የሚኒስትሮች ምክር ቤት ትናንት ባካሄደው 89ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።
ምክር ቤቱ በቅድሚያ የተወያየው ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ለማቋቋም በቀረበ ረቂቅ ደንብ ላይ ሲሆን፥ በዚህም ከዚህ ቀደም በብረታ ብረት እና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ስር የነበሩና በብረታብረት፣ በአውቶሞቲቭ፣ በእርሻ መሳሪያዎች ምርት፣ የኤሌክትሪክና ኤሌክትሮኒክስ፣ የኮንስትራክሽን ማሽነሪና ፕላንት እንዲሁም የፖሊመር ምርት ዘርፎች የተሰማሩትን ተቋማት ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ስር በማደራጀት የሃብት አጠቃቀሙን ውጤታማ ለማድረግ እና ወደ አትራፊነት እንዲሸጋገር ለማስቻል የማቋቋሚያ ረቂቅ ደንብ ለውሳኔ ቀርቧል።
ምክር ቤቱም በቀረበው ረቂቅ ደንብ ላይ ከተወያየ በኋላ የተሰጡ ግብአቶች ተካተው ረቂቅ ደንቡ በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ በስራ ላይ እንዲውል ውሳኔ አሳልፏል።
በመቀጠልም ምክር ቤቱ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ ፌዴሬኝን መካከል የኒኩሌር ሀይልን ለሰላማዊ ዓላማ ለመጠቀም የተደረገ የትብብር ስምምነት ማጽደቂያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።
በዚህም ሁለቱ ሀገራት የ1968ቱ የኒኩሌር መሳሪያዎች እሽቅድምድምን የሚከለክለውን ዓለም አቀፍ ስምምነት እና ከዓለም አቀፉ አቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ጋር የገቡትን ስምምነት ባከበረ መልኩ የኒኩሌር ኢነርጂን ለሰላማዊ ዓላማዎች ጥቅም ላይ ማዋላቸው በሀገራቱ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እድገት ጉልህ አስተዋጽኦ ያለው መሆኑን በመግለፅ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የማጽደቂያ ረቂቅ አዋጁን አዘጋጅቶ አቅርቧል።
#PMOEthiopia
@YeneTube @FikerAssefa

በኡጋንዳ ከ 200 በላይ ታራሚዎች ለእስር ቤት አመለጡ!
ከ 200 በላይ ታራሚዎች በሰሜን ምስራቅ ከሚገኝ እስር ቤት ማምለጣቸው ተሰምቷል፡፡ የጸጥታ ሀይሎች የህዝቡን ትብብር እየጠየቁና እያሰሱ ናቸው፡፡ሞሮቶ ከተሰኘው ማረሚያ ቤት ሲያመልጡ እስረኞቹ ወታደር ገድለዋል ተብሏል፡፡ጦር ሀይሉና የእስር ቤቱ ጥበቃዎች 15 ሽጉጦችና በርካታ ጥይቶች ይዘው የተሰወሩትን እስረኞች እያሰሱ ናቸው፡፡
የጦር ሀይሉ ቃል አቀባይ እንደተናገሩት 2 እስረኞች ተገድለዋል 2 ሌላ እስረኞች ደግሞ በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡ማረሚያ ቤቱ ከ ሞሮቶ ተራራ ስር የተገነባ ነው፡፡እንደ አሶሴትድ ፕሬስ ዘገባ ከሆነ እስረኞቹ በቀላሉ እናዳይለዩ ቢጫ ዩኒፎርማቸውን በማውለቅ ነው ወደ ተራራው መውጣት የጀመሩት፡፡የተኩስ ልውውጡ በሞሮቶ አከባቢ ያለ የንግድም ሆነ ማንኛውንም መደበኛም እንቅስቃሴ አስቁሟል፡፡ሞሮቶ በከብት ዝርፍያና በጦር መሳርያ ጥቃት የምትተወቀው ካራሞጃ ውስጥ የምትገኝ ትልቅ ከተማ ነች፡፡
[Ethio FM & AP]

በአዲስ አበባ በነሐሴ አጋማሽ ከነበረው የኮሮና ቫይረስ ምርመራ አቅም አሁን ላይ መቀነሱን የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ገልጿል፡፡
በሀገር አቅፍ ደረጃ እስካሁን የኮሮና ቫይረስ ምርመራ የተደረገላቸው ሰዎች ቁጥር አንድ ሚሊዮን ሁለት መቶ ሺህ ተጠግቷል፡፡በአዲስ አበባ የላብራቶሪ ቁጥርም በመጨመር በቀን እስከ 6 ሺህ ሰዎችን መመርመር ተችሏል፡፡ይሁን እንጂ አሁን ላይ የመመርመር አቅሙ በግማሽ ቀንሷል አሐዱ ሬዲዮ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እያሻቀበ የመመርመር አቅሙ ለምን ሊቀንስ ቻለ ሲል ጠይቆ የአዲስ አበባ ጤና ቢሮም የመመርመሪያ ማሽኖች ዝግጅት ማነስ ነው ብሏል፡፡

ዩ.ኤስ.ኤይድ በአፋር ክልል በጎርፍ ለተፈናቀሉ ዜጎች የ650 ሺህ ዶላር የአስቸኳይ ጊዜ ድጋፍ አደረገ!
የአሜሪካ ልማት ተራድኦ ድርጅት (ዩ.ኤስ.ኤይድ) በአፋር ክልል በጎርፍ ለተጎዱ ዜጎች የ650 ሺህ ዶላር የአስቸኳይ ጊዜ ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ፡፡ ድርጅቱ ድጋፉ ለህይወት አድን ስራዎች እንደሚውል ነው የገለጸው፡፡ እንዲሁም በተለያዩ ወረዳዎች ውስጥ ምግብ ነክ ያልሆኑ ድጋፎችና በጎርፍ ለተጎዱ ዜጎች መጠለያ ማቅረብን እንደሚጨምር ነው የጠቀሱት፡፡
[FBC]

አቶ ልደቱ አያሌው ያልተፈቀደ የጦር መሳሪያ በመያዝ ወንጀል ክስ ቀረበባቸው!
አቶ ልደቱ አያሌው የጦር መሳሪያ አስተዳደር አዋጅ 1177/2012 አንቀጽ 22 ንዑስ አንቀጽ 3ትን በመተላለፍ ያልተፈቀደ የጦር መሳሪያ በመያዝ ወንጀል ክስ ቀረበባቸው።ክሱ በምስራቅ ሸዋ ዞን ጠቅላይ አቃቤ ህግ የቀረበባቸው ሲሆን በዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው ክስ የተመሰረተባቸው።
አቶ ልደቱ ከዚህ በፊት በሰኔ 23 እና 24 በቢሾፍቱ ከተማ አመጽና ሁከት እንዲቀሰቀስ በገንዘብ ሲደግፉና ሲያስተባብሩ ነበር ተብለው ምርምራ ሲከናወንባቸው እንደነበረ የሚታወስ ነው።ይሁንና አቃቤ ህግ በዚህ ምርመራ ላይ ፍቃድ የሌላቸው የጦር መሳሪያ አግኝቼባቸዋለሁ በማለት ነው ህገወጥ የጦር መሳሪያ ይዞ መገኘት ወንጀል ክስ ያቀረበባቸው።በአሁኑ ወቅት በፍርድ ቤቱ ጉዳያቸው እየታየ እንደሚገኝ ኤፍቢሲ ዘግቧል።

ባለፈው ሳምንት የሽብርተኝነት ክስ የተመሰረተባቸው እነ እስክንድር ነጋ ዛሬ ሐሙስ መስከረም 7፤ 2013 ፍርድ ቤት ቀረቡ።
የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ሊቀመንበር በሆኑት አቶ እስክንድር እና ሌሎች ስድስት ተከሳሾች ላይ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ያቀረበው ክስ ባለፈው ሳምንት ሐሙስ ለተጠርጣሪዎቹ እንዲደርስ ቢደረግም በችሎት በንባብ አልቀረበም።የተከሳሾቹን ጉዳይ የሚመለከተው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የጸረ ሽብር እና የህገመንግስት ጉዳዮች አንደኛ ችሎት በዛሬው ውሎው ክሱን በንባብ አሰምቷል። ከዚህ በተጨማሪም አቃቤ ህግ እና የተከሳሽ ጠበቆች "የዋስትና መብት ሊፈቀድ ይገባል፤ አይገባም" በሚል ያደረጉትን ክርክር አድምጧል። ችሎቱ በተከሳሾች የዋስትና መብት ላይ ብይን ለመስጠት ለመጪው ማክሰኞ መስከረም 12፤ 2013 ቀጠሮ ሰጥቷል።
[ኢትዮጵያ ኢንሳይደር]

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ነባሮቹን የብር ኖቶች በአዲስ የመቀየር ሥራ በይፋ መጀመሩን አስታወቀ!
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በፌስቡክ ገፁ እንደገለፀው ከሆነ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዢ ዶ/ር ይናገር ደሴ እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ አዲስ አበባ ቅርንጫፍ በመገኘት አዲሱን የብር ኖቶች ሥርጭት ያስጀመሩ ሲሆን አዳዲስ የብር ኖቶችን በመጠቀምም የመጀመሪያዎቹ ሆነዋል፡፡
ትላንት የተጀመረው አዳዲስ የብር ኖቶችን የማሰራጨት ሥራ በጥቂት ቀናት ውስጥ ወደ ክልሎች ማሰራጨት እንደሚጀመር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዢ ዶ/ር ይናገር ደሴ ገልፀዋል፡፡
ይህ ከፍተኛ ዝግጅት የሚጠይቅ የብር ኖቶችን የመቀየር ሥራ በተሟላ መልኩ ተጠናቅቆ በመጀመሩ ደስታ እንደተሰማቸው ዶ/ር ይናገር አክለው የገለፁ ሲሆን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ በበኩላቸው ህብረተሰቡ አሮጌውን ብር በመመለስና አዳዲሶችን የብር ኖቶች በመውሰድ ብሩን የመቀየር ሂደት እንዲያቀላጥፍ አሳስበው፤ ከአምስት ሺህ ብር በላይ መቀየር የሚፈልግ ተጠቃሚ ነባር የባንክ ደብተር ከሌለው አዲስ መክፈት እንደሚጠበቅበትም ገልፀዋል፡፡

በኢትዮጵያ መስማት ለተሳናቸው ዜጎች የተሸከርካሪ መንጃ ፍቃድ ሊሰጥ ነው!
በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ መስማት ለተሳናቸው ዜጎች የተሸከርካሪ መንጃ ፍቃድ ሊሰጥ መሆኑን መስማት የተሳናቸው ማህበር አስታውቋል።ማኅበሩ ከ1967 ዓ.ም ጀምሮ ላለፉት ለ45 ዓመታት ሲጠይቀው የነበረው የተሸከርካሪ መንጃ ፍቃድ ጉዳይ አሁን መፈቀዱ ትልቅ ደስታ መፍጠሩን የማህበሩ ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ትዕግስት ዓለማየሁ ገልፀዋል።ወደ ተግባር ለመቀየር ቀሪ የቤት ስራዎች መኖራቸውን የገለፁት ወ/ሮ ትዕግስት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች እና ከትራፊክ ፖሊስ በጋር የሚሰሩ በተሽከርካሪ ላይ የሚለጠፉ ምልክቶች ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ገልፀዋል።ሮቤል አምሃ የተባለ መስማት የተሳው ወጣት በበኩሉ በተለይ ለኢቲቪ እንደገለፀው “መስማት ለተሳናቸው የተሸከርካሪ መንጃ ፍቃድ እንዲሰጥ በመወሰኑ ደስተኛ ነኝ፤ ኩራት ተስምቶኛል፤ እኛ ከዚህ በኋላ በግልም ሆነ በመንግስት የስራ እድል እንድናገኝ ያስችለናል” ብሏል።
በህብረተሰቡ ውስጥ ያለው የተሳሳተ አመለካከትን ለማስተካከል የግንዛቤ ማሳደጊያ ስራዎችን መስራት እንደሚገባ ደግሞ ያሳሰቡት የማህበሩ አባል አቶ ንጉሴ ሞገስ ናቸው።የትራፊክ ባለሙያዎችም የምልክት ቋንቋ እንዲማሩ ማድረግ ተገቢ መሆኑም ተጠቁሟል።መንጃ ፍቃዱን ተግባራዊ ለማድረግ የአሽካርካሪ ማሰልጠኛ ተቋማት መስማት ለተሳናቸው ምቹ በማድረግ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ የኢትዮጵያ የአካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ወ/ሮ ምህረት ንጉሴ ተናግረዋል።ኢትዮጵያ፣ ኬንያን፣ ኡጋንዳን፣ ታንዛኒያን ጨምሮ በአፍሪካ መስማት ለተሳናቸው የተሸከርካሪ መንጃ ፍቃድ ለመስጠት ፈቃደ የሰጠች 23ኛ ሀገር ሆናለች።
[ETV]

ባይቶና የተሰጠን አንድ ወንበር አይገባንም አለ!
በቅርቡ በተካሄደው የትግራይ ክልል ምርጫ ላይ ከተሳተፉት ፓርቲዎች መካከል አንዱ የሆነው ባይቶና አባይ ትግራይ የተሰጠን ወንበር አይገባንም አለ።ፓርቲው ዛሬ [ሐሙስ] ባወጣው መግለጫ "የምርጫው ፍትህዊነትና ዴሞክራሲያዊነት ተበላሽቷል" ብሏል።ምርጫውን ገዢው ፓርቲ ህወሓት ከ98 በመቶ በላይ የመራጮችን ድምፅ በማግኘት እንዳሸነፈ መገለጹ ይታወሳል።በአዲሱ የክልሉ ምክር ቤት የመቀመጫ ድልድል ሕግ መሠረት ህወሓት ካገኛቸው 152 የምክር ቤት መቀመጫዎች በተጨማሪ 38 ወንበሮች ለተቃዋሚ ፓርቲዎች ይከፋፈላሉ ተብሎ ተጠብቆ ነበር።ነገር ግን የምርጫ ኮሚሽኑ ባወጣው ውጤት መሠረት ህወሓት 189 ወንበሮች ሲያገኝ 1 ወንበር ደግሞ ባይቶና ማግኘቱ ተነግሯል።
ነገር ግን ባይቶና ዛሬ ባወጣው መግለጫ "ውሳኔው ባንቀበለውም ሕግን እናከብራለን። በሕጉ መሠረት ደግሞ ይህ ወንበር ለእኛ ይገባናል ብለን አናምንም" ብሏል።ከትግራይ ክልል ምርጫ በፊት የወጣው ሕግ 20 በመቶ ወንበሮች በተፎካካሪ መካከል የሚከፋፈል ነው ይላል። ነገር ግን ይህ ሕግ በጊዜው ከተፎካካሪ ፓርቲዎች ተቃውሞ ገጥሞት ነበር።ፓርቲው በመግለጫው "የትግራይ የምርጫ አዋጅ ከመጀመሪያውም ህወሓትን ለማገልገል የወጣ ነው ብለን እናምናለን" ብሏል።"ይሁን እንጂ በቀመሩ መሠረት እኛ የደርስንበት የተሰጠን የሕዝብ ድምፅ ወንበር ለማግኘት የሚበቃ እንዳልሆነ ነው" ይላል መግለጫው አክሎ።ይሁን እንጂ ባይቶና፤ ለእኛ እንደሚገባ የሚያረጋግጥ የሕግ አገባብ ወይም ስሌት ካለ የተሰጠንን ወንበር በፀጋ ለመቀበል ዝግጁ ነን ይላል።
ፓርቲው የትግራይ ሕዝብ ምርጫውን ለማሳካት ላደረገው አስተዋፅዖ ክብር እንዳለው በመግለጫው አትቷል። አክሎም ለምርጫ ኮሚሽኑ ለክልሉ የፀጥታ ኃይሎችም ምስጋናውን አቅርቧል።ፓርቲው በምርጫው ቀንና ከምርጫው በኋላ አጋጠመ ያለውን እንቅፋት በተመለከተም መልዕክት አስተላልፏል።"ማንን እንደመረጣችሁ እናውቃለን"፤ "ከምርጫው በኋላም የት እንደምትገቡ እናያለን"፤ "ምርጫው እስኪያልቅ ድረስ ከተቃዋሚ ፓርቲ ዕጩዎች ጋር እንዳትታዩ" የሚሉ ኢ-ሕገ መንግሥታዊ ማስፈራራቶች የደረሱባቸው ሰዎች እንዳሉ ገልጿል።አልፎም የህወሓት መዋቅር ቤት ለቤት እየዞሩ ባይቶና ላይ የሠሩት ስም ማጥፋት በምርጫው ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እንዳሳደረበት ፓርቲው ገልጿል።ጳጉሜ 04/2012 ዓ.ም በትግራይ ክልል ምርጫ የተካሄደው ምርጫን በተመለከተ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ሕጋዊ ያልሆነ እና ተፈጻሚነት የሌለው እንዳለው ይታወሳል።
[BBC]

“የአብርሃም ስምምነትን” ተከትሎ እስራኤል እና ፍልስጤም ድርድር እንዲያደርጉ የተመድ ዋና ጸሐፊ አሳሰቡ!
ስምምነቱ ለፍልስጤም እና እስራኤል ችግር መፍትሔ ለማምጣት እንደሚረዳ ዋና ጸሐፊው ገልጸዋል፡፡ከዩኤኢ ጋር በተደረሰ ስምምነት መሰረት እስራኤል የዌስት ባንክን ግዛቶች የመቆጣጠር እቅዷን መሰረዟ ይታወቃል፡፡
[Al ain]
@YeneTube @FikerAssefa
ስምምነቱ ለፍልስጤም እና እስራኤል ችግር መፍትሔ ለማምጣት እንደሚረዳ ዋና ጸሐፊው ገልጸዋል፡፡ከዩኤኢ ጋር በተደረሰ ስምምነት መሰረት እስራኤል የዌስት ባንክን ግዛቶች የመቆጣጠር እቅዷን መሰረዟ ይታወቃል፡፡
[Al ain]
@YeneTube @FikerAssefa
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የተከሰተውን ግድያ እና መፈናቀል አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የተሰጠ ይፋዊ መግለጫ
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የተከሰተውን ግድያ እና መፈናቀል አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የተሰጠ ይፋዊ መግለጫ @YeneTube @FikerAssefa
የኢሰመኮ ይፋዊ መግለጫ
በቤኒሻንጉል-ጉሙዝ ክልል የተከሰተውን ግድያ እና መፈናቀል አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የተሰጠ ይፋዊ መግለጫ
(አሶሳ፤ መስከረም 7 ቀን 2013 ዓ.ም.) የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኮሚሽኑ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በአንዳንድ አካባቢዎች እየታዩ ያሉ የፀጥታ መደፍረሶችን ተከትሎ ያጋጠሙ ክስተቶች እጅግ አሳስበውታል፡፡ኮሚሽኑ ከክልሉ ከመተከል ዞን፣ ቡለን ወረዳ አጳር ቀበሌ እንዲሁም ከወንበራ ወረዳ መልካን ቀበሌ እጅግ አሳሳቢ መረጃዎች እየደረሱት ነው፡፡ኮሚሽኑ በጳጉሜ 1፤ 2012 ዓ.ም እንዲሁም ከጳጉሜ 2 አስከ መስከረም 3፤2013 ዓ.ም መካከል ቢያንስ ሁለት ጥቃቶች ማጋጠማቸውን ከክልሉ መንግስት ለማረጋጥ ችሏል፡፡በቦታው ላይ ከሚገኝ አንድ መንግስታዊ ምንጭ መረዳት እንደተቻለው ቢያንስ በሁለት ዙር በደረሱ ጥቃቶች ባልታጠቁ ሲቪሎች ላይ ግድያዎች መፈፀማቸውን እንዲሁም በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መፈናቀላቸውን ኮሚሽኑ ማረጋገጥ ችሏል፡፡የክልሉ መንግስት እንደጠቆመው ከተፈናቃዮቹ መካከል 300 ያህል የሚሆኑት ወደ ቀያቸው የተመለሱ ሲሆን የሀገር መከላከያ ሰራዊት እና የፌደራል ፖሊስ ከክልሉ የፀጥታ ኃይሎች ጋር በመተባበር አካባቢውን ለማረጋጋት እየሰሩ ነው፡፡
ስለሆነም ኮሚሽኑ፡-
👉በክልሉ ባልታጠቁ ሲቪሎች ላይ የደረሱትን ጥቃቶች፣ ግድያዎች እና መፈናቀሎችን ሙሉ በሙሉ ያወግዛል፤
👉በክልሉ ሰላምና መረጋጋት እንዲኖር በመከላከያ ሰራዊት፣በፌዴራል ፖሊስ እና በክልል የጸጥታ ኃይሎች ሰላምን ለማስጠበቅ እየተደረገ ያለውን ጥረት ያበረታታል፤
👉በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ሕገ-መንግስትና እንዲሁም ኢትዮጵያ ተቀብላ ባጸደቀቻቸው የቃል ኪዳን ሰነዶች ማለትም፡ በአፍሪካ የሰብዓዊና ሕዝቦች መብቶች ቻርተር፣ በአለም አቀፍ የሲቪል እና የፖለቲካ መብቶች ቃል ኪዳን (ICCPR) እና በሌሎች አግባብነት ባላቸው የሰብአዊ መብቶት ሰነዶች የተደነገጉትን በሕይወት የመኖር መብቶች እንዲከበሩ ይጠይቃል፤
👉በክልሉ ከዚህ ቀደምም ተመሳሳይ ጥቃቶች በተደጋጋሚ ማጋጠማቸውን ከግምት ውስጥ በማስገባት፤ ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸው አካላት ገለልተኛ፣ ፈጣን እና ውጤታማ ምርመራዎችን በማካሄድ ግድያው በተከሰተባቸው ሁኔታዎች ላይ የጥፋተኞችን ተጠያቂነት እንዲያረጋግጡ ያሳስባል፤
👉የሚመለከታቸው የክልሉ መንግስት አካላት ተጎጂዎች እና ቤተሰቦቻቸው ወደ ቀደመ ህይወታቸው የሚመለሱበትን መንገድ እንዲያመቻቹ ጥሪ ያቀርባል፤
👉ኮሚሽኑ በተለይም መሰረታዊ የሆነው በህይወት የመኖር መብት ይረጋገጥ ዘንድ የሚመለከታቸው የክልሉ የመንግስት አካላት እንዲሰሩ ያሳስባል፡፡በአጠቃላይ ኮሚሽኑ ሁሉም የፖለቲካ ቡድኖች እና ባለድርሻ አካላት ገንቢ ውይይት እንዲያደርጉ እና ከማንኛውም ዓይነት የሁከት ድርጊቶች እንዲታቀቡ ጥሪውን ያቀርባል፡እንዲሁም በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ-መንግስት እና ኢትዮጵያ ፈርማ የተቀበለቻቸውን ሌሎች አግባብነት ያላቸውን የሰብአዊ መብት ድንጋጌዎች ውስጥ የተቀመጡ መብቶችን እና ግዴታዎችን እንዲያከብሩ ኮሚሽኑ እየጠየቀ፤ በቀጣይም ጉዳዩን በንቃት እንደሚከታተለው ይገልፃል፡፡

ዓባይ ባንክ ጠቅላላ ሐብቱ 22 ቢሊየን ብር መድረሱን አስታወቀ!
ዓባይ ባንክ በአስር ዓመታት ጉዞው ጠቅላላ ሐብቱ 22 ቢሊየን ብር እንዲሁም ተቀማጩ 17.6 ቢሊየን ብር መድረሱን አስታውቋል፡፡ባንኩ የ10ኛ አመት ምስረታ በዓሉን እያከበረ ነው፡፡የዓባይ ባንክ ዋና የሪቴል ባንኪንግ ባለሙያ አቶ በለጠ ዳኛው ባንኩ በ10 አመታት ውስጥ በዘርፉ ስኬታማ ውጤት እንዳስመዘገበ ተናግረዋል፡፡በዚህም በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች 235 ቅርንጫፎችን መክፈቱን የገለጹት አቶ በለጠ፣ ደንበኞችን ከማፍራት እና የቁጠባን ስራ ከማሳደግ አኳያ በላቀ ደረጃ እየተሰራ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
የአለም አቀፍ የባንክ አሰራር ለደንበኞች ፈጣን የአገልግሎት መስጠት ከጀመረ ወራቶች አስቆጥረዋል ያሉት ባለሙያው፣ የባንኩን አገልግሎት ለሁሉም ተደራሽ ለማድረግ ለትምህርት ቤቶች፣ ለውሃ እና ለመብራት ክፍያ አመቺ እንዲሆን “ዩኒካሽ” የተሰኘ የሞባይል መተግበሪያ ተጠቅሞ ደንበኞች በስልካቸው መክፈል እንዲችሉ እየሰራ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡በኢትዮጵያ አዲስ የታተመ የብር ኖቶች ላይ ለሰራተኞች እና ለደንበኞቹ በተለይ በህገወጥ መንገድ የሚሰራጩ የሐሰት ብሮችን ለመከላከል የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ማጠናቀቁን አስታውቀዋል፡፡ባንኩ ከ4ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ እድል መፍጠሩ ታውቋል፡፡
[Walta]

ከቤንሻንጉል ጉምዝ በፀጥታ ችግር ምክንያት ከቀያቸው የተፈናቀሉ ከ25 ሺህ በላይ ዜጎች ወደ መኖሪያቸው መመለሱን የመከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ!
በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል የተፈጠሩ ችግሮችን ለማረጋጋት የመከላከያ ሰራዊት በወሰደው ሁሉን አቀፍ ዘመቻ በግጭት ምክንያት ከቀያቸው የተፈናቀሉ ከ25 ሺህ በላይ ዜጎች ወደ መኖሪያቸው እንዲመለሱ ማድረጉን የመከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት ሜጀር ጀኔራል መሀመድ ተሰማ ሰሞነኛ ጉዳዮችን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ በክልሉ የተፈጠረው የፀጥታ ችግር ከክልሉ የፀጥታ ኃይሎች አቅም በላይ አልነበረም ሊከሰትም አይገባው ነበር ብለዋል።ችግሩ በተፈጠረበት ሰዓት መከላከያ የራሱ ተልዕኮ ላይ ነበር ያሉት ሜጀር ጀኔራሉ ሠራዊቱ ወደ ስፍራው በማቅናት የአከባቢውን ሰላምና ደህንነት የማስከበር ስራ በጀግንነት ተሰርቷል ብለዋል።
መከላከያ ከገባ በኋላ በአጥፊዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ በመውሰዱ አሁን በክልሉ ያለው ሁኔታ ወደ ቀድሞ ሰላማዊና መረጋጋት እንቅስቃሴ መመለሱንም አስታውቀዋል።በማህበራዊ ሚዲያዎች “መካላከያ ቀድሞ ወደ ስፍራው አልደረሰም” በሚል እየተናፈሰ ያለው መረጃ ከእውነት የራቀ መሆኑንም ነው ሜጀር ጄነራሉ የተናገሩት።በክልሎች የፀጥታ ችግሮች ሲከሰቱ የማረጋጋት ግዴታ በዋናነት የክልልና የወረዳ የጸጥታ ኃይል ነው ያሉት ሜጀር ጄነራሉ መከላከያ የራሱ ግዳጆች ቢኖሩትም ከክልሎቹ አቅም በላይ የሆነ የፀጥታ ችግር ሲያጋጥም አስፈላጊውን እርምጃ እየወሰደ ይገኛል ብለዋል።በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል መከላከያ ግዳጅ እንደተሰጠው ከ150 ኪሎ ሜትር ውስጥ 50 ኪሎ ሜትሩን በእግሩ በመጓዝ በታጣቂዎች ላይ አስፈላጊውን እርምጃ መውሰዱንም ነው የተገለፀው።በአሁኑ ሰአት አከባቢው ወደ ሰላምና መረጋጋት መመለሱን ነው የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሜጀር ጀኔራል መሀመድ ተሰማ በመግለጫቸው የገለፁት።

በኢትዮጵያ በ10 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንት 25 ጊጋ ዋት ተጨማሪ ኃይል ለማመንጨት ፍላጎት እንዳለው አንድ ዓለም አቀፍ ተቋም አስታወቀ!
የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር 25 ጊጋ ዋት ተጨማሪ ኃይል ለማመንጨት የሚያስችል ውይይት ፎርቲስኪው ከተባለ ዓለም አቀፍ ድርጅት ጋር አካሂዷል።ድርጅቱ 15 ጊጋ ዋት ከውኃና 10 ጊጋ ዋት ከጂኦ ተርማል ለማመንጨት እና 10 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስት ለማድረግ እንደሚፈልግ አስታውቋል።የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ ይህ ለኢትዮጵያ ትልቅ እድል ነው ሲሉ ገልጸዋል።አሁን በኢትዮጵያ 45 በመቶ ብቻ የሆነውን የኃይል ተደራሽነት ለማሻሻል መንግሥት በቅርቡ ሪፎርም ማድረጉን የገለጹት ሚኒስትሩ አሁን ላይ አነስተኛ የሆነውን የኃይል ተደራሽነትን ለማሻሻል ንፁህና ታዳሽ ኃይል በማልማት፣ ዘርፉንም ፋይናንስ በማድረግ፤ የግሉን ባለሃብት የማሳተፍ እንዲሁም ጠንካራ ተቋማትን የመገንባት ሥራ እየተሠራ መሆኑን አብራርተውላቸዋል።
በተለይም እ.አ.አ. በ2030 ኢትዮጵያ ለዜጎቿ መቶ በመቶ ኃይል ለማቅረብ ያቀደች በመሆኑ ይህ ውይይትና የድርጅቱ ተነሳሽነት ጠቀሜታ ያለው ነው ብለዋል።ፎርቲስኪው የተሰኘው የዓለም አቀፍ ድርጅት በአውስትራሊያ በጊኒና በሌሎችም ሃገራት ተመሳሳይ ሥራ በመሥራት ውጤታማ እንደነበር ገልጸው በኢትዮጵያ 25 ጊጋ ዋት ሃይል ለማመንጨት ያላቸውን ፍላጎት ለሚኒስትሩ ገልጸውላቸዋል።ፎርቲስኪው በማዕድን፣ በማዳበሪያ፣ በኃይል ማመንጨት፣ በንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት እና በሌሎችም ሥራዎች ላይ የመሰማራት ፍላጎት እንዳለውም ከውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

የትግራይ ክልል መንግስት በአፋር ክልል በጎርፍ ምክንያት ለተፈናቀሉ ዜጎች ድጋፍ አደረገ!
የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በአፋር ክልል በጎርፍ ኣደጋ ምክንያት ከመኖሪያቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች የተለያዩ ድጋፎችን አደረገ። የክልሉ መንግስት በጎርፍ ምክንያት ለተፈናቀሉ ዜጎች ያደረገው ከ5 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመቱ የተለያዩ የምግብ ግብአቶችና ቁሳቁሶች ድጋፍ ማድረጉን የክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ አስታውቋል።

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 689 ሰዎች በኮሮና ሲያዙ የ 15 ሰዎች ህይወት አለፈ!
ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 10,605 የላቦራቶሪ ምርመራ ተጨማሪ 689 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡420 ሰዎች ሲያገግሙ 15 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።እስካሁን በአጠቃላይ 66 ሺ 913 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ 27 ሺ 085 ሰዎች ያገገሙ ሲሆን የ 1,060 ሰዎች ህይወት ማለፉን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል።

ዛሬ መስከረም 08 ቀን 2013 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 5ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ አስቸኳይ ስብሰባውን ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ በጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ ማካሄድ ይጀምራል፡፡
[HPR]
@YeneTube @FikerAssefa
[HPR]
@YeneTube @FikerAssefa
የሊቢያ የአንድነት መንግስት ሃላፊ ስልጣን ለመልቀቅ ዝግጁ ነኝ አሉ!
በተባበሩት መንግስታት እውቅና ያለው የሊቢያ ብሄራዊ ስምምነት መንግስት የሰላም ስምምነቱን ለማስኬድ ሲባል በ6 ሳምንታት ውስጥ ስልጣን እንደሚለቁ አስታውቀዋል፡፡ባለፈው ወር ሁለቱ ኃይሎች ለሰላም ስምምት ሞሮኮ በመገናኘት ድንገተኛ የሆነ የተኩስ አቁም ስምምነት አድርገው፣ብሄራዊ ምርጫ ለማካሄድ ቃል ገብተው ነበር፡፡
[Al ain]
@YeneTube @FikerAssefa
በተባበሩት መንግስታት እውቅና ያለው የሊቢያ ብሄራዊ ስምምነት መንግስት የሰላም ስምምነቱን ለማስኬድ ሲባል በ6 ሳምንታት ውስጥ ስልጣን እንደሚለቁ አስታውቀዋል፡፡ባለፈው ወር ሁለቱ ኃይሎች ለሰላም ስምምት ሞሮኮ በመገናኘት ድንገተኛ የሆነ የተኩስ አቁም ስምምነት አድርገው፣ብሄራዊ ምርጫ ለማካሄድ ቃል ገብተው ነበር፡፡
[Al ain]
@YeneTube @FikerAssefa
ፎርቲስኪው በኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች የመሰማራት ፍላጎት አለው!
በማዕድን ፣ በማዳበሪያ፣ በኃይል ማመንጨት፣ በሃይድሮጂን ምርት እና በሌሎችም ሥራዎች ላይ የተሰማራው ፎርቲስኪው በኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች የመሰማራት ፍላጎት እንዳለው አስታውቋል፡፡ድርጅቱ በማዕድን ልማት፣ በማዳበሪያ አቅርቦትና በሃይድሮጂን ምርት ሲሰማራ የሚያስፈልገውን ኃይል በራሱ ከማሟላት ባሻገር የሚያመርተውን ኃይል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመሮችና የኃይል ቋት በመጠቀም እስከ 25 ጊጋ ዋት ኃይል ለማመንጨት ፍላጎት አለው፡፡የፎርቲስኪው እንቅስቃሴ የሀገሪቱን የኃይል አቅርቦት በከፍተኛ ሁኔታ በማሻሻል ኤሌክትሪክ ለሁሉም ለማዳረስ የሚደረገውን ጥረት እንደሚያግዝ ታምኖበታል፡፡ድርጅቱ ከኢትዮጵያ ጋር በመሆን በሀገሪቱ የተጀመረውን የአረንጓዴ ልማት ስትራቴጂ በማሳካት በአህጉሪቱ በቀዳሚነት ለመሰለፍ ማለሙን ይፋ አድርጓል፡፡
[EEPCo]