"ኢትዮጵያ በመጭዎቹ ሁለት ሳምንታት የግድቡን ቀሪ የግንባታ ስራዎች በማጠናቀቅ ሙሌት ትጀምራለች፣ በነዚህ ሁለት ሳምንታት ሀገራቱ ስምምነት ላይ ለመድረስ ወስነዋል።"
#PMOEthiopia
@YeneTube @FikerAssefa
#PMOEthiopia
@YeneTube @FikerAssefa
የህዳሴ ግድብ ውሀ ሙሌት ተራዝሟል ተብሎ የሚፃፈው እና የሚነገረው ስህተት እንደሆነ የውሀ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢ/ር ስለሺ በቀለ ዛሬ አሳውቀውኛል!
"ትክክል አይደለም! በሁለት ሳምንት ግዜ ውስጥ ስምምነት ላይ እንድንደርስ፣ እስከዛውም ለውሀ ሙሌት ዝግጅት እንድናደርግ ነው ያለን አካሄድ" ብለውኛል።
Via Elias Meseret
@YeneTube @FikerAssefa
"ትክክል አይደለም! በሁለት ሳምንት ግዜ ውስጥ ስምምነት ላይ እንድንደርስ፣ እስከዛውም ለውሀ ሙሌት ዝግጅት እንድናደርግ ነው ያለን አካሄድ" ብለውኛል።
Via Elias Meseret
@YeneTube @FikerAssefa
ከጀሞ 2 እስከ ጀነራል ዊንጌት የሚገነባው የፈጣን ከተማ አውቶብስ መንገድ ግንባታ ተጀመረ!
የመንገዱን ግንባታ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድና ኢ/ር ታከለ ኡማ አስጀምረውታል።መንገዱ በአጠቃላይ 20 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ሲሆን ወደ ሁለት አቅጣጫ የሚዘረጋ ነው ተብሏል።የፈጣን አውቶብስ መንገዱ አዲስ ከተማ፣ልደታ፣ቂርቆስና ኮልፌ በመሳሰሉ ቦታዎች የአውቶብስ መቆሚያዎች ይኖሩታል መባሉን ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል።

በቦሌ ክ/ከተማ የመብራት ኃይል ሠራተኞች ነን በሚል ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል አስተላላፊ የሆነ ትራንስፎርመር በክሬን ጭነው ለማምለጥ ሲመክሩ በአካባቢው ነዋሪዎች ጥርጣሬ ለፖሊስ በተሰጠ ጥቆማ እሰከጫኑበት ክሬን እጅ ከፍንጅ ሊያዙ መቻላቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 10 ሐያት ቁ.1 በሚባል አካባቢ ሠኔ 19/2012 ዓ.ም ከቀኑ 9፤30 አካባቢ ለ80 አባወራዎች አገልግሎት እየሰጠ የሚገኘውን ትራንስፎርመር ከመስሪያ ቤቱ ዕውቅና ውጭ ኮድ3ኢ.ት84535 በሆነ ክሬን ተሸከርካሪ ታግዘው በመስረቅ ለማምለጥ ሲመክሩ በአካባቢው ነዋሪ ጥርጣሬ ለፖሊስ በተሰጠ ጥቆማ እጅ ከፍንጅ ሊያዙ መቻላቸውን በቦሌ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ የወንጀል መከላከልና የማህበረሰብ አቀፍ የፖሊስ አገልግሎት ም/ዳይሬክቶሬት የሆኑት ኮማንደር ያሲን ሁሴን ለአዲስ ፖሊስ ገልዋል፡፡ግለሰቦቹ በኃላፊያቸው ታዘው ትራንስፎርመር ለመቀየር መምጣታቸውን ቢናገሩም በኢትዮጲያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን የምስራቅ አዲስ አበባ ዲስትሪክት የኮንስትራክሽንና ሜንቴናንስ ኃላፊ አቶ ሱልጣን ሰርሞሎ ግለሰቦቹን መሥሪያ ቤቱ እንደማያውቃቸውና ከመሥሪያ ቤቱ የታዘዙ ቢሆኑ እንኳን የትዕዛዝ ደብዳቤ መያዝ እንደነበረባቸው ገልጸው ለማነኛውም ትዕዛዝ ሰጥቶናል እንድንሰራ ያሉትንም ሓላፊ ከፖሊስ ጋር በጋራ እንደሚያጣሩት በበኩላቸው አስረድተዋል ፖሊስ የምርመራ ሂደቱን ለመቀጠል ተጠርጣሪዎቹንና በእግዚቢትነት የተያዙ ንብረቶችን በቁጥጥር አውሎ ምርመራ መጀመሩን የገለጹት ኮማንደር ያሲን ሁሴን ገልጸዋል።
Via Addis Ababa Police Commission

ለ2013 በጀት አመት የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ትልቁን በጀት እደሚወስድ ይጠበቃል!
ለበጀት አመቱ ለባለስልጣኑ ይፀድቃል ተብሎ የሚጠበቀው የገንዘብ መጠን 50 ቢሊየን ብር ከመንግስት ካዝና እንዲሁም 9.6 ቢሊየን ብር ከውጭ ብድር እና እርዳታ ነው፡፡የመንገዶች ባለስልጣን የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ሳምሶን ወንድሙ ለካፒታ እንደገለፁት በበጀት አመቱ ተቋማቸው ለሚያከናውናቸው ስራዎች በጠቅላላው የ 59.6 ቢሊየን ብር መጀት ይመደብለታል ተብሎ ይጠበቃል ይህም ከ2012 በጀት አመት አንፃር የ29 በመቶ ብልጫ ያለው ነው፡፡
Via Capital

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የውኃ ሙሌትን በተመለከተ አል አህራም፣ አልጀዚራና ሮይተርስ እያሠራጩ ያለው ዘገባ ትክክል አለመሆኑን አስታውቋል፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ከአብመድ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደተናገሩት የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ የውኃ ሙሌት በተያዘለት ጊዜ ይከናወናል፡፡
‘‘የኢትዮጵያ መንግሥት አቋም ግልጽ ነው፤ ዓለማቀፍ ሕግጋትንም እናከብራለን’’ ያሉት አምባሳደር ዲና ግድቡን ለመገንባት የማንም ፈቃድ እንዳልተጠየቀው ሁሉ ለውኃ ሙሌቱም ፈቃድ እንደማያስፈልግና በተያዘለት የጊዜ ገደብ እንደሚካሄድ አስታውቀዋል፡፡
ዛሬ አል አህራም፣ ሮይተርስ እና አልጀዚራ የተሰኙ የመገናኛ ብዙኃን የውኃ ሙሌቱ ሦስቱ ሀገራት ስምምነት እስኪደርሱ እንደተራዘመ አስመስለው የዘገቡት ዘገባ የተሳሳተና የጋራ አቋም ያልተያዘበት እንደሆነም ተናግረዋል፡፡ግብጽ ‘‘የአፍሪካን ችግር በአፍሪካ መፍታት’’ የሚለውን መርህ ተቀብላ በድጋሜ ወደ ድርድሩ መመለሷ መልካም መሆኑን የጠቀሱት አምባሳደር ዲና በድርደሩ ይነሱ የነበሩ የቴክኒክና የሕግ ጉዳዮችን በአፍሪካ ኅብረት አደራዳሪነት በቀጣይ ሁለት ሳምንታት ተነጋግሮ መልክ ለማስያዝ መግባባት ላይ መደረሱን አስታውቀዋል፡፡ ‘‘የውኃ ሙሌቱን ግን በተያዘለት መርሀ ግብር መሠረት ይቀጥላል’’ ነው ያሉት፡፡
ምንጭ: አብመድ

‘‘የውኃ ሙሌቱ ማንም የሚያስቆመው አይደለም’’-
ስለሺ በቀለ (ዶክተር ኢንጂነር)
የውኃ መስኖና ኢነርጅ ሚኒስትሩ ስለሺ (ዶክተር ኢንጂነር) የአፍሪካን ችግር በአፍሪካ ለመፍታት ከኅብረቱ ጋር በመሆን ውይይት መጀመሩ መልካም መሆኑን በመጥቀስ በቀጣይ ሁለት ሳምንታት እልባት ለመስጠት አቅጣጫ መቀመጡን ገልጸዋል፡፡
ግብጽ ጉዳዩን ወደተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት መውሰዷን ተከትሎ ምክር ቤቱ ሰኞ እንደሚወያይበት መርሀ ግብር መያዙን በተመለከተ ለተነሳላቸው ጥያቄም ‘‘የፀጥታው ምክር ቤት ጉዳዩ ወደ አፍሪካ ኅብረት መመለሱን እንዲያውቀው መደረጉን ተከትሎ ምን እንደሚወስን ወደፊት የምናዬው ይሆናል’’ ብለዋል፡፡ ቀጣይ ውይይቶች በፖለቲካ መሪዎች ሳይሆን በቴክኒክ ባለሙያዎች እንደሚቀጥሉ መግባባት ላይ መደረሱንም አስታውቀዋል፡፡
በኢትዮጵያ ጥያቄ መሠረት የሦስትዮሽ ውይይቱን ደቡብ አፍሪካ እንድትታዘብ መመረቷንና የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤና የአውሮፓ ኅብረትም እንደሚታዘቡት ሚኒስትሩ አስታውቀዋል፡፡ ውሳኔው የሦስቱ ሀገራት የጋራ ስምምነት ብቻ እንደሚሆንም ተናግረዋል፡፡የግድቡን የውኃ ሙሌት በተመለከተ ግን በኢትዮጵያ በኩል ተለዋጭ ሐሳብ እንደሌለና በተያዘው መርሀ ግብር መሠረት እንደሚቀጥል ነው ዶክተር ኢንጂነር ስለሽ ያስታወቁት፡፡ ‘‘የውኃ ሙሌቱ ማንም የሚያስቆመው አይደለም’’ ብለዋል፡፡
Via AMMA

የወላይታ ማህበረሰብ ቴሌቪዥን ስርጭት ለመጀመር ከኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን ህጋዊ የብሮድካስት አገልግሎት ፈቃድ ማግኘቱን የዞኑ አስተዳደር ጽ/ቤት አስታውቋል።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
በቦሌ ለሚ ኢንደስትሪ መንደርና አካባቢው በተፈፀመ የከፍተኛ ኃይል ተሸካሚ ምሰሶ ስርቆት ለቀናት ምክንያት ተቋርጦ የነበረው የኤሌክተሪክ ሃይል ከዛሬ አመሻሽ ጀምሮ ወደ ስራ እንደሚገባ የኢትዮጵያ መብራት ሃይል አስታወቀ፡፡
የኢትዮጵያ መብራት ሃይል የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ሞገስ መኮንን ለካፒታል ጋዜጣ እንደገለፁት የተቋሙ የትራንስሚሽንና ሰብስቴሽን ኦፕሬሽን የጥገና ባለሙያዎች ችግሩን እስከ ዛሬ 10 ሰዓት ድረስ እንደሚፈቱት ይጠበቃ በመሆኑም የተፈጠረው ችግር በግዛዊ ምሰሶ አማካኝነት ተጠግኖ ወደ ስራ ይገባል ተብሎ ይጠበቃል ብለዋል፡፡መሰል ዝርፊያ በገጠራማ የአገሪቱ አካባባ አልፎ አልፎ ይከሰታል ያሉት አቶ ሞገስ በአዲስ አበባ ሲከሰት ለመጀመሪያ ግዜ ነው፡፡በስርቆቱ የኢንደስትሪ መንደሩን ጨምሮ በሰሚት ኮንዶሚኒየም፣ በቦሌ አራብሳ፣ በአየር መንገድ ማህበር፣ በጎሮ፣ በአይሲቲ ፓርክ፣ በገርጂ ወረገኑና በገርጂ ካሳንቺስ አካባቢዎች ከእሮብ አነስቶ ኃይል ተቋርጦ ቆይቷል።

YeneTube
በቦሌ ለሚ ኢንደስትሪ መንደርና አካባቢው በተፈፀመ የከፍተኛ ኃይል ተሸካሚ ምሰሶ ስርቆት ለቀናት ምክንያት ተቋርጦ የነበረው የኤሌክተሪክ ሃይል ከዛሬ አመሻሽ ጀምሮ ወደ ስራ እንደሚገባ የኢትዮጵያ መብራት ሃይል አስታወቀ፡፡ የኢትዮጵያ መብራት ሃይል የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ሞገስ መኮንን ለካፒታል ጋዜጣ እንደገለፁት የተቋሙ የትራንስሚሽንና ሰብስቴሽን ኦፕሬሽን የጥገና ባለሙያዎች ችግሩን እስከ ዛሬ 10…
በተያያዘም የኤሌክትሪክ ኃይል አስተላላፊ የሆነው ማማ የወደቀው የቆመበት ቅስት ብረቶች ባልታወቁ ሰዎች በመሰረቃቸው ጉልበት አጥቶ በነፋስ ኃይል መሆኑን አረጋግጫለው፣ አሁን ላይ ጥበቃ እያደረኩለት ነው ብሏል የቦሌ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ፡፡
የመምሪያው የወንጀል መከላከልና የማህበር አቀፍ የፖሊስ አገልግሎት ም/ዳይሬክቶሬት የሆኑት ኮማንደር ያሲን ሁሴን ወንጀል ፈጻሚዎቹን በቁጥጥር ሥር ለማዋል ፖሊስ ብርቱ ክትትል እያደረገ ነው ብለዋል፡፡
ምንጭ: የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ ኮምሽን
@YeneTube @FikerAssefa
የመምሪያው የወንጀል መከላከልና የማህበር አቀፍ የፖሊስ አገልግሎት ም/ዳይሬክቶሬት የሆኑት ኮማንደር ያሲን ሁሴን ወንጀል ፈጻሚዎቹን በቁጥጥር ሥር ለማዋል ፖሊስ ብርቱ ክትትል እያደረገ ነው ብለዋል፡፡
ምንጭ: የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ ኮምሽን
@YeneTube @FikerAssefa
የኮሮና ቫይረስ በሽታን ለመከላከል፣ ለመቆጣጠር የሚያስችል ከ700 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የህክምና ግብዓቶች መሰብሰብ መቻሉን የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታውቋል።
በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ በሽታን ለመቆጣጠር መጠነ ሰፊ ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙ ኢንስቲትዩቱ አስታውቋል።እስከ ዛሬ ሰኔ 20/2012 ዓ.ም ድረስም ግዢ የተፈፀመባቸውን እና በመጓጓዝ ሂደት ላይ ያሉትን ሳይጨምር ለሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ግምታቸው ከ700 ሚሊዮን ብር በላይ የሆኑ የህክምና ግብዓቶች ማሰባሰብ እና ማሰራጨት መቻሉን ገልጿል፡፡ከዚህም ውስጥ 60 በመቶ የሚሆነው በመንግስት ሲሸፈን ቀሪው 40 በመቶ በተለያዩ አጋር አካላት የተሸፈነ ነው ተብሏል።
በሀገር አቀፍ ደረጃ እስካሁን ከተሰባሰቡት ግብዓቶች መካከል ከ513 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ወጪ ያላቸው የህክምና ግብዓቶች ወደ ክልል እና የተለያዩ ማዕከላት መሠራጨታቸውን የገለጸው ኢንስቲትዩቱ ከዚህም የግል ደኅንነት መከላከያ ከፍተኛውን ድርሻ ይይዛል ብሏል።ከዚህም በተጨማሪ ከ13 ሚሊዮን ሊትር በላይ ኦክስጅን ማቅረብ የሚያስችሉ 3 ሺህ 600 የኦክስጅን ሲሊንደሮችን እና 1 ሺህ 100 በህሙማን ደም ውስጥ ያለውን የኦክስጅን መጠን ለመለካት የሚያስችሉ መሳሪያዎች ለክልሎች እና ለሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች የህክምና ማዕከላት ተሰራጭቷል።
#EPHI

አንዳርጋቸው ፅጌ የኢሳት ዋና ስራ አስኪያጅ ሆኑ!
የቀድሞው የግንቦት ሰባት ከፍተኛ አመራር የነበሩት አንዳርጋቸው ፅጌ የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን (ኢሳት) ዋና ስራ አስኪያጅ በመሆን ስራ ጀምረዋል።
የአዲስ ማለዳ ምንጮቹን ጠቅሶ እንደዘገበው ጣቢያው ከመጪው ሐምሌ 1/2012 ጀምሮ በአዳዲስ የአሰራር ስርዓት እና አዳዲስ ዝግጅቶች ወደ ህዝብ እንደሚቀርብ እና ጣቢያውንም የህዝብ ሚዲያ ለማድረግ ዝግጅት መጨረሱ ታውቋል።ኢሳት በአዳዲስ ዝግጅቶች እና አቀራረቦች ለሕዝብ ለመድረስም ተጨማሪ እና ብቃት ባላቸው የሰው ኃይል ለመደራጀት ሰዎችን መቅጠሩንም ምንጮች ለአዲስ ማለዳ ጨምረው አስታውቀዋል። ጣቢያው ከዓመታት በፊት በተደጋጋሚ በትግል ላይ የነበረውን የግንቦት ሰባትን እንቅስቃሴ እና የበረሀ ውሎ በመዘገብ ለሕዝብ ሲያደርስ መቆየቱ የሚታወስ ነው።
Via Addis Maleda

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 145 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተይዘዋል፣ የአምስት ሰዎች ህይወትም አልፏል።
ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 5552 የላቦራቶሪ ምርመራ 145 ሰዎች የኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸውና የ5 ሰዎች ህይወት ማለፉን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ።በአጠቃላይ በአገሪቱ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 5570 ደርሷል።
ተጨማሪ የ5 ሰዎች ህይወት ማለፉን ተከትሎ ፣ ባጠቃላይ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 94 ደርሷል፡፡
ህይወታቸው ያለፈ 5 ሰዎች ሁኔታ:
1.በህክምና ማዕከል የነበሩ የ64 አመት የአዲስ አበባ ነዋሪ (ወንድ)
2.በጤና ተቋም የነበሩ የ90 አመት የአዲስ አበባ ነዋሪ(ሴት)
3.በህክምና ላይ የነበሩ የ65 አመት የአዲስ አበባ ነዋሪ (ወንድ)
4.በህክምና ማዕከል የነበሩ የ65 አመት የአዲስ አበባ ነዋሪ (ወንድ)
5.በአስከሬን ምርመራ የተገኘባት የ40 አመት የአዲስ አበባ ነዋሪ

በትናንትናው ዕለት 327 ሰዎች ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን፤ይህም ከበሽታው ያገገሙ ሰዎችን ብዛት 2015 አድርሶታል፡፡
👉ያገገሙት 327 ሰዎች:
(317 ከአዲስ አበባ፣ 1 ከትግራይ ክልል፣1 ከኦሮሚያ ክልል እና 8 ከአማራ ክልል) ሲሆኑ በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 2015 ነው።
ቫይረሱ የተገኘባቸው 145 ሰዎች ሲሆኑ ሁሉም ኢትዮጵያውያን ናቸው። በፆታ ሲታይ ደግሞ ወንድ(86) ሴት(59) ናቸው!
👉ዕድሜያቸው ከ2 ወር-90 አመት የሆኑ
👉የተገኘባቸው:-
• 94 ሰዎች ከአዲስ አበባ፣
• 10 ሰዎች ከሶማሌ ክልል፣
• 10 ሰዎች ከአማራ ክልል፣
• 6 ሰዎች ከድሬዳዋ ከተማ፣
• 22 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል እና
• 3 ሰዎች ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ናቸው ተብሏል።
👉በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 5570 ደርሷል።
👉በጠና የታመሙት ቁጥር ደግሞ 34 ነው።
👉በ24 ሰዓት ውስጥ 5 ሞት የተመዘገበ ሲሆን፣ እስካሁን በቫይረሱ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 94 ነው።

ኢትዮጵያ ለእዳ ክፍያ 37 ቢሊየን ብር በጀት መድባለች!
ከሳምንት በኋላ ይፀድቃል ተብሎ ከሚጠበቀው 476 ቢሊየን ብር በጀት ውስጥ ለእዳ ክፍያ 37 ቢሊየን ብር መመደቡን ካፒታል ጋዜጣ አረጋግጫለው ብሏል። መጠኑ ከቀዳሚው አመት በ12 ቢሊየን ብር ብልጫ እንዳለው የገንዘብ ሚኒስትር ደኤታው እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) በቅርቡ ለገቢ፣ በጀት እና ፋይናንስ ቋሚ ኮሚቴ ገልፀዋል፡፡ላለፉት ጥቂት አመታት የአገሪቱ የውጭ እዳ በከፍተኛ ሁኔታ ከመቆለሉ ጋር ተያይዞ ኢትዮጵያ የከፍተኛ ስጋት ውስጥ ገብታ የነበር የሚታወስ ነው፡፡ በቅርቡ በፓርላማ የተገኙት ጠ/ሚ አብይ አህመድ (ዶ/ር) የስጋት ደረጃው ወደ መካከለኛ ደርጃ መውረዱን መግለፃቸው ይታወሳል፡፡
Via @CapitalEthiopia

በአዲስ አበባ ከተማ በ24 ሰዓት ውስጥ 317 ሰዎች ከኮሮናቫይረስ ሕመም አገገሙ!
ባለፉት 24 ሰዓታት በአዲስ አበባ ከተማ 94 ሰዎች የኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው የከተማ ጤና ቢሮ አስታውቋል።በአዲስ አበባ ከተማ የኮሮናቫይረስ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥርም 3636 ደርሷል።በትላንትናው ዕለት 317 ሰዎች ከአዲስ አበባ ከኮሮናቫይረስ ሕመም ማገገማቸው ተገልጿል።ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በአዲስ አበባ ከኮሮናቫይረስ ጋር በተገናኘ የአምስት ኢትዮጵያውያን ሕይወት ማለፉም ታውቋል።
አዲስ አበባ ከተማ ባለፉት 24 ሰዓታት ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች በክፍለ ከተማ፤-
👉አዲስ ከተማ 13
👉ቦሌ 2
👉ጉለሌ 6
👉ልደታ 12
👉ኮልፌ ቀራንዮ 12
👉ቂርቆስ 6
👉አራዳ 5
👉የካ 11
👉ንፋስ ስልክ ላፍቶ 11
👉አቃቂ ቃሊቲ 7
👉አድራሻቸው በመጣራት ላይ ያለ 6

የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የወጣውን አዋጅ በመተላለፍ በተከራይ ላይ የቤት ክራይ የጨመረው ግለሰብ ተቀጣ።
በፍርድ ቤት የጥፋተኝነት ውሳኔ የተላለፈበት ግለሰብ በአርሲ ዞን፣ሙኔሳ ወረዳ ቀርሳ ከተማ ውስጥ በ500 ብር አከራይቶት የነበረውን ግለሰብ በፊት ከሚከፍለው 500 ላይ ሌላ 500 ብር በመጨመር 1000 ብር እንዲከፍል አሊያም ከቤቱ እንዲወጣ በመጠየቁና የኮሮናቫይረስን ለመከላከል የወጣውን አዋጅ ተላልፎ በመገኘቱ የወረዳው ፖሊስ ጉዳዩን በማስረጃ በማስደገፍ የምርመራ መዝገቡን ለፍርድ ቤት ማቅረቡ ተገልጿል፡፡የአርሲ ዞን ሙኔሳ ወረዳ ፍ/ቤትም የቤት አከራዩ ጥፋተኛ ሆኖ በማገኘቱ በ 10 ሺ ብር እንዲቀጣ የወሰነበት መሆኑን የአርሲ ዞን ፖሊስ ኮሙኒኬሽንን ጠቅሶ ሸገር ታይምስ ዘግቧል።