ባለፋት 24 ሰዓታት በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር በተደረገ 307 የናሙና ምርመራ 13 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል። በአስተዳደሩ እስካሁን ድረስ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥርም 794 ደርሷል።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ 391 ሰዎች በተደረገው የላብራቶሪ ምርመራ 16 ሰዎች ላይ የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸዉ ተገለጸ፡፡
ከክልሉ ላብራቶሪ ምርመራ ማዕከል የተገኘዉ መረጃ እንደሚያመላክተዉ በአጠቃላይ ምርመራ የተደረገላቸው ሰዎች ቁጥር 15,286 ደርሷል፡፡በክልሉ እስካ አሁን ድረስ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸዉ ሰዎች ቁጥር 441 የደረሰ ሲሆን ከእነዚህ መካከል 196 ግለሰቦች በተደረገላቸዉ የህክምና ክትትልና ድጋፍ አገግመዉ ወደ ማህበረሰቡ ተቀላቅለዋል፡፡

በአማራ ክልል ተጨማሪ 121 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ተገኘባቸው፤ የሁለት ሰዎች ሕይወት አልፏል፤ 26 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል።
ባለፉት 24 ሰዓታት ለ 4 ሺህ 442 ናሙናዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ በ 121 ሰዎች ላይ ቫይረሱ መገኘቱን የአማራ ክልል ጤና ቢሮ አስታውቋል። ይህንን ተከትሎም አጠቃላይ በክልሉ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ወደ 1 ሺህ 772 ከፍ ብሏል።
@YeneTube @FikerAssefa
ባለፉት 24 ሰዓታት ለ 4 ሺህ 442 ናሙናዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ በ 121 ሰዎች ላይ ቫይረሱ መገኘቱን የአማራ ክልል ጤና ቢሮ አስታውቋል። ይህንን ተከትሎም አጠቃላይ በክልሉ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ወደ 1 ሺህ 772 ከፍ ብሏል።
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 1,368 ሰዎች በኮቪድ-19 ሲያዙ፣ 25 ሰዎች ደግሞ ህይወታቸው አልፏል!
ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገው 19,776 የላብራቶሪ ምርመራ 1,368 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ25 ሰዎች ህይወት አልፏል።በተጨማሪም 567 ሰዎች አገግመዋል።በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 39,033 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 662 ደርሷል፤ አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 14,480 ደርሷል።

የወላይታ ዞን አመራሮች ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ ተወሰነ!
በደቡብ ክልል የብልጽግና ፓርቲ አስተባባሪ ኮሚቴ በወላይታ ዞን የፓርቲው አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት ከፓርቲው እና ከመንግስት ስራ ኃላፊነታቸው ከትላንት በስቲያ ሐሙስ ነሐሴ 14፤ 2012 ጀምሮ እንዲነሱ መወሰኑን አስታወቀ። የወላይታ ዞን አመራሮች "ለውጡን በጉልበት ለመቀልበስ የተለያዩ ታክቲኮችን በመንደፍ፥ በክልል የመደራጀት ጥያቄ አመላለስ ለማወሳሰብ አቅደዉ በመፈፀም፣ በዞኑ ያለመረጋጋትና የንጹሃን ዜጎች ህይወት እንዲቀጠፍ ምክንያት ሆነዋል" ሲል አስተባባሪ ኮሚቴው ገልጿል።"የወላይታ ዞንን እንዲመሩ ኃላፊነት የወሰዱ አመራሮች ከፓርቲዉ ዲስፒሊንና ከተሰጣቸው ህዝባዊና መንግስታዊ ኃላፊነት በተቃራኒ በመቆም የህዝቡን ጥያቄ ሽፋን በማድረግ ለዉጡን ለማደናቀፍ በግልፅና በህቡዕ ተደራጅቶ ከሚንቀሳቀሱ የዉስጥ እና የውጪ ኃይሎች ጋር እየሰሩ እንዳሉ ተረጋግጧል" ሲል ኮሚቴው ዛሬ ማምሻውን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
[ኢትዮጵያ ኢንሳይደር]

#FakeNewsAlert
በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገፆች በአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ላይ በዛሬው እለት የተቃጣ የግድያ ሙከራ ከሸፈ በሚል እየተሰራጨ የሚገኝ መረጃ እንዳለ ተመልክተናል።ይሁንና በስም የተጠቀሱት ከፍተኛ አመራሮቻችን ማለትም አቶ ተመስገን ጥሩነህ ፤አቶ አገኘሁ ተሻገር ፤እንዲሁም ኮሚሽነር አበረ አዳሙ እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮቻችን ላይ ምንም አይነት የተቃጣ የግድያ ሙከራ የሌለና ልክ እንደወትሮው ሁሉ ያለምንም ችግር በስራ ላይ የሚገኙ መሆኑን እየገለፅን እንዲህ አይነት ህዝባችንን ለማደናገር የሚለቀቁ መረጃወች የሚለቀቁበት አላማና ፍላጎት ከማን እንደሚመነጭ በመረዳት መረጃወቹን ከማሰራጨት በፊት አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ ለማሳሰብ እንወዳለን።
-የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት

YeneTube
የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ፓርቲዎች በብሔራዊ መግባባት ላይ በኢሲኤ ባደረጉት ውይይት እንዲካፈል ጥሪ እንዳልቀረበለት አስታወቀ። @YeneTube @FikerAssefa
ኦነግ በዛሬው "ብሔራዊ መግባባት" ላይ በተደረገው ውይይት እንድካፈል ጥሪ አልቀረበልኝም ቢልም ቃል አቀባዩ አቶ ቀጀላ መርዳሳ ውይይቱን በተመለከተ ለኢቲቪ ዜና አስተያየት ሲሰጡ ተመልክተናል።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
ኃይሌ ጎርጎራ ላይ በአንድ ቢሊዮን ብር ሪዞርት ሊገነባ ነው!
ኃይሌ ሆቴሎች በጣና ዳርቻ ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ግዙፍና ዘመናዊ ሪዞርት ለማልማት እንዳቀደ ታወቀ፡፡ጎርጎራ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) በቀጣይ ለማልማት ካሰቧቸው ሦስት የቱሪስት መዳረሻዎች አንዱ ነው፡፡ ኃይሌ ኩባንያው በጎርጎራ በዓይነቱ ከዚህ በፊት ከተገነቡ ሪዞርቶች ለየት ያለ ሪዞርትና የመዝናኛ ማዕከል ለመገንባት እንዳቀደ ለሪፖርተር ተናግሯል፡፡ ሪዞርቱ የሚገነባው ቀድሞ ጎርጎራ ሆቴል ተብሎ በሚታወቀው በአሥር ሔክታር ቦታ ላይ ነው፡፡ ይህ ቦታ የቀድሞ የኢትዮጵያ ባህር ኃይል ማሠልጠኛና የቀድሞ ፕሬዚዳንት መንግሥቱ ኃይለ ማርያም ያርፉበት የነበረ ሥፍራ ነው፡፡
ፕሮጀክቱ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ሪዞርትና መዝናኛ ማዕከል፣ ሰው ሠራሽ ባህር ዳርቻና ቪላ ቤቶች ግንባታ ያጠቃልላል፡፡ ‹‹ጎርጎራ ድብቅ ገነት ነው፡፡ ውኃው ንፁህና ጥልቀት ያለው በመሆኑ ለዋናና ለጀልባ ሽርሽርና ሌሎች የውኃ ላይ ጨዋታዎች ምቹ ነው፤›› ያለው ኃይሌ፣ ኩባንያው የውጭ ባለሀብቶች በሽርክና ለማስገባት እያሰበ እንደሆነ ተናግሯል፡፡ ‹‹ብቻችንን የታለመውን ውጤት ላናመጣ እንችላለን፤›› ብሏል፡፡ኃይሌ ሪዞርት በሕግ ጉዳዮች ላይ እየሠራ ሲሆን፣ የፕሮጀክቱ የመጀመርያ ዙር ንድፍ ሥራ እንደተጀመረ ታውቋል፡፡
በተያያዘ ዜና ኃይሌ ሪዞርት በአዳማ ከተማ በ400 ሚሊዮን ብር የገነባው ባለ አራት ፎቅ ዘመናዊ ሆቴል ባለፈው ሳምንት ሥራ ጀምሯል፡፡በ12,000 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈው አዳማ ኃይሌ ሪዞርት 110 መኝታ ክፍሎች ያሉት ሲሆን፣ የመዋኛ ገንዳ፣ የልጆች መጫወቻ ሥፍራ፣ ጂምናዚየም፣ ስፓ፣ ምግብ ቤቶችና የተለያዩ መጠን ያላቸው የስብሰባ አዳራሾች አሟልቶ የያዘ ነው፡፡የሆቴሉ ግንባታ ሦስት ዓመት እንደፈጀ የገለጸው ኃይሌ፣ ሆቴሉ አንድ ዘመናዊ ሆቴል ሊኖረው የሚገባው አገልግሎቶች ሁሉ እንዲማሉ መደረጉን ገልጿል፡፡ ፕሮጀክቱ ከ400 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ እንደተደረገበት ተናግሯል፡፡ ኃይሌ ሪዞርት የማስፋፊያ ሥራ ለማከናወን ከአጠገቡ የሚገኘውን ባዶ ቦታ እንዲሰጠው ለአዳማ ከተማ አስተዳደር አመልክቷል፡፡
‹‹ምክር ቤቱ የሠራነውን ሥራ ተመልክቶ ከሆቴሉ አጠገብ ያለውን ባዶ ቦታ ቢፈቅዱልን ቅንጡ የእንግዳ ማረፊያ ቤቶች እንገነባበታለን፤›› ብሏል፡፡ የአዳማው ሆቴል ሙሉ በሙሉ ሥራ ሲጀምር ለ300 ዜጎች የሥራ ዕድል እንደሚፈጥር ታውቋል፡፡ኃይሌ ሪዞርት ሰባት ሆቴሎች ያሉት ሲሆን፣ 1,400 ሠራተኞች ያስተዳድራል፡፡ በቅርቡ የሐዋሳና አርባ ምንጭ ሆቴሎቹ የትሪፕ አድቫይዘር 2020 ሽልማት አሸናፊ ሆነዋል፡፡ኃይሌ ሪዞርት ሦስት ሆቴሎችን በአዲስ አበባ፣ ሶዶና ኮንሶ በመገንባት ላይ ሲሆን፣ በጎርጎራና ደብረ ብርሃን ዘመናዊ ሆቴሎች ግንባታ ለመጀመር በዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡‹‹የመንግሥት ቢሮዎች ቢሮክራሲን በመቀነስ የተቀላጠፈ አገልግሎት ቢሰጡን ተጨማሪ የኢንቨስትንመንት ፕሮጀክቶች ቀርፀን ተግባራዊ ማድረግ እንችላለን፡፡ የአርባ ምንጭ ሪዞርት ግንባታ አንድ ዓመት ከአምስት ወራት ብቻ ነው የፈጀብን፡፡ አገራችን ትልቅ የቱሪዝም ዕምቅ ሀብት አላት፡፡ ከእኛ የሚጠበቀው ጠንክሮ መሥራት ነው፤›› ብሏል፡፡ ቀጣዩ የኢንቨስትመንት መዳረሻው ደብረ ብርሃን እንደሆነች ኃይሌ አረጋግጧል፡፡
[Reporter]

ከፍተኛ የምዕራብ አፍሪካ ልዑካን ከመፈንቅለ መንግስት በኋላ በማሊ ተወያዩ!
የሲቪል መንግስት መመስረት በሚቻልበት ጉዳይ ላይ ነው ከወታደራዊ ባለሥልጣናት እና ከስልጣን ከተነሱት ፕሬዝዳንት እና ሌሎች ባለስልጣናት ጋር ዉይይት የተደረገው፡፡
[Al Ain]
@YeneTube @FikerAssefa
የሲቪል መንግስት መመስረት በሚቻልበት ጉዳይ ላይ ነው ከወታደራዊ ባለሥልጣናት እና ከስልጣን ከተነሱት ፕሬዝዳንት እና ሌሎች ባለስልጣናት ጋር ዉይይት የተደረገው፡፡
[Al Ain]
@YeneTube @FikerAssefa
የጉራጊኛ የፊደል ገበታ በ 2013 ዓ.ም በሁሉም ወረዳዎች በተመረጡ ትምህርት ቤቶች የቅድመ መደበኛ ተማሪዎችን ለማስተማር ዝግጅት እየተደረገ እንደሆነ ተገለጸ።
የፊደል ገበታዉ ለሙከራ የቅድመ መደበኛ ተማሪዎች የሚማሩ ሲሆን ይህንንም የሚያስተምሩ መምህራኖች ስልጠና እንደሚሰጥ ተነግሯል።መምህራኖች ስልጠናውን ከወሰዱ በኋላ ህጻናትን መሰረት ማስያዝ እንዳለባቸዉም የገለፁት በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የስነ ልሳንና ስነ ተግባቦት መምህር ዶክተር ፈቀደ ምኑታ በሚቀጥለዉ አመት ለ1ኛ ክፍል ለማስተማር ግብአት የማዘጋጀት ስራም እንደሚሰራ አብራርተዋል።በተመሳሳይ የጉራጌ ዞን ባህል ቱሪዝም ስፖርት መምሪያ የቋንቋና ስነ ጥበብ ቡድን መሪ አቶ ባህሩ ሊላጋ የጉራግኛ ፊደል ገበታ ማስተማር በቀጣዩ ዓመት እንደሚጀመር አረጋግጠዋል።
[FBC]

የፍርድ ቤት ውሎ በቀጥታ ሥርጭት ለሕዝብ ተደራሽ እንዲሆንና ምክር ሐሳብ ቀረበ፡፡
በድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ሞት ምክንያት ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙ ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦችን ጨምሮ በርካታ ተጠርጣሪዎች የፍርድ ቤት ውሎ በቀጥታ የቴሌቪዥን ሥርጭት ለሕዝብ ተደራሽ እንዲደረግ ምክር ሐሳብ ቀረበ፡፡
ለሙሉ ንባብ👇👇👇
https://telegra.ph/-08-23-221

በኦሮሚያ ክልል ተጨማሪ 156 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው!
በኦሮሚያ ክልል ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 5007 ናሙና የላብራቶሪ ምርመራ 156 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የክልሉ ጤና ጥበቃ ቢሮ አስታውቋል፡፡በአጠቃላይ በክልሉ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 4624 ደርሷል፡፡
[OBN]
@YeneTube @FikerAssefa
በኦሮሚያ ክልል ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 5007 ናሙና የላብራቶሪ ምርመራ 156 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የክልሉ ጤና ጥበቃ ቢሮ አስታውቋል፡፡በአጠቃላይ በክልሉ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 4624 ደርሷል፡፡
[OBN]
@YeneTube @FikerAssefa
በአማራ ክልል ተጨማሪ 42 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው።
በአማራ ክልል ተጨማሪ 42 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ተገኘባቸው፤ የአንድ ሕይወት አልፏል፤ 44 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል።ባለፉት 24 ሰዓታት ለ 2 ሺህ 727 ናሙናዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ በ 42 ሰዎች ላይ ቫይረሱ መገኘቱን የአማራ ክልል ጤና ቢሮ አስታውቋል። ይህንን ተከትሎም አጠቃላይ በክልሉ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ወደ 1ሺህ 814 ከፍ ብሏል።

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 1,638 ሰዎች በኮቪድ-19 ሲያዙ፣ 16 ሰዎች ደግሞ ህይወታቸው አልፏል!
ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገው 20,153 የላብራቶሪ ምርመራ 1,638 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ16 ሰዎች ህይወት አልፏል።በተጨማሪም 515 ሰዎች አገግመዋል።በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 40,671 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 678 ደርሷል፤ አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 14,995 ደርሷል።

የዓለም ጤና ድርጅት አዲስ የጤና መመሪያ አውጥቷል።
መመሪያው ዕድሜያቸው 12 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ታዳጊዎች ባሉበት አገር አሊያም አካባቢ ለአዋቂዎች በሚመከረው መሰረት የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማድረግ ይገባቸዋል ይላል።
ህፃናት ቫይረሱን እንዴት ሊያስተላልፉ እንደሚችሉ ብዙም የሚታወቅ ነገር እንደሌለ የገለፀው ድርጅቱ፤ ነገር ግን ልክ እንደ አዋቂዎች ሁሉ ታዳጊዎችም በሽታውን ወደ ሌላ ሰው ሊያስተላልፉ እንደሚችሉ የሚያመላክቱ መረጃዎችን ጠቅሷል።ዕድሜያቸው ከ5 ዓመት በታች ያሉ ህፃናት የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማድረግ እንደሌለባቸው መክሯል።እስካሁን ዓለማችን ከ800 ሺህ በላይ ሰዎች በበሽታው ሳቢያ ሕይወታቸው አልፏል። እንደ ጆንስ ሆፕኪንስ መረጃ ከሆነ ቢያንስ 23 ሚሊየን ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። አብዛኞቹም የተመዘገቡት በአሜሪካ፣ ብራዚል እና ሕንድ ነው።ይሁን እንጂ በቂ ምርመራ ባለመደረጉና የበሽታው ምልክት የማይታይባቸው ሰዎች በመኖራቸው ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች ቁጥር ከዚህም ሊበልጥ እንደሚችል ይታመናል።
በበሽታው የሚያዙ ሰዎች ቁጥርም በደቡብ ኮሪያ ፣ በአውሮፓ ሕብረት አገራት እና በሊባኖስ በድጋሜ እያገረሸ ነው ነው።የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ቴድሮስ አድሃኖም በጎርጎሮሳዊያኑ 1918 የተከሰተውንና በአገራችን 'የኅዳር በሽታ' ተብሎ የሚጠራው 'የስፔን ጉንፋን' በሁለት ዓመት መጥፋቱን ገልፀው፤ ኮቪድ-19ም በሁለት ዓመት ውስጥ እንደሚጠፋ ተስፋ እንዳላቸው ተናግረዋል።በዩናይትድ ኪንግደም ያሉ ከፍተኛ የሳይንስ አማካሪ ግን ኮቪድ-19 በጭራሽ ላይጠፋ ይችላል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።ምክንያታቸው ደግሞ የዓለም የሕዝብ ብዛትና እንቅስቀሴ ከ100 ዓመታት በፊት ከነበረው ጋር አይመሳሰልም፤ የሰዎች እንቅስቃሴም በሽታውን ያዛምተዋል የሚል ነው።
በመሆኑም አማካሪው "በሽታው እንደ ሌሎች በሽታዎች አብሮን ሊኖር ይችላል፤ ሰዎችም በተወሰነ ጊዜ ልዩነት መደበኛ ክትባት ሊያስፈልጋቸው ይችላል" ብለዋል።
[BBC]

የጠ/ሚር ጽህፈት ቤት የእድሳት ስራ የሰራውና መሰረቱ ዱባይ የሆነው አሌክ (ALEC Engineering Contracting LLC) የተባለው ኩባንያ የአዲስ አበባ ከተማ ማዘጋጃ ቤትን በተመሳሳይ መልኩ ማደስ ጀምሯል። ለዚህም 1.8 ቢሊዮን ብር ወጪ ይደረጋል ሲል የዘገበው ፎርቹን ነው።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
የ8ኛ እና 12ኛ ክፍል ሀገራዊ ፈተና እና የቀጣይ አመት የትምህርት ዘመንን በተመለከተ:-
ውድ ተማሪዎች እና ወላጆች በተደጋጋሚ የ 8ኛ እና 12ኛ ክፍል ሀገራዊ ፈተና መቼ እንደሚሰጥ እና የቀጣይ አመት የትምህርት ዘመን የሚጀመርበትን የግዜ ሰሌዳ በተመለከተ ተደጋጋሚ ጥያቄዎችን ስትጠይቁን እንደነበር ይታወቃል።
ስለሆነም በቅርቡ ለጥያቄዎቻችሁ መልስ የምንሰጥ ስለሆነ እስከዚያው ድረስ አስፈላጊውን ዝግጅት በማድረግ በትዕግስት እንድትጠባበቁ እንጠይቃለን ሲል ትምህርት ሚንስትር አስታውቋል።

ስለሆነም በቅርቡ ለጥያቄዎቻችሁ መልስ የምንሰጥ ስለሆነ እስከዚያው ድረስ አስፈላጊውን ዝግጅት በማድረግ በትዕግስት እንድትጠባበቁ እንጠይቃለን።
ለወቅታዊና ትክከለኛ መረጃዎች የሚከተሉትን አድራሻዎች ይጠቀሙ ፡👇👇👇👇
Facebook_ 👉
https://www.facebook.com/fdremoe/
Telegram_👉 https://tttttt.me/ethio_moe

በኮሮና የተዘጋው የቱሪዝም ዘርፍ ሊከፈት ነው!
የቱሪዝም ኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክተር አቶ ስለሺ ግርማ የተዘጋውን የቱሪዝም ዘርፍ ለማንቀሳቀስ አስፈላጊው ዝግጅት እየተደረገ እንደሆነ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ለዓለም አቀፍ ቱሪስቶች በር ለመክፈት ዝግጅት እየተደረገ እንደሆነ አቶ ስለሺ ተናግረዋል፡፡ዓለም አቀፍ ትራቭል ኤንድ ቱሪዝም ካውንስል ያወጣውን የጉዞ ፕሮቶኮል በመቀበል፣ ሊደረጉ የሚገባቸውን የጤና ጥንቃቄዎች ላይ ዝግጅት እየተረገደ እንደሆነ አቶ ስለሺ ገልጸዋል፡፡ ፕሮቶኮሉ በጉዞ ወቅት ሊከሰቱ የሚችሉ ተጋላጭነት የሚቀነስ እንደሆነ ታውቋል፡፡
ቱሪዝም ኢትዮጵያ የጉዞ ፕሮቶኮል አዘጋጅቶ በቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ በሚመራው ቦርድ በቅርቡ አፅድቋል፡፡ ቱሪዝም ኢትዮጵያ ከባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ሆቴሎች፣ ክልሎችና አስጎብኚ ድርጅቶችን በማስተባበር በቱሪስት መዳረሻዎች አስፈላጊው የፀረ ተዋስያን ርጭት እንዲካሄድ፣ ሳኒታይዘር አቅርቦት እንዲኖርና መታጠቢያ ቤቶች እንዲገነቡ በመሥራት ላይ እንደሆነ ታውቋል፡፡የተዘጋጀው የጉዞ ፕሮቶኮል ለቱሪስቶች ከኤርፖርት ጀምሮ በመኪኖች፣ በሆቴሎችና በቱሪስት መስዕቦች ሊደረጉ ስለሚገቡ ጥንቃቄዎች ይዘረዝራል፡፡የቱሪስት መኪኖች በግማሽ አቅማቸው እንዲጭኑ፣ አስጎብኚዎች እንደ ሳንታይዘር ማስክና ጓንት ያሉ መከላከያዎች ይዘው እንዲጓዙ ያዛል፡፡ የጉዞ ፕሮቶኮሉ ከአስጎብኚ ድርጅቶች ጋር በመተባበር እንደተዘጋጀ አቶ ስለሺ ተናግረዋል፡፡
‹‹እንደ ላሊበላና ጎንደር ያሉ ዋና ታሪካዊ መስዕቦቻችን መታጠቢያ ቤት የላቸውም፡፡ የብሔራዊ ሙዚየሙ መታጠቢያ ቤት ንፁህ አይደለም፡፡ ዩኒቲ ፓርክ ደረጃቸውን የጠበቁ መታጠቢያ ቤቶች አሉት፡፡ በክልሎች በሚገኙ የቱሪስት መስዕቦች መታጠቢያ ቤቶች መገንባት አለብን፤›› ያሉት አቶ ስለሺ፣ ከክልሎች ቱሪዝም ቢሮዎች ጋር ባለፈው ሳምንት በአዳማ ከተማ ውይይት እንደተደረገ ተናግረዋል፡፡የቱሪስት መዳረሻዎቹ ገቢ ሲያስገቡ የነበሩ በመሆኑ ክልሎች መታጠቢያ ቤቶች ሊገነቡ እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡ ‹‹ቢያንስ ተንቀሳቃሽ መታጠቢያ ቤቶች ሊዘጋጁ ይገባል፡፡ሳኒታይዘር ሊቀርብ ይገባል፡፡ ቱሪስቶች ከገንዘብ ንክኪ እንዲኖራቸው የሚያስገድዱ ሁኔታዎች መቀነስ ያስፈልጋል፤›› ያሉት አቶ ስለሺ፣ ቱሪዝም ኢትዮጵያ ይህን ሁሉ ብቻውን ሊወጣ እንደማይችል ገልጸዋል፡፡ አክለውም ቱሪዝም ኢትዮጵያ በሐረር ከተማ ሞዴል ጣቢያ እንደሚገነባ ተናግረዋል፡፡የሐረር ሞዴል ጣቢያው የፀረ ተዋስያን መርጫ ማሽን፣ መታጠቢያ ቤት እንደሚኖረው ታውቋል፡፡አስፈላጊው ዝግጅት ከተጠናቀቀ የተዘጉ የቱሪስት መስዕቦች ከኅዳር 2013 ዓ.ም. ጀምሮ ተከፍተው ጎብኚዎችን ማስተናገድ እንደሚጀምሩ ታውቋል፡፡

ዓመታዊው የአምባሳደሮች ጉባኤ እየተካሄደ ነው!
ዓመታዊው የአምባሳደሮች ጉባኤ በቢሾፍቱ ከተማ እየተካሄደ መሆኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡‘’ዲፕሎማሲያዊ ተልዕኮችን ለአገራዊ ብልፅግናችን’’ በሚል መሪ ሀሳብ የዋናው መ/ቤት የስራ ሀላፊዎች እና ሚሲዮን መሪዎች፤ ዲፕሎማቶች፤ አምባሳደሮች እየተሳተፉ ይገኛሉ።በጉባኤው መክፍቻ ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በአገሪቱ በ2012 ዓ.ም ዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲን በመተግበር ውጤታማ ስራዎች መሰራታቸውን ተናግረዋል።በጉባኤው በኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ በተከለሰዉ ረቂቅ የውጭ ጉዳይ ደህንነት ፖሊሲ እና አገራዊ ለውጥ ግምገማን በተመለከተ ወይይት ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።
[AMN]