YeneTube
119K subscribers
31.4K photos
484 videos
79 files
3.86K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በኢትዮጵያ የመንግሥትም ሆኑ የግል ባንኮች ከውጭ አበዳሪ ተቋማት በዶላር መበደር እንዲችሉ ተፈቀደ!

በኢትዮጵያ የመንግሥትም ሆኑ የግል ባንኮች ከውጭ አበዳሪ ተቋማት በዶላር መበደር እንዲችሉ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ፈቅዷል።ይህም አሠራር በአገሪቱ የሚስተዋለውን የውጭ ምንዛሬ እጥረት ለማቃለል ይረዳል ተብሏል።ይህ የተገለጸው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ዶ/ር ይናገር ደሴ በዛሬው ዕለት በሰጡት መግለጫ ላይ ነው።በግለሰቦች ወይንም በኩባንያዎች ከባንክ ውጭ ከ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ ማስቀመጥ ደግሞ ተከልክሏል።

የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማትም ወደ ባንክነት ማደግ የሚችሉበት መመሪያ መውጣቱን ዶ/ር ይናገር ይፋ አድርገዋል።የኤሌክትሮኒክስ ግብይት ሥርዓትን ለማሳለጥ ሲባል ከባንኮች በተጨማሪ ሌሎች ፋይናንሻል ያልሆኑ ተቋማትም በክፍያ ሥርዓት ላይ መሳተፍ እንደሚችሉ በመግለጫው ተመልክቷል።ተቋማቱ ከብሔራዊ ባንክ ፈቃድ ወስደው በኤቲኤም፣ በፖስ ማሽን እንዲሁም ሌሎች አማራጮች የክፍያ ሥርዓት ላይ መሳተፍ ይችላሉም ነው ያሉት።በኢትዮጵያ የብር ኖቶች ላይ መጻፍም ሆነ ሥዕል መሣል የተከለከለ ስለመሆኑም መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
የወርቅ መግዣው ዋጋ ማሻሻያ እንዳደረገ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ። ይህንንም ተከትሎ ባለፈው ሐምሌ ወር ብቻ የ72 ሚሊዮን ወርቅ ግዢ መፈፀሙም ታውቋል።

[አዲስ ማለዳ]
@YeneTube @FikerAssefa
አርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳን በመግደል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉት ጥላሁን ያሚ እና አብዲ ዓለማየሁ ዛሬ ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን፥ ፍርድ ቤቱ ለፖሊስ 10 ቀን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ፈቅዷል።

በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ተረኛ ችሎት ከዚህ በፊት አያያዛቸውን በተመለከተ የእስረኞች አስተዳደር ቀርቦ እንዲያብራራ ትእዛዝ መስጠቱን ተከትሎ ችሎቱ የምርመራ ውጤቱን ለመጠባበቅ የተሰየመ ሲሆን፥ ከእስረኞች አስተዳደር ግን ማንም ሰው ሳይገኝ ቀርቷል።መርማሪ ፖሊስም በጉዳዩ ላይ መረጃ እንደሌለው ጠቅሶ ሌላ ጊዜ እንዲቀርቡ ጠይቋል።መርማሪ ፖሊስ ከዚህ በፊት በተሰጠው ተጨማሪ ጊዜ የሰራቸውን የምርመራ ስራዎች ይፋ አድርጓል።ተጨማሪ የምስክሮችን ቃል መቀበሉን፣ የተለያዩ የቴክኒክ ማስረጃዎች መሰብሰቡን፣ ሌሎች አባሪዎች እና ግብረ አበሮችን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያደረገ መሆኑን ለችሎቱ አስረድቷል።

አርቲስት ሃጫሉ የተተኮሰበት ሽጉጥም የፎረንሲክ ምርመራ ተደርጎበት የወንጀሉ ፍሬ መሆኑን የሚያሳይ ውጤት እንደደረሰው አብራርቷል።እንዲሁም የሟች አስክሬን የምርመራ ውጤትን መቀበሉን የገለፀው መርማሪ ፖሊስ፥ ለብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎትም የስልክ ልውውጣቸውን እንደላከና ከግድያው በስተጀርባ ያሉ ተጨማሪ ጉዳዮችን በጥንቃቄ እየመረመረ መሆኑን ነው የዘረዘረው።በተጨማሪም ከጀርባቸው ብዙ አባሪዎች አሉ የሚል ጥርጣሪ ስላለኝ በጥንቃቄ ምርመራውን እያደረኩኝ መሆኑን ተከትሎ በወንጀለኛ መቅጫ ስነስርዓት ህጉ መሰረት ተጨማሪ የ14 ቀን ጊዜ ይሰጠኝ ሲል ፍርድ ቤቱን ጠይቋል።

አንደኛ ተጠርጣሪ ጥላሁን ያሚ በበኩሉ ”ወጥቼ የፀሃይ ብርሃን አላገኘሁም፣ ቅያሪ ልብስ አላገኘሁም፣ ስለዚህ ፍርድ ቤቱ ትእዛዝ ይስልጥኝ፣ ካተናዬም እንዲወልቅና ከፖሊስ ጣቢያ ወደ ማረሚያ ቤት እንድዛወር ይፍቀድልኝ” ሲል አቤቱታ አቅርቧል።ሁለተኛ ተጠርጣሪ አብዲ ዓለማየሁ ”ወደ ውጭ ወጥቼ የፀሃይ ብርሃን እንዳገኝ ፍርድ ቤቱ ይፍቀድልኝ” ሲል አመልክቷል።ፍርድ ቤቱም አያያዛቸውን በተመለከተ በቂ የፀሃይ ብርሃን እንዲያገኙ እንዲደረግ እና በዛሬው ትእዛዝ ያልቀረቡ የማረሚያ ቤት አስተዳደር ተወካዮች ለምን ቀርበው እንዳላብራሩ እንዲያስረዱ በድጋሚ እንዲቀርቡ ትእዛዝ ሰጥቷል።ለመርማሪ ፖሊስም ተጨማሪ የምርመራ ስራዎችን አከናውኖ እንዲመጣ 10 ቀን ፈቅዶለታል።

[FBC]
@YeneTube @FikerAssefa
ብሄራዊ ባንክ ከባንክ ውጭ ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ ማከማቸትን የሚከለክል መመሪያ አወጣ!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ማንኛውም ግለሰብ በቤት ውስጥ ወይም በሌላ አካባቢ ሊይዝ የሚችለውን የጥሬ ገንዘብ መጠን የሚገድብ መመሪያ አወጣ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ዶክተር ይናገር ደሴ እንደተናገሩት መመሪያው ከባንክ ውጪ ከ1.5 ሚሊዮን ብር በላይ ማስቀመጥ ክልክል እንደሆነ ይገልፃል።የባንኩ ገዥ ይህን ያሉት ብሄራዊ ባንክ ያወጣቸውን አራት መመሪያዎችን አስመልክቶ ለጋዜጠኞች መግለጫን በሰጡበት ወቅት ነው። ከተቀመጠው የገንዘብ መጠን በላይ ከባንክ ውጪ ማስቀመጥ መከልከሉም ሀገሪቱ የምታሳትመው የገንዘብ ኖት በተገቢው መልኩ ኢኮኖሚው ውስጥ እንዲዘዋወር ያግዛል ያሉ ሲሆን በተጨማሪም ህገ ወጥነትን ለመከላከል ይረዳል ብለዋል።የብሄራዊ ባንክ ገዥ ዶክተር ይናገር ደሴ እስከ 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ድረስ በቤትም ሆነ በሌላ ቦታ መያዝ እንደሚፈቀድና ከዚህ በላይ ገንዘብ ይዞ መገኘት እንደሚያስቀጣ ይፋ ያደረጉ ሲሆን የገንዘብ ኖት ባልተገባ ሁኔታ ጥቅም ላይ በመዋሉ ሀገሪቱ በውጭ ምንዛሬ የምታሳትመው የገንዘብ ኖት እየተበላሸ ለተጨማሪ ወጪ እንደዳረጋትም ገልፀዋል።

[Addis Zeybe]
@YeneTube @FikerAssefa1
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስር ሹመቶችን ዛሬ ሰጡ!

በዚህም መሰረት:

1. ዶ/ር ቀንዓ ያደታ የመከላከያ ሚኒስትር

2.ዶ/ር ጌድዮን ጢሞቴዎስ፤ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ

3.ዶ/ር ሳሙኤል ሁርካቶ፤ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር

4.ታከለ ኡማ፤ የማዐድንና ነዳጅ ሚኒስትር

5.ተስፋዬ ዳባ፤ ምክትል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ

6. ዮሐንስ ቧያለው፤ የኢትዮጵያ የውጭ ግነኙነት ስትራቴጂክ ጥናት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር

7.ንጉሡ ጥላሁን፤ የሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን ኮሚሽነር

8. እንደአወቅ አብቴ፤ የብረታ ብረት ኢንጅኔሪንግ ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተር

9.ፍቃዱ ጸጋ፤ ምክትል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ

10.ፕሮፌሰር ኂሩት ወልደ ማርያም፤ በሚኒስትር ማዕረግ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማኅበራዊ ዘርፍ አማካሪ

#PMOEthiopia
@YeneTube @FikerAssefa
ኢ/ር ታከለ ኡማ ከስልጣናቸው ተነሱ!

የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ምክትል ከንቲባ ሆነው ሲያገልግሉ የቆዩት ታከለ ኡማ ከስልጣናቸው ተነሱ። ምክትል ከንቲባው በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አማካኝነት የማዕድን እና ነዳጅ ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል።ከዛሬው ሹም ሽር ጋር ይገናኝ እንደው በግልጽ ባይነገርም የአዲስ አበባ ምክር ቤት ዛሬ ማክሰኞ ነሐሴ 12፤ 2012 አስቸኳይ ስብሰባ እንደሚያካሄድ ምንጮች ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገልጸዋል። የምክር ቤቱም አጀንዳ በይፋ አልተገለጸም።አቶ ታከለ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ሹመት ተከትሎ በግል የፌስ ቡክ ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት “አዲስ አበባን መምራት ትልቅ ዕድል ነው። ደጋግመን እንደምንለው፤ ‘በታሪክ አጋጣሚ ያገኘነውን እድል’ ላለማባከን ጥረናል” ሲሉ ጽፈዋል።

አዲስ አበባን በሚመሩበት ጊዜ ላገዟቸው ልባዊ ምስጋና ያቀረቡት ምክትል ከንቲባው “በፍጹም ቅንነት ላጎደልናቸው ነገሮችም ይቅርታ እጠይቃለሁ” ብለዋል።ታከለ ኡማን ይተካሉ ተብሎ ከፍተኛ ግምት ሲሰጣቸው የቆዩት እና ከወራት በፊት ጠቅላይ አቃቤ ህግ ሆነው የተሾሙት አዳነች አቤቤ በምክትላቸው ጌድዮን ጢሞቴዎስ መተካታቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ይፋ ካደረጉት የሹመት ዝርዝር መረዳት ተችሏል።በአዲስ አበባ መስተዳድር በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የማህበራዊ ዘርፍ ክላስተር አስተባባሪ ሲሰሩ የቆዩት እንዳወቅ አብቴም በዛሬው ሹም ሹር ከተካተቱ አስር ባለስልጣናት አንዱ ሆነዋል። አቶ እንዳወቅ የብረታ ብረት ኢንጅኔሪንግ ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሆነው መሾማቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

[ኢትዮጵያ ኢንሳይደር]
@YeneTube @FikerAssefa
በሕይወትና በንብረት ውድመት ፍርድ ቤት በቀረቡ ተጠርጣሪዎች ላይ ስለሚቀርቡ ዘገባዎች የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ምክረ ሀሳብ አቀረበ፡፡

ተቋሙ ምክረ ሀሳቡን ያቀረበው ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ነው፡፡የእንባ ጠባቂ ተቋም ለጠቅላይ ፍርድ ቤት በፃፈው ደብዳቤ የሰዎችን ሚዛናዊ መረጃ የማግኘትና የማሰራጨት መብትን ተግባራዊ ማድረግ መሆኑን ጠቅሷል፡፡የአርቲስት ሐጫሉ ሁንዴሳን ህልፈት ተከትሎ በደረሰው ጥፋት የተጠረጠሩ ታዋቂ ግለሰቦችና የተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮች አባላት የመንግስት የስራ ሀላፊዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስታውሶ ከፖሊስ ምርመራ ውጤት ጀምሮ የክርክሩ ሂደትና ውሳኔውን ለመከታተል የሚፈልገው ብዙ መሆኑን እንደሚረዳ ጠቅሷል፡፡ይሁንና ችሎቱን ለመከታተል የሚፈለገውን የሰው ቁጥር ያህል የሚበቃ ቦታ ባለመገኘቱ የተወሰኑት እንዲመለሱ መደረጋቸው በሰዎች መካከል ህጋዊ ያልሆነ ልዩነት መፍጠር እንዳይሆን ስጋቱን ጠቅሷል፡የሰዎችን ሚዛናዊ መረጃ የማግኘትና የማሰራጨት መብት ተግባራዊ ማድረግ ተገቢ መሆኑን ያመለከተው የእንባ ጠባቂ ተቋም አማራጭ ምክረ ሀሳቦችን አቅርቧል፡፡

የችሎቱን ሂደት ሁሉም የመንግስትና የግል መገናኛ ብዙሃን እንዲዘግቡት ማድረግና የችሎቱን ነፃነትና ገለልተኛነት ጥያቄ የሚያስገባ የተዛባ ወይም የተከለከለ መረጃ ካቀረቡ ህጋዊ ርምጃ መውሰድ እንደ አንድ አማራጭ እንዲታይ ሀሳብ አቅርቧል፡፡ይኽ ካልተቻለም በመንግስትና በግል የኤሌክትሮኒክስና መገናኛ ብዙሃን ፣ በሌላ በኩል በመንግስትና የግል ህትመት መገናኛ ብዙሃን አካላት የጨረታ ውድድር አድርጎ አሸናፊው የሚዲያ አካል በቀጥታ ስርጭት ለህዝብ እንዲያዳረስ የማድረግ አማራጭ እንዲታይ ሀሳብ አቅርቧል፡፡የችሎቱን የፍርድ ሂደት ፣መከታተል ለሚፈልጉም በፕላዝማ ቴሌቪዥን ተደራሽ ማድረግና የሚገኝ ከሆነ ለታዳሚዎቹ ደህንነትና ጥበቃ አመቺ በሆነ ሰፊ አዳራሽ እንዲከናወን ማድረግን በአማራጭነት ማየት አስፈላጊ መሆኑን አመላክቷል፡፡

[ሸገር ኤፍ ኤም]
@YeneTube @FikerAssefa
በአፋር ክልል በጎርፍ ውሃ የተከበቡ ወገኖችን በሄሊኮፕተር የማውጣቱ ስራ መጠናቀቁ ተገለፀ!

በአፋር ክልል በጎርፍ ተከበው የነበሩ ወገኖችን በሄሊኮፕተር ታግዞ የማውጣቱ ስራ መጠናቀቁን የክልሉ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።የመከላከያ እና አየር ኃይል አባላት ላበረከቱት አስተዋጽኦ የክልሉ መንግስትና ህዝብ ከፍተኛ ምስጋናና አክብሮት እንዳላቸውም ተገልጿል።የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ መሐመድ ሁሴን በክልሉ ዘንድሮ የጣለው ከባድ ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ በአዋሽ ዳር የሚገኙትን ጨምሮ በ11 ወረዳዎች ከ67 ሺህ ሰዎች በላይ ጉዳት ደርሶባቸዋል ብለዋል።ክእነዚህ ውስጥ ከ40 ሺ 700 በላይ ሰዎች በጎርፉ ምክንያት ከመኖሪያ አካባቢያቸው መፈናቀላቸውን ተናግረዋል።ብዛት ያላቸው ሰዎችም በጎርፍ ውሃ ተከበው ለአደጋ ተጋልጠው እንደነበር አውስተዋል።ክልሉ ከኢፌዲሪ መከላከያ እና አየር ኃይል ጋር በመተባበር ላለፉት አስር ቀናት በሄሊኮፕተሮች በመታገዝ በውሃ ተከበው የነበሩ ሰዎችን የማውጣትና አስቸኳይ የምግብ እርዳታ የማድረሱ ስራ በትጋት ሲያከናውን ቆይቷል ብለዋል።

በዚህም በአሳኢታ፣ አፋምቦ እና ገረኒ ወረዳዎች በውሃ ተከበው የነበሩ 4 ሺ 915 ሰዎችን በሁለት ሄሊኮፕተሮች በመታገዝ ወደ ሌሎች አካባቢዎች እንዲወጡ በማድረግ ትናንት በስኬት ማጠናቀቅ መቻሉን አቶ መሐመድ አስታውቀዋል።3 ሺህ 640 ሰዎች በአስቸጋሪ ሁኔታ በደራሽ ጎርፍ ተከበው የነበሩባቸው አካባቢዎች መከላከያ እና አየር ኃይል አስቸኳይ ምግብና ምግብ ነክ ቁሳቁሶችን ድጋፍ በማድረግ የላቀ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።በዚህም በክልሉ ተከስቶ በነበረው የጎርፍ ውሃ ምክንያት አንድም የሰው ህይወት እንዳይጠፋ በተለይ የምስራቅ ዕዝ አየር ኃይል አባላት የላቀ አስተዋጽኦ አድርገዋል ብለዋል።የሰራዊቱ አባላት እራሳቸውን ለአደጋ አጋልጠው ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ወገናቸውን ለመታደግ ላበረከቱት አስተዋጽኦ የክልሉ መንግስትና ህዝብ ከፍተኛ ምስጋናና አክብሮት ያላቸው መሆኑን አቶ መሐመድ አስታውቀዋል።

[FBC]
@YeneTube @FikerAssefa
ማስታወቂያ !

ምግብ ዶክመንት የላውንድሪ ልብስ ወይንም ማንኛውንም የረሱትን እቃ እናምጣልዎት!

📞6101 #GoFlex

የሞባይል መተግበሪያውን ያውርዱ ⬇️
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.goflex.app
ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ሆነው ተሾሙ

ወይዘሮ አዳነች አቤቤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሆነው ተሾሙ።

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት በዛሬው እለት ባካሄደው አስቸኳይ ጉባዔ ነው የምክትል ከንቲባ ሹመትን ያፀደቀው።

በዚህም መሰረት የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ወይዘሮ አዳነች አቤቤን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አድርጎ ሾሟል።

የቀድሞ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ባለፉት ሁለት አመታት የከተማ አስተዳደሩን በምክትል ከንቲባነት የመሩት ኢንጂነር ታካለ ኡማን የሚተኩ ይሆናል።

ኢንጂነር ታከለ ኡማ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ዛሬ በሰጡት የከፍተኛ የመንግስት የስራ ሐላፊዎች ሹመት የማዕድን እና ኢነርጂ ሚኒስትር ሆነው መሾማቸው ይታወሳል።

አዲስ የተሾሙት ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤም በምክር ቤቱ ቀርበው ቃለ መሃላ ፈፅመዋል።

Via:- FBC
@Yenetube @Fikerassefa
ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ሆነው ተሾሙ።
@YeneTube @Fikerassefa
የማሊው ፕሬዚዳንት ከስልጣናቸው ተነሱ!

የማሊው ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ቡባካር ኬታ ከዋና ከተማዋ ባማኮ በወታደሮች ከተያዙ በኋላ ከስልጣናቸው መልቀቃቸውን በቴሌቭዥን ቀርበው ተናግረዋል። በተጨማሪም የሀገሪቱን ፓርላማ እንደሚበትኑም አሳውቀዋል። እኔ በስልጣን ላይ እንድቆይ ምንም አይነት ደም መፍሰስ ስለሌለበት ከስልጣኔ ተነስቻለው ሲሉም ተደምጠዋል።እንደ ቢቢሲ ዘገባ የተያዙበት ምክንያት በወታደሮች ዘንድ ከደሞዝ ጋር የተያያዘ ቅሬታና ከጂዲስት ቡድኖች ጋር የሚደረገው ጦርነት አሁንም መቀጠሉ ሲሆን የሀገሪቱ ዜጎች ለፀጥታና የኢኮኖሚ ቀውስ ዳርገውናል በሚል የተቃውሞ ሰልፍ ሲወጡ ነበር የሰነበቱት።የማሊ የቀድሞ ቅኝ ገዥዋ ፈረንሳይ፣ እንዲሁም የአውሮፓና የአፍሪካ ህብረት ህገመንግስታዊ ያልሆነ ለውጥ በሀገሪቱ እንዳይደረግ በቅርቡ አስጠንቅቀው ነበር። አሁን ላይ ሀገሪቱ መሉ በሙሉ በመከላከያ ሰራዊቱ ቁጥጥር ስር ትሁን አትሁን የሚታውቅ ነገር የለም።

@YeneTube @FikerAssefa
ዓለም አቀፉ የመብት ተሟጋች ቡድን አምነስቲ ኢንተርናሽናል በቅርቡ በማሕበራዊ ሚድያ ገፁ ላይ የለጠፈውን ተንቃሳቃሽ ምስል 'የአምነስቲን የውስጥ ሂደት ያልተከተለ ነው' ብሏል።

የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የአፍሪካ ቀንድ የሰብዓዊ መብቶች አጥኚ የሆኑት አቶ ፍሰሃ ተክሌ ፍሰሃ አንዳንድ የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን አምነስቲ ትናንት ይቅርታ የጠየቀበትን ጉዳይ ድርጅቱ ግንቦት ወር ላይ ካወጣው ሪፖርት ጋር ማያያዛቸው ስህተት መሆኑንም ጠቁመዋል።የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን አምነስቲ በግንቦት ወር በኦሮሚያ እና አማራ ክልሎች በአንዳንድ ቦታዎች ስላለው የሰብዓዊ መብት አያያዝ ያወጣው ሪፖርት ስህተት መሆኑን ገልጾ ይቅርታ ጠየቀ ሲሉ ዘግበዋል።"ዓርብ ዕለት የወጣው ተንቀሳቃሽ ምስል ከሰኔ 23ቱ ግርግር እና እሱን ተከትሎ ስለሞቱ እና ስለታሰሩ ሰዎች ነው የሚመለከተው። ከዚያ ሪፖርት ጋር ምንም ግንኙነት የለውም። በዚያ ሪፖርታችን ውስጥ ያሉት ግኝቶች እና ምክረ ሃሳቦች አሁንም አሉ። የአገር ውስጥ ሚዲያዎች ዘገባ ተገቢ አይደለም" ብለዋል አቶ ፍሰሃ።

[BBC]
@YeneTube @FikerAssefa
በኦሮሚያ እና ድሬዳዋ ባጋጠሙ ግጭቶች ቢያንስ አራት ሰዎች መገደላቸው ተነገረ!

ትናንት እና ከትናንት በስቲያ በኦሮሚያ ክልል የሃረርጌ ዞኖች፣ በምዕራብ አርሲ ዞን እና በድሬዳዋ ከተማ ባጋጠሙ ግጭቶች ቢያንስ 4 ሰዎች መገደላቸውን እና በርካቶች መቁሰላቸውን ፖሊስ፣ የሆስፒታል ምንጮች እና የየአካባቢዎቹ ነዋሪዎች ለቢቢሲ ገልጸዋል።

👉ጭሮ

በመንግሥት ቁጥጥር ሥር የሚገኘው የአቶ ጃዋር መሐመድ ጤና ታውኳል የሚለው ዜና መሰማቱን ተከትሎ ሰዎች ከትናንት በስቲያ እና ትናንት በጭሮ ለተቃውሞ ከወጡ በኋላ ግጭት ተከስቶ ቢያንስ ሁለት ሰዎች መገደላቸውን የሆስፒታል ምንጭ ለቢቢሲ ተናግረዋል።የጭሮ ሆስፒታል ተጠባባቂ ሜዲካል ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ሳዳም አሉዋን በጥይት ተመትተው ወደ ሆስፒታላቸው ከመጡ 24 ሰዎች መካከል የሁለት ሰዎች ሕይወት ማለፉን ትናንት ለቢቢሲ ተናግረዋል።"በጥይት ተመትተው የመጡ ሰዎች አሉ። አጠቃላይ ቁጥራቸው 24 ነው። ከእነዚህ መካከል የ2 ሰዎች ሕይወት አልፏል" ብለዋል።ዶ/ር ሳዳም "ከሞቱት መካከል አንዷ ትልቅ ሴት ነች። በ40ዎቹ የእድሜ ክልል ውስጥ ትሆናለች። ጀርባዋን ተመትታ ነው የተገደለችው። ሌላኛው በ20ዎቹ ውስጥ የሚገኝ ወጣት ወንድ ነው። እሱም ከጀርባው ነው የተመታው" ሲሉ ተናግረዋል።

እንደ ዶ/ር ሳዳም ከሆነ፤ አንድ በጽኑ የተጎዳ ወጣት ለተጨማሪ የሕክምና እርዳታ ወደ አዳማ መላኩን ተናግረው፤ የተቀሩት አብዛኛዎቹ እጃቸውን እና እግራቸውን የተመቱ እና የአጥንት መሰበር ያጋጠማቸው መሆናቸውን ገልጸዋል።ለደህንነታቸው ሲባል ስማቸውን እንዳንገልጽ የጠየቁን የጭሮ ከተማ ነዋሪ፤ ከትናንት በስቲያ ከሰዓት 11 ሰዓት አካባቢ ቀበሌ 03 ተብሎ በሚጠራው ሥፍራ ግጭት ተከስቶ እንደነበረ ተናግረዋል።ትናንትም ከጭሮ ዙሪያ በርካቶች ለተቃውሞ ወደ ጭሮ ከተማ በሚመጡበት ወቅት የመንግሥት የጸጥታ ኃይል ሰዎቹን ለመበተን ተኩስ መክፈታቸውን ተናግረዋል።

👉ድሬዳዋ

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ትናንት በሰጠው መግለጫ በከተማዋ ከተከሰተው ሁከት እና ረብሻ ጋር ተያይዞ የሁለት ሰው ህይወት ማለፉን እና በአራት ሰዎች ላይ የመቁሰል አደጋ መድረሱን አስታውቋል።የከተማው ፖሊስ አስተዳደር "እኩይ አላማን ያነገቡ ኃይሎች ሰላማዊው ህብረተሰብ ውስጥ ተሸሽገው "12.12.12" በሚል ከውጪ የተሰጣቸውን የጥፋት ተልዕኮ ለማስፈፀም ላይ ታች ሲሉ የዋሉና የጣሩ ቢሆንም በጸጥታ ሃይላችን እና በሰላም ወዳዱ የከተማችን ነዋሪ ጥረት የጥፋት ድግሳቸው መና አድርጎ በቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል" ብሏል በመግለጫው።የከተማው ፖሊስ ጨምሮም፤ ለከተማዋ ሰላም እና የሕግ የበላይነትን ለማስከበር 'ለአፍታም ሸብረክ እንደማንል በድጋሚ ማረጋገጥ እንወዳለን' ሲል አስታውቋል።

👉አወዳይ

ትናንት እና ከትናንት በስትያ (ሰኞ 11/12/2012 እና ማክሰኞ 12/12/2012) በአወዳይ ከተማ ለተቃውሞ የወጡ ሰዎች ከመንግሥት የጸጥታ ኃይል ጋር መጋጨታቸው ተነግሯል።አንድ የአወዳይ ከተማ ነዋሪ ሰኞ እኩለ ቀን ላይ አቶ ጃዋር ታመዋል የሚለው ዜና ሲሰማ፤ 'ጃዋር መታከም አለበት፣ ከእስር መለቀቅ አለበት' የሚሉ መፈክሮችን የሚያሰሙ ወጣቶች መሰባሰብ ሲጀምሩ የመንግሥት የጸጥታ ኃይል አባላት ሰዎችን ለመበተን ተኩስ መክፈት መጀመራቸውን ለቢቢሲ ተናግሯል።"መፈክር እያሰሙ ሰልፍ ለመውጣት ሲሞክሩ የኦሮሚያ ልዩ ኃይል እና መከላከያ ሰራዊት ሰዎችን ማስቆም ጀመሩ። ከዛ ተኩስ ተከፍቶ ወደ 10 ሰዎች በጥይት ተመተዋል" ያሉ ሲሆን እኚህ የዐይን እማኝ ሁለት ሰዎች በጥይት ተመትተው መገደላቸውን አስረድቷል።ማክሰኞ እለትም በአወዳይ የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ ሙከራ መደረጉን የከተማ ነዋሪው ለቢቢሲ ተናግሯል።"ከ4 ሰዓት ጀምሮ ሰልፍ ሲካሄድ ነበር። በሽር የሚባል አካባቢ ተኩስ ተከፍቶ አንድ ሰው ተገድሏል። ከተማው አሁን ጸጥ ብላለች። የትራንስፖርት እንቅስቃሴ የለም። ሱቆችም ዝግ ናቸው" ብሏል።

👉ሐረር

የተቃውሞ ሰልፍ እና የገበያ አድማ መደረግ አለበት የሚሉ ሰዎች ለተቃውሞ ትናንት ረፋድ ላይ ለመሰባሰብ ሲሞክሩ በመንግሥት ጦር መበተናቸውን የከተማዋ ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል።ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ሐረር ከተማ በሚገኘው የሃረማያ ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል ውስጥ ሕክምና እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ቢቢሲ ካነጋገራቸው የሐረር ከተማ ነዋሪዎች ሰምቷል።

👉ሻሸመኔ

በተመሳሳይ በሻሸመኔ ከተማም የአቶ ጃዋር የመታመም ዜና ሲሰማ "ሰዎች እየተጯጯሁ ወደ ዋና መንገድ መውጣት" መጀመራቸው ተነግሯል።አንድ የከተማው ነዋሪ ለቢቢሲ ስትናገር፤ በተፈጠረው አለመረጋጋት ተኩስ ተከፍቶ አንድ በጥይት ተመቶ የወደቀ ወጣት መመልከቷን ተናግራለች።

👉የክልል መንግሥት ምላሽ

የኦሮሚያ ክልል ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ባልቻ በበኩላቸው፤ በአርሲ እና ሃረርጌ ዞኖች ግጭት መከሰቱን ገልጸው፤ በሰው እና በንብረት ላይ ስለደረሰው የጉዳት መጠን ግን መረጃ እስካሁን እንደሌላቸው ተናግረዋል።"ስለ ሻሸመኔ ብዙ መረጃ የለኝም። እንደ ዶዶላ እና አሳሳ ባሉ ከተሞች ግን እንደዚህ አይነት [የግጭት] ምልክቶች ታይተዋል። በአወዳይም መንገድ ለመዝጋት ጥረት ተደርጎ ነበር። ይህ ግን ከሙከራ ያለፈ አይደለም" በማለት አቶ ጌታቸው ለቢቢሲ ገልፀዋል።ቃል አቀባዩ ምንም እንኳ በተለያዩ አካላት በመላው ኦሮሚያ የሚጸና የተቃውሞ እና የገበያ አድማ ጥሪዎች ቢቀርቡም ይህ ሳይሳካ መቅረቱን ተናግረዋል።"በየትኛው የኦሮሚያ አቅጣጫ የመጓዝ እቅድ ያለው መሄድ ይችላል። መንገድ የተዘጋበት አካባቢ ስለመኖሩ ምንም አይነት መረጃ የለኝም" ብለዋል አቶ ጌታቸው።"በዚህች አገር ሁሉም ሰው ከሕግ ፊት እኩል ነው።በሕግ መጠየቅ ያለበት በሕግ ይጠየቃል" ያሉት አቶ ጌታቸው፤ ሰዎች ድምጻቸውን በሰላማዊ መልኩ ማሰማት የሚፈልጉ ከሆነ ሕጋዊ ስርዓቱን ተከትለው ለሚመለከተው አካል ስለ ሰላማዊ ሰልፉ አሳውቀው ድማጻቸውን ማሰማት ይችላሉ። ከዚህ ውጪ በዘፈቀደ የሚኖርባት አገር አይደለችም" ብለዋል።"ከአሁን በኋላ በፈለጉበት እየኖሩ የአመጽ እና የመንገድ መዝጋት ጥሪ በማቅረብ ተግባራዊ ለማድረግ መሞከር የሚቻል አይደለም" ሲሉም አቶ ጌታቸው አክለዋል።

[ቢቢሲ]
@YeneTube @FikerAssefa
8ኛው የበጎ ሰው ሽልማት በልዩ ሁኔታ ጷጉሜ 1 ይካሄዳል!

በየዓመቱ ማብቂያ ላይ የሚካሄደው የበጎ ሰው ሽልማት የ2012 ስምንተኛ መርሃግብር ጿጉሜ 1 ቀን 2012 በኢንተርኮንቲነንታል ሆቴል ይካሄዳል።የበጎ ሰው ሽልማት ድርጅት ዛሬ ሐምሌ 12/2012 በኢንተርኮንቲነንታል ሆቴል በሰጠው መግለጫ፤ የዘንድሮው የሽልማት መርሃ ግብር በልዩ ሁኔታ እንደሚካሄድ አስታውቋል።የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ ቀለመወርቅ ሚደቅሳ እንደተናገሩትም፤ ከየካቲት 1 ጀምሮ እስከ መጋቢት 15 እጩዎችን የመቀበልና አበርክቷቸውን የማጥናት ሥራ ሲሠራ ቆይቷል። በዚህም ከ200 በላይ እጩዎችን ተቀብሏል። ሆኖም በተከሰተው የኮቪድ ወረርሽኝ ምክንያት የጥናት ሥራው በእቅዱ መሠረት ሊከናወን እንዳልተቻለ አውስተዋል።

ስለዚህም ለወትሮው ልዩ ተሸላሚ በሚመረጥበትና በሚሸለምበት የቦርድ አባላት የጥቆማና ምርጫ ሂደት መሠረት፤ በታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ሥራ እንዲሳካ ላደረጉ እንዲሁም የኮሮና ቫይረስን በመከላከል ሥራ ላይ ግንባር ቀደም ከሆኑት መካከል ተሸላሚዎች ተመርጠዋል ተብሏል።በዚህ መሠረት ስምንት ተሸላሚዎች እንደሚኖሩና በሽልማቱ እለት ይፉ እንደሚደረግ ቀለመወርቅ አስታውቀዋል።የድርጅቱ የቦርድ ሊቀመንበር ዳንኤል ክብረት በበኩላቸው፤ ምንም እንኳን አገር በብዙ አስጨናቂ ክስተቶች መካከል ብትሆንም በጎዎችን ማመስገንና ማጉላትም አስፈላጊ እንደሆነ አንስተዋል።ሽልማት መርሃ ግብሩ ላይ ተገቢው ጥንቃቄ እንደሚደረግና ተመልካችም በቀጥታ ስርጭት እንደሚመለከተው ተናግረዋል።

[አዲስ ማለዳ]
@YeneTube @FikerAssefa
ከጎረቤት ሀገራት እየመጣለት ያለውን የኃይል አቅርቦት ጥያቄ ለመፍታት እየሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ገለጸ፡፡

ተቋሙ በ2012 የበጀት ዓመት ከኤሌክትሪክ ኤክስፖርት ለማግኘት ካቀደው ውጥን በላይ ማሳካቱን ተናግሯል፡፡ለሱዳን እና ጅቡቲ በየዓመቱ የአሌክትሪክ ኃይል የሚያቀርበው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከኬንያ ለቀረበለት ተመሳሳይ ጥያቄ መልስ ለመስጠት እየሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታውቋል። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በ2012 የበጀት ዓመት ወደ ሱዳን እና ጂቡቲ 992 ጊጋ ዋት ኃይል ልኮ ከ57 ሚሊዮን ዶላር በላይ ለመሰብሰብ ወጥኖ ከእቅድ በላይ ማሳካቱ ተነግሯል።

[አሐዱ ሬዲዮ]
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
የማሊው ፕሬዚዳንት ከስልጣናቸው ተነሱ! የማሊው ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ቡባካር ኬታ ከዋና ከተማዋ ባማኮ በወታደሮች ከተያዙ በኋላ ከስልጣናቸው መልቀቃቸውን በቴሌቭዥን ቀርበው ተናግረዋል። በተጨማሪም የሀገሪቱን ፓርላማ እንደሚበትኑም አሳውቀዋል። እኔ በስልጣን ላይ እንድቆይ ምንም አይነት ደም መፍሰስ ስለሌለበት ከስልጣኔ ተነስቻለው ሲሉም ተደምጠዋል።እንደ ቢቢሲ ዘገባ የተያዙበት ምክንያት በወታደሮች ዘንድ ከደሞዝ…
#Update

በማሊ በትናንትናው እለት ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ቡባካር ኬታ ላይ በመከላከያ ሰራዊቱ መፈንቅለ መንግሥት ከተፈፀመ በኋላ የአፍሪካ ህብረትና ተመድ በድርጊቱ ላይ ወቀሳ ሰነዘረው ነበር። ከዚህ መግለጫ በኋላ ወታደራዊ አመራሮች ፍላጎታቸው የሽግግር መንግሥት ለማቋቋም እንደሆነ ማሳወቃቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
በአገር ውስጥ የሚፈጠሩ አለመረጋጋቶች ህገወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር እንዲስፋፋ በር እየከፈቱ ነው-የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን
መንግስት የጦር መሳሪያ አስተዳደር እና ቁጥጥር አዋጅ አውጥቶ ተግባራዊ ማድረግ ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ጥብቅ የሆነ ቁጥጥር መደረጉ በተለያዩ ጊዜያት ሲታቀዱ የነበሩ የጦር መሳሪያ ዝውውርን ማምከን አስችሏል ብሏል።ህገወጥ የጦር መሳሪያ ንግድ በተለይ በአገሪቱ ውስጥ ግጭቶች እና አለመረጋጋቶች ሲስፋፉ እይተበራከተ ነው።ለዚህም የፌዴራል ፖሊስ የማዕከላዊ መረጃ ወንጀል ኢንተሊጀንስ በጥብቅ ቁጥጥር እየሰራ እንደሆነ ተነግሯል፡፡

[አሐዱ ሬዲዮ]
@YeneTube @FikerAssefa