አቶ ልደቱ አያሌው የጦር መሳሪያ ይዞ መገኘት ክስ ላይ መቃወሚያ አቀረቡ፡፡
የአቶ ልደቱ አያሌው ሁለት ጠበቆች ዛሬ ከሰዓት ባቀረቡት መቃወሚያ የጦር መሳሪያ አስተዳደር አዋጅ መሰረት እስከ አንድ ዓመት መገልገል ይቻላል፤ የመጠቀሚያ ጊዜ አለው ብለዋል።ለዚህም በዚህ አዋጅ ተጠያቂ ማድረግ ተገቢነት የለውም፤ ስለዚህ በዚህ አዋጅ ሊከሰሱ አይገባም ያለ ሲሆን፥ በሁለተኛ ደግሞ የተከሰሱበት አንቀፅ ከፍ ያለ ነው፤ ክሱ ላይም ብዛት ያለው የጦር መሳሪያ ተብሎ የተጠቀሰው ነገር ግን አንድ መሳሪያ ነው፤ ይህም ተገቢነት የለውም የሚል መቃወሚያቸውን አቅርበዋል፡፡ካላቸው የጤና ሁኔታም በውጭ ሀገር መታከም እንደሚገባቸው እና ዋስትና እንዲሚያስፈጋቸውም አቅርበዋል፡፡
በጉዳዩ ላይ ምላሽ የሰጠው የአዳማ ከተማ ፍትህ ቢሮ አቃቤ ህግ በአዋጁ የተሰጠው ህግ ወጥ የጦር መሳሪያ ሳይሆን በአንድ ዓመት ውስጥ መሳሪያ ያለው ሰው እንዲስመዘግብ ለማስቻል ነው፤ ይህም የሃገሪቱን ሰፋት ከግምት ውስጥ አስገብቶ እንጂ ህገ ወጥ መሳሪያ ይዞ እንዲቀመጥ አይደለም የተተረጎመው ፤ በዚህ መልኩ አንድ ዓመት ሙሉ የጦር መሳሪያ መታጠቅ አይቻልም ያለ ሲሆን፥ በአዋጁ አንቀፅ ስድስትም ቢሆን ሌላ የጦር መሳሪያ ፍቃድ እያላቸው ሁለተኛ መያዝ አይቻልም ብሏል።እንዲሁም በሌላ ሰው ስም ተመዘገበ ሽጉጥ መያዝ አይችሉም፣ ሽጉጡም በሌላ ሰው ስም የወጣ ነው ያለው አቃቤ ህግ፥ የጤናቸውን ሁኔታ በሃገር ውስጥ ህክምና ያገኙ በመሆኑ የህክምና ክትትል ስለከሆነ ወደ ውጪ ሃገር የሚወጡት በዛው ወጥተው ሊቀሩ ስለሚችሉ ለዚህም ማረጋገጫ የለም ሲል ተቃውሞ ተከራክሯል፡፡የሁለቱን ክርክር ያዳመጠው የምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጉዳዩን መርምሮ ትዛዝ ለመስጠት ለመስከረም 12 2013 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል።
@YeneTube @FikerAssefa

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጨምሮ የክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በመተከል ዞን ጥቃት የደረሰባቸውን ሰዎችን አጽናኑ!
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በመተከል ዞን ቡለን ወረዳ ባለፈው ጳጉሜን ሕገ ወጥ ታጣቂዎች ባደረሱት የተኩስ ጥቃት ቁጥራቸው በመጠናት ላይ ያሉ የንጹኃን ሰዎች ሕይወት አልፏል።የነዋሪዎች ሰብዓዊ መብት ተጥሷል፤ሥነ ልቦናዊ እና ኢኮኖሚያዊ ኪሳራ ደርሷል። የንጹኃን ሀብትና ንብረትም ወድሟል።ባለፉት ሁለት ዓመታት በተለያዮ መነሻዎች ምክንያት ቀጣናው ለነዋሪዎች ሰላማዊ መሆን አለመቻሉ ከጊዜ ወደጊዜ አሳሳቢ እየሆነ መጥቷል።
ይህንን ተከትሎ የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፣ የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ተመሥገን ጥሩነህ፣ የቤኔሻንጉል ክልል ርእሰ መሥተዳድር አሻድሌ ሐሰን፤ የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ኢታማዦር ሹም ጀነራል አደም ሙሐመድ፣ የሰላም ሚኒስትር ሙፈርያት ካሚልና ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ዛሬ ጥቃት የደረሰባቸውን ቤተሰቦች ቡለን ወረዳ ዶቢ ቀበሌ በመገኘት አጽናንተዋል።
ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎቹ ‘‘አካባቢው የልማት ቀጣና መሆን ሲገባው የችግር ምንጭ መሆን የለበትም’’ ብለዋል።መንግሥት አስፈላጊውን ዘላቂ የመፍትሔ ሐሳብ ለማስቀመጥ ቁርጠኛ መሆኑንም ለተጎጂዎች አስታውቀዋል።ተጎጂ ቤተሰቦችም ‘‘ንጹኃን ሠርተው በአካባቢያቸው እንዲኖሩ ሕግ የማስከበር ሥራው መዘናጋት አያስፈልገውም’’ ብለዋል።የሁሉም ቀበሌ ተጎጂዎች የደረሰባቸውን ጉዳት ለከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ማስረዳታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 602 ሰዎች በኮሮና ሲያዙ የ 12 ሰዎች ህይወት አለፈ!
ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 8,221 የላቦራቶሪ ምርመራ ተጨማሪ 602 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡553 ሰዎች ሲያገግሙ 12 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።እስካሁን 1,184,473 ምርመራ ተደርጎ በአጠቃላይ 67 ሺ 515 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ 27 ሺ 638 ሰዎች ያገገሙ ሲሆን የ 1,072 ሰዎች ህይወት ማለፉን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል።

ቢምቢ ወይም ትንኝ የሚያመጣቸው በሽታዎች ስጋት በድሬደዋ
ወቅትን ተከትሎ በድሬደዋ እየተቀሰቀሰ ባለው የቺኩንጉንያ ፣ ደንጊ እና ወባ በሽታዎች የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መሆኑን መመልከታቸውን ከቀናት በፊት በደንጊ በሽታ እንደተያዙ ለዶይቸ ቨሌ አስተያየት የሰጡ የከተማ ነዋሪ ተናግረዋል። የበሽታው ስሜት በሆኑ ብርድ ብርድ ፣ ትኩሳት እና በከፍተኛ አቅም በማጣት መቸገራቸውን የተናገሩት አስተያየት ሰጪው በተለይ ከአንድ አመት በፊት በከፍተኛ ደረጃ ህብረተሰቡን ያጠቃው የቺኩንጉንያ እና ደንጊ በሽታ በስፋት እንዳይቀሰቀስ ኅብረተሰቡ እና መንግሥት ትኩረት ሰጥተው ሊሠሩ ይገባል ብለዋል፡፡ የህክምና ባለሞያ የሆኑት ዶ/ር ፈቲ በበኩላቸው በእነዚህ የትኩሳት በሽታዎች ሳቢያ ኮሮና ይበልጥ ሊስፋፋ እንደሚችል ስጋታቸውን በመግለፅ በጋራ መረባረብ ይገባል ብለዋል፡፡ የድሬደዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ለምለም በዛብህ በሽታዎቹ መከሰታቸው በላብራቶሪ ምርመራ ውጤት መረጋገጡን ጠቁመው መንግስት ችግሩን ለመፍታት እየሠራ መሆኑን ገልጸዋል። ከአንድ አመት በፊት በመስተዳድሩ ተከስተው በነበሩት የችኩንጉንያ እና ደንጊ በሽታዎች ሳቢያ ከሃምሳ ሺህ በላይ ሰዎች ለበሽታው መጋለጣቸውን መረጃዎች ያመለክታሉ።
[DW]

ዶ/ር ዑባህ አደም የድሬደዋ ዩኒቨርስቲን እንዲመሩ ተሾሙ፡፡
ዶ/ር ዑባህ አደም በድሬደዋ ዩኒቨርስቲ የተካሄደውን የፕሬዘዳንትነት ውድድር አሸንፈው በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ዛሬ ተሹመዋል፡፡በዚህም ዩኒቨርስቲው የመጀመሪያዋን የሴት ፕሬዚዳንት አግኝቷል፡፡ከጥር 2012 ዓ.ም ጀምሮ ድሬደዋ ዩኒቨርስቲን ተወካይ ፕሬዚዳንት ሆነው ሲመሩ የቆዩት ዶ/ር ዑባህ የዶክትሬት ዲግሪያቸውን ያገኙት ከህንድ አንድራ ዩኒቨርስቲ ነው፡፡ዶ/ር ዑባህ በአገራችን የዩኒቨርስቲዎች ታሪክ ሁለተኛዋ ሴት ፕሬዚዳንት ሲሆኑ የመጀመሪያዋ የሴት ፕሬዚዳንት ባህርዳር ዩኒቨርስቲን ከመስከረም 2001 እስከ ጥር 2003 ዓ.ም የመሩት ዶ/ር የሺመብራት መርሻ ካሳ ናቸው፡፡የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ለዶ/ር ዑባህ መልካም የስራ ዘመን ተመኝቷል፡፡
[MoSHE]

የኮቪድ 19 ህክምና ለመስጠት የሚያገለግሉ 380 የመተንፈሻ መሳሪያዎች ድጋፍ ተደረገ።
በትላንትናው እለት የተባበሩት መንግስታት የህፃናት መርጃ ድርጅት (UNICEF)፣ የአሜሪካን እና የእንግሊዝ መንግስት እንዲሁም FCDO የሚባል ልማታዊ ድርጅት ጋር በጋራ በመሆን የኮቪድ 19 ህክምና ለመስጠት የሚያገለግሉ 380 የመተንፈሻ መሳሪያዎችን ለጤና ሚኒስቴር ድጋፍ አድርገዋል፡፡በድጋፍ ከተገኙት 380 የመተንፈሻ መሳሪያዎች መሀከል አንድ መቶ የሚሆኑት በቅርቡ ለተመረቀው የአዲስ አበባ ኮቪድ 19 ፊልድ ሆስፒታል የሚሰጡ መሆናቸው ተገልጿል፡፡
[EPHI]

በባህር ዳር ከተማ ዳግማዊ ሚኒልክ ክ/ከተማ ኢንዱስትሪ ሰፈር በህገወጥ መልኩ የተከማቸ 6,000 ጀሪካን ባለ20 ሊትር ዘይት በቁጥጥር ስር መዋሉን የባህር ዳር ከተማ ሰላም እና ደህንነት መምሪያ አስታወቋል።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
የእግር ኳስ ውድድሮች በተመረጡ ሜዳዎች እንዲካሄዱ የኮሮናቫይረስ መከላከል ፕሮቶኮል መዘጋጀቱን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታወቀ፡፡
የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፉ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ማኅበር ታገኝ የነበረውን 300 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር አሳጥቷል፡፡በኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መከሰቱን ተከትሎ የእግር ኳስ ውድድሮችን ማቋረጥ አንዱ የቅድመ መከላከል እርምጃ ነበር፡፡“በእግር ኳስ ዙሪያ ያሉ ባለሙያዎች፣ አሰልጣኞች፣ ተጫዋቾች ገቢ እንዳይኖራቸው ሆኗል” ሲሉ ውድድሮቹ በመቋረጣቸው ምክንያት የመጡ ተፅዕኖዎችን የነገሩን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ባሕሩ ጥላሁን ናቸው፡፡ሁሉም ባይባሉም የእግር ኳስ ቡድኖች ደመወዝ በአግባቡ ባለመክፈል ቅሬታ ተነስቶባቸዋል፡፡ቡድኖቹ በጨዋታ ጊዜ ወደሜዳ ከሚገባው ተመልካች ያገኙት የነበረው ገቢ ተቋርጧል፡፡
የአውሮፓውያኑ 2020 ዓለም አቀፉ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ማኅበር “ፊፋ ኮንግረስ” በሚል የሚጠራው ጉባኤ በአዲስ አበባ ሊካሄድ ዝግጅት ተደርጎ የኮሮና ወረርሽኝ እንቅፋት ፈጥሮበታል፡፡ በአፍሪካ ለእግር ኳስ ዕድገትና ጉባኤው በተሳካ ሁኔታ እንዲካሄድ አንድ ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር በ“ፊፋ” ተመድቧል፡፡ ከዚህ ከተመደበው ገንዘብ የኢትዮጵያ ድርሻ 33 በመቶ ወይም 300 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ነው፡፡ እናም ሀገሪቱ ይህን ገንዘብ አጥታለች፡፡
እግር ኳስ ፌዴሬሽኑ በ“ስፖንሰርሺፕ” ያገኝ የነበረውን ገቢም አስቀርቶበታል፡፡ ለአብነት ከዋሊያ ቢራ ይገኝ የነበረው ገንዘብ ሙሉ በሙሉ መቋረጡን አቶ ባሕሩ ተናግረዋል፡፡“የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ባይጠፋም እንዴት የእግር ኳስ ውድድሮችን ማስቀጠል ይቻላል?” በሚል የሊግ ተወካዮች የተካፈሉበት ውይይት መደረጉን ኃላፊው ጠቁመዋል፡፡ በፊት በተለያዩ መጫወቻ ሜዳዎች (ስታዲየም) በመዟዟር ይደረግ የነበረው የእግር ኳስ ጨዋታ በተመረጡ የተወሰኑ ሜዳዎች እንዲካሄዱ ከጤና ሚኒስቴር፣ ማኅበረሰብ ጤና ኢንስቲትዩትና ስፖርት ኮሚሽን ጋር በመተባበር የኮሮናቫይረስ መዘጋጀቱን አቶ ባሕሩ አስረድተዋል፡፡ ውድድሮችን ለማስጀመር የመንግሥት ይሁንታ እየተጠበቀ ነው፡፡ ቡድኖች በቀዳሚነት ማድረግ የሚያስፈልጋቸውን እንዲያከናውኑም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በቅርብ ክትትል እያካሄደ ስለመሆኑ ኃላፊው ጠቅሰዋል፡፡
[AMMA]

በመተከል ዞን በተደጋጋሚ እየተስተዋለ ያለውን የጸጥታ ችግር በዘላቂነት ለመፍታት ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት በግልገል በለስ ከተማ እየመከሩ ነው።
በመተከል ዞን ቡለን ወረዳ ኤጻር ቀበሌ የተከሰተውን የሰዎች ሞት ተከትሎ በአካባቢው ዘላቂ ሰላም ለማምጣት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮነንን ጨምሮ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ኢታማዦር ጀኔራል አደም መህመድ፣ የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪያት ከሚል፣የብልጽግና ፓርቲ ሃላፊን አቶ ብናልፍ አንዱዓለም እና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች እየተወያዩ ነው።
በውይይቱ በቀጠናው ዘላቂውን መፍትሄ ለማምጣት እና የዜጎችን ደህነት ለማስጠበቅ የተለያዩ ውሳኔዎች ይተላለፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
[Metekel Zone Communication]

YeneTube
በመተከል ዞን በተደጋጋሚ እየተስተዋለ ያለውን የጸጥታ ችግር በዘላቂነት ለመፍታት ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት በግልገል በለስ ከተማ እየመከሩ ነው። በመተከል ዞን ቡለን ወረዳ ኤጻር ቀበሌ የተከሰተውን የሰዎች ሞት ተከትሎ በአካባቢው ዘላቂ ሰላም ለማምጣት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮነንን ጨምሮ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ኢታማዦር ጀኔራል አደም መህመድ፣ የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪያት ከሚል፣የብልጽግና…
“ጥቂት የፖሊስ ኃይሎችን የመደብን ቢሆንም ታጣቂዎቹ ሲመጡ ሸሽተው መጥፋታቸው አሳዝኖናል”- አሻድሊ ሃሰን
ከሰሞኑ የደረሰው ጥቃት ኢ-ሰብዓዊ እና መደገም የሌለበት እንደሆነ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሠ መሥተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን ተናገሩ፡፡በጥቃቱ ማዘናቸውን የገለጹት ርዕሰ መስተዳድሩ ክልሉ ከጥቃቱ በፊት በደረሰው መረጃ በቡለን ወረዳ ኤጳር ቀበሌ ጥቂት የፖሊስ ኃይሎችን የመደበ ቢሆንም ታጣቂዎቹ ሲመጡ ሸሽተው መጥፋታቸውን እንዳሳዘናቸው እና ሙያዊ መገለጫ አለመሆኑን ተናግረዋል፡፡
በቀጣይ ሕግ በማስከበር፣ ተጎጂዎችን የመካስ እና የማቋቋም ሥራ ይሰራልም ነው ርዕሰ መስተዳድሩ ያሉት፡፡ከሰሞኑ ዜጎችን ለሞትና መፈናቀል የዳረገ ጥቃት በተፈጸመበት መተከል ዞን ቡለን ወረዳ ጉብኝት ያደረጉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በበኩላቸው ጥቃት የተፈጸመባቸው ሰዎች የሚካሱት ወንጀሉን የፈጸሙና የተባባሩ አካላትን በቁጥጥር ስር በማዋል ነው ብለዋል፡፡በጥቃቱ የተበታተኑ ቤተሰቦች በአጭር ጊዜ እንዲገናኙ፣ የተጎዱ ወገኖችም ሃይማኖታቸው በሚያዘው ልከ እንዲያርፉ መሥራት ያስፈልጋልም ነው ያሉት፡፡
ከዕለት ምግብ አቅርቦት ጀምሮ እስከ ዘላቂ ማቋቋም ድረስ ያሉ እገዛዎች በፍጥነት ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ማስቻልና ወንጀሉን የፈጸሙና የተባበሩ አካላትንም በቁጥጥር ሥር ማዋል የቀጣይ ዐበይት ተግባራት መሆናቸውንም አቶ ደመቀ አስታውቀዋል፡፡በተፈጸመው ወንጀል መንገድ የመራ፣ የጠቆመ፣ ያስፈጸመ፣ የተጠቂዎችን ንብረት ያወደመ፣ የዘረፈውን ሁሉ በዜጎች ጥብቅ ተሳትፎ ለሕግ የማቅረብ ሥራ ይጀመራል ስለማለታቸውም ነው አብመድ የዘገበው፡፡“ወንጀለኞች ስለሸሹ የሚቀሩ አይደሉም”ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ጠንካራ መርማሪ ቡድን በማቋቋም በሕግ መፋረድ የመንግሥት የቀጣይ የቤት ሥራ እንደሚሆንም ለተጎጂዎች ቃል ገብተዋል፡፡
ጥፋቱ እንዲፈጸም ከላይ እስከ ታች ያሉ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ሚና ምን እንደነበር በጥልቀት ይመረመራል ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ኃላፊነታቸውን ያልተወጡ፣ በቸልተኝነትና በእንዝላልነት ጥቃቱ እንዲፈጸም ያደረጉ የሥራ ኃላፊዎች ላይ ፍትሕን ለመታደግ” እርምጃ እንደሚወሰድም ገልጸዋል፡፡የኢትዮጵያውያን ዐይን የሆነውን የሕዳሴው ግድብ ደኅንነት ለማረጋገጥ እና ለዜጎች ሰላምና ተጠቃሚነት ዘላቂነት እንዲኖረው የአካባቢውን የጸጥታ ኃይል አደረጃጀት ለማሻሻል መከላከያ በቅርበት ይሠራልም ተብሏል፡፡በጉብኝቱ የሰላም ሚኒስትሯን ሙፈሪያት ካሚልን ጨምሮ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀነራል አደም መሀመድ እና የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄኔራል እንደሻው ጣሰው ተሳትፈዋል፡፡
[Al ain]

በእነ ጀዋር መሐመድ ላይ የክስ መዝገብ መክፈቱን ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አስታወቀ!
ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ እንዳስታወቀው በጃዋር መሀመድ፣ በቀለ ገርባ፣ ሀምዛ አዳነ ላይ በይፋ የክስ መዝገብ መክፈቱን በዛሬው ዕለት አስታውቋል፡፡
በተጨማሪም በሌሉበት የተከሰሱትን የኦሮሚያ ሜዲያ ኔትወርክ (OMN)፤ ደጀኔ ጉተማ ፤ብርሃነመስቀል አበበ(ዶ/ር) እና ፀጋዬ ረጋሳን ጨምሮ በአጠቃላይ በ24 ሰዎች ላይ እንደየተሳትፏቸው ከክስ መዝገቡ ስር ተካተዋል፡፡
በመሆኑም ተከሳሾች እንደየተሳትፏቸው በ1996 የወጣውን የወንጀል ሕግ አንቀፅ 240 በመተላለፍ ብሔርን እና ሐይማኖትን መሰረት ያደረገ የእርስ በርስ ግጭት በመቀስቀስ አንዱ ወገን በሌላው ወገን ላይ እንዲነሳሳ በማድግ ፤የሽብር ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የወጣውን አዋጅ ቁጥር 1176/2012 ፤ የቴሌኮም ማጭበርበር ወንጀል አዋጅ ቁጥር 761/2004 እና የጦር መሳሪያ አስተዳደርና ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር 1177/2012 በመተላለፍ በፈፀሙት ወንጀል በመጥቀስ የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የክስም መዝገብ መክፈቱን አስታውቋል፡፡
ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ መስከረም 6 ቀን 2013 ዓ.ም በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ወንጀል ችሎት በመዝገብ ቁጥር 260215 የከፈተው ክስ አስር ተደራራቢ ክሶች የያዘ መሆኑን አስታውቋል፡፡
ተከሳሾቹም መስከረም 11 ቀን 2013 ዓ.ም ፍርድ ቤት ቀርበው ክሱ ይደርሳቸዋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ባወጣው መረጃ አስታውቋል።

የኬንያ የጭነት አውሮፕላን በሞቃዲሾ ተከሰከሰ!
ንብረትነቱ የኬንያ ሲልቨርስቶን ኤር የሆነ እቃ ጫኝ አውሮፕላን በሞቃዲሾ አደን አዴ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ መከስከሱን የአይን እማኞች ገለጹ፡፡አውሮፕላኑ ከማኮብኮቢያው ወጥቶ በባህር ዳርቻ ከተገነባው የአየር ማረፊያው አጥር ጋር መጋጨቱ ተገልጿል፡፡ጥቂት የበረራ አባላቱ ሳይጎዱ አልቀሩም እንዳለው እንደ ጎብጆግ ዘገባ ከሆነ የነፍስ አድን ስራዎች በመሰራት ላይ ናቸው፡፡የኬንያ አውሮፕላኖች በዚህ ዓመት ብቻ ይህን ጨምሮ 4 ተመሳሳይ አደጋዎች በሶማሊያ ደርሰውባቸዋል፡፡

የባህርዳር ከተማ ተቀዳሚ ም/ከንቲባ ከኃላፊነት ተነሱ!
የባህርዳር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ዶ/ር ማህሪ ታደሰ ለሶስት ወር ከ15 ቀናት ያህል ስራ ላይ ባለመገኘታቸው ምክንያት ከኃላፊነት መነሳታቸውን የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ለአል አይን አማርኛ በስልክ አረጋግጧል፡፡ምክትል ከንቲባ ለአንድ ወር ያህል ፍቃድ የነበራቸው ቢሆንም ለሶስት ወራት በመቆየታቸው ከስራ እንዲነሱ መወሰኑን ኃላፊው አስታውቀዋል፡፡ዶክተር ማህሪ በውጭ ሀገር በተለይም በካናዳ ለረጅም አመት የኖሩ ሲሆን ለአማራ ክልል መንግስት የባህርዳርን ከተማ በከንቲባነት እንዲመሩ ከአንድ አመት በፊት ነበር የሾማቸው፡፡ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ከተፈቀደላቸው አንድ ወር በላይ ስለቆዩ ክልሉ ከስልጣን እንዲነሱ መወሰኑ ታውቋል፡፡
Via Al ain

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአትራፊነት ከተጠቀሱ 3 የአለማችን አየር መንገዶች አንዱ ሆነ!
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአትራፊነት ከተጠቀሱ 3 የአለማችን አየር መንገዶች አንዱ ለመሆን ችሏል።እ.ኤ.አ በ2020 ኮቪድ-19 በሽታ የአለምን ኢኮኖሚ ባቃወሰበት ወቅት ሶስት አየር መንገዶች በትርፋማነታቸው ቀዳሚ ለመሆን መብቃታቸው ተነግሯል፡፡እነዚህም በቅደም ተከተል የኮሪያ፣ የኤስያና እና የኢትዮጵያ አየር መንገዶች እንደሆኑ ፎርብስ በድረ-ገፁ አስፍሯል፡፡አየር መንገዶቹ ሳይከስሩ ቢያንስ ወጪያቸውን በመሸፈን ትርፋማ ሊሆኑ የቻሉት በሚሰጡት አገልግሎት ላይ ለውጥ ማድረጋቸው እንደሆነ ተነግሯል፡፡በተለይ የኮሮና ወረርሺኝ ከተከሰተ ወዲህ የመንገደኞች አውሮፕላኖችን ወደ እቃ ጫኝ ትራንፖርት መቀየራቸው ለትርፋማነታቸው ዋንኛ ምክንያት እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ነገ እሁድ በአዲስ አበባ በተመረጡ ቅርንጫፎች አግልግሎት ይሰጣል!
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲስ የብር ኖት ስርጭት መጀመሩን በማስመልከት በነገው ዕለት በአዲስ አበባ በተመረጡ ቅርንጫፎች አግልግሎት እንደሚሰጥ አስታውቋል፡፡"በነገው ዕለት እሁድ መስከረም 10, 2013 ዓ.ም በአዲስ አበባ በተለያዩ ቦታዎች በተመረጡ የባንኩ ቅርንጫፎች የባንክ አግልግሎት እንደሚሰጥ" ባንኩ በይፋዊ የፌስቡክ ገፁ አስታውቋል፡፡

በእነ ጃዋር መሃመድ ላይ ተከፍቷል ከተባለው የክስ መዝገብ ጋር በተያያዘ በመጪው ሳምንት መግለጫ ሊሰጥ ነው!
ጃዋር ሲራጅ መሀመድን ጨምሮ በአጠቃላይ በ24 ሰዎች ላይ በመዝገብ ቁጥር 260215 10 ተደራራቢ ክሶች ማስከፈቱን ያስታወቀው ጠቅላይ ዐቃቤ ጉዳዩን በማስመልከት በመጪው ሳምንት የመጀመሪያ ቀናት መግለጫ እንደሚሰጥ የአል ዐይን አማርኛ ምንጮቹ እንደገለፁት ዘግቧል፡፡“ክስ መመስረት ባለበት ጊዜ ውስጥ ባለመመስረቱ ተከሳሾቹ ከሰኞ ጀምሮ ከእስር ሊለቀቁ ነው የሚል ወሬ በህዝብ ዘንድ ተሰራጭቷል” ያሉት ምንጮቹ መግለጫው ዐቃቤ ህግ ተቋሙ እየሰራ ያለውን ስራ ማህበረሰቡ እንዲያውቀው ለማድረግ የሚሰጥ ነው ብለዋል፡፡
የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የክስ መዝገብ መከፈቱን በተመለከተ ዛሬ በይፋዊ የፌስቡክ ገጹ አጭር ጥቅል መረጃን ሰበር በሚል ርዕስ ሰጥቷል፡ሆኖም ይህ ክስ መመስረቱን ለማሳወቅ ብቻ እንደሆነ ነው ምንጮቹ ለአል ዐይን የገለጹት፡፡“አዋጅ ቁጥር 761/2004 ፣አዋጅ ቁጥር 1177/2012 ሲባል ምን ለማለት ነው” በሚል ስለ አጭሯ መግለጫ የሚጠይቁት ምንጮቹ “ፍርድ ቤት ራሱ ክሱ በዝርዝር ሳይቀርብ እና ሳይነበብ ቀድሞ ለህዝብ ለሚዲያ መገለጹ ተገቢ አይደለም ማለቱ ስለማይቀር ክስ መመስረቱን ብቻ ለማሳወቅ ነው” ሲሉም ነው መግለጫው ተከፈተ የተባለውን ክስ የተመለከቱ ዝርዝር መረጃዎች ለህዝብና ለሚዲያ እንደሚሰጡበት የሚጠቆሙት፡፡
መግለጫው ክሱ ሰኞ ፍርድ ቤት ለሚቀርቡት ተጠርጣሪዎች ከተነበበ በኋላ በእለቱ አለበለዚያም ተከትለው ባሉት ቀናት ሊሰጥ ይችላል፡፡“ለዚህም ዝግጅቶች እየተደረጉ ነው፤ ሁሉም ሚዲያዎች ይጠራሉም” ተብሏል ምንጮቹ እንደሚያመለክቱት ከሆነ፡፡ምክትል ጠቅላይ ዐቃቤ ህጉን አቶ ፍቃዱ ጸጋን ጨምሮ በምርመራው ላይ ተሳትፎ ያላቸው ፖሊሶች ተገኝተው ዝርዝር መረጃዎች እንደሚሰጡም ይጠበቃል፡፡ዐቃቤ ህግ በጃዋር ሲራጅ መሀመድ፣ በቀለ ገርባ እና ሀምዛ አድናን እንዲሁም በሌሉበት የተከሰሱትን የኦሮሚያ ሜዲያ ኔትወርክ (OMN)፣ደጀኔ ጉተማ፣ዶ/ር ብርሃነመስቀል አበበ እና ፀጋዬ ረጋሳን ጨምሮ 10 ተደራራቢ ክሶች ማስከፈቱን መግለጹ የሚታወስ ነው፡፡
[አል አይን]