የአዲስ አበባ ፖሊስ በህገወጥ መንገድ ወደ ስጋ ቤቶች የገቡ እርዶችን ዛሬ ማለዳ ጀምሮ በማሰስ ላይ ይገኛል።
ዛሬ ማለዳ ጀምሮ በከተማዋ ያሉ ስጋ ቤቶች ከቄራ ድርጅት ውጪ እርድ እየተፈጸመ ለህብረተሰቡ እየተሸጡ ነው የሚል ጥቆማ የደረሰው የአዲስ አበባ ፖሊስ ስጋ ቤቶችን በመፈተሽ ላይ ይገኛል።እስካሁን በተደረገው አሰሳም ከፍተኛ መጠን ያለው ጤንነቱ ያልተረጋገጠ ስጋ ተገኝቷል።ስጋ ቤቶች አንድ በሬ በቄራዎች ድርጅት እርድ ካከናወኑ በኋላ በዚህ ሽፋን ተጨማሪ በሬዎችን ከቄራዎች ድርጅት እንደታረዱ በማስመሰል ህገወጥ ስጋ ለህብረተሰቡ ሊሸጡ በዝግጅት ላይ እያሉ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልጿል።ይህ የተያዘው ህገወጥ ስጋም ከስጋቤቶቹ እንዲነሳ መደረጉን ኢትዮ ኤፍ ኤም በአካል ሄጄ አረጋግጫለው ብሏል።የእንስሳት እርዶችን ከቄራዎች ድርጅት የፈጸሙ እና ለዚህም ማስረጃ ማቅረብ የቻሉ ግን ስራቸውን ቀጥለዋል።
Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ የኦሮሚያ ክልል የዜግነት አገልግሎት በይፋ አስጀመሩ!
ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አህመድ በኦሮሚያ ክልል የዜግነት አገልግሎትን ዛሬ በወሊሶ በይፋ አስጀምረዋል። አገልግሎቱ የወሊሶ ሊበን የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤትን በማደስ ተጀምሯል።አገልግሎቱ ዘርፈ ብዙ መልክ ያለው ሲሆን፡የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እንዳካተተበትም ተመልክቷል።
Via ENA/AMN

በኮሮናቫይረስ ከተያዙት 7.6 ሚሊዮን ሰዎች ውስጥ ወደ ግማሽ የሚጠጉት አገግመዋል!
በርካታ ሊቃውንት በዓለም ዙሪያ በሚገኙ ቤተ ሙከራዎች ውስጥ ለዚህ በሽታ መከላከያ ክትባት እንዲሁም መፈወሻ መድኃኒት ለማግኘት ሌት ተቀን እየጣሩ ቢሆንም እስካሁን የተረጋገጠ ውጤት አልተገኘም።በየዕለቱ በሺህና በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ቫይረሱ እየተገኘባቸው ነው። በርካቶችም በወረርሽኙ ሰበብ ህይወታቸውን እያጡ ነው። ምንም እንኳን ለወረርሸኙ ፈዋሽ መድኃኒት ባይገኝም ባለሙያዎች እንደሚሉት በሽታው የያዘውን ሁሉንም ሰው ለሞት አይዳርግም።በዚህም ምክንያት በርካቶች ከወረርሽኙ እያገገሙ መሆናቸውን ኢትዮጵያን ጨምሮ ከየአገራቱ የሚወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ።
Via BBC

በተከታታይ አምስት ቀናት ውስጥ ከ38.9 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የኮንትሮባንድ ዕቃዎች በቁጥጥር ስር እንዲውልመደረጉን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
በጉምሩክ መቆጣጠሪያ ጣቢያዎችና ኬላዎች ላይ በተደረገው ክትትልና ፍተሻ ልዩ ልዩ ተሸከርካሪ፣ ጎማዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ አልባሳት፣ ምግብና የምግብ ነክ ቁሳቁሶች ፤የንግድ ማጭበርበር እና የተለያዩ ዓይነት የጦር መሳሪያዎችና እንዲሁም ጥይቶች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ነው የተገለጸው፡፡
Via AMN

አዲስ አድማስ ጋዜጣ በግንቦት 29/2012 እትሙ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጥናት ነው በሚል ያወጣውና በኢትዮጵያ እስከ ህዳር 2013 ድረስ 8.5 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሊያዙ ይችላሉ፤ ከ26000 በላይ ሰዎች ደግሞ በበሽታው እንደሚሞቱ የዘገበው ዜና ኢንስቲትዩቱን የማይመለከት እና የተሳሳተ መረጃ መሆኑን ሕብረተሰቡ እንዲገነዘብልኝ ብሏል ኢንስቲቲዩቱ፡፡
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
በደቡብ ክልል 3ኛው የኮሮና ቫይረስ መመርመሪያ ማዕከል በጋሞ ዞን አርባምንጭ ዩንቨርስቲ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታውቋል።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
የጤና ሚኒስቴር የጤና አገልግሎቶችን ተደራሽ ለማድረግና የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል የሚያግዙ አምቡላንሶችን ለሁሉም ክልሎች እና ለሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች በ3 ዙር ያከፋፈለ ሲሆን የአምቡላሶቹም ግዢ የተፈጸመው ክልል ጤና ቢሮዎች 50% እና ጤና ሚኒስቴር 50% የገንዘብ መዋጮ (Matching-Fund) በተጨማሪም ጤና ሚኒስቴር ፍትሃዊ ስርጭትን ለማረጋገጥ በሚያስችል መልኩ የፌዴሬሽን ቀመርና የአለም ጤና ድርጅት ስታንዳርድን ታሳቢ አድርጎ ግዢ በመፈጸም ለክልሎች እና የከተማ አስተዳደሮች ያስተላለፈው ነው፡፡ የየክልሎቹ እና የከተማ አስተዳደሮች የአምቡላንስ ስርጭት በሚከተለው መልኩ ከላይ በዝርዝር ቀርቧል፡፡
Via MoHE
@YeneTube @FikerAssefa
Via MoHE
@YeneTube @FikerAssefa
በባሌ ዞን ዲንሾ ከተማ የተቃውሞ ሰልፍ ተደረገ። ተቃዋሚዎቹ መንገዶችን የዘጉ ሲሆን፣ ፖሊስ አስለቃሽ ጭስ ተኩሷል። ባሳለፍነው ሰኞ ሳዲቅ ሃጂ ኢብሮን የተባሉ የጭነት መኪና አሽከርካሪ በአካባቢው መገደላቸውን ተከትሎ ቅሬታ ተፈጥሯል።
Via Ethiopia Live Updates
@YeneTube @FikerAssefa
Via Ethiopia Live Updates
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የቀድሞ የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) ንብረት እንዲያጣሩ ሁለት ኦዲተሮችን ሾመ፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በአዋጅ ቁጥር 1162/2011 መሰረት ጥር 20 ቀን 2012 ዓ.ም ኢሕአዴግ እንዲፈርስ እንዲሁም የቀድሞ ሶስቱ የግንባሩ አባላት ወራሽ የሆነው ብልጽግና ፓርቲ እና በህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሐት) በስድስት ወር ውስጥ የንብረት ክፍፍል ተጠናቆ እንዲያቀርቡ ክፍፍሉም የሶስት ፓርቲዎች ወራሽ የሆነው ብልፅግና የሃብቱን ሶስት አራተኛ (3/4) በራሱ ህጋዊ እውቅና ያለው ህወሃት አንድ አራተኛ ( ¼) እንዲወስዱ መወሰኑ ይታወሳል፡፡ በውሳኔውም ፓርቲዎቹ የጋራ ንብረት አጣሪ ሾመው የባለመብቶችን (creditors) መብት እንዲጠበቅ እንዲሁም በተገለጸው ቀመር መሰረትም የንብረት ክፍፍሉ እንዲፈጸም ወስኖ አሳውቆ ነበር፡፡
በሌላ በኩል የብልጽግና ፓርቲ የንብረት ክፍፍሉ እያንዳንዱ ፓርቲ በተናጠል በነበረው የአባላት ብዛት ላይ የተመሰረተ እንጂ በእኩልነት ሊሆን አይገባም የሚል አቤቱታ ያቀረበ ሲሆን ቦርዱ የሃብት ክፍፍሉን የወሰነው የፓርቲው ህገደንብ “ሁሉም ፓርቲዎች በግንባሩ የጋራ ንብረት እኩል የመጠቀም መብት አላቸው” ሲል ያስቀመጠውን መሰረት በማድረግ መሆኑን ገልጾ ሆኖም ግን ብልጽግና ከዚህ የተለየ ውጤት ሊያስከትል የሚችል ማስረጃ ወይም ሰነድ ካለው ለአጣሪው ማቅረብ እንደሚችል ተገልጾለታል፡፡
የመፍረስ ውሳኔው ከተሰጠበት ጊዜ ጀምሮ ሁለቱም ወገኖች የሚስማሙበት አንድ የጋራ አጣሪ እንዲመርጡ ለማስቻል የተደረገው ጥረት አልተሳካም፡፡ ስለሆነም ቦርዱ ብልጽግና ፓርቲ እና ህወሃት በየበኩላቸው የመረጧቸው አንድ አንድ የሂሳብ አጣሪዎች በጋራ በመሆን የንብረት ማጣራት ስራውን እንዲያከናውኑ ውሳኔ አሳልፏል፡፡በዚህም ውሳኔ መሰረት የንብረት ማጣራቱን እንዲያደርጉ የተመረጡት ድርጅቶች የጋራ የስራ እቅድ፣ የጊዜ ሰሌዳ፣ ስራውን የሚያከናውኑበት ቦታ፣ ሁኔታ እና የስራ ህግጋት ለቦርዱ እንዲያቀርቡም በደብዳቤ ተገልጾላቸዋል፡፡ የንብረት ማጣራቱ ሂደት ሙሉ ወጪ በፓርቲዎቹ የሚሸፈን ሲሆን ቦርዱ ሂደቱ የሚደርስበትን ደረጃ በየጊዜው ለህዝብ የሚያሳውቅ ይሆናል፡፡
-የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

'የትግራይ ነፃነት ፓርቲ' የተባለው አዲስ የተመሰረተ የፖለቲካ ድርጅት ዛሬ በመቐለ መስራች ጉባኤው እያካሄደ ነው፡፡ "ያለ ነፃና ሉአላዊት ሃገረ ትግራይ፣ ብሔራዊ ክብርና ጥቅም ማረጋገጥ አይቻልም" ይላል የፓርቲው መስራች ጉባኤ መሪ ሐሳብ፡፡
Via Million HaileSelasie
@YeneTube @FikerAssefa
Via Million HaileSelasie
@YeneTube @FikerAssefa
በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ከደብረ ብርሃን ደነባ-ለሚ መገንጠያ እና ጅሁር -ደነባ የአስፓልት መንገድ ግንባታ በዛሬው ዕለት ጀመረ።
የመንገድ ግንባታው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን፣የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ፣ የትራንስፖርት ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ እና ሌሎች የፌዴራልና የአማራ ክልል መንግሥት የሥራ ኃፊዎች በተገኘቡበት ተጀምሯል።108 ኪሎ ሜትር የሚረዝመው ከደብረ ብርሃን ደነባ-ለሚ መገንጠያ እና ጅሁር -ደነባ የአስፓልት መንገድ በአራት ዓመታት ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል። ለግንባታው 3 ቢሊየን 613 ሚሊዮን 767 ሺህ ብር ወጪ የሚደረግበት ሲሆን ግንባታው ሲጠናቀቅ ለ5 ወረዳ ህዝብ አገልግሎት እንደሚሰጥ ነው ከዞኑ ከሙኑኬሽ ጉዳዮች ፅህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
#FBC

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 268 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው።
ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 5644 የላብራቶሪ ምርመራ ሁለት መቶ ስልሳ ስምንት (268) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 3,166 ደርሷል።
@YeneTube @FikerAssefa
ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 5644 የላብራቶሪ ምርመራ ሁለት መቶ ስልሳ ስምንት (268) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 3,166 ደርሷል።
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ ተጨማሪ የ8 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን ፣ ባጠቃላይ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 55 ደርሷል፡፡
ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ ህይወታቸው ያለፈ 8 ሰዎች ሁኔታ
1.በህክምና ላይ የነበሩ የ65 አመት የአዲስ አበባ ነዋሪ (ወንድ)
2.በህክምና ላይ የነበረች የ34 አመት የአዲስ አበባ ነዋሪ
3.በህክምና ላይ የነበረ የ45 አመት የአዲስ አበባ ነዋሪ
4.በህክምና ላይ የነበረች የ40 አመት የአዲስ አበባ ነዋሪ
5.በአስክሬን ምርመራ ቫይረሱ የተገኘበት የ50 አመት የአዲስ አበባ ነዋሪ
6.በአስክሬን ምርመራ ቫይረሱ የተገኘባቸው የ90 አመት የአዲስ አበባ ነዋሪ(ወንድ)
7.በአስክሬን ምርመራ ቫይረሱ የተገኘባት የ45 አመት የአዲስ አበባ ነዋሪ
8.በአስክሬን ምርመራ ቫይረሱ የተገኘበት የአዲስ አበባ ነዋሪ

ዛሬ ቫይረሱ የተገኘባቸው 268 ሰዎች ሲሆኑ በዜግነት 267 ኢትዮጵያውያን፣ አንዱ የውጭ ሀገር ዜጋ ነው። በፆታ ሲታይ ደግሞ ወንድ(177) ሴት(91) ናቸው!
➡️ዕድሜያቸው ከ1-90 አመት የሆኑ
➡️ተጨማሪ 44 ሰዎች ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 495 ነው።
➡️የተገኙት ከአዲስ አበባ(232)፣ ከኦሮሚያ ክልል(12)፣ከአማራ ክልል(8)፣ ከደቡብ ክልል(2)፣ ከሀረሪ ክልል(5) ፣ ከትግራይ ክልል(6)፣ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል(1) እና ከአፋር ክልል(2) በድምር 268 ሰዎች ናቸው።
➡️በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 3166 ደርሷል።
➡️በጠና የታመሙት ቁጥር ደግሞ 39 ነው።
➡️በ24 ሰዓት ውስጥ 8 ሞት የተመዘገበ ሲሆን፣ እስካሁን በቫይረሱ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 55 ነው።

በአማራ ክልል በ2012 ዓ.ም የልጅነት ጋብቻን ለማጥፋት የታቀደው አመለሳካቱን የክልሉ ሴቶች፣ ሕጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ አስታውቋል፡፡
የአማራ ክልል ሴቶች፣ ሕጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ሰላማዊት ዓለማየሁ እንዳስታወቁት የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከተከሰተ ወዲህ በክልሉ ደቡብ ጎንደር ዞን ከሌሎች ዞኖች በተለዬ በርካታ ያለዕድሜ ጋብቻዎች ተፈጽመዋል፡፡ ከዚህን በፊት ትምህርት ቤቶች ያለዕድሜ ጋብቻዎች እንዳይፈጸሙ ጥሩ የጥቆማ ምንጮች እንደነበሩ ጠቁመዋል፤ ትምህርት ቤቶች መዘጋታቸው ጥቆማውን እንደቀነሰው ምክትል ኃላፊዋ ተናግረዋል፡፡
“የትምህርት ቤቶች ጥቆማ ሲቋረጥ ቢሮ በሚያሰማራቸው በጎ ፈቃደኞች አማካኝነት ጥቆማ እንዲመጣና የግንዛቤ ፈጠራ እንዲሠሩ እያደረግን ነው” ብለዋል ወይዘሮ ሰላማዊት፡፡ የግንዛቤ ፈጠራውን ከፍ ለማድረግ የብዙኃን መገናኛዎችን እየተጠቀሙ እንደሆነና ቀጣይም በስፋት እንደሚጠቀሙ ነው የተናገሩት፡፡
“የሚደርሰው የጋብቻ ጥቆማ ሁሉ ያለዕድሜ ጋብቻ አይደለም” ብለዋል ምክትል ቢሮ ኃላፊዋ፤ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከተከሰተ ወዲህ 1 ሺህ 193 የጋብቻ ጥቆማ ደርሶ 562 የልጅነት ጋብቻ በመሆናቸው እንዲቋረጡ መደረጋቸውን አስታውቀዋል፡፡ “ከእነዚህም መካከል 259 ጋብቻዎች ተፈጽመዋል፡፡ ይህም የሆነው ሳይደረሰባቸው የቀሩና በተለያዩ ስልቶች ጋብቻ የመፈጸም ሂደት ስላጋጣመ ነው” ብለዋል፡፡ ጋብቻ ከተፈጸመባቸው መካከል 114 ላይ ርምጃ እንደተወሰደም አብራርተዋል፡፡ ቀሪዎቹ ራሱ በማኅበረሰቡ እንዲቋረጡ እየተደረገ መሆኑንም አስታውዋል፡፡ ደቡብ ጎንደር፣ ምሥራቅ ጎጃምና ሰሜን ወሎ በቅደም ተከተል በብዛት የልጅነት ጋብቻ የተፈጸመባቸው ተብለው ተጠቅሰዋል፡፡
የምሥራቅ ጎጃም ዞን ሴቶች፣ ሕጻናትና ወጣቶች ጉዳይ መምሪያ የሴቶች ተሳትፎና ንቅናቄ ቡድን መሪ ዳግማዊ ገበየሁ በተለይም በፋሲካ ወቅት በርካታ ጋብቻዎች እንደሚፈጸሙ ጠቁመዋል፡፡ እንደ አቶ ዳግማዊ ማብራሪያ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከተከሰተ ወዲህ እንደ ዞን 3 ሺህ 259 ጋብቻዎች ተጠይቀዋል፤ ከእነዚህ 293 የሚሆኑት ያለዕድሜ ጋብቻ መሆናቸው ተረጋግጧል፤ 243 ሳይፈጸሙ በድርድር እንዲቋረጡ ተደርጓል፤ ቀሪ 50 የሚሆኑት ተፈጽመው ከመቋረጣቸውም በተጨማሪ ፈጻሚዎቹ ተቀጥተዋል፤ 2 ሺህ 686 ዕድሜያቸው የደረሰ ቢሆንም የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል ሲባል ድግስ እንዳይኖር ተደርጓል፡፡ ክልከላውን የተላለፉ 217 ሰርጎች ድግሱ በፍትሕ እንዲቋረጥ መደረጉም ታውቋል፡፡
በ2017 ዓ.ም በአማራ ክልል የልጅነት ጋብቻን ለማጥፋት የሚያስችል ፍኖተካርታ መዘጋጀቱን ምክትል ኃላፊዋ አስታውቀዋል፡፡ ፍኖተ ካርታው የልጅነት ጋብቻ እና የሴት ልጅ ግርዛትን ማስቀረት ያለመ እንደሆነ እና የሴት ልጅ ግርዛት በክልሉ እንደቀነሰም ጠቁመዋል፡፡
Via AMMA

በአዲስ አበባ በ 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ ሁለት መቶ ሰላሳ ሁለት (232) ሰዎች ቫይረሱ የተገኘባቸው ሲሆን በከተማው ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ሁለት ሺህ ሶስት መቶ ስድሳ ስምንት (2368) ደርሷል፡፡
ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ በ ሃያ አራት ሰዓታት ውስጥ በከተማው የስምንት (8) ኢትዮጵያውያን ህይወት አልፏል።
በሌላ በኩል ደግሞ በትላንትናው እለት ሃያ ስምንት (28) ሰዎች ከአዲስ አበባ ከኮሮና በሽታ አገግመዋል፡፡
በ24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች በክፍለ ከተማ፦
አዲስ ከተማ 39፤
ልደታ 18፤
ጉለሌ 8፤
ኮልፌ ቀራንዮ 17፤
ቦሌ 18፤
አራዳ 19፤
የካ 19፤
ንፋስ ስልክ ላፍቶ 16፤
አቃቂ ቃሊቲ 8፤
ቂርቆስ 24፤ የ46 ሰዎች ክፍለ ከተማ በመጣራት ላይ መሆኑን የከተማው ጤና ቢሮ አስታውቋል፡

YeneTube
ምርጫን የማስፈፀም ስልጣን የተሰጠው በህግመንግስቱ አንቀፅ 102 የተቋቋመው ምርጫ ቦርድ ስለሆነ ሌላ አካል በዚህ ጉዳይ ላይ ጣልቃ ልግባ ቢል ከስልጣን ገደቡ በላይ የምርጫ ቦርድን ስልጣን መጋፋት እና መዳፈር ስለሚሆን መንግስት የምርጫ ቦርድን ውሳኔ አክብሮ ይፈጽማል ሲሉ የጠቅላይ ሚንስትር ጽህፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ሃላፊው አስታወቁ። ሀላፊው አቶ ንጉሡ ጥላሁን ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት፤…
የትግራይ ክልል ኮ/ጉ/ቢሮ ለጠቅላይ ሚ/ር ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን ንግግር ምላሽ ሰጥቷል።
በምላሹም "በኢፌድሪ ህገ-መንግስት በየትኛዉም አንቀፅ ያልተፃፈን ጉዳይ አይኑን ጨፍኖ በማንበብ አባገነናዊ የቡድን ፍላጎቱን ለማርካት ሲባል፣ የህዝብን የመወሰን ስልጣን ለመደፍጠጥ የሚደረግ ሩጫ በትግራይ ህዝብና ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ምክርቤት ፈፅሞ ተቀባይነት እንደሌለዉ ወዳጅም ጠላትም ሊያዉቅ ይገባል" ብሏል።