YeneTube
119K subscribers
31.4K photos
484 videos
79 files
3.86K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የቻይና የመድሃኒት አምራች ድርጅት በተያዘው የፈረንጆቹ ዓመት መጨረሻ የኮቪድ -19 ክትባት ዝግጁ ይሆናል ተብሎ እንደሚጠበቅ አስታወቀ።

የዚህ ሲኖፋርም የተባለው ድርጅት ኃላፊ ሊዩ ጂንግዠን ለኮቪድ -19 ክትባት ይሆናል ተብሎ የሚጠበቀው አንደኛው ክትባት አሁን ላይ በዩናይትድ አረብ ኤምሬቶች ደረጃ ሦስት በሰዎች ላይ በሚደረግ ክሊኒካል ሙከራ ላይ እንደሚገኝ ለመገናኛ ብዙኃን ተናግረዋል።ይህ ክትባት በታህሳስ ወር መጨረሻ ላይ ገበያ ላይ ይውላል ተብሎ ይጠበቃል።ኃላፊው ራሳቸውም ሁለት መጠን [ዶዝ] ክትባት እንደወሰዱና እስካሁን ምንም ዓይነት የጎንዮሽ ጉዳት እንዳልገጠማቸው ለግሎባል ታይምስ ተናግረዋል።ቻይና በቤጂንግ በዓመት 120 ሚሊየን ዶዝ እና በዉሃን ደግሞ 100 ሚሊየን ዶዝ ማምረት የሚያስችል ማዕከላት አሏት።

ክትባቱ ለሁለት ዶዝ ከ144 ዶላር ባነሰ ዋጋ ለገበያ ይቀርባል ተብሏል።ይሁን እንጂ ዋጋውን አስመልክቶ አንዳንድ ቅሬታዎች ይነሳሉ። የቻይና የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ዋጋው በገጠር ለሚኖሩና የኢኮኖሚ አቅማቸው ዝቅተኛ የሆኑ ሰዎችን አቅም ሊፈታተን ይችላል እያሉ ነው።ቻይና አሁን ላይ በአገር ውስጥ በቫይረሱ የተያዘ ሰው አልመዘገበችም። በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ከውጪ የገቡ ናቸው። ነገር ግን በገጠራማ አካባቢ ወረርሽኙ ሊያገረሽ ይችላል የሚል መጠነኛ ስጋት አለ።በዓለማችን ከ200 የሚበልጡ ክትባቶች በምርምር ላይ ሲሆኑ ከእነዚህ መካከል ከ20 የሚበልጡት በሰዎች ላይ የክሊኒካል ሙከራ ደረጃ ላይ ደርሰዋል።

[ቢቢሲ]
@YeneTube @FikerAssefa
የደብረ ታቦር በዓል( ቡሄ) በደብረ ታቦር ከተማ በዛሬው ዕለት እየተከበረ ይገኛል።

በዓሉ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን አማንያን ዘንድ ኢየሱስ ክርስቶስ በታቦር ተራራ ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበትን በማሰብ በየአመቱ ነሃሴ 13 ይከበራል።የደብረ ታቦር በዓል (ቡሄ) በበዓሉ ስያሜ በምትጠራው ጥንታዊቷ የደብረታቦር ከተማ ኢየሱስ ቤተክርስትያን ነው እየተከበረ የሚገኘው።የቡሄ በዓል ከሃይማኖታዊ አከባበሩ ባለፈ ህዝባዊ በዓልም ሲሆን አሮጌውን አመት ለመጨረስ አዲሱን አመት ለመቀበል ዝግጅት በሚደረግበት ወቅት የሚከበር በመሆኑ ተስፋን ይዞ የሚመጣ በዓል መሆኑ በብዙዎች ዘንድ ይነገራል።

በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ ሕጻናት በዓሉ ከመድረሱ በፊት ቀደም ብለው ጅራፍ ሲገምዱና ሲያጮሁ ይቆያሉ።በደብረ ታቦር ከተማ መከበሩ የከተማዋን የጎብኚዎች ቁጥር በማሳደግ ኢኮኖሚውን ከፍ ለማድረግ አስተዋጽኦው የላቀ መሆኑም ተነግሯል።በተለይ የቡሄ በዓልና መሰል በዓላት የሰዎችን ግንኙነት ከፍ የሚያደርጉ በመሆኑ ወንድማማችነትን ለማጠናከር፣ አብሮ መኖርን ለማሳደግ፣ አንድነትን ለማጠናከርና ፍቅርንም ለማጎልበት የጎላ ጠቀሜታ እንዳለው ተጠቁሟል።

[FBC]
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ በኮሌራ ምክንያት የ8 ሰዎች ህይወት ማለፉን የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ።

ኢንስቲትዩቱ በላከው መግለጫ እስከ ሀምሌ ወር የመጨረሻው ሳምንት 145 ሰዎች በኮሌራ ወረርሽኝ ሲያዙ 8 ሰዎች ደግሞ ህይወታቸው አልፏል ብሏል፡፡የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የኮሌራ በሽታን በተመለከተ የሕብረተሰብ ጤና ስጋቶች እና ምላሽ አሰጣጥ ላይ ለጣቢያችን በላከው መግለጫ በአገር አቀፍ ደረጃ እስከ ሃምሌ የመጨረሻው ሳምንት በተለያዩ አካባቢዎች የኮሌራ በሽታ ተከስቶ እስካሁን 145 የሚሆኑ ሰዎች አዲስ በበሽታው ሲያዙ 8 ሰዎች ደግሞ በኮሌራ ምክንያት ህይወታቸውማለፉን አስታውቋል፡፡

በደቡብ ክልል በ6 ወረዳዎች እና በኦሮሚያ ክልል በ1 ወረዳ የኮሌራ ወረርሽኝ ከተከሰተባቸው አካባቢዎች የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ ይሁን እንጂ ይህ አሃዝ ከባለፈው ሳምንት ሪፖርት ጋር ሲነጻጸር በ50 በመቶ መቀነሱ ታውቋል፡፡እስከ ሃምሌ የመጨረሻው ሳምንት ድረስ በምዕራብ ኦሞ ዞን ፣ በጋጪት እና በጎርጎርሻ ወረዳዎች በአዲስ መልክ በሽታው መከሰቱም ሪፖርቱ ያመላክታል፡፡ የኮሌራ ወረርሽኝን ለመከላከል የህክምና አገልግሎት የማስፋፋት፣ የውሃ ንጽህና መጠበቂያ ኬሚካሎችን የማሰራጨት፣ የቤት ለቤት ርጭት እና በበሽታው ከተያዙ ሰዎች ጋር ግንኙነት ያላቸውን ሰዎች የማፈላለግ እና የክትትል ስራዎች ተጠናክረው ቀጥለዋልም ተብሏል፡፡

በተጨማሪም እስከ ሃምሌ ወር የመጨረሻ ሳምንት ድረስ በሃገር አቀፍ ደረጃ ለወባ በሽታ ከተመረመሩት ውስጥ 27 ሺ 898 ሰዎች ምልክት የታየባቸው ሲሆን 2 ሰዎች በዚሁ ምክንያት ህይወታቸው አልፏል፡፡በሃገራችን በ42 ወረዳዎች ና በ19 ዞኖች የወባ ወረርሺኝ ተከስቷል፤ በኦሮሚያ 7 ዞኖችና 15 ወረዳዎች ፣ በደቡብ 1 ዞንና በ2 ወረዳዎች ፣ በአማራ በ 7 ዞኖችና በ21 ወረዳዎች ፣ በሶማሊያ በ1 ዞንና በ1 ወረዳ እንዲሁም በትግራይ በ3 ዞኖችና በ3 ወረዳዎች ወረርሺኙ የተከሰተባቸው አካባቢዎች ሲሆኑ የምላሽ ስራ እየተሰራባቸው ነው ተብሏል፡፡በተመሳሳይም እስከ ሃምሌ ወር መጨረሻ ድረስ በሃገራችን 32 ሰዎች ፖሊዮ እንደተገኘባቸው ተነግሯል፡፡በዚህ ሳምንት በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ሐረርጌ በቦኬ ወረዳ እና በአዳማ ከተማ 2 ሰዎች በፖሊዮ መያዛቸውን ከኢንስቲትዩቱ ሪፖርት ተመልክተናል፡፡

[ኢትዮ ኤፍ ኤም]
@YeneTube @FikerAssefa
ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት በተጠረጠሩበት ወንጀል ዐቃቤ ህግ በ10 ቀን ውስጥ ክስ እንዲመሰርት ብይን ተሰጠ!

ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት በተጠረጠሩበት ሁከትና አመጽ በማስነሳት በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት ማድረስ ወንጀል አቃቤ ህግ በ10 ቀን ውስጥ ክስ እንዲመሰርት ብይን ተሰጠ፡፡መርማሪ ፖሊስ በኢኒጂነር ይልቃል ላይ ሲያከናውን የነበረውን ምርመራ ማጠናቀቁን እና መዝገቡንም ለዐቃቤ ህግ መስጠቱን ለችሎቱ ገልጿል፡፡ዐቃቤ ህግም በስነ ስርዓት ህጉ 109 መሰረት በቂ ማስረጃ ስላለኝ ክስ መመስረቻ 15 ቀን ጊዜ ይሰጠኝ ሲል አመልክቷል፡፡ኢንጂነር ይልቃል በበኩላቸው እኔ በፖለቲካ ተሳትፎዬ ነው የታሰርኩት ያሉ ሲሆን ÷ የታሰሩበት ቦታ ለኮሮናቫይረስ ተጋላጭ መሆኑንም አቤቱታ በማቅረብ ዋስትና እንዲፈቀድላቸው ጠይቀዋል፡፡ዐቃቤ ህግም የተጠረጠሩበት ወንጀል ስልጣን ባለው ፍርድ ቤት ክስ ቢመሰርት ከ15 አመት በላይ የሚያስቀጣ እና ዋስትና የሚያስከለክል በመሆኑ የዋስትና ጥያቄያቸው ውድቅ እንዲደረግ ጠይቋል፡፡ጉዳዩን የተከታተለው የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ አራዳ ምድብ ተረኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎትም የዋስትና ጥያቄያቸውን ውድቅ በማድረግ ዐቃቤ ህግ በ10 ቀን ውስጥ ክስ እንዲመሰርት ብይን ሰጥቷል፡፡

[FBC]
@YeneTube @FikerAssefa
የ"ገበታ ለሀገር" የገቢ ማሰባሰቢያ የባንክ ሒሳብ ቁጥር ይፋ ተደረገ!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለገበታ ለሀገር የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ-ግብር የባንክ ሒሳብ ቁጥር በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ይፋ አድርገዋል። "የዛሬ ዓመት ቃል የገባነውን ፈጽመን በተግባር አሳይተናል" ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ አሁን ደግሞ መላው ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች በገበታ ለሀገር ተሳትፈው ዐሻራቸውን በኢትዮጵያ እንዲያሳርፉ ጋብዘዋል።
በዚህም፦

👉የ10 ሚሊ. እና የ5 ሚሊ. ብር ገቢ ለማድረግ፣ እንዲሁም ከሀገር ውስጥ ማንኛውም መጠን ያለውን የገንዘብ አስተዋጽዖ ለማድረግ: የባንክ ሂሳብ ቁጥር፦ 1000339911267፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ አዲስ አበባ ቅርንጫፍ፤

👉 ከሀገር ውጪ ሆነው ማንኛውም መጠን ያለውን የገንዘብ አስተዋጽዖ ለማድረግ: የባንክ ሂሳብ ቁጥር፦ 0100101300591፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ

👉 በተጨማሪም፣ መላው ኢትዮጵያውያን የሚፈልጉትን ያህል የገንዘብ መጠን ለማዋጣት ወደ 333 አጭር የጽሑፍ መልዕክት በመላክ አሻራቸውን እንዲያሳርፉ ተጋብዘዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
10 የማዕድን ምርመራ እና 2 የማዕድን ምርት ፈቃዶች ተሰጡ!

የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር በተለያዩ የሃገራችን ክፍሎች የማዕድናት ፍለጋ እና ልማት ለማካሄድ ፈቃድ ለጠየቁና የፈቃድ መውሰጃ መስፈርቶችን አሟልተው ለቀረቡ ለ12 የማዕድን ኩባንያዎች ፈቃድ ተሰጥቷል፡፡ሁለቱ የምርት ፈቃዶች ሲሆኑ አስሩ የምርመራ ፈቃዶች ናቸው፡፡
የምርት ፈቃድ የተሰጣቸው የባዛልት እና የዕምነበረድ ማዕድን ምርት ሲሆኑ ሌሎች አስር ኩባንያዎች ደግሞ በደለል ወርቅ፣ ወርቅና መሰል ማዕድናት፣ ብረት፣ ማንጋኔዝ፣ ክሮማይት፣ ብር እና ጀም ስቶን ማዕድናት ምርመራዎች ናቸው፡፡ሁለቱ የምርት ፈቃዶች ለኢንቨስትመንት 270,186,310.00 (ሁለት መቶ ሰባ ሚሊዮን አንድ መቶ ሰማንያ ስድስት ሺ ሶስት መቶ አስር) የተመዘገበ ካፒታልና ለ187 ዜጎች የስራ ዕድል የሚፈጥሩ ሲሆን የምርመራ ፈቃዶች ደግሞ 131,935,555.00 (አንድ መቶ ሰላሳ አንድ ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ መቶ ሰላሳ አምስት ሽህ ዘጠኝ አምስት መቶ አምሳ አምስት) ብር የተመዘገበ ካፒታል እና በምርመራ ወቅት በድምሩ ለ293 ዜጎች የስራ ዕድል ይፈጥራሉ ተብሏል፡፡

[የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር]
@YeneTube @FikerAssefa
ኢ/ር ታከለ ኡማ አዲስ ከተሾሙት ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ጋር የስራ ርክክብ አደረጉ።

የምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከከተማው ካቢኔ አካላት ጋርም ትውውቅ አድርገዋል።“ኢንጂነር ታከለ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን በንቃት ሲያከናውን ቆይቷል” ያሉት ም/ከንቲባ አዳነች አቤቤ “አሁንም ውጤታማ ስራ መስራት የሚችል ወጣት መሪ ስለሆነ በሄደበት መልካም እና ስኬት እንዲሆንለት ከልብ እመኝለታለሁ።”በማለት በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡ኢ/ር ታከለ ኡማ በበኩላቸው በከተማዋ አጠቃላይ የሥራ ሂደት ላይ ሰፊ ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸው ለም/ከንቲባዋ መልካም የስራ ዘመን እንዲሆንላቸው ተመኝተዋል፡፡በተጨማሪም ኢ/ር እንዳወቅ አብቴ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ ሆነው ከተሾሙት አቶ ጃንጥራር አባይ ጋር የስራ ርክክብ አድርገዋል።

[የአዲስ አበባ ከተማ ፕሬስ ሴክሬቴሪያት]
@YeneTube @FikerAssefa
👍1
በመተከል ዞን የህዝብን ሰላም ሲያውኩ የነበሩ የታጠቁ ሃይሎች መደምሰሳቸውን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አስታወቀ።

በዞኑ ከ20 ቀናት በፊት ሰላማዊ ዜጎችን በመግደል እና በተለያዩ ወንጀሎች ተጠርጥረው በህግ ቁጥጥር ስር የዋሉ ሰዎች ቁጥርም 225 መድረሱ ተገልጿል።የክልሉ መንግስት ኮሚንኬሽን ዳሬክተር አቶ መለሰ በየነ ለኢት ኤፍ ኤም እንዳሉት በመተከል ዞን ወንበራ ወረዳ ፒሬ አካባቢ 5 ታጣቂዎች ሲገደሉ 3 ተጨማሪ ግለሰቦች እስከ ትጥቃቸው በመንግስት የፀጥታ ሀይሎች መማረካቸውን ገልጸዋል።እነዚህ ሀይሎች በመተከል ዞን በጉባ እና ወንበራ ወረዳዎች የሚኖሩ ነባር የጉምዝ የሀገር ሽማግሌዎችን ለብልፅግና ፓርቲ መረጃ እየሰጣችሁ ነው በሚል በማገትና ጫካ ውስጥ በመውሰድ ድብደባ በማድረስ እንዲሁም የሰብዓዊ መብት ጥሰት የመፈፀም ድርጊቶችን ሲፈፅሙ እንደነበረ ገልፀዋል፡፡የክልሉ መንግስት እነዚህ መረጃዎች እንደደረሱን ከመከላከያ ሰራዊትና ልዩ ሀይል ጋር በመቀናጀት በቀጥታ ከእነዚህን ሀይሎች ጋር ውጊያ መጀመሩን ተናግረዋል።

ታትጥቀው በጫካ ከሸፈቱት ሀይሎች ጋር በነበረው የተክስ ልውውጥ ብዙዎችን በቁጥጥር ስር ማዋል በመጀመሩ ተስፋ እየቆረጡ በተበታተነ ሁኔታ እየተማረኩ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡በወንበራ ወረዳ ፒሬ በሚባል አካባቢ መከላከያ ሰራዊት በወሰደው ኦፕሬሽን አጣብቂኝ ውስጥ በመክተት በተደረገው የተክስ ልውውጥ 5 ታጣቂዎች በኦፕሬሽኑ መገደላቸውን ገልፀዋል፡፡በተጨማሪም 3 ተጨማሪ ግለሰቦችን እስከትጥቃቸው በፀጥታ አካሉ እንደተማረኩ አክለው ገልፀዋል፡፡ የተቀሩትን ሀይሎች በፍጥነት ለመቆጣጠር ጥረት ቢደረግም ያመለጡ አሉ ያሉት አቶ መለስ እነርሱን አድኖ በቁጥጥር ስር ለማዋል እርምጃዎች እንደቀጠሉ ናቸው ብለዋል፡፡ጫካ ሸፍተው የነበሩት እነዚህ ታጣቂዎች በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል መተከል ዞን ጉባና ወንበራ በሚባሉ ወረዳዎች በውስጥም በውጭም የተሰጣቸውን ተልዕኮ ለማስፈፀም ሲንቀሳቀሱ እንደነበረ ተናግረዋል።

እነዚህ የታጠቁ ሀይሎች ከመከላከያ ሰራዊት በተለያዩ ምክንያቶች እንደሆኑ መረጋገጡንም ሃላፊው ነግረውናል።አቶ መለሰ አክለውም የሀገሪቱን የፀጥታ ሁኔታዎችን ለማስተጓጎል ከህወሀትና ከግብፅ ተልዕኮ የተሰጣቸው መሆኑን ደርሰንበታል ይላሉ፡፡አሁን የሸፈቱት ታጣቂዎች ተስፋ እየቆረጡ እና ቁጥራቸውም እየመነመነ መሆኑን የሚናገሩት አቶ መለስ እስካሁንም በክልሉ ሁከት ሲያስነሱ የነበሩ የወረዳ አመራሮችን ጨምሮ በአጠቃላይ ከ225 በላይ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር አውለናል ብለዋል፡፡የክልሉና የፌደራል መንግስት ለስፍራው ልዩ ትኩረት በመስጠት የአካባቢው ፀጥታ እንዳይደፈርስ በቁርጠኝነት ስራዎች ሲሰሩ እንደነበር ተናግረዋል፡፡ በዚህም አርኩ ውጤቶች ታይተዋል ያሉት ሀላፊው አሁን ላይ በክልሉ ሁሉም ዞኖችና ወረዳዎች ሰላማዊ እንቅስቃሴ እንደቀጠለ መሆኑን ተናግረዋል።

[ኢትዮ ኤፍ ኤም]
@YeneTube @FikerAssefa
በጋምቤላ ክልል ማንነታቸው ያልታወቁ ግለሰቦች ባደረሱት ጥቃት የ2 ሴቶች ህይወት አለፈ፡፡

ከሰሞኑ በክልሉ ላይ ሁሉት ሴቶች ማንነታቸው አልታወቁም በተባሉ ግለሰቦች ጥቃት ሳቢያ ህይወታቸው ሊያልፍ መቻሉን የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ አስታውቋል፡፡የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ዘርፍ ም/ሃላፊ ኦቶው ኦኮት እንዳስታወቁት ግለሰቦቹ ከሰሞኑን በሁለት ሴቶች ላይ በፈፀሙት ጥቃት ሳቢያ ህይወታቸው ሊያልፍ ችሏል፡፡ድርጊቱን ተከትሎ የክልሉ ፓሊስ ባደረገው ምርመራና ማጣራት ጥቃት አድርሰዋል የተባሉ ግለሰቦችን ተከታትሎ መያዝ መቻሉንና እነዚህ ግለሰቦችም ክስ እንዲመሰረትባቸው የማድረግ ስራ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ከድርጊቱ ጋር ተጠርጣሪ የሆኑ አካላት አብዛኛዎቹ በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም ነው የተናገሩት፡፡የደረሰውን ጥቃት ተከትሎ የአካባቢው ወጣቶች በመቆጣት በከተማዋ ሊፈጠር የነበረ ግርግር ቢኖርም የሃገር ሽማግሌዎችና የፀጥታ አካላት በጋር በመሆን ሁኔታውን ማረጋጋታቸውን ተናግረዋል።አሁን ላይ ከተማዋ ወደ ቀደመ ሰላሟ መመለሷን ሰምተናል፡፡

[Ethio FM]
@YeneTube @FikerAssefa
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ሠራተኞች የአንድ ወር ደመወዛቸውን "ለገበታ ለሀገር" አበረከቱ

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ሠራተኞች የአንድ ወር ደመወዛቸውን "ለገበታ ለሀገር" ማበርከታቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው አስታውቀዋል።
"ገበታ ለሀገር የሁላችንም ነው" ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ለዕቅዱ እንዲውል የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ባልደረቦች የአንድ ወር ደመወዛቸው በማዋጣት አብረዋቸው በመሆናቸውም አመስግነዋል።

እያንዳንዱ የጽ/ቤቱ ባልደረባ አሻራውን እየተወ መሆኑን ገልጸው፣ ሁሉም ኢትዮጵያዊ እንዲሁ ድጋፉን እንደሚያደርግ ተስፋ እንደሚያደርጉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
ሁሉም ሕፃናት ትምህርት ቤት እንዲገቡ የሚያስገድድ ረቂቅ ሕግ ተዘጋጀ!

ሁሉም ሕፃናት ትምህርት ቤት እንዲገቡ የሚያስገድድ ረቂቅ ሕግ ተዘጋጅቶ ውይይት እየተደረገበት መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡ትምህርት ሚኒስቴር የተማሪዎች የመማር መብትና ትምህርት የሚከታተል ግዴታን አካቶ ባረቀቀው ሕግ መሠረት፣ ዕድሜው ለትምህርት የደረሰ ማንኛውም ሕፃን በመንግሥት ትምህርት ቤቶች ከቅድመ መደበኛ እስከ ስምንተኛ ክፍል ድረስ ትምህርት በነፃ የመማር መብት አለው፡፡ ትምህርቱን የመከታተል ግዴታ እንዳለበትና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ደግሞ በነፃ እንደሚሰጥም ይደነግጋል፡፡ማንኛውም ወላጅ ወይም አሳዳጊ ልጁን ወደ ትምህርት ቤት መላክና ትምህርቱን እንዲከታተል የማድረግ ግዴታ እንዳለበት በረቂቅ ሕግ ተካቷል፡፡ተማሪዎች ትምህርታቸውን ያለማቋረጥ መከታተላቸውን ማረጋገጥ ደግሞ የትምህርት ቤቱ ግዴታ መሆኑን ያትታል፡፡የሕፃናትን የመማር መብት የሚያረጋግጠው ረቂቅ ሕግ ውይይት እየተደረገበት ሲሆን፣ በሚመለከተው አካል ሲፀድቅ ተግባራዊ እንደሚደረግ ከአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

[Reporter]
@YeneTube @FikerAssefa
ሁከት በማስነሳት የተጠረጠሩ 4 የአሥራት ቴሌቪዥን ጋዜጠኞች ዛሬ 8 ተጨማሪ የምርመራ ቀናት እንደተሰጠባቸው አሥራት ሜዲያ ሃውስ ዘግቧል፡፡ችሎቱ ተጨማሪ ቀናት የፈቀደው፣ ፖሊስ የተጠርጣሪዎቹን ቃል እንደተቀበለ ገልጾ ተጨማሪ ምርመራ እንደሚቀረው በመጠየቁ ነው፡፡ ተጠርጣሪዎቹ የእስር አያያዛችን ለኮሮና ቫይረስ ስለሚያጋልጠን እንዲስተካከልልን ትዕዛዝ ይሰጥልን ሲሉ በድጋሚ ለችሎቱ አቤት ብለዋል፡፡ቀደም ሲል ችሎቱ የሰጠውን ትዕዛዝ ለምን እንዳልፈጸመ፣ የእስረኞች ጥበቃ እና አስተዳደር ቀርቦ እንዲያስረዳ ችሎቱ አዟል፡፡

[Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 1,336 ሰዎች በኮቪድ-19 ሲያዙ፣ 28 ሰዎች ደግሞ ህይወታቸው አልፏል!

ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገው 21,326 የላብራቶሪ ምርመራ 1,336 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ28 ሰዎች ህይወት አልፏል።በተጨማሪም 370 ሰዎች አገግመዋል። በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 34,058 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 600 ደርሷል፤ አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 13,308 ደርሷል።

@YeneTube @FikerAssefa
በድሬዳዋ የቺኩንጉንያና ደንጊ በሽታ ምልክቶች መታየት መጀመራቸውን የአስተዳደሩ ጤና ቢሮ አስታወቀ።በሽታዎቹ ከመስፋፋታቸው በፊት አስቀድሞ የመከላከል ሥራ እንዲሰራ የከተማዋ ከንቲባ አቶ አህመድ መሀመድ ቡህ ጥሪ አቅርበዋል። ያቆሩ ወሃዎችን የማፋሰስ ሥራ ትኩረት እንዲሰጠው ተጠይቋል።

[VoA]
@YeneTube @FikerAssefa
በጎንደር ዙሪያ ወረዳ ከሰሞኑ በደረሰ የመሬት መንሸረታት አምስት የቤተሰብ አባላት ሕይወት አለፈ፡፡

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ጎንደር ዙሪያ ወረዳ ደብረሰላም ቀበሌ ከሰሞኑ በጣለው ከባድ ዝናብ በተፈጠረ የመሬት መንሸራተት አምስት የቤተሰብ አባላት ሕይወታቸው አልፏል፤ ሀብትና ንብረታቸውም በናዳው ጠፍቷል፡፡የተጎጂዎች ቤተሰብ ቄስ ዓለሙ ሞትባይኖር ለአብመድ እንደተናገሩት እህታቸው ከባለቤታቸውና ከሶስት ልጆቻቸው ጋር ሕይወታቸው አልፏል፡፡ናዳው በሌሊት በመከሰቱ ተጎጂዎች ሰው ሳይደርስላቸው እንደቀረ የተናገሩት ቄስ ዓለሙ እስከቤቱ ተደርምሶ እንደተገኙ ተናግረዋል፡፡ ሕይወታቸውን ያጡት ቤተሰቦች ሁለት ልጆቻቸው በወቅቱ ከቤት ስላልነበሩ ተርፈዋል ነው ያሉት፡፡ ልጆቹ አሁን ላይ ረዳት እንደሌላቸውም ተናግረዋል፡፡

በመንግሥት በኩልም እስካሁን ድረስ መጥቶ ከማዬት የዘለለ ነገር የተደረገ ድጋፍ አለመኖሩንም ተናግረዋል፡፡ናዳው አምስት የቤተሰብ አባላቱን ከማጥፋቱም በላይ በአካባቢው ማኅበረሰብ ሰብል ላይ ገዱት ማድረሱንም ተናግረዋል፡፡አካባቢው ከአሁን ቀደም እንደዚህ አይነት አደጋ ተከስቶበት እንደማያውቅ ያስታወሱት ቄስ ዓለሙ እንደከዚህ ቀደሙ ምንም አይፈጠር በማለት እንደተዘናጉ ጉዳት እንደደረሰባቸው ነው የተናገሩት፡፡አሁንም በተራራው ግርጌ የሚኖሩ የማሕበረሰብ ክፍሎች በስጋት ላይ እንደሚኖሩ ተናግረዋል፡፡ለማሕበረሰቡም ጊዜያዊ መጠለያ መዘጋጀት እንዳለበት ነው የተናገሩት፡፡ ዝናብ በዘነበ ቁጥር መደናገጥ እየተፈጠረ መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡

[AMMA]
@YeneTube @FikerAssefa
የአንበጣ መንጋ ከትናንት በስትያ ጀምሮ በትግራይ ክልል ሦስት ወረዳዎች መከሰቱን የክልሉ ግብርናና ገጠር ልማት ቢሮ አስታውቋል። የአምበጣ መንጋው እስከ አሁን በተወሰነ የጤፍ አዝርዕት ላይ ጉዳት ያደረሰ ሲሆን የጉዳት መጠኑ እየተጠና ነው ተብሏል።

[VoA]
@YeneTube @FikerAssefa
በህገ-ወጥ መንገድ ከሀገር ሊወጣ የነበረ 449,700 የአሜሪካ ዶላር ተያዘ!

ብዛቱ 449,700 የሆነ የአሜሪካ ዶላር በሁመራ መስመር በሦስት የኢትዮጵያ ዜግነት ባላቸው ግልሰቦች ከሀገር ለማስወጣት ሲሞከር ነው ነሐሴ 12 ቀን 2012 ዓ.ም የተያዘው፡፡በወቅታዊ ምንዛሪ ተመን 17.8 ሚሊዮን ብር ዋጋ ያለው ገንዘብ እና በህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውሩ የተጠረጠሩ ሶስት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

[የገቢዎች ሚኒስቴር]
@YeneTube @FikerAssefa
በትግራይ ክልል ከከተማ ቦታ ጋር በተያያዘ የሚፈጠሩትን የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት የሚያግዝ ዘመናዊ የከተማ መሬት ምዝገባ /የካዳስተር / መጀመሩን የክልሉ የካዳስተር ኤጀንሲ ገለጸ።

ችግሮቹን በዘላቂነት ለመፍታት ዘመናዊ አዲስ የከተማ መሬት የአስተዳደር አሰራር ለመዘርጋት በቴክኖለጂ የታገዘ የከተማ መሬት የባለቤትነት ምዝገባ መጀመሩን በኤጀንሲው የምዝገባና ቅየሳ ማረጋገጫ ዳይሬክተር አቶ ሙሉብርሃን ገብረመድህን ተናግረዋል።

በምዝገባው የመንግስትም ሆነ የግለሰብ የመሬት ይዞታ ስፋትና በውስጥ ያለውን ሁሉ በዝርዝር እንዲሰፍር የሚደረግ መሆኑን አስረድተዋል።እያንዳንዱ ባለ ይዞታ የራሱ መለያና ሚስጢራዊ ቁጥር ስለሚኖረው በቀላሉ ሊጭበረበር በማይችል መልኩ እንዲመዘገብ እየተደረገ ነው ብለዋል።

[ENA]
@YeneTube @FikerAssefa
በኮረና ቫይረስ ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ የሚውል ጤፍ መግዛት እንፈልጋለን በማለት መቶ ኩንታል ጤፍ አታለው የተሰወሩ 3 ተጠርጣሪዎች ከነ ኤግዚቢቱ መያዛቸውን የአ/አ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

@YeneTube @FikerAssefa
👍1
የአፍሪካ ህብረት ማሊን ከአባልነት አገደ!

በማሊ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት መካሄዱን ተከትሎ የአፍሪካ ህብረት ሀገሪቱን ከአባልነት አግዷል።እገዳው ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱ እስኪመለስ ድረስ እንደሚቆይ ተጠቁሟል።በተጨማሪም በእስር ላይ የሚገኙት የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ቡባካር ኬታን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ ባለሥልጣናት እንዲለቀቁም ህብረቱ መጠየቁን ሮይተርስ ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa