YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.87K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ብሄራዊ መግባባት በሚል ርዕስ በፕሮፌሰር መረራ ጉዲና የቀረበው ጥናታዊ ጽሁፍ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጥያቄን፤ነቀፌታ እንዲሁም ትችትን ያስነሳ ሆኗል፡፡

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሀገራዊ መግባባትን ለመፍጠር የሀይማኖት አባቶች፤የማህበረሰብ ተወካይዎች እንዲሁም ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት ነሀሴ 16 2012 ዓ.ም የውይይት መድረክ ማካሄዱ ይታወሳል፡፡በውይይቱም ብሄራዊ መግባባትን ለመፍጠር የሚያስችል በሀገር ግንባታ ዙሪያ ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ጥናታዊ ጽሁፍ አቅርበዋል፡፡ለሀገር ግንባታ ይበጃል ያሉትን ጥናታዊ ጽሁፍ ታሪክን መሰረት አድርገው ሀገራዊ መግባባት ለማምጣት ጠቃሚ ናቸው ያሉትን ነጥቦችም አስቀምጠዋል፡፡

ይሁን እንጂ ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ያቀረቡት ጥናታዊ ጽሁፍ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ብዙ ነቀፌታ፣ ትችት እነዲሁም ጥያቄን አስነስቷል፡፡የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ሊቀ መንበር አቶ ማሙሸት አማረ ለአሐዱ እንደተናገሩት ሀገሪቱ ካጋጠማት ችግር እንዴት እንውጣ በሚል የተጀመረው እንቅስቃሴ እና የምክክር መድረክ ጥሩ ጅማሮ ቢሆንም ብሄራዊ መግባባትን ለመፍጠር አሻጋሪ ሀሳብ ላይ በፕሮፌሰር መረራ ጉዲና የቀረበው ጽሁፍ ላይ ፍሬ ነገር አላገኘሁበትም ሲሉ ተችተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ የሸዋስ አሰፋ እንደተናገሩት የቀረበው ጥናታዊ ጽሁፍ የታሪክ መልካም ጎኖች ያልተነሱበት፣ መጥፎው ላይ ብቻ ያተኮረ፣ አሻጋሪ ሀሳብ የሌለው፣ ብሄራዊ መግባባትን ለመፍጠር ግቡን ያልመታና የማይመጥን ነው ሲሉ ለአሁዱ ተናግረዋል፡፡የኢትዮጵያ ሶሻል ዲሞክራቲክ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ በየነ ጴጥሮስ በበኩላቸው የቀረበው ጽሁፍ ብዙ ጥያቄዎችን ያስነሳና ቁጭትን የቀሰቀስ ነው ብለዋል፡፡ወቅታዊ ችግሮችን በውይይት እንዴት እንፍታ የሚለው ላይ ትኩረት ያደረገ አልነበረም ሲሉ ለአሀዱ ገልጸዋል፡፡የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ብሄራዊ መግባባት ላይ ለመድረስ በሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ያለፉ ታሪኮችን እያነሱ ከመተቻቸት ይልቅ የወደፊቷን ኢትዯጵያ ለመገንባት አንድ አይነት አስተሳሰብ ሊኖር እንደሚገባ አሳስቧል፡፡

[አሐዱ ሬዲዮ]
@YeneTube @FikerAssefa
የሚጠበቅባቸውን መስፈርቶች ያሟሉ ሁለት የቴሌኮም ኩባንያዎች በቅርቡ ስራ ይጀምራሉ ተባለ፡፡

ላለፉት ሁለት ሳምንታት የውጭ መገናኛ ብዙሃን የኢትዮጵያ መንግስት አዳዲስ ወደ ቴሌኮም ዘርፍ የሚገቡ ኩባንያዎችን ማስገባት አቁሟል ወይም ስምምነቱ ፈርሷል በሚል ሲዘግቡ ቆይተዋል፡፡የገንዝብ ሚኒስቴር ከፍተኛ አማካሪ ዶክተር ብሩክ ታየ ዘገባው ሃሰተኛ ነው ሲሉ ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡ዶክተር ብሩክ አክለውም በቴሌኮም ዘርፉ ፍላጎት ካሳዩ 12 የውጭ ኩባንያዎች መካከል መስፈርቱን አሟልተው 2 ኩባንያዎች ገበያውን ይቀላቀላሉ፣ ሂደቱም እንደቀጠለ ነው ብለዋል፡፡

[አሐዱ ሬዲዮ]
@YeneTube @FikerAssefa
ብልጽግና ፓርቲ ለተለያዩ የስራ ሃላፊዎች ሹመት ሰጠ!

ብልጽግና ፓርቲ ለተለያዩ የስራ ኃላፊዎች ሹመት መስጠቱን ፓርቲው በዛሬው እለት አስታውቋል።

በዚህም መሰረት፡-
1. አቶ መለስ አለሙ- የአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ
2. አቶ ተስፋዬ በልጅጌ- በብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽህፈት ቤት የፖለቲካና ርዕዮተ አለም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ
3. ዶክተር ቢቂላ ሁሪሳ- በብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽህፈት ቤት የአለም አቀፍና ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ሃላፊ ሆኖ ተመድበዋል።

#FBC
@YeneTube @FikerAssefa
በ2012 በጀት ዓመት በኮንትሮባንድ መከላከል 27.4 ቢሊዮን ብር ማዳን ተችሏል!

ባለፈው 2012 በጀት አመት በኮንትሮባንድ መከላከል እንዲሁም በክትትል ሒደት 27 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ማዳን እንደተቻለ ተገለጸ፡፡የገቢዎች ሚኒስቴር ለአዲስ ማለዳ እንዳስታወቀው ኮንትሮባንድን እና የንግድ ማጭበርበርን ለመቆጣጠር በተደረገው ድንገተኛ ፍተሻዎችና የክትትል ስራዎች አገር ልታጣው የነበረ 27 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር ማዳን መቻሉን የተገለፀ ሲሆን የተገልጋይ እርካታንም 74 በመቶ ደርሷል ተብሏል።

[Addis Maleda]
@YeneTube @FikerAssefa
የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት፤ የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) አመራር የሆኑት አቶ ደጀኔ ጣፋ እና አብረዋቸው በአንድ መዝገብ ችሎት የቀረቡ ሁለት ተጠርጣሪዎች በ10 ሺህ ብር ዋስትና ከእስር እንዲለቀቁ ዛሬ ብይን ሰጠ።

በሌላ መዝገብ ዛሬ ሰኞ ነሐሴ 18፤2012 የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የቀረበው የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ(OMN) ጋዜጠኛ ጉዮ ዋሪዮም በተመሳሳይ የዋስትና የገንዘብ መጠን(10ሺህ ብር) ከእስር እንዲወጣ ብይን መሰጠቱን ጠበቃ ከዲር ቡሎ ተናግረዋል።

[Ethiopia Insider]
@YeneTube @FikerAssefa
 አቶ ልደቱ አያሌው በቢሾፍቱ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት ለአራተኛ ጊዜ ቀርበው  ያቀረቡት የዋስትና ጥያቄ ውድቅ ሲሆን መርማሪ ፖሊስም  ለምርመራ ተጨማሪ ሰባት ቀናት ተፈቅዶለታል።

[FBC]
@YeneTube @FikerAssefa
የፌደራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን የኮሮና ቫይረስ መከላከያ የንጽህና መጠበቂያ እጥረት እንደገጠመው አስታወቀ።

በማረሚያ ቤቶች ውስጥ የሳኒታይዘር እና የአልኮል አቅርቦት እንደሌለ ነው የተገለጸው፡፡የፌደራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ለታራሚዎች የንፅህና መጠበቂያ ሳሙና እና ሶፍቶችን ቢያቀርብም እንደ አልኮል እና ሳኒታይዘር የመሳሰሉ የንጽህና መጠበቂያዎች እንደሌሉ ነው ያስታወቀው፡፡የፌደራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን የህዝብ ግኑኝነት ሀላፊ አቶ ገረመው አያሌው ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት ማረሚያ ቤቶቹ ለታራሚዎች የተለያዩ የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን እያቀረቡ ቢሆንም በተወሰኑ ቁሳቁሶች ላይ ግን ከፍተኛ እጥረት አለ ብለዋል፡፡

እስካሁን ድረስ በፌደራል ደረጃ በሚገኙ ማረሚያ ቤቶች ውስጥ አንድም ታራሚ በኮሮና እንዳልተያዘ የተናገሩት ሀላፊው አሁንም ከፍተኛ ጥንቃቄ እየተደረገ ይገኛል ሲሉ ተናግረዋል፡፡በማረሚያ ቤት ለሚገኙ ሁሉም የህግ ታራሚዎች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ እንዲደርሳቸው ተደርጓል ብለዋል፡፡በመሆኑም ሀገር በቀል ድርጅቶች እና ባለሀብቶች ለታራሚዎች የሚሆን የንጽህና መጠበቂያዎችን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡

[Ethio FM]
@YeneTube @FikerAssefa
መንግሥት ጸጥታና ሰብዓዊ መብት የመጠበቅ ኃላፊነቱን እንዲወጣ የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ጠየቀ!

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በእስልምና ሊቃውንት ላይ ይጸማል ያለው ጥቃት እንዲቆም ጠየቀ። ምክር ቤቱ ዛሬ ባወጣው መግለጫ "የኃይማኖት ሊቃውንት ዑለማ እና ኢማሞች በጠራራ ጸሐይ በተከበሩ የአምልኮ ቦታዎች ሳይቀር" ጥቃት እየተፈጸመባቸው ነው ብሏል።የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በእስልምና ሊቃውንት ላይ ይጸማል ያለው ጥቃት እንዲቆም ጠየቀ።

ምክር ቤቱ ዛሬ ባወጣው መግለጫ "የኃይማኖት ሊቃውንት ዑለማ እና ኢማሞች በጠራራ ጸሐይ በተከበሩ የአምልኮ ቦታዎች ሳይቀር" ጥቃት እየተፈጸመባቸው ነው ብሏል።ምክር ቤቱ "ፍጹም ተገቢነት የሌለው" በማለት ያወገዘው ጥቃት መቼ፣ የት እና በማን እንደተፈጸመ በዝርዝር ያለው ነገር የለም።ከድምፃዊ ሐጫሉ ሁንዴሳ ግድያ በኋላ "በሰው እና በንብረት ላይ የደረሰው ጉዳት እጅግ አሳዝኖናል" ያለው የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት "በኦሮሚያ ክልል በወቅቱ ከደረሰው ጉዳት ባልተናነሰ ጉዳዩን አንድም ኃይማኖታዊ ገጽታ ለማላበስ እና በግርግሩ ሌላ ተጨማሪ አጀንዳ ለመፍጠር የተቀናጀ የሚመስል እንቅስቃሴ መታዘቡን" በመግለጫው አትቷል።

"ይህን ጥረት በተለይም ሙስሊሙን በማሸማቀቅ የአገሪቱን ሰላም እና መረጋጋት ብሎም የሕዝቦች አብሮነት እና መቻቻል በሚንድ መልኩ ከፍተኛ ዘመቻ በመክፈት የራሱን አሉታዊ ተፅዕኖ በማሳደር ላይ ይገኛል" ብሏል።ምክር ቤቱ "በተከበሩ የእምነት ቦታዎች እና መካነ መቃብር ላይ አንዳችም የኃይል እርምጃ እንዳይወስድ፤ መንግሥት የሕብረተሰቡን ሰላም እና ጸጥታ እንዲሁም የሰብዓዊ መብቶችን" የመጠበቅ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጠይቋል። ምክር ቤቱ እንደሚለው መንግሥት የአምልኮ ቦታዎችን ክብር የመጠበቅ ኃላፊነቱንም መወጣት ይጠበቅበታል።የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት "ተንኳሽ" ባለው ተግባር "ሙስሊሙ ሕብረተሰብ ሳይወናበድ የአካባቢውን ሰላም ከሌሎች ወገኖች ጋር በመሆን እንዲጠብቅ" ጥሪ አስተላልፏል።

[DW]
@YeneTube @FikerAssefa
ፍርድ ቤቱ በእነ ጃዋር መሐመድ መዝገብ ቀሪ ምስክሮችን መስማት ጀመረ!

የፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ተረኛ ምድብ ችሎት በእነ ጃዋር መሐመድ መዝገብ ቀሪ ምስክሮችን መስማት ጀመረ።ፍርድ ቤቱ ባለፈው ቀጠሮ ዐቃቤ ሕግ እና የተጠርጣሪ ጠበቆች ባቀረቧቸው አቤቱታዎች ላይ ትእዛዝ ሰጥቷል።ጃዋር እና በቀለ ገርባ ያለ ፈቃዳችን ፎቶግራፍ እና ቪዲዮ እየተቀረጽን ስለሆነ ይህም ሊታገድልን ይገባል በማለት አመልክተዋል።

ተጠርጣሪዎቹ በችሎቱ ቤተሰቦቻችን ይግቡ የሚል አቤቱታም አንሥተዋል።
የኮቪድ-19 ምርመራ ያላደረጉ አራት ተጠርጣሪዎችም አገልግሎቱ እንዲሰጣቸው ይሁን ብለው አመልክተዋል።ችሎቱ መገናኛ ብዙኃን ያለተጠርጣሪዎቹ ፈቃድ ለዘገባ ፎቶአቸውንና ቪዲዮአቸውን እንዳይጠቀሙ ሲል አዝዟል።የኮቪድ-19ን ታሳቢ ባደረገ መልኩ ከአራት ያልበለጡ የተጠርጣሪ ቤተሰቦች እንዲገኙ የሚለውንም በትእዛዙ አካትቷል።ከሃይማኖት አባቶቻቸው እና ከጠበቆቻቸው ጋር ለ40 ደቂቃ ያህል ተገናኝተው እንዲያወሩም ችሎቱ አዟል።

[Addis Maleda]
@YeneTube @FikerAssefa
ET-SMART-RSS የተባለችው የመሬት ምልከታ ናኖ ሳተላይት በታህሳስ ወር እንድምታመጥቅ የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ!

8.9 ኪ.ግ የምትመዝነው ሁለተኛዋ የመሬት ምልከታ ናኖ ሳተላይት ETRSS-1 የማትሸፍነውን አካባቢ በተሻለ የምስል ጥራት መረጃ የምትልክ መሆኑን ኢኒስቲትዩቱ አመልክቷል፡፡የሳተላይት ስራው ከቻይናው ቤጂንግ ስማርት ሳተላይት ቴክኖሎጂ ኮርፖሬሽን ጋር በጋራ እየተከናወነ መሆኑም ተመልክቷል፡፡ከቻይናው ስማርት ኩባንያ በተገኘ 1.5 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ግንባታው የሚከናወነው የሳተላይቷ ፕሮጀክት የቅድመ ዲዛይን ስራዉን ኢትዮጵያዉያን መሐንዲሶች አከናውነውታል፡፡የፍብረካና ሙከራ ስራዉን ደግሞ ቻይናዉያን ከኢትዮጵያውያን መሐንዲሶች ጋር በመመካከር ሰርተዉታል ተብሏል፡፡ በ2013 ታህሳስ መጨረሻ ላይ ቻይና ከሚገኘው ዊን ቻንግ ማምጠቂያ ጣቢያ የምትመጥቀው ET-SMART-RSS ለአንድ ዓመት ኢትዮፕያን እንደምትጠቅም የፕሮጀክቱ አስተባባሪ ዶ/ር ይሹሩን አለማየሁ መግለጻቸውን ከኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ኢንስቲትዩት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

[ETV]
@YeneTube @FikerAssefa
ማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ወደ ባንከ ለማደግ CAMEL rating ማለፍ እንደሚጠበቅባቸው ታወቀ!

ባሳለፍነው ሳምንት ማይክሮ ፋይናንስ ተቋማትን ወደ ባንከ እንዲያድጉ የሚያደርግ መመሪያ በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ (ኢብባ) መውጣቱ ይታወቃል፡፡በዚህም በክልል ወይም ከተማ አስተዳደር ስር ያሉ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ብቻ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ታውቋል፡፡ሆኖም የክልል መንግስታት ወይም የከተማ አስተዳደሮች የሚይዙት ድርሻ ከ 70 በመቶ እንዳይበልጥም ተደንግጓል፡፡ሆኖም የኢብባ SSB/74/2020 መመሪያ እንዳስቀመጠው የመንግስት የልማት ድርጅቶች እንደ መንግስት መስሪያ ቤት ስለማይቆጠሩ በቀሪው የ 30 በመቶ ድርሻ ላይ ከሌሎች ግለሰቦች ጋር ድርሻ ልይዙ ይችላሉ፡፡

በተጨማሪም የኢብባ መመሪያ ያከለው ወደ ባንክ ለሚደረገው እድገት የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት CAMEL rating ማለትም የካፒታል አቅም፣ የሃብት ጥራት፣ አስተዳደር፣ ገቢ፣ የገንዘብ መጠን ተገምግሞ ይሁንታ ማግኘት ይኖርባቸዋል፡፡የCAMEL rating ስራው የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ወደ ባንክ ለማደግ ለኢብባ ካመለከቱበት ቀን አንስቶ በአንድ አመት ግዜ ውስጥ የሚከናወን መሆኑን ያመለክታል የኢብባ መመሪያ፡፡ ይህ ማለት ምናልባት የሽግግር ግዜው ቢያንስ አንድ አመት ሊወስድ እንደሚችል አመላካች ነው፡፡ አሁን ላይ 38 ማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ስራ ላይ ሲሆኑ አብዛኞቹ በግል የተያዙ ናቸው፡፡ እኚህ ተቋመት እስካለፈው በጀት አመት ግማሽ ከ43 ቢሊየን ብር በላይ ተቀማጭ መሰብሰብ የቻሉ ሲሆን፡፡ከጠቅላላ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት አምስቱ ማለትም የአማራ፣ ደደቢት፣ ኦሮሚያ፣ ኦሞ እና አዲስ 83 በመቶ የሚሆነውን ካፒታል፣ 90 በመቶ ተቀማጭ፣ 86 በመቶ ብድር እና 87 በመቶ የሚሆነውን ሃብት ይዘዋል፡፡

[Capital]
@YeneTube @FikerAssefa
አትሌት ዩሴን ቦልት በኮሮና ቫይረስ ተያዘ!

የዓለማችን የአጭር ርቀት ንጉሱ ጃማካዊው ዩሴን ቦልት በኮሮና ቫይረስ መያዙ ተገለፀ፡፡አትሌቱ በኮቪድ-19 የተያዘው በቅርቡ በጀማይካ 34ኛ የልደት በዓሉን ከጓደኞቹ ጋር ማክበሩን ተከትሎ መሆኑ ተገልጿል፡፡አትሌቱ በቫይረሱ መያዙን ተከትሎ እራሱን አግልሎ እንደሚቆይ ነው የዴይሊ ሜል ዘገባ ያመለከተው፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ ነገ ወደ ካርቱም እንደሚያቀኑ ተገለጸ።

ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለአንድ ቀን ጉብኝት ነገ ወደ ሱዳን ዋና ከተማ ኻርቱም ያመራሉ። ዛሬ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሉቴናንት ጄኔራል አብዱል ፋታሕ አል ቡርሐን ያቀረቡትን አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ ጠቅሶ ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ ነገ ወደ ኻርቱም እንደሚያመሩ የጀርመን ድምጽ ሬድዮ የሱዳን ዜና ኤጀንሲን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።የኢትዮጵያ ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለአንድ ቀን ጉብኝት ነገ ወደ ሱዳን ዋና ከተማ ኻርቱም ያመራሉ።የሱዳን ዜና ወኪል (ሱና) ዛሬ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሉቴናንት ጄኔራል አብዱል ፋታሕ አል ቡርሐን ያቀረቡትን አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ ጠቅሶ ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ ነገ ወደ ኻርቱም እንደሚያመሩ ዘግቧል።

አምባሳደር ይበልጣል ከሉቴናንት ጄኔራል አብዱል ፋታሕ አል ቡርሐን ተገናኝተው የሹመት ደብዳቤያቸውን እንዳቀረቡ በኻርቱም የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በፌስቡክ ባሰራጨው መረጃ አረጋግጧል።ይሁንና ስለ ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጉዞ ምንም ያለው ነገር የለም።ኢትዮጵያ በታላቁ የኅዳሴ ግድብ ጉዳይ ከሱዳን እና ግብጽ የምታደርገው ድርድር እስካሁን ሶስቱንም ወገኖች ከሚያስማማ የመፍትሔ ሐሳብ አልደረሰም።በአፍሪካ ኅብረት አማካኝነት የሚደረገው ድርድር በሱዳን ጥያቄ ከተቋረጠ በኋላ እንደገና ተጀምሯል።

የግብጽ የመስኖ እና የውኃ ሐብቶች ሚኒስቴር ከአምስት ቀናት በፊት ባወጣው መግለጫ ድርድሩ እስከ ነሐሴ 22 ቀን 2012 ዓ.ም. እንደሚቀጥል አስታውቆ ነበር።ባለፈው ነሐሴ 9 ቀን 2012 ዓ.ም. የግብጹ ጠቅላይ ምኒስትር ሙስጠፋ ማዶብሊ ወደ ኻርቱም አቅንተው ከጠቅላይ ምኒስትር ዐብደላ ሐምዶክ ጋር ከተወያዩ በኋላ ተቋርጦ የነበረው የኅዳሴ ግድብ ድርድር ለቀጠል መስማማቷን ሱዳን አስታውቃለች።ማዶብሊ በወቅቱ ወደ ሱዳን ያቀኑት የግብጽ የውኃ እና መስኖ፣ ኤሌክትሪክ ኃይል፣ የጤና፣ የንግድ እና ኢንዱስትሪ ምኒስትሮች አስከትለው ነበር።  

ጠቅላይ ምኒስትሩ በኻርቱም ቆይታቸው ከሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ሊቀ-መንበር ሉቴናንት ጄኔራል አብዱል ፋታኅ አል-ቡርኻን፤ ከምክትላቸው መሐመድ ሐምዳን ዳጋሎ ተገናኝተው ተወያይተዋል።የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ምኒስትር ማይክ ፖምፔዎ ከትናንት ነሐሴ 17 እስከ 22  ቀን 2012 ዓ.ም. ድረስ ሱዳንን ጨምሮ አራት አገሮችን እንደሚጎበኙ የመሥሪያ ቤታቸው ቃል አቀባይ ሞርጋን ኦርታጉስ አስታውቀዋል።ፖምፔዎ የሚጎበኟቸው አገራት እስራኤል፣ ሱዳን፣ ባሕሬን እና የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ናቸው።ውጭ ጉዳይ ምኒስትሩ የእስራኤል ጉብኝታቸውን የጀመሩ ሲሆን ወደ ሱዳን ሲያቀኑ ከጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ ይገናኙ እንደሁ የታወቀ ነገር የለም።

[ኢትዮ ኤፍ ኤም]
@YeneTube @FikerAssefa
የ2013 የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ምዝገባ ነገ እንደሚጀመር የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አስታወቀ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2013 የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ምዝገባ በሁሉም ትምህርት ቤቶች ከነገ ነሀሴ 19 /2012 ዓ.ም ጀምሮ ከኮቪድ 19 ወረርሽኝ ተገቢዉን ጥንቃቄ በማድረግ የሚጀመር መሆኑን አስታውቋል፡፡በመንግሰት ትምህርት ቤቶች ለሚደረገዉ ምዝገባ ትምህርት ቤቶች አስፈላጊዉን ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ ቢሮው ያሳሰበ ሲሆን የግል የትምህርት ተቋማትም ከነገ ጀምሮ ምዝገባ ማካሄድ እንደሚችሉ ቢሮው አስታውቋል፡፡

[AMN]
@YeneTube @FikerAssefa

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 1472 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተያዙ፡፡

ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 18,851 የላብራቶሪ ምርመራ 1472 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን የጤና ሚኒስትር ተናግሯል፡፡ባለፋት 24 ሰዓታት የ14 ሰዎች ሕይወት አልፏል፤አጠቃላይ የሟቾች ቁጥርን 692 አድርሶታል። በሌላ በኩል በትናንትናው ዕለት 267 ሰዎች ማገገማቸው የተነገረ ሲሆን ይህም ከበሽታው የገገሙ ሰዎችን ቁጥር 15,262 አድርሶታል፡፡በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 42,143 ደርሷል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ፍርድ ቤቱ በእነ ጃዋር መሐመድ መዝገብ ቀሪ ምስክሮችን ለመስማት ለነሐሴ 20 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠ!

የፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ተረኛ ምድብ ችሎት በእነ ጃዋር መሐመድ መዝገብ ቀሪ ምስክሮችን መስማት ጀመረ፡፡ፍርድ ቤቱ ባለፈው ቀጠሮ ዐቃቤ ሕግ እና የተጠርጣሪ ጠበቆች ባቀረቧቸው አቤቱታዎች ላይ ትእዛዝ ሰጥቷል።አቶ ጃዋር እና በቀለ ገርባ ያለ ፈቃዳችን ፎቶግራፍ እና ቪዲዮ እየተቀረጽን ስለሆነ ይህም ሊታገድልን ይገባል በማለት አመልክተዋል። ተጠርጣሪዎቹ በችሎቱ ቤተሰቦቻችን ይግቡ የሚል አቤቱታም አንሥተዋል።የኮቪድ-19 ምርመራ ያላደረጉ አራት ተጠርጣሪዎችም አገልግሎቱ እንዲሰጣቸው ይሁን ብለው አመልክተዋል። ችሎቱ መገናኛ ብዙኃን ያለተጠርጣሪዎቹ ፈቃድ ለዘገባ ፎቶአቸውንና ቪዲዮአቸውን እንዳይጠቀሙ ሲል አዝዟል።

የኮቪድ-19ን ታሳቢ ባደረገ መልኩ ከአራት ያልበለጡ የተጠርጣሪ ቤተሰቦች እንዲገኙ የሚለውንም በትእዛዙ አካትቷል። ከሃይማኖት አባቶቻቸው እና ከጠበቆቻቸው ጋር ለ40 ደቂቃ ያህል ተገናኝተው እንዲያወሩም ችሎቱ አዟል። መለሰ ድሪብሳ የሚባል ተጠርጣሪም ከምግብ እና ስልክ ጋር በተያያዘ ካቀረበው አቤቱታ ጋር በተያያዘ ከቤተሰቦቹ ምግብ እንዲገባለት እና በስልክም እንዲያገኛቸው ብሏል-ፍርድ ቤቱ።የተጠርጣሪ ጠበቆች እንዲሁ በችሎቱ ተንቀሳቃሽ ስልክ ይዘን እንዳንገባ ተከልክለን ለዐቃቤ ሕግ መፈቀዱ ተገቢ አይደለም በማለት ያቀረበውን አቤቱታ ተቀብሎ ዐቃቤ ሕግም ተንቀሳቃሽ ስልክ ይዞ ወደ ችሎት እንዳይገባ አዝዟል።

እነ ጀዋር መሀመድ የባንክ አካውንታቸውና ንብረታችን ታግዷል በማለት እንዲነሳላቸው ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል፡፡ ፍርድ ቤቱም ምንም ዓይነት ንብረትም ሆነ የባንክ አካውንትን አላገድኩም፤ ያገዳውን አካል መጠየቅ ትችላላችሁ በማለት ምላሽ ሰጥቷል፡፡ ፍርድ ቤቱ ይህንና ሌሎች ትእዛዛትን በማስተላለፍ አቃቤ ህግ ከቀረባቸው ምስክሮች መካከል የአንድን ምስክር ከ3 ሰዓታት በላይ የፈጀ የምስክርነት ቃል አዳምጦ የዛሬውን ውሎ አጠናቋል፡፡ የሌሎችን ምስክሮች ቃል ለመስማትም የ20/12/2012 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ ስምንት ተጠርጣሪዎች ከችሎት ጠበቆቻቸው ጋር በችሎት መገኘታቸውንም ለማወቅ ተችሏል።

[EBC]
@YeneTube @FikerAssefa
በአማራ ክልል 14 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ የነብር ቆዳ ተቃጠለ!

በአማራ ክልል ህገወጥ የዱር እንስሳት አደን እየተስፋፋ መምጣቱን የአካባቢው ነዋሪዎች አመልክተዋል፣ 14 ሚሊዮን ብር የሚገመት ህገወጥ የነብር ቆዳ ሰሞኑን መቃጠሉን የአማራ ክልል አካባቢ፣ ደንና ዱር እንስሳት ጥበቃና ልማት ባለስልጣን አስታውቋል፡፡ በአማራ ክልል አካባቢ፣ ደንና ዱር እንስሳት ጥበቃና ልማት ባለስልጣን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ጋሻው እሸቱ አንዳሉት ህገወጥ የዱር እንስሳት አደን አሁን አሁን እየሰፋ መጥቷል፡፡ ሰሞኑን በተለያዩ ጊዜዎች በህገወጥ መንገድ ከሀገር ሊወጡ ሲሉ የተሰበሰቡ 14 ሚሊዮን ብር ማውጣት የሚችል 84 የነብርና አንድ የአዞ ቆዳ  መቃጠላቸውን አቶ ጋሻው ተናግረዋል፡፡ ለምን ተቃጠሉ ለክልሉ ልማት መዋል አይችሉም ወይ ተብለው ተጠይቀው ዓለም አቀፍ ህጉ እንደማይፈቅድ አቶ ጋሻው ገልፀዋል፡፡ አደን ህገወጥ ቢሆንም አንዳንዴ የሚፈቀድበት ሁኔታ መኖሩን ጠቁመው ይህም የሚሆነው እንስሳቱ እድሜያቸው ሲያረጅ መሆኑን አስታውቀው ለውጪ አዳኞች የሚፈቀድበት ሁኔታ ይኖራል ብለዋል፡፡

[DW]
@YeneTube @FikerAssefa
የኦፌኮው ደጀኔ ጣፋ እና የOMN ጋዜጠኛ ጉዮ ዋሪዮ ይግባኝ ተጠየቀባቸው!

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ፤ የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) አመራር የሆኑት አቶ ደጀኔ ጣፋ እና አብረዋቸው በአንድ መዝገብ ችሎት የቀረቡ ሁለት ተጠርጣሪዎች በ10 ሺህ ብር ዋስትና ከእስር እንዲለቀቁ ዛሬ ብይን ቢሰጠም “ፖሊስ ይግባኝ ጠይቋል” በመባሉ ሳይፈቱ መቅረታቸው ፓርቲው አስታወቀ። በሌላ መዝገብ ዛሬ ሰኞ ነሐሴ 18፤ 2012 ችሎት ፊት የቀረበው የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ (OMN) ጋዜጠኛ ጉዮ ዋሪዮም በተመሳሳይ የዋስትና የገንዘብ መጠን ከእስር እንዲወጣ ፍርድ ቤቱ ቢበይንም በተመሳሳይ ምክንያት አለመፈታቱ ተገልጿል።

የኦፌኮ የወጣት ሊግ ሊቀመንበር አቶ ደስታ ዲንቃ ለ “ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” እንደተናገሩት ለአራቱ ተጠርጣሪዎች የተጠየቀው የ40 ሺህ ብር ዋስትና ክፍያ ቢፈጸምም “ፖሊስ ይግባኝ ለመጠየቅ መዝገቡን ወስዶታል” በመባሉ ምክንያት የፍቺ ሂደታቸው ሳይፈጸም ቀርቷል። የይግባኝ ጉዳዩን የሚመለከት ዳኛ ከሰዓት ባለው ጊዜ ባለመኖሩም ጉዳዩ ለነገ እንዳደረ ጨምረው ገልጸዋል።

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በዛሬው ውሎው፤ ከኦፌኮው ፖለቲከኛ አቶ ደጀኔ ጋር በተመሳሳይ መዝገብ የተካተቱ ሶስት ተጠርጣሪዎችን ጉዳይ ተመልክቶ የዋስትና መብታቸው እንዲከበርላቸው የወሰነው የፖሊስን ጥያቄ ውድቅ አድርጎ እንደነበር ጠበቃ ከዲር ቡሎ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል። ሶስቱ ተጠርጣሪዎች የድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያን ተከትሎ በአዲስ አበባ፣ ቡራዮ እና በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች በተቀሰቀሰው ሁከት፤ “ተሳትፎ አላቸው” በሚል በፖሊስ ተጠርጥረው የተያዙ ናቸው። 

[Ethiopia Insider]
@YeneTube @FikerAssefa
በምዕራብ ጎንደር ዞን የመተማ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ሰው በማገት ወንጀል የተከሰሱ ግለሰቦችን በጽኑ እስራት እንዲቀጡ ማድረጉን ገለጸ።

የወረዳው ፖሊስ ጽ/ቤት ሃላፊ የሆኑት ኢንስፔክተር ወለላው ተገኘ እንደገለጹት በወረዳው በተለያዩ አካባቢዎች ሰው በማገት የተከሰሱ እና በተለያየ መንገድ የወረዳውን የሰላም እንቅስቃሴ ሲያውኩ የነበሩ ግለሰቦች የወረዳው ፖሊስ ባደረገው እንቅስቃሴ ለፍርድ በማቅረብ በጽኑ እስራት እንዲቀጡ አድርጓል።

1ኛ/ በዲቢኮ ቀበሌ 1 ወር ከ20 ቀን ከሽንት ቤት አንድ ሰው በማገት ወንጀል የተያዘው ግለሰብ አቶ ሙሉቀን ሰፈፈ 9 ዓመት ከ6ወር ፅኑ እስራት በመተማ ወረዳ ፍርድ ቤት የተወሰነበት ሲሆን
2ኛ/ በወዲ አንበሶ ቀበሌ ህጻን በማገት ወንጀል የተያዘው አቶ ገብረመድህን ገብሬ 11 ዓመት እና ለዚሁ ወንጀል ተባባሪ የሆኑ ሁለት ሴቶች ለእያንዳንዳቸው 12 ዓመት በከፍተኛ ፍርድ ቤት ተወስኖባቸዋል።
3ኛ/ በሌላ በኩል በመቃ ቀበሌ ሰው በማገት ወንጀል የተያዙ 5 ግለሰቦች
አቶ አየልኝ እያዩ፣ አቶ መዝገበ እያዩ፣አቶ ጓዴ ፈረደ፣ አቶ ገላጋይ ተገኘ፣ አቶ የኛሁን አበበ ለእያንዳንዳቸው ከ10-11 ዓመት እስራት በወረዳ ፍርድ ቤት የተወሰነባቸው ሲሆን፣
4ኛ/ በአሻሚት ቀበሌ አቶ በውቀት ስንታየሁን ያገቱ ሁለት ግለሰቦች ማለትም፣ አቶ ታገለ ደሴ እና አቶ አበበ የኛሁን ለእያንዳንዳቸው 14 ዓመት በከፍተኛ ፍርድ ቤት ተወስኖባቸዋል ። በሌላ በኩል
5ኛ/ ህፃን በላይነህ ደሴን ከነጋዴ ባህር ወደ መቃ ቀበሌ በማምጣት የዕገታ ወንጀል የፈፀመ ግለሰብ አቶ ሲሳይ አቡሽ በ14 ዓመት በጽኑ እስራት እንዲቀጡ የተወሰነ መሆኑን ኢንስፔክተር ወለላው አክለው አስረድተዋል።

ወረዳው ላይ በርከት ያለ የሰው እገታ ወንጀል እየተፈፀመ በመሆኑ የፀጥታ መዋቅሩ ከድሮው በተለየ እንቅስቃሴ በማድረግ ወንጀለኞችን ለፍርድ በማቅረብ የፍርድ ቤት ውሳኔ በማሰጠት የህግ እርምት እንዲወሰድባቸው አድርገናል። አሁንም ከዚህ የተሻለ ስራ በመስራት ወረዳችን ሰላም የሰፈነባት እና ማንኛውም ማህበረሰብ በነፃነት እንዲንቀሳቀስ እና ውሎ እንዲገባ ያለሰለሰ ጥረት የምናደርግ መሆኑና ህብረተሰቡ ከዚህ በፊት ላደረገው ጥቆማ ሠላምን የማረጋገጥ ተሳትፎ ምስጋና እያቀረብን ቀጣይም ህዝቡ ከጸጥታ አካላት ጋር በመሆን በጋራ ህግ የማስከበር ስራ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ዘገባው:- የመተማ ወረዳ መንግስት ኮምዩኒኬሽን ነው
@YeneTube @FikerAssefa
የቁጠባ መጠን ከትሪሊየን ብር አለፈ!

የብሄራዊ ባንክ የ2012 ሁለተኛ ሩብ አመት (ከጥር እስከ መጋቢት ያሉትን ግዜያት የሚዳስስ) ሪፖርት እንደሚያሳየው በተጠቀሰው ግዜ በባንኮች በተለያየ መልክ የተቀመጠው የብር መጠን ለ አንድ ትሪሊየን ብር ምንም የቀረው አይደለም፡፡ይህም አሁን ላይ የተቀማጭ መጠን ከትሪሊየን ብር ለማለፉ የሚያጠያይቅ አይሆንም፡፡ስለጉዳዩ ካፒታል ያነገረቻቸው የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) እድገቱ የሚበረታታ ቢሆንም የአገሪቱ የቁጠባ መጠን አሁንም እጅግ ስራ ይፈልጋል በማለት መልሰዋል፡፡በመሆኑም ያለውን አቅም አውጥቶ ይበልጥ ቁጠባን ማሳደግ ይገባል ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው፡፡የአገሪቱን ጠቅላላ የስራ ውጤት ወይም አመታዊ ጥቅል ምርት በማነጻፀር አገሪቱ የቁጠባ መጠን ማደግ እንዳለበት ይነገራል፡፡እስከ መጋቢት ባሉት ግዜያት የአገሪቱ ቁጠባ መጠን 989.2 ቢሊየን ብር የደረሰ ሲሆን ይህም ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት አንፃር የ 18 በመቶ እድገት አለው፡፡

ለእድገቱ የባንክ ቅርንጫፎች መስፋት፣ የህብረተሰቡ የቁጠባ ባህል ማደግ፣ የገቢ ማደግ እና የፋይናንስ ተደራሽነት እንደ ምክንያት ተጠቅሰዋል፡፡ከዛም ባለፈ እየተወሰዱ ያሉ የፖሊሲ እርምጃዎች እመርታ እያመጡ መሆኑን ዶ/ር እዮብ ተናግረዋል፡፡ በቅርቡ ተግባራዊ ያደረግነው በጥሬ ገንዘብ ከባንክ የሚወጣ የገንዘብ መጠን መመሪያ የተቀማጭ መጡን ከሚታሰበው በላይ ማሳደግ ችሏል ብለው፡፡ ከባንክ ውጭ ገንዘብ ሲያስቀምጡ እና ሲጠቀሙ የነበሩ በጠረፍ አካባቢ የሚገኙ የመንግስት ተቋማትን ጨምሮ በርካቶች በባንክ የሚያደርጉት እንቅስቃሴ በከፍተኛ ማደጉን ታዝበናል ሲሉ አክለዋል፡፡ይህም ለተቀማጭ ማደግ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያበረከተ መሆኑን ሚኒስትር ዴኤታው አብራርተዋል፡፡እስከ መጋቢት መጨረሻ በአገሪቱ ያሉት የባንክ ቅርንጫፎች መጠን 6,362 የደረሰ ሲሆን 70 በመቶ የሚሆኑት በግል ባንኮች የተያዙ ናቸው፡፡

[Capital]
@YeneTube @FikerAssefa