስ 'ጁንታ'ውን በመያዝ ኦፕሬሽን ሂደት ውስጥ ለማምለጥ ስትሞክር ገደል ውስጥ በመግባት ሕይወቷ ማለፉን ብርጋዴር ጀነራል ተስፋዬ አያሌው ገልጸዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
#NewsAlert

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ6ተኛውን አገር አቀፍ የመጨረሻ የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ይፋ አደረገ!

የድምፅ መስጫ ቀን ግንቦት 28/2013 ዓም እንዲሆን ተወስኗል።

የጊዜ ሰሌዳው ከላይ የቀረበውን ይመስላል።

@YeneTube @FikerAssefa
የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ክለሳ መደረጉን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የዘርፉ ተሳታፊዎች ትርፍ ህዳግ እንዲሻሻል መንግስት በሰጠው ውሳኔ መሰረት የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋን በመከለስ አዲስ ዋጋ መዘጋጀቱን ሚኒስቴሩ ለኢቲቪ በላከው መግለጫ አመልክቷል፡፡

በዚሁ መሰረት በአዲስ አበባ ከጥር 1 እስከ 30 ቀን 2013 ዓ.ም ተግባራዊ የሚደረገው የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ፡-

👉 ቤንዚን በሊትር 23 ብር ከ67 ሳንቲም

👉 ኤታኖል ድብልቅ ቤንዚን በሊትር 23 ብር ከ27 ሳንቲም

👉 ነጭ ናፍጣ በሊትር 21 ብር ከ03 ሳንቲም

👉 ኬሮሲን በሊትር 21 ብር ከ03 ሳንቲም

👉 ቀላል ጥቁር ናፍጣ በሊትር 18 ብር ከ63 ሳንቲም

👉 ከባድ ጥቁር ናፍጣ በሊትር 18 ብር ከ17 ሳንቲም

የአውሮፕላን ነዳጅ በሊትር 32 ብር ከ76 ሳንቲም መሆኑን የንግድና ኢንዱትሪ ሚኒስቴር አስታውቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) በዘንድሮው ሀገር ዐቀፍ እና ክልላዊ ምርጫ የሚያቀርባቸውን ዕጩዎች ከነገ ጀምሮ እንደሚያሳውቅ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡ምርጫ ቦርድ የካቲት 8 የዕጩዎች ምዝገባ እንደሚጀምር ቀደም ሲል ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa