የሲዳማ ክልል ልዩ ኃይሎች ነገ በይፋ ሊመረቁ ነው
ከደቡብ ክልል ተነጥሎ ባለፈው ሰኔ ወር በይፋ የተቋቋመው የሲዳማ ክልል፤ የራሱን ልዩ ኃይል አባላት በነገው ዕለት ሊያስመርቅ ነው። ተመራቂዎቹ ቀደም ሲል በደቡብ ክልል ልዩ ኃይል ሲያገልግሉ የነበሩ የሲዳማ ተወላጆች ናቸው ተብሏል።
ቅዳሜ ነሐሴ 16፤ 2012 የምረቃ ስነ ስርዓታቸው የሚከናወነው የሲዳማ ክልል ልዩ ኃይል አባላት በቁጥር አንድ ሺህ እንደሚጠጉ የክልሉ የኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ፊሊጶስ ኖሆም ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል። የመጀመሪያው የሲዳማ ርዕሰ መስተዳድር የሆኑት አቶ ደስታ ሌዳሞ በሚገኙበት በነገው ስነ ስርዓት ላይ፤ ለልዩ ኃይል አባላቱ የተሰራላቸው አዲስ የደንብ ልብስ በይፋ ይመረቃል ብለዋል።
ተመራቂዎቹ የልዩ ኃይል አባላት ለ12 ቀናት የተሰጣቸውን ስልጠና ተከታትለው ማጠናቀቃቸውንም የኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ገልጸዋል። ስልጠናው ቴክኒካዊ ጉዳዩችን ያካተተ አለመሆኑንም አክለዋል። ይልቁንም ስልጠናው በተለያዩ የደቡብ ክልል አካባቢዎች ተመድበው ሲሰሩ የቆዩት የልዩ ኃይል አባላት፤ በሲዳማ ክልል ካለው ህብረተሰብ ሲቀላቀሉ በሚኖራቸው መስተጋብር ላይ ያተኮረ እንደሆነ አብራርተዋል።
“የልዩ ኃይል አባላቱ ከዚህ በፊት በደቡብ ክልል ውስጥ ስር ነው ሲሰሩ የነበሩት። አሁን የወሰዱት ስልጠና ሲዳማ ተወላጆች ሆነው ወደ ሲዳማ ሲመጡ ሲዳማ ተወላጅነታቸውን ብቻ ይዘው እንዳይመጡ፣ የተለየ መዋቅር እንደሆነ እና በህዝቦች አንድነት ላይ እና በአመለካከት ላይ ነው ስልጠና የወሰዱት” ሲሉ ኃላፊው ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” አስረድተዋል።
የሲዳማ ክልል አሁን ከሚመረቁት በተጨማሪ አዲስ የልዩ ኃይል አባላት ለመመልመል እንቅስቃሴ አለመጀመሩን የሚገልጹት አቶ ፊሊጶስ ያንን ለማድረግ ክልሉ የራሱ የሆነ ማሰልጠኛ እንደሚያስፈልገው ጠቁመዋል። አሁን በክልሉ እየተደረገ ያለው ምልመላ ለመከላከያ ሰራዊት እና ለፌደራል ፖሊስ አባልነት እንደሆነም አመልክተዋል።
ነገ በሐዋሳ ዩኒቨርስቲ በሚካሄደው የምረቃ ስነ ስርዓት ላይ የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የካቢኔ አባላት እና ጥሪ የተደረገላቸው የሀገር ሽማግሌዎች ይገኛሉ ተብሏል።
Via:- (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
@Yenetube @Fikerassef

የአንበጣ መንጋ በ2011 ክረምት ወራት 3.5 ሚሊዮን ኩንታል እህል ላይ ጉዳት አድርሷል!
ሰኔ 2011 አጋማሽ ላይ ከየመን በሶማሌ ላንድ አድርጎ ወደ አፋር እና ሶማሌ ክልል የገባው የአንበጣ መንጋ ሊገኝ ከታቀደው ምርት 2 በመቶውን ወይንም 3.5 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ማውደሙ ተገለጸ።መንጋው ከ70 እሰከ 100 ፐርሰንት ምርት ሊያጠፋ ይችል ነበር ያሉት በግብርና ሚንስቴር የዕጽዋት ጥበቃ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ታምሩ ከበደ በተደረገው ርብርበብ የደረሰው ጉዳት አነስተኛ ሊሆን ችሏል ብለዋል።የአንበጣ መንጋው ሶማሌ እና አፋር ክልል ላይ የመከላከል ሥራ ሲሠራ ቢቆይም ከአፋር የተረፈው ወደ ወሎ እና ደቡብ ትግራይ ወጥቶ ማሳ ላይ ጉዳት አድርሷል። ከሶማሌ ክልል በመነሳት ደግሞ ምስራቅ እና ምዕራብ ሐረርጌ ላይ ጉዳት አድርሶ ነበር ብለዋል።
[BBC]
@YeneTube @FikerAssefa

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን በሁለት ዓመታት ውስጥ መቆጣጠር እንደሚቻል የዓለም የጤና ድርጅት አስታወቀ፡፡
ወርርሽኙን ለመከላከል የሚያስችሉ ድጋፎች ላይ የሚፈጸም ሙስና ሰው የመግደል ወንጀል ያህል መሆኑን የዓለም ጤና ድርጅት አሳስቧል።ድርጅቱ ትናንት አርብ በጄኔቫ ይፋ እንዳደረገው ቫይረሱ የመሰራጨት እድሉ ከፍተኛ ቢሆንም በሁለት ዓመታት ውስጥ መቆጣጠር ይቻላል፡፡የድርጅቱ ዋና ጸሐፊ ቴድሮስ አድሃኖም (ዶክተር) በሰጡት መግለጫ (እ.አ.አ) በ1918 ተከስቶ የነበረው (ስፓኒሽ ፍሉ) ወረርሽኝ በሁለት ዓመታት ውስጥ እንደቆመ አስታውሰዋል፤ አሁን ግን በቴክኖሎጂ ወቅታዊ መሻሻል ዓለም የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ከዚያ ባነሰ ጊዜ ማቆም እንደሚያስችላት ጠቅሰዋል፡፡
“በእርግጥ የዓለም መተሳሰርና መቀራረብ ለቫይረሱ የበለጠ የመሰራጨት ዕድል ይፈጥርለታል፤ ነገር ግን ወረርሽኙን ለማስቆም ቴክኖሎጂውም ሆነ ዕውቀት አለን፤ የብሔራዊ አንድነት እና ዓለም አቀፍ ቅንጅት ግን ግድ ይለናል” ብለዋል ዋና ጸሐፊው በመግለጫቸው፡፡
በ1918 (እ.አ.አ) ተከስቶ የነበረው (ስፓኒሽ ፍሉ) 50 ሚሊዮን ያህል ሰዎችን ሕይወት ቀጥፏል፡፡ የኮሮና ቫይረስ ደግሞ ይህ መግለጫ እስከተሰጠበት ጊዜ ድረስ 800 ሺህ ሰዎችን ለሞት ሲዳርግ 22 ነጥብ 7 ሚሊዮን ሰዎች በበሽታው ተጠቅተዋል፡፡
ወረርሽኙን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት ውስጥ ስለሚፈጸሙ የሙስና ወንጀሎች ለተነሳላቸው ጥያቄ ዋና ጸሐፊው ጉዳዩ ተቀባይነት እንደሌለውና የሚወገዝ ወንጀል እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ወርርሽኙን ለመከላከል የሚያስችሉ ድጋፎች ላይ የሚፈጸም ሙስና “ሰው የመግደል ወንጀል ያህል ነው” ሲሉም ገልጸውታል፡፡ምክንያቱም የጤና ባለሙያዎች ያለ መከላከያ ራሳቸውን ለቫይረሱ አጋልጠው የሚሰሩ ከሆነ ሕይወታቸውን አደጋ ላይ እየጣሉ ነው። ያ ደግሞ የእነሱን እርዳታ የሚፈልጉ ሰዎችን ሕይወት አደጋ ላይ እንደሚጥል አብራርተዋል፡፡
ምንጭ፡-ቢቢሲ

ሰው በማገት ክስ የተመሰረተበት ግለሰብ በ12 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጣ!
በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ታች አርማጭሆ ወረዳ በሰው ማገት ወንጀል ክስ የተመሰረተበት ግለሰብ በ12 አመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ የተወሰነበት መሆኑን የአካባቢው አቃቤ ህግ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡የጽህፈት ቤቱ ተወካይ አቶ ጌታሁን ታከለ ለኢዜአ እንደተናገሩት የእስራት ቅጣቱ ውሳኔ የተላላፈበት ናቃቸው ተዘራ የተባለ የሙሴ ባንብ ቀበሌ ነዋሪ ነው፡፡ግለሰቡ መጋቢት 7 ቀን 2012 ዓ.ም የማይገባውን ጥቅም ለማግኘት በማሰብ ካንፈንታ በተባለው ቀበሌ ካገተው ግለሰብ 20ሺ ብር አስከፍሎ መልቀቁ በአቃቤ ህግ የሰውና የሰነድ ማስረጃ ተረጋግጦበታል ብለዋል።ድርጊቱን አልፈጸምኩም ብሎ ክዶ ቢከራከም በአቃቤ ህግ ምስክሮች በማረጋገጥ የሙሴ ባንብ ንኡስ ወረዳ ፍርድ ቤት የጥፋታኝነት ውሳኔ ማሳለፉን ተናግረዋል፡፡ተከሳሹ ከአራት ዓመት በፊት በስርቆት ወንጀል ተከሶ የእስራት ጊዜውን አጠናቆ ከወጣ በኋላ በድጋሚ የሰው እገታ ወንጀል በመፈጸሙ ፍርድ ቤቱ ድርጊቱን በቅጣት ማክበጃነት እንደያዘበትም ኃላፊው አመላክተዋል፡፡ተከሳሹ ፈጽሟል በተባለው የሰው እገታ ወንጀል ጥፋተኝነቱ በመረጋገጡም ፍርድ ቤቱ ትናንት በዋለው ችሎት እጁ ከተያዘበት ጊዜ ጀምሮ የእስራት ቅጣት ውሳኔውን ማስተላለፉን አስታውቀዋል፡፡
[ENA]

ከሐምሌ 27 እስከ ነሐሴ 14 ቀን 2012 ዓ.ም ባሉት 16 ቀናት ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ከ129 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ ልዩ ልዩ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች፣ ህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር እና የታክስ ማጨበርበሮች ተደርሶባቸው ለመንግስት ገቢ ተደርገዋል፡፡
[የገቢዎች ሚኒስቴር]
@YeneTube @FikerAssefa
[የገቢዎች ሚኒስቴር]
@YeneTube @FikerAssefa
አሜሪካ በ14 የኢራን ባለስልጣናት ላይ የጉዞ ማእቀብ ጣለች።
አሜሪካ በአደገኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት ተሳትፈዋል ባለቻቸው 14 የኢራን ባለስልጣናት ላይ የጉዞ ማእቀብ መጣሏን አስታውቃለች፡፡
[Al Ain]
@YeneTube @FikerAssefa
አሜሪካ በአደገኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት ተሳትፈዋል ባለቻቸው 14 የኢራን ባለስልጣናት ላይ የጉዞ ማእቀብ መጣሏን አስታውቃለች፡፡
[Al Ain]
@YeneTube @FikerAssefa
የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የሙያ መስኮች ያሰለጠናቸውን 118 ተማሪዎች አስመረቀ!
ዩኒቨርሲቲው በድህረ ምረቃና በቅድመ መደበኛ መርሃ ግብር ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ነው ያስመረቀው።ከተመራቂዎች መካከል 56ቱ የድህረ ምረቃ ተማሪዎች ሲሆኑ 23 ተማሪዎች ደግሞ በጤና ሳይንስ ኮሌጅ የሰለጠኑ የህክምና ዶክተሮች እንዲሁም በቴክኖሎጂ ኢኒስቲቲዩት 39 ተማሪዎች በኪነ ህንፃ በመጀመሪያ ዲግሪ ያሰለጠናቸው ናቸው፡፡
[OBN]

በጁባ በደረሰው የአውሮፕላን አደጋ የበርካታ ሰዎች ህይወት አልፏል
ከደቡብ ሱዳን ጁባ ተነስቶ ሲበር የነበረ የጭነት አውሮፕላን በመከስከሱ ምክንያት የበርካታ ሰዎች ህይወት ማለፉን የተለያዩ የሃገሪቱ ሚዲያዎች ዘግበዋል፡፡
ዘገባውን ቀድሞ ያወጣው አይ ራዲዮ ጣቢያ አውሮፕላኑ ሳውዝ ዌስት የተሰኘ አየር መንገድ ንብረት ነው ብሏል፡፡
የሟቾቹ ቁጥር ለጊዜው አለመታወቁንም ነው የዘገበው፡፡
በአደጋው የበርካታ ሰዎች ህይወት ማለፉን የአይን እማኞች አረጋግጠውልኛል ያለው ኒያማይል የተሰኘ ሚዲያ በበኩሉ አውሮፕላኑ ወደ ሰሜናዊ ባህር ኤል ጋዛል ክልል ዋና ከተማ አዊል ለመብረር ከጁባ ከተነሳ ጥቂት ደቂቃዎች በኋላ መከስከሱን ዘግቧል፡፡
“ ዛሬ ጠዋት በጁባ የአውሮፕላን መከስከስ አደጋ አጋጥሟል፡፡ አውሮፕላኑ የሳውዝ ዌስት አየር መንገድ ነው፡፡ አየርመንገዱ አሮጌ አውሮፕላኖችን እንደሚጠቀም ታውቃለህ ለዚህም ነው አደጋው የደረሰው፡፡ ትክክለኛው ቁጥር ባይታወቅም እንኳን በርካታ ሰዎች ሞተዋል” ሲሉም ነው አንድ በስፍራ የነበሩ የዓይን እማኝ ለኒያማይል የተናገሩት፡፡
አንድ ሰው ብቻ መትረፉንም ገልጸዋል፡፡
የአደጋውን መንስዔ በተመለከተ ግን እስካሁን በውል የታወቀ ነገር የለም፡፡
via:- Al Ain
@Yenetube @FikerAssefa

በቀጣዮቹ ቀናት በአዲስ አበባ አንዳንድ አካባቢዎች ለማሻሻያ ሥራ ሲባል የኃይል አቅርቦት ይቋረጣል!
👉ሰኞ ነሀሴ 18 ቀን 2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 5፡00 ድረስ፡-
• በሲኤሚሲ የተባበሩት፣ በሰሚት ሰንሻይን ሪል እስቴት እና አካባቢዎቻቸው፣
👉በተመሳሳይ ቀን ከጠዋቱ 1፡00 እስከ ቀኑ 7፡00 ድረስ፡-
• በፔትራም፣ በክራውን ሆቴል፣ በC.R.B.C ቻይና ዋና መስርያ ቤት፣ በካዲስኮ ቀለም ፋብሪካ፣ በኦሮምያ ውሃ ስራዎች እና አካባቢዎቻቸው፤
👉በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 8፡30 ድረስ፡-
• በኮርያ ሰፈር፣ በእንደራሴ ሆቴል፣ በሞናሊዛ ሆቴል፣ በአቧሬ፣ በቤሌር፣ በራስ አምባ ሆቴል፣ በሚኒሊክ ሆስፒታል፣ በጀርመን ድልድይ እና አካባቢዎቻቸው፤
👉እንዲሁም ከጠዋቱ 1፡00 እስከ ቀኑ 10፡00 ድረስ፡-
• በኮተቤ 02፣ በደህንነት፣ በሃና ማርያም፣ በሃይሌ ጋርመንት፣ በቆጣሪ ኮንደሚኒየም፣ በኦሮሚያ ኮንደሚኒየም፣ በማንጎ ሰፈር እና አካባቢዎቻቸው፣
👉በተጨማሪም ማክሰኞ ነሀሴ 19 ቀን 2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 7፡00 ሰዓት ድረስ፡-
• በአድዋ ድልድይ፣ በአቧሬ፣ ኳስ ሜዳ፣ በቤሌር፣ በእንደራሴ ሆቴል፣ በመለስ ፋውንዴሽን፣ በልቤ ፋና ኮንደሚኒየም፣ በካዛንቺስ በከፊል እና አካባቢዎቻቸው፤
👉በተመሳሳይ ቀን ከጠዋቱ 1፡00 እስከ ቀኑ 9፡00 ድረስ፡-
• በሃና ማርያም፣ በሃይሌ ጋርመንት፣ በቆጣሪ ኮንደሚኒየም፣ በኦሮሚያ ኮንደሚኒየም፣ በማንጎ ሰፈር እና አካባቢዎቻቸው፤
👉እንዲሁም ከጠዋቱ 1፡00 እስከ ቀኑ 10፡00 ድረስ፡-
• በኮኮብ መካሮኒና ፓስታ ፋብሪካ፣ በግንቦት 20 ት/ቤት፣ በላፍቶ ኮንደሚኒየም፣ በላፍቶ ሚካኤል እና ካባቢዎቻቸው፤በከፍተኛ የኤሌክትሪክ ተሸካሚ መስመር ላይ የማሻሻያ ሥራ ለማከናወን ሲባል የኃይል አቅርቦት የሚቋረጥ በመሆኑ፤ ክቡራን ደንበኞቻችን ከወዲሁ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንድታደረጉ በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡
[የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት]

የሚኒስትሮች ም/ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 88ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል፡፡
#PMOEthiopia
@YeneTube @FikerAssefa
#PMOEthiopia
@YeneTube @FikerAssefa
የመከላከያ አዛዥነትና ስታፍ ኮሌጅ ለ14ኛ ዙር በወታደራዊ አመራርነት ያሰለጠናቸውን ከፍተኛ መኮንኖች አስመረቀ፡፡
በስነ ስርዓቱ ላይ የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀነራል አደም መሀመድ ተመራቂዎች የሀገራቸውን ሉዓላዊንትና የህዝባቸውን ደህንነት ለመጠበቅ ወታደራዊ አመራሮች በዕውቀት ላይ ተመስርተው ሀገርን እና ህዝብን ማገልገል እንደሚጠበቅባቸው ገልፀዋል፡፡የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት የአቅም ግንባታ ግብ በሁሉም አውዶች መፋለም የሚችል ጠንካራ ሀይል መገንባት መሆኑንም ተናግረዋል፡፡የኮሌጁ ኮማንዳንት ብርጋዴር ጀነራል ዳኛቸው ይትባረክ በበኩላቸው፥ ዛሬ በከፍተኛ ስልታዊ አመራር 90 ስልጣኞች መመረቃቸውን ገልፀው ÷ 18ቱ ከአምስት የጎረቤት ሀገር የመጡ መሆናቸውን ተናግረዋል።በስነ ስርዓቱ ላይ የመከላከያ ህብረት ስልጠና ዋና መምሪያ ሀላፊ ሌተናል ጀነራል ሀሰን ኢብራሂምን ጨምሮ ከፍተኛ አመራሮች መገኘታቸውን ከኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
[FBC]

የህዳሴ ግድብ ቦንድ ግዥ መመለሻው ቢደርስም በእድሳት እንዲደግፉ ጥሪ ቀረበ!
ለህዳሴ ግድብ ቦንድ የገዙ ዜጎች የመመለሻ ጊዜው ቢደርስም በእድሳት ድጋፋቸውን እንዲቀጥሉ ጥሪ ቀረበ፡፡የግድቡ ግንባታ ከጅማሮው እስካሁን ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ለግድቡ ስኬት የቻሉትን ሁሉ ድጋፍ ሲያደርጉ ቆይተዋል።በርካቶች ቦንድ በመግዛት ድጋፍና አጋርነታቸውን በማሳየታቸው ግድቡ የመጀመሪያ ውሃ ሙሌት ላይ የደረሰ ሲሆን ለፍፃሜ ለማብቃትም ድጋፉ ተጠናክሮ ቀጥሏል።በመሆኑም ቀደም ሲል ቦንድ ገዝተው የነበሩ ዜጎች የቦንዱ መመለሻ ጊዜ ቢደርስም ወለዱን ጨምሮ ዳግም ቦንድ እየገዙ ድጋፋቸውን መቀጠል እንደሚችሉ ተገልጿል።የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድቡ ግንባታ ሕዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ብሔራዊ ምክር ቤት ፅህፈት ቤት የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሃይሉ አብርሃም እንደገለጹት፤ የድጋፍ ማሰባሰቡ ሂደት እንደቀጠለ ነው።
[ኢዜአ]

ማስታወቂያ !
ምግብ ዶክመንት የላውንድሪ ልብስ ወይንም ማንኛውንም የረሱትን እቃ እናምጣልዎት!
📞6101 #GoFlex
የሞባይል መተግበሪያውን ያውርዱ ⬇️
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.goflex.app

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ፓርቲዎች በብሔራዊ መግባባት ላይ በኢሲኤ ባደረጉት ውይይት እንዲካፈል ጥሪ እንዳልቀረበለት አስታወቀ።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
በኢቦላ ከተያዙት 100 ሰዎች የ43ቱ ህይወት አለፈ!
በምዕራባዊ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ከ3 ወራት በፊት በተቀሰቀሰው የኢቦላ ቫይረስ ተይዘው ከነበሩ 100 ሰዎች መካከል 43ቱ መሞታቸውን የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ፡፡
[Al Ain]
@YeneTube @FikerAssefa
በምዕራባዊ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ከ3 ወራት በፊት በተቀሰቀሰው የኢቦላ ቫይረስ ተይዘው ከነበሩ 100 ሰዎች መካከል 43ቱ መሞታቸውን የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ፡፡
[Al Ain]
@YeneTube @FikerAssefa
የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) ፓርቲ መንግስት የኃይል እርምጃዎቹን በአስቸኳይ እንዲያቆም ጠየቀ። ሀገሪቱ ትረጋጋ ዘንድም መንግስት በእስር ላይ ያሉ የፖለቲካ ፓርቲ አባላትን እንዲፈታ አሳስቧል።
ፓርቲው ጥሪውን ያቀረበው “በኢትዮጵያ ውስጥ ለተከሰተው ወቅታዊ ችግር ፖለቲካዊ መፍትሄ ያሻል” በሚል ርዕስ ስር ዛሬ ቅዳሜ ነሐሴ 16፤ 2012 ባወጣው መግለጫ ነው። “በሺህዎች የሚቆጠሩ የቄሮዎች ሕይወት ተገብሮበት የመጣው እና ተስፋ ሰጪ የተባለው ለውጥ አጣብቂኝ ውስጥ ከገባ ውሎ አድሯል” ያለው ኦፌኮ “ሞት፣ እስር፣ ድብደባ ተመልሶ መጥቶብናል” ሲል በመግለጫው አስፍሯል።
በኢትዮጵያ የተጀመረው ለውጥ “አደገኛ መስቀለኛ መንገድ ላይ ይገኛል” የሚለው ተቃዋሚ ፓርቲው ከድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ መገደል በኋላ በተለይ “ሁኔታዎች የበለጠ እየተወሳሰቡ መጥተዋል” ብሏል። ፓርቲው ክስተቱን ተከትሎ ሊመጣ የሚችለውን “ውስብስብ ሁኔታ በመገመት የድምጻዊውን ግድያ በነጻና ገለልተኛ አካል እንዲጣራ እና ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ ጠይቆ እንደነበር አስታውሷል።
[Ethiopia Insider]

በኦሮሚያ ክልል ተጨማሪ 325 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው!
በኦሮሚያ ክልል ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 5ሺህ 4 መቶ 41 ናሙና የላብራቶሪ ምርመራ 3መቶ 25 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የክልሉ ጤና ጥበቃ ቢሮ አስታውቋል፡፡በአጠቃላይ በክልሉ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 4ሺህ 4 መቶ 68 ደርሷል፡፡