YeneTube
117K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በሊባኖስ ይኖሩ የነበሩ ተጨማሪ 28 ኢትዮጵያውያን ዛሬ መስከረም 8 ቀን 2013 ዓ.ም. ጧት ወደ አገር ቤት ተመልሰዋል፡፡

በአጠቃላይ 148 ኢትዮጵያውያን ዛሬ፣ ትናንትና፣ ባለፉት ቀናት ወደ አገር ቤት ገብተዋል፡፡ተመላሾቹ የጉዞ ሰነዶች ያልነበራቸው ሲሆኑ በቆንስላው በኩል የጉዞ ሰነዶች እና የመውጫ ቪዛ ተሰርቶላቸው የተመለሱ ናቸው፡፡ኢትዮጵያውያኑ በሊባኖስ እስር ቤቶች የነበሩ፣ ሆስፒታል ህክምናቸውን ሲከታተሉ የነበሩ፣ በቤሩት ወደብ ፍንዳታ መጠለያ ያጡና ችግር ላይ የነበሩ፤ እንዲሁም በአሰሪዎች በደልና የመብት ጥሰቶች፣ የአካልና የስነ-ልቦና ጉዳት የደረሰባቸው እና መጠለያና ምግብ ያጡ የነበሩ ናቸው፡፡ ወደ አገራቸው መመለስ የሚፈልጉ ሆኖም ግን ምንም አይነት የጉዞ ሰነዶችና ፓስፖርት የሌላቸውን ኢትዮጵያውያን መመለስ እንዲችሉ የጉዞ ሰነድና የመውጫ ቪዛዎችን እንዲያገኙ የማድረጉን ስራ ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤቱ ትኩረት ሰጥቶ እየተሰራበት ይገኛል፡፡

[Ethiopian Consulate in Beirut]
@YeneTube @FikerAssefa
የጤና ሚኒስትሯ ሊያ ታደሰ (ዶ/ር) አገራዊ ምርጫ ማካሄድ ይቻላል አሉ!

የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረቡት አጭር ሪፖርት
ኮቪድ-19ኝ መከላከልን ከግምት ውስጥ ያስገባ የምርጫ ስነምግባር፣ ደንብና ማስፈፀሚያ መመሪያዎችን በማዘጋጀት ሃገራዊ ምርጫ ማካሄድ ይቻላል ማለታቸውን ኢሳት አስታወቀ፡፡

በዚህ ሂደት ውስጥ አንዳንድ ቦታዎች ላይ ከፍተኛ የሆነ የወረርሽኝ ስርጭት ከተከሰተ በተለየ ሁኔታ መታየት ሊያስፈልገው እንደሚችል ታሳቢ በማድረግ መዘጋጀት እንደሚያስፈልግም ሊያ ባቀረቡት ሪፖርት አመላክተዋል ነው የተባለው።

@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
የጤና ሚኒስትሯ ሊያ ታደሰ (ዶ/ር) አገራዊ ምርጫ ማካሄድ ይቻላል አሉ! የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረቡት አጭር ሪፖርት ኮቪድ-19ኝ መከላከልን ከግምት ውስጥ ያስገባ የምርጫ ስነምግባር፣ ደንብና ማስፈፀሚያ መመሪያዎችን በማዘጋጀት ሃገራዊ ምርጫ ማካሄድ ይቻላል ማለታቸውን ኢሳት አስታወቀ፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥ አንዳንድ ቦታዎች ላይ ከፍተኛ የሆነ የወረርሽኝ ስርጭት…
#NewsAlert

በኮቪድ 19 ምክንያት ተራዝሞ የነበረው ሀገራዊ ምርጫ አሁን ላይ ቅድመ ሁኔታዎችን አሟልቶ ማካሄድ እንደሚቻል የጤና ሚኒስቴር ምከረ ሀሳብ አቀረበ!

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 5ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ አስቸኳይ ስብሰባውን እያካሄደ ይገኛል።የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምላሽና ቀጣይ እርምኝጃዎች በሚመለከት ለምክር ቤቱ ሪፖርት እና ምክረ ሀሳብ ለምክር ቤቱ አቅርበዋል።በቀረበው ሪፖርት እና ምክረ ሀሳብ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ስርጭት እየቀነሰ ባይሆንም የቅድመ መከላከል እና ስርጭቱን በመግታት ሂደት ውስጥ በሁሉም ደረጃ አቅም ማሳደግ መቻሉን ገልፀዋል።

በኢትዮጵያ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ በሁሉም ክልሎች የተሰራጨ ሲሆን፥ በሀገር አቀፍ ደረጃ የኮቪድ 19 በሽታ ከገተኘባቸው ውስጥ 95 በመቶ የታወቀ የጉዞ ታሪክ የሌላቸው መሆኑ ተረጋግጧል ብለዋል።እስከ መስከረም 6 2013 ዓ.ም ድረስ 1 ሚሊየን 165 ሺህ 647 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን፥ በዚህም 66 ሺህ 224 ሰዎች ላይ ቫይረሱ መገኘቱን እና 1 ሺህ 45 ሰዎች በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው ማለፉንም አስታውቀዋል።አሁን ላይ የመመርመርም ሆነ ክትትል የማድረጉ አቅም በማደጉ በነሃሴ ወር ብቻ ከፍተኛ የሚባል ቁጥር ያላቸውን ሰዎች ቤት ለቤት መጎብኘት መቻሉን እና ለበሽታው ተጋላጭ የሆኑ ሰዎችን መለየት እንዲሁም ግንዛቤ የመፍጠር ስራ ማከናወን መቻሉንም በሪፖርቱ ላይ አብራርተዋል።

የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ስርጭትን በተሻለ ከማወቅ በተጨማሪ የመከላከል እና የመቆጣጠር አቅምን በከፍተኛ ደረጃ መፍጠር መቻሉንም ገልፀዋል።ከእነዚህ ውስጥ አመራሩ ትኩረት አንዲሰጥ ማድረግ መቻሉ፣ በሚዲያ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ መከናወኑ፣ የቅኝት ስራ ላይ የሚያስፈልጉ አደረጃጀቶችን ማስፋት መቻሉ እንዲሁም ከ10 ሺህ 500 በላይ የድንገተኛ ምላሽና የበሽታ ቅኝት የሚከናውኑ ቡድኖችን ማደራጀት መቻሉንም አስታውቅዋል።የላቦራቶሪ ናሙና መሰብሰቢያ ቦታዎችን በየወረዳው መስፋት መቻለኩንም በሪፖርታቸው አንስተዋል።

የምርመራ አቅም በከፍተኛ ደረጃ ማሳደግ ተችሏል ያሉት ዶክተር ሊያ፥ የጤና ተቋማትና የአልጋ ቁጥር ማሳደግና የቤት ውስጥ ህክምና አገለግሎት ማስጀመር መቻሉንም አንስተዋል።የመመርመሪያ ኪቶች ማምረቻም ማቋቋም እንደተቻለም በሪፖርታቸው ላይ አቅርበዋል።

በዚሁ መሰረት የቀጣይ ወራት ትንብያ በበሽታው የሚያዙ ሰዎች ቁጥር፣ የሞት ቁጥር እና ወረርሽኙ ከፍተኛውን ጣሪያ የሚደርስበት ጊዜ በዋናነት የሚወሰነው በአካላዊ መራራቅ እንዲሁም የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምበል በሚተገበርበት ደረጃ ነው ብለዋል።ለምሳሌ ያክል አካላዊ ርቀት 5 በመቶ እና የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ 50 በመቶ የህብረተሰብ ክፍል ውስጥ መተግበር ከተቻለ ምንም አይነት እርምጃ ባይወሰድ ሊደርስ ከሚሽለው የበሽታ ስርጭት እና ሞት አንጻር በ92 በመቶ መቀነስ እንደሚቻል ተመላክቷል።

እነዚህና ሌሎችም ነጥቦችን ታሳቢ ያደረጉ በርካታ እርምጃዎች ሲወሰዱ የቆዩ ሲሆን፥ በቀጣይም በተሻለ ደረጃ ማስቀጠል ይገባል ብለዋል።በዚሁ መሰረት ሀገራዊ ምርጫን የማካሄድ ሂደት ውስጥ በርካታ ዓለም አቀፍ ተሞክሮዎች ምልከታ የተደረገባቸው ሲሆን፥ በአንዳንዶቹ በወረርሽኝ ወቅት ምርጫ ተካሂዷል፤ በአብዛኞቹ ደግሞ እንዲተላለፍ ተደርጓል።

በኢትዮጵያም በሽታውን የመከላከልም ሆነ የመቆጣጠር ዝግጅነቱ ዝቅተኛ በነበረበት ወቅት ምርጫን ማከናወን ስጋቱ የበለጠ የሚያሳድገው በመሆኑ በተላለፈው ውሳኔ እንዲራዘም መደረጉ ይታወሳል።ወረርሽኙ አሁንም የጤና ስጋት ቢሆንም ቀደም ሲል ከነበሩት ለምዶች እንፃር ከፍተኛ አለመሆኑ፣ ኮቪድ 19 በሽታ ረዘም ላለ ጊዜ አብሮን ሊቆይ ሰለሚችልና አንፃራዊ በሆነ ሰዓት ምርጫው ሲራዘም ከነበርንበት ሁኔታ ለስርጭቱ የተሻለ መረጃ ያለን በመሆኑ ቀደም ሲል ከነበረበት በተሻለ የመከላከል ሁኔታዎች በመኖራቸው፣ የህብረተሰቡ ግንዛቤ መሻሻል በማሳየቱ፣ የማስክና የሳኒታይዘር ምርት በሀገር ውስጥ በስፋት በመኖሩ፣ የጤና ተቋማት ዝግጁነት እና ግብአት አቅርቦት መሻሻሉ፣ የምርመራ ኪት ማምረትን ጨምሮ የላቦራቶሪ አቅንም ማገድና የዘርፈ ብዙ ምላሽ በተሻለ ሁኔታ የሚገኝ መሆኑ እንዲሁም የሀራት የምርጫ ተሞክሮን በማየት የሚከተሉትን ቅድመ ሁኔታዎቸን አማልቶ ሀገራዊ ሁኔታን ማካሄድ ይቻላል።

👉 ከዚህ በፊት ከነበረው የምርጫ ሂደት በተለየ መልኩ ኮቪድ 19ኝ መከላከልን ከግምት ውስጥ ያስገባ የምርጫ ስነ ምግባር ደንብ እና ማስፈጸሚያ ነነሪያዎችን ማዘጋጀትና በተዘጋጁ ዝርዝሮች መሰረት በሁሉም ደረጃ በበቂ ዝግጅቶች ወደ ትግበራ መግባት ያስፈልጋል።

👉 በዚህ ሂደት ውስጥ አንድ አንድ ቦታዎች ላይ ከፍተኛ የሆነ የወረርሽኝ ስርጭት ከተከሰተ በተለየ ሁኔታ መታየት ሊያስፈልገው እንደሚችል ታሳቢ በማድረግ መዘጋጀት ያስፈልጋል ሲል ሚኒስቴሩ ምክረ ሀሳቡን አቅርቧል።

በቀረበው ሪፖርትና እና መክረ ሀሳብ ላይ የምክር ቤቱ አባላት አስተያየት እየሰጡ ሲሆን፥ ከተወያዩብ በኋላ ውሳኔ ያሳልፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

[FBC]
@YeneTube @FikerAssefa
ሰበር ዜና!

የጤና ሚኒስቴር የዓለም አቀፉ የጤና ድርጅት ያስቀመጣቸውን መስፈርቶች በመተግበር ትምህርት ቤቶችን መክፈት ይቻላል የሚል ምክረ ሀሳብ አቀረበ!

የዓለም አቀፉ የጤና ድርጅት ያስቀመጣቸውን መስፈርቶች በመተግበር እንደየአከባቢው ተጨባጭ ሁኔታ ትምህርት ቤቶችን መክፈት እንደሚቻል የጤና ሚኒስቴር ምክረ ሀሳብ አቅርቧል።

[EBC]
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮ- ጅቡቲ ምድር ባቡር ስራ ከጀመረ ጊዜ አንስቶ ባለፊት ሁለት አመታት 130ሺ መንገደኞችና 2 ነጥብ 3 ሚሊዮን ቶን እቃ ማጓጓዝ መቻሉ ተገለጸ።

የኢትዮ- ጅቡቲ ምድር ባቡር መስመር በኮሮና ምክንያት የሚሰጠው የመንገደኞች አገልግሎት ቢቀንስም በ15 እቃ ጫኝ ባቡሮች በመታገዝ የእቃ ጭነት አገልግሎት እየሰጠ መሆኑ ተገልጿል።

[ETV]
@YeneTube @FikerAssefa
አቃቤ ህግ የታገደው የእነ ጃዋር መሐመድ ንብረት ሊመለስላቸው አይገባም አለ!

የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ከጃዋር መሐመድ ቤት በብርበራ የተወሰዱ ገንዘቦች እና ዕቃዎች በፖሊስ ኢግዚቢትነት የያዛቸው ስለሆነ ልጠየቅበት አይገባም አለ።በአቶ በቀለ ገርባ፣ ሀምዛ አዳነ ቦና ትቢሌ እንዲሁም በኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ (OMN) ስም የተመዘገቡ እና በፖሊስ ቁጥጥር ስር የሚገኙ ስድስት መኪኖችም በወንጀል ድርጊት የተገኙ ንብረቶች ስለሆኑ ሊመለሱ እንደማይገባ ተከራክሯል።

አቃቤ ህግ ክርክሩን ያቀረበው አቶ ጃዋርን ጨምሮ 15 ተጠርጣሪዎች ያቀረቡትን የንብረት እገዳ ይነሳልን አቤቱታ በመቃወም ለፍርድ ቤት ዛሬ አርብ መስከረም 8፤ 2013 በጹሁፍ በሰጠው ምላሽ ነው። ጉዳዩን የሚመለከተው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ የጊዜ ቀጠሮ ወንጀል ችሎት ምላሹን መርምሮ ውሳኔ ለመስጠት ለመስከረም 19 ቀጠሮ ሰጥቷል።

[ኢትዮጵያ ኢንሳይደር]
@YeneTube @FikerAssefa
የኦሮሚያ ክልል በአፋር ክልል በአዋሽ ወንዝ ሙላት ለተጎዱ ሰዎች ድጋፍ አደረገ!

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በአፋር ክልል በአዋሽ ወንዝ ሙላት በጎርፍ ምክንያት ቤት ንብረታቸው ለወደመባቸውና በመጠለያ ለሚገኙ ወገኖች የምግብና ቁሳቁስ ድጋፍ አበርክቷል::በኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳ የተመራ የክልሉ ከፍተኛ የስራ አመራር ቡድን በአፋር ክልል የአዋሽ ወንዝ ጉዳት ያደረሰባቸውን አካባቢዎች እየጎበኘ ይገኛል፡፡የተደረገው ድጋፍ የአንድነታችን ማሳያ ነው ያሉት የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ የሚገጥሙን ችግሮች ከአንድነታችን በታች መሆናቸውን ተምረንበታል ብለዋል፡፡

የጉዳቱ ሰለባዎች ለተደረገላቸው ድጋፍ አመስግነው የችግሩ መጠን ከፍተኛ እንደመሆኑ በቋሚነት መቋቋም እንደሚፈልጉ ተናግረዋል፡፡እኛ ኢትዮጵያውያን ወንድማማችነታችን ባጠናከርን ቁጥር ሀገራችንን ከፍ እናደርጋለን ያሉት የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሽመልስ አብዲሳ አዋሽን በሚገባ ከተጠቀምንበት የጋራ ሀብታችን ነው ብለዋል፡፡መሰል ችግሮች እንዳይፈጠሩ በቀጣይ አዋሽን ከመነሻው ጀምሮ በጋራ የመቆጣጠር ስራ እንሰራለን ብለዋል፡፡

[OBN]
@YeneTube @FikerAssefa
መስቀል አደባባይ ለደመራ በዓል አከባበር ዝግጁ ሆኗል ተባለ!

መስቀል አደባባይ ፕሮጀክት ለደመራ በዓል ዝግጁ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ አስታወቁ፡፡ምክትል ከንቲባዋ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ ብጽዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ጋር በመሆን የአደባባዩን የግንባታ ፕሮጄክት እና በዓሉ የሚከበርበትን ስፍራ ጎብኝተዋል፡፡ስፍራው ለደመራ በአል ዝግጁ መሆኑን የገለጹት ምክትል ከንቲባዋ በዓሉ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት በአነስተኛ ሰዎች ቁጥር እንደሚከበር ገልጸዋል፡፡አቡነ ማቲያስ በበኩላቸው ስፍራው በዓሉን ማከበር በሚያስችል መልኩ ተዘጋጀቶ ማየታቸውን ተናግረዋል፡፡ለበዓሉ ላይደርስ ይችላል በሚል በብዙዎች የቤተ እምነቱ ተከታዮች ዘንድ ጥያቄን ያስነሳው የግንባታ ፕሮጀክቱ ከ3 ወራት በፊት መጀመሩ የሚታወስ ነው፡፡

[ETV]
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
#NewsAlert በኮቪድ 19 ምክንያት ተራዝሞ የነበረው ሀገራዊ ምርጫ አሁን ላይ ቅድመ ሁኔታዎችን አሟልቶ ማካሄድ እንደሚቻል የጤና ሚኒስቴር ምከረ ሀሳብ አቀረበ! የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 5ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ አስቸኳይ ስብሰባውን እያካሄደ ይገኛል።የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምላሽና ቀጣይ እርምኝጃዎች በሚመለከት…
ምክር ቤቱ አገራዊ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምላሽና ቀጣይ እርምጃዎች ላይ የውሳኔ ሀሳብ እንዲያቀርቡ ለቋሚ ኮሚቴዎች መራ!

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አገራዊ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምላሽና ቀጣይ እርምጃዎችን አስመልክቶ ከጤና ሚኒስቴር በቀረበ ምክረ ሀሳብ ላይ የውሳኔ ሀሳብ እንዲያቀርቡ ለሚመለከታቸው ቋሚ ኮሚቴዎች መርቷል።ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው አምስተኛ አመት የሥራ ዘመን ሦስተኛ አስቸኳይ ስብሰባው ከጤና ሚኒስቴር በቀረበለት ሪፖርት ላይ ተወያይቷል።

የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምላሽና ቀጣይ እርምጃዎች ላይ ያተኮረ ሪፖርትና ምክረ ሀሳብ ለምክር ቤቱ አቅርበዋል።

ዶክተር ሊያ አጠቃላይና ዝርዝር ምክረ ሀሳቦችን ያቀረቡ ሲሆን ትምህርት ቤቶችን ስለመክፈትና አገራዊ ምርጫን ማካሄድን በተመለከተም በዝርዝር አቅርበዋል።

ወረርሽኙን ለመከላከል እየተወሰዱ ያሉ የጥንቃቄ እርምጃዎችን በአግባቡ በመተግበር ትምህርት ቤቶች ቢከፈቱ የሚል ምክረ ሀሳብ አቅርበዋል።

ትምህርት ለመጀመር ከመወሰኑ በፊት ግን ጠንካራ ግብረ ኃይል በየደረጃው ተቋቁሞ ወደ ሥራ መገባት እንዳለበት ነው ሚኒስትሯ ያስታወቁት።

አገራዊ ምርጫ ማካሄድን በተመለከተም ከዚህ በፊት ከነበሩ ምርጫዎች በተለየ መልኩ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን መከላከል ከግምት ያስገቡ ቅድመ ሁኔታዎችን አሟልቶ ምርጫ ማካሄድ እንደሚቻል ምክረ ሃሳብ ማቅረባቸውን የኢዜአ ዘገበ ያመለክታል።ምክር ቤቱ በቀረበው ምክረ ሃሳብ ላይ ውይይት ካደረገ በኋላ በዋናነት ለሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ቋሚ ኮሚቴ እና ለህግ፣ ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የውሳኔ ሃሳብ እንዲያቀርቡ መርቷል።

[EBC]
@YeneTube @FikerAssefa
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጎርፍ ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች 29 ሚሊየን ብር የሚገመት ድጋፍ በገንዘብ እና በአይነት ድጋፍ አደረገ።ድጋፉ እንደጉዳቱ መጠን እና ስፋት የተከፋፈለ መሆኑን የገለጹት ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከሁሉ በላይ ለወገኖቻችን የአብሮነት ማሳያችን ነው ብለዋል።

በዚህም መሰረት ለአፋር ክልል12 ሚሊየን ፣ በኦሮሚያ 8 ሚሊየን ፣ ለአማራ ክልል 5 ሚሊየን እና ለደቡብ ክልል 4 ሚሊየን ብር ድጋፍ ተደርጎላቸዋል።ድጋፉ ከከተማ አስተዳደር በጀት፣ ከብልጽግና ወጣቶች ሊግ፣ በጎፍቃደኞች እና አሚባራ ኃ.የ.ግ.ማ የተሰበሰበ መሆኑ ተገልጿል።

[AMN]
@YeneTube @FikerAssefa
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ጅማ ከተማ ገብተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ ጅማ አባ ጅፋር አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም በአባ ገዳዎች፣ በሀይማኖት አባቶች የሀገር ሽማግሌዎች እና የተለያዩ የህብረተሰብ ተወካዮች አቀባበል አደርገውላቸዋል።

በአቀባበሉ ላይም ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ እና ለሌሎችም እንግዶች የተለያዩ ስጦታዎች እንደተበረከቱም የጅማ ዞን የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጽህፈት ቤትን ጠቅሶ የዘገበው ፋና ነው።

@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ጅማ ከተማ ገብተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ ጅማ አባ ጅፋር አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም በአባ ገዳዎች፣ በሀይማኖት አባቶች የሀገር ሽማግሌዎች እና የተለያዩ የህብረተሰብ ተወካዮች አቀባበል አደርገውላቸዋል። በአቀባበሉ ላይም ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ እና ለሌሎችም እንግዶች የተለያዩ ስጦታዎች እንደተበረከቱም የጅማ ዞን የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን…
ጠቅላይ ሚኒስቴር የዉጭ ባለሀበቶች ጋር የዳውሮ ዞን ተፈጥሯዊ ሀብቶችን ጎበኙ!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ከተለያዩ የውጪ ልማታዊ ባለሀበቶች ጋር የዳውሮ ዞን እምቅ ተፈጥሯዊ ሀብቶችን ጎበኝተዋል፡፡ከኮይሻ እስከ ንጉስ ሀላላ ኬላ እንዲሁም በዙሪያው ያሉ የተፈጥሮ ሀብቶችን ለማልማት ይፍ በተደረገው የገበታ ለሀገር ፕሮጀክት ሲጠናቀቅ በዙሪያው የተለያዩ የኢንቨስትመንት ሥራዎችን የሚያከናውኑ የውጭ ባለሀብቶች የአካባቢውን እምቅ የተፈጥሮ ሀብቶችን ከዶክተር አብይ ጋር በጋራ ጎነዉ የጎበኙት።የአካባቢው ነዋሪዎችም በደመቀ ሁኔታ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

[SRTA]
@YeneTube @FikerAssefa
አዲሱን የብር ኖት በኤቲኤም አገልግሎት መስጠጥ ተጀመረ!

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ነባሮቹን የብር ኖቶች በአዲሶቹ የመቀየር አገልግሎት በቅርንጫፎች ከመስጠቱ ጎን ለጎን የኤቲኤም ማሽኖች በአዲሶቹ የብር ኖቶች አገልግሎት እንዲሠጡ እያደረገ ነው፡፡በአሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲስ አበባ ቅርጫፍ የሚገኙት ኤቲኤም ማሽኖች በአዲሶቹ የብር ኖቶች አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙ ሲሆን በአጭር ጊዜ ውስጥ ሁሉም የባንኩ ኤቲኤም ማሽኖች ተመሳሳይ አገልግሎት መስጠት ይጀምራሉ፡፡

[CBE]
@YeneTube @FikerAssefa
አዲስ የታተሙ የብር ኖቶች አይነት፣ የደህንነት መጠበቂያ ምልክቶችና ምስሎች:

1. ተከታታይ ቁጥሮች

የገንዘቡ ቁጥሮች በሚያጎላ ማሽን ሲታዩ ከጥቁር ወደ አረንጓዴ ፍሎረሰንት ቀለም ይለወጣሉ፡፡

2. ማየት ለተሳናቸው እውቅና ምልክት

የብሩን ዋጋ የሚገልጽ ማየት የተሳናቸው በእጅ ዳሰሳ ማወቅ የሚችሉበት የደህንነት መጠበቂያ ምልክት፡፡

3. ጎርባጣ መስመሮች (PEAK)

የባንክ ኖቱ ሲዳሰስ የመጎርበጥ ስሜት እንዲሁም የኖቱ ዋጋ ይታያል፡፡

4. ደማቅ አንፀባራቂ ምልክት

ገንዘቡ ወደላይ ወይም ወደታች ሲዞር የሚንቀሳቀስ ደማቅ የቀለም ፍንጣቂ (SPARK) የደህንነት መጠበቂያ ምልክት፡፡

5. የደህንነት መጠበቂያ ክር

የሚሽከረከር ደማቅ ቀለም ኮከብ አዲስ የደህንንት መጠበቂያ ክር፡፡ በክሩ ውሰጥ NBE፣ ኢብባ እና የገንዘቦቹ አይነት ተጽፎ ይገኛል፡፡

6. የውሃ ምልክት

ገንዘቡ ወደብርሃን አቅጣጫ ተደርጎ ሲታይ በላዩ ላይ ከሚገኘው ምስል ፊት ለፊት ተመሳሳይ ደብዛዛ የውሃ መልክ ያለው ምልከት ይታያል፡፡

7. ትይዩ ምልክት

የብር ኖቶች ከብርሃን አቅጣጫ ሲታዩ ኳስ መሳይ ምልክት ከገንዘቡ በስተኋላው ካለው ተመሳሳይ ምልክት ጋር በፍጹም ትይዩ ሆነው በአንድ ቦታ ላይ ያርፋሉ፡፡

8. ፈሎረሰንስ ምልክት

አንበሳው ምስል ራስ ላይ አልትራቫዮሌት ጨረር ሲበራበት ወደቢጫነት የሚለወጥ ፈሎረሰንት ምልክት፡፡

ያስተውሉ፡

አዲስ የታተሙት የብር ዓየነቶች በአካላቸው ላይ የሚገኙ የደህንነት መጠበቂያ ምልክቶች ያሉባቸው ናቸው፡፡ እነዚህን ያላሟሉ ወይም ተመሳስለው የተዘጋጁ ገንዘቦቸን የያዙ ወይም የሚጠቀሙ ግለሰቦች ካጋጠሙዎት ወዲያውኑ በአቅራቢያዎ ለሚገኘው ፖሊስ ጣቢያ/ የጸጥታ አካል ያሳወቁ፡፡

[CBE]
@YeneTube @FikerAssefa
የፀጥታ ኃይሎች ከ1 በጥብ 5 ሚሊየን ብር በታች የሆነን ገንዘብ በህገ ወጥነት መያዝ እንደሌለባቸው ተገለፀ።

የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ እና የብሄራዊ ባንክ ገዢ ዶክተር ይናገር ደሴ በዛሬው እለት አዲሱን የብር ኖት ለውጥ ተከትሎ መግለጫ ሰጥተዋል።በመግለጫው ላይም የብሔራዊ ባንክ ገዢ ዶክተር ይናገር ደሴ፥ ከብር ኖት ለውጡ ጋር በተያያዘ የተወሰነ ውዥንብር መፈጠሩን ገልጸዋል።በዚህም የፀጥታ ሀይሎች በመቶ ሺዎች ይዘው የሚንቀሳቀሱ ሰዎችን እየያዙ መሆኑን እና ይህም ተገቢ አለመሆኑን ጠቅሰው እስከ 1 ነጥብ 5 ሚልየን ብር ያላቸው ሰዎች ያለመሳቀቅ መንቀሳቀስ ይችላሉ ብለዋል።ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ መያዝን የሚከለክለው መመሪያ እንደ ነዳጅ ማደያ እና ሌሎች ከፍተኛ ሽያጭ የሚያከናውኑ ተቋማትን እንደማይመለከትም ተጠቅሷል።

ነገር ግን ባለሀብቶች በእነዚህ ተቋማት በኩል ገንዘባቸውን በዚህ መንገድ እናስገባለን ብለው ከሞከሩ የንግድ ተቋማቱ የሽያጭ ታሪካቸው ክትትል ስለሚደረግበት እንዳይሞክሩትም አሳስበዋል።አንዳንድ ግለሰቦች መመሪያው ባንክ ብቻን የሚመለከት ነው በሚል በርከት ያለ ገንዘብ በማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት በኩል ለማስገባት ሙከራ እያደረጉ የተገለፀ ሲሆን፥ መመሪያው ለባንኮችም ለማይክሮ ፋይናስ ተቋማትን እኩል የሚያገለግል መሆኑ ተነስቷል።

በተለያዩ ባንኮች ሂሳብ በመክፈት ገንዘብ በትኖ ለማስቀመጥ የሚሞክሩ ካሉም ይህንን የሚቆጣጠር ግብረ ሀይል መቋቋሙ እና ይህንን ተግባር ፈጽሞ በተገኙት ላይ ብራቸውን እስከ መውረስ የሚደርስ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድም ተነስቷል።እንዲሁም በተለያዩ ሰዎች አማካኝነት ገንዘብ ማስቀመጥ እንዲሁም በሌላ ሰው ስም ገንዘብ ማስገባት እንደማይቻልም በመግለጫው ላይ ተጠቅሷል።ከአሽከርካሪዎች ጋር በተያያዘም ከጎረቤት ሀገራት በተለይ ከጅቡቲ ጋር በተያያዘ አሽከርካሪዎች ገንዘብ ይዘው ስለሚንቀሳቀሱ፤ ሁሉም ገንዘብ ህገ ወጥ ነው ተብሎ መያዝ እንደሌለበት በመግለጫው ተጠቅሷል።አሽከርካሪዎች ከሀገር ሲወጡ እስከ 30 ሺህ ብር ይዘው መውጣት እንደሚችሉ፤ ሲገቡ ደግሞ እስከ 10 ሺህ ብር መያዝ የሚችሉ መሆኑም ታውቋል።ሆኖም ግን በህገ ወጥ መንገድ ብር በተሽከርካሪያቸው ውስጥ ደብቀው ለማስገባት የሚመክሩ ካሉም እንደሚወረስባቸው ተነስቷል።

[FBC]
@YeneTube @FikerAssefa
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሆራ ፊንፊኔ የኢሬቻ በአል ማክበሪያ ስፍራ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ለአባገዳዎች አስረከበ!

የኦሮሞ ህዝብ ጭጋጋማውን የክረምት ወቅት አልፎ ወደ ብርሃን ላሸጋገረው ፈጣሪ ምስጋናውን የሚያቀርብበት የኢሬቻ በአል በዚህ አመት በአዲስ አበባ ከተማ መስከረም 23 ቀን ይከበራል፡፡የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም ለሆራ ፊንፊኔ የኢሬቻ በዓል ማክበሪያ ስፍራ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ለአባገዳዎች ማስረከቡ ተነግሯል፡፡ካርታውን ያስረከቡት የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ስፍራው የቀደመ የኢሬቻ በአል የሚከበርበት ቦታ መሆኑ በመረጋገጡ የማረጋገጫ ሰነድ መሰጠቱን ተናግረዋል፡፡

የኢሬቻ በዓል የአብሮነትና የሰላም እሴት መሆኑን የተናገሩት ምክትል ከንቲባዋ ምንም እንኳን በጋራ የሚከበር ቢሆንም በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት በተወሰኑ ሰዎች እንደሚከበርም ተናግረዋል፡፡የኦሮሚያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ከበደ ዴሲሳ በበኩላቸው አስተዳደሩ እሴቱ እንዲጎለብት ለበአሉ ቋሚ ማበክበሪያ ቦታ የማረጋገጫ ሰነድ በመስጠቱ ማመስገናቸውን ከአዲስ ሚድያ ኔትዎርክ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡አስተዳደሩ የህዝቡን ጥያቄ በመመለሱ ምስጋናቸውን ያቀረቡት አባገዳዎችም የዘንድሮ የኢሬቻ በአል አከባበር በአዲስ አበባ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት በተወሰኑ ሰዎችን እንደሚከበርም ገልጸዋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በሕገ-ወጥ መንገድ ገንዘብ ያዘዋወረ፣ በዝውውሩ የተሳተፈና ለአዘዋዋሪዎች ሽፋን የሰጠ 10 ዓመት የሚደርስ ጽኑ እስራትና የገንዘብ ቅጣት እንደሚጠብቀው የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ አስታወቀ።

ለዝርዝሩ👇👇👇
https://telegra.ph/-09-18-599
ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል አካባቢ መረጋጋት እየሰፈነ እንደሆነ ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡

የጠፉ ሰዎችም መኖራቸውንና እስከ ዛሬ ድረስ ወደቤታቸው የሚመለሱ እንዳሉም ነዋሪዎቹ ገልጸዋል፡፡በቤኒሻጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ቡለን ወረዳ ንጹኃን ዜጎች ላይ ጥቃት መፈጸሙ ይታወሳል፡፡ ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ የቡለን ከተማ ነዋሪዎች አካባቢው እየተረጋጋ እንደሆነ በስልክ ለአብመድ ተናግረዋል፡፡ ሟች ቤተሰብ ማርዳት እና የለቅሶ ሥነ ስርዓት እየተካሄደ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡ቀብሩን የፀጥታ አካሉ እንደፈጸመው እና ጫካ ተደብቀው የነበሩ እና በአጋቾቹ እጅ ያልገቡ ሰዎች ወደ ቡለን ከተማ እየተመለሱ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡

አሁንም ከታጣቂዎቹ ሸሽተው ጫካ ተደብቀው የነበሩ እና የት እንደደረሱ ያልታወቁ ሰዎች መኖራቸውን አስተያየት ሰጪዎቻችን ተናግረዋል፡፡ “ባልና ሚስት አስተማሪዎች አሁን ጠፍተው የት እንደገቡ አይታወቅም፤ ሚስቱ እርጉዝ ደግሞ ነበረች፤ ስልክ እየደወሉ ነበር ከጫካ ውስጥ እኔ ራሱ የማውቀው ጓደኛዬ ነው፡፡ስደውልለት ‘ጫካውን አላውቀውም፤ የት እንዳለሁ አላውቀውም’ ነው ያለኝ፤ አስካሁን የት እንዳለ አይታወቅም፤ ይሙቱ አይሙቱ አይታወቅም፤ ስልኩ አይሠራም፤ ‘ዝግ ነው’ ነው የሚለው” ብለዋል አንዱ አስተያየት ሰጪ፡፡ጥቃቱ ከተፈጸመበት አካባቢ የተፈናቀሉ ነዋሪዎች ከጫካ ወደ ቡለን ከተማ እስከ ዛሬ ድረስ እየመጡ እንደሆነም ግልጸዋል፡፡በአካባቢው አንጻራዊ ሰላም መስፈኑንም ተናግረዋል፡፡

[አብመድ]
@YeneTube @FikerAssefa
የአሥራት ጋዜጠኞች ከእሥር እንዲለቀቁ ፍርድ ቤቱ ወሰነ!

የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ጋዜጠኞቹ ከ44 ቀን እስር በኃላ በዋስ እንዲፈቱ አዟል።ላለፉት ቀናት በእሥር ላይ የነበሩት የአሥራት ሚዲያ ሀውስ ጋዜጠኞች ቀደም ብለው ባስያዙት ዋስ ከእስር እንዲለቀቁ ሲል ፍርድ ቤት መወሰኑ ተገለጸ፡፡ የአሥራት ባልደረቦች በላይ ማናዬ፣ ሙሉጌታ አንበርብርና ምስጋናው ከፈለኝ ቀደም ሲል በዋስ እንዲወጡ ቢወሰንም ከእሥር ሳይወጡ መቆታቸው ይታወሳል፡፡

በመቀጠልም ከአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያ በኋላ አመፅ አስነስተዋል በሚል ሌላ የምርመራ መዝገብ የተከፈተባቸው ሲሆን ፍርድ ቤቱ ግን ከእሥር እንዲለቀቁ መወሰኑን የጋዜጠኞቹ ቤተሰቦች ለአል ዐይን ገልጸዋል፡፡የልደታ ፍ/ቤትየፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት እንዲወጡ አዟል፡፡ዛሬ በዋለው ችሎት ፍርድ ቤቱ ምንም አዲስ ነገር ያገኘው እንደሌለ ገልጾ ጋዜጠኞቹ በነፃ እንዲወጡ ትዕዝዛ ሰጥቷል።

[Al ain]
@YeneTube @FikerAssefa

አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የሁለተኛ ዲግሪ ተማሪዎችን መግቢያ ቀን አሳውቋል።

በተከሰተዉ የኮቪድ 19 ምክንያት ሁሉም የትምህርት እንቅስቃሴ ተቋርጦ መቆየቱ ይታወሳል።ነገር ግን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ Regular Graduate ተማሪዎችን መዝግቦ ትምህርት የሚያስጀምርበትን ቀን ቆርጦ በድህረ ገጹ እና በ ማህበራዊ ገጹ ላይ  አሳውቋል። 

በዚህም መሰረት ሁሉንም ተማሪዎች ባይሆንም ከ ሁለተኛ ዓመት በላይ የሆኑ Regular Graduate ተማሪዎችን ምዝገባ እና ትምህርት የሚጀመርበትን ቀን አሳውቋል።

ምዝገባ የሚጀመርበት ቀን በ September 21, 2020 እና September 22, 2020  ሲሆን ትምህርት የሚጀመረዉን ደግሞ በ September 23, 2020 እንደሆነ የዩኒቨርሲቲዉ ሬጅስትራር ገልጿል።
ተማሪዎቹም  ለምዝገባዉ ስኬታማነት ተገቢዉን ትብብር እንዲያደርጉም አሳውቋል።

ምንጭ፡- የዩኒቨርሲቲዉ ድረ ገጽ (www.aau.edu.et)
@Yenetube @Fikerassefa