YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.88K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
249 ኢትዮጵያዊያን ዜጎች ከኩዌት ወደ አገራቸው ተመለሱ!

249 ኢትዮጵያዊያን ዜጎች ከኩዌት ወደ አገራቸው ዛሬ ተመልሰዋል።እነዚህ ኢትዮጵያውያን ዜጎች ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተወካዮች ተገኝተው አቀባበል አድርገውላቸዋል።ዛሬ የመጡትን ጨምሮ እስካሁን በችግር ምክንያት በመጠለያ የነበሩ 748 ዜጎች ከኩዌት ወደ አገራቸው እንዲመለሱ መደረጉን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

#FBC
@YeneTube @FikerAssefa
በቀን እስከ 400 ናሙና ተቀብሎ የመመርመር አቅም ያለው የድሬደዋ ኮቪድ- 19 የላቦራቶሪ ምርመራ ማዕከል አግልግሎት መስጠት ጀመረ!

በቀን እስከ 400 ናሙና ተቀብሎ የመመርመር አቅም ያለው የድሬደዋ ኮቪድ- 19 የላቦራቶሪ ምርመራ ማዕከል የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጄ ዱጉማ እና የድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አህመድ ቡህ በተገኙበት በዛሬው ዕለትተመርቆ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

#ETV
@YeneTube @FikerAssefa
የሶማሊያው ታጣቂ ቡድን አል-ሸባብ ለኮሮና ሕሙማን የሕክምና ማዕከል ማቋቋሙን አስታወቀ።

ታጣቂ ቡድኑ አንዳሉስ በተባለው ራዲዮ ጣቢያው እንዳለው ማዕከሉ የተቋቋመው ከሞቃዲሾ 380 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ጂሊብ የተባለች ቦታ በአል-ሸባብ የኮሮና ተሕዋሲ መከላከያ እና ማከሚያ ኮሚቴ ነው።"ዓለም አቀፍ የጤና ድርጅቶች ኮቪድ-19 በአፍሪካ አገራት በአደገኛ ፍጥነት እየተስፋፋ ነው" ማለታቸውን አል-ሸባብ ጠቅሷል። በአንዳሉስ ራዲዮ በተላለፈው መግለጫ ራሳቸውን ሼይክ መሐመድ ባሊ ብለው የገለጹ ግለሰብ አል-ሸባብን ሲያመሰግኑ፤ የሕመሙ ምልክት ያለባቸውም ወደ ማዕከሉ እንዲሔዱ ጥቆማ ሲያቀርቡ ተሰምቷል።"አስተዳደሩ ማዕከሉን በማቋቋሙ እናመሰግናለን። ተሕዋሲው እንዳይዛመት ሰዎች ወደ ማዕከሉ ሔደው ሪፖርት እንዲያደርጉ እንጠይቃለን" ብለዋል። ሌላ ማንነታቸው ያልተገለጸ ሰው በዚያው ሥርጭት ማዕከሉ በኮሮና ተይዘው ሊሆን ይችላል ተብለው የሚጠረጠሩ ግለሰቦችን ለማጓጓዝ ተሽከርካሪዎች ማዘጋጀቱን ተናግረዋል።

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
የአዲስ አበባ ፖሊስ በህገወጥ መንገድ ወደ ስጋ ቤቶች የገቡ እርዶችን ዛሬ ማለዳ ጀምሮ በማሰስ ላይ ይገኛል። ዛሬ ማለዳ ጀምሮ በከተማዋ ያሉ ስጋ ቤቶች ከቄራ ድርጅት ውጪ እርድ እየተፈጸመ ለህብረተሰቡ እየተሸጡ ነው የሚል ጥቆማ የደረሰው የአዲስ አበባ ፖሊስ ስጋ ቤቶችን በመፈተሽ ላይ ይገኛል።እስካሁን በተደረገው አሰሳም ከፍተኛ መጠን ያለው ጤንነቱ ያልተረጋገጠ ስጋ ተገኝቷል።ስጋ ቤቶች አንድ በሬ በቄራዎች…
በአዲስ አበባ ሕገወጥ እርድ ያከናወኑ 132 ልኳንዳ ቤቶች ላይ እርምጃ መወሰዱ ተገለጸ!

በህገወጥ መንገድ የታረደ የ50 ከብት ስጋ እና ከ360 በላይ የበግ እና የፍየል ስጋ በቁጥጥር ስር መዋሉንና በ132 ልኳንዳ ቤቶች ላይ እርምጃ መወሰዱን የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ገልጿል፡፡የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ኮሚሽነር አዱኛ ደበላ ማምሻውን በሰጡት መግለጫ፣ የደንብ ማስከበር ዘርፍ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጋር በመተባበር በአስሩም ክፍለ ከተሞች ከሌሊቱ 10፡00 ሰዓት ጀምሮ በተደረገ ድንገተኛ የኦፕሬሽን ስራ ጨለማን ተገን አድርገው በህገወጥ መንገድ የበግ፣የፍየል እና የበሬ እርድ ሲያከናውኑ በተገኙ ልኳንዳ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወስዷል ብለዋል፡፡

በድንገተኛ የኦፕሬሽን ስራ በህገወጥ መንገድ ከአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ውጪ የታረዱ የ50 የከብት ስጋ እና 360 የበግ እና የፍየል ስጋ በቁጥጥር ስር መዋሉን ኮሚሽነር አዱኛ ተናግረዋል፡፡ለኮሮና ቫይረስን በይበልጥ በሚያስፋፋ እና ንጽህናው ያልጠበቀ እንዲሁም በሚመለከተው አካል ያልተመረመረ ስጋ ሲሸጡ በተገኙ 132 ልኳንዳ ቤቶች ላይ እርምጃ መወሰዱን ሃላፊው ገልጸዋል፡፡

የተወሰኑ ስጋ ቤቶች አንድ በሬ በቄራዎች ድርጅት እርድ ካከናወኑ በኋላ በዚህ ሽፋን ተጨማሪ በሬዎችን ከቄራዎች ድርጅት እንደታረዱ በማስመሰል ህገወጥ ስጋ ለህብረተሰቡ ሊሸጡ መገኘታቸውን ጠቁመዋል፡፡በዚህ ተግባር የተሳተፉ በርካታ ግለሰቦች እና የልኳንዳ ቤት ባለንብረቶች በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው እየተጣራ መሆኑን የገለጹት ኮሚሽነሩ፣ የህብረተሰቡን ጤና አደጋ ላይ የሚጥል ተግባር ከመፈጸማቸው በተጨማሪ መንግስት ማግኘት የነበረበትን ገቢ በማሳጣታቸው በህግ እንደሚጠየቁም አመልክተዋል፡፡በአዲስ አበባ ከተማ በተደረገ የዳሰሳ ጥናት 90 በመቶ የከብት እርድ ፣ከ20 እስከ 30 በመቶ የበግ እና የፍየል ከቄራዎች ውጪ በህገወጥ መንገድ በጫካ እና በወንዞች ዳርቻ እርድ እንደሚፈጸም መገለጹን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

Via ETV
@YeneTube @FikerAssefa
በታላቁ የኅዳሴ ግድብ ላይ በሚደረገው የሶስትዮሽ ድርድር ኢትዮጵያ "ግትር አቋም" ይዛለች ስትል ግብጽ ወነጀለች።

የግብጽ የውኃ ሐብት እና መስኖ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ መሐመድ አል-ሴባይ ዛሬ ባወጡት መግለጫ "እየተካሔደ በሚገኘው ድርድር ከአንዳች ስምምነት ይደረሳል የሚል ተስፋ የለኝም" ብለዋል። ቃል-አቀባዩ እየተካሔደ በሚገኘው የሶስቱ አገሮች የውኃ ሐብት ምኒስትሮች ድርድር "ግትር" ያሉት የኢትዮጵያ አቋም ታይቷል ብለዋል።ኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን ተቋርጦ የነበረውን ድርድር በኢንተርኔት አማካኝነት የጀመሩት ማክሰኞ ሰኔ 2 ቀን 2012 ዓ.ም. ነበር። ኢትዮጵያ በመጪው ሐምሌ ግድቡን ውኃ መሙላት ከመጀመሯ በፊት ሶስቱ አገሮች ከአንዳች ስምምነት ይደርሳሉ ተብሎ ቢጠበቅም የግብጽ የውኃ ሐብት እና መስኖ ሚኒቴር ቃል አቀባይ ልዩነቶች መካረራቸውን የሚጠቁም መግለጫ ሰጥተዋል።

"የኢትዮጵያ አቋም ግብጽ እና ሱዳን ለኢትዮጵያ ፍላጎት እና አምሮት ታጋች እንዲሆኑ የሚያደርግ ሰነድ እንዲፈርሙ አሊያም ታላቁ የኅዳሴ ግድብን በተናጠል ለመሙላት የደረሰችበትን ውሳኔ ተቀበሉ" የሚል ነው ሲሉ ወንጅለዋል።እንደ አዲስ የተጀመረውን ድርድር አሜሪካ፣ የአውሮፓ ኅብረት እና ደቡብ አፍሪካ በታዛቢነት ይሳተፉበታል። ሶስቱ አገሮች የታዛቢዎቹ ሚና ምን ይሁን በሚለው ጉዳይ ላይ እንዳልተስማሙ ኢትዮጵያ አስታውቃለች።

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from Delivery Hawassa
You Order, We Deliver ! #DeliveryHawassa

Ordering Methods :-

➡️Call to call center 09 52 62 62 62

➡️ Using our website www.deliveryhawassa.com
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ወደ ጅቡቲ አቀኑ!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የልዑካን ቡድናቸው በሶማሊያ እና በሶማሌላንድ ግንኙነት ዙሪያ በሚደረገው የምክክር መድረክ ላይ ለመሳተፍ ጅቡቲ መድረሳቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት አስታውቋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮጵያ በሕዳሴ ግድብ ድርድር የቴክኒክና የህግ ቡድኖች ቢኖሩ በሚል ያቀረበችውን ሀሳብ ሱዳን ተቀብላለች፡- የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር

ኢትዮጵያ በድርድሩ ሁለት የቴክኒክና የህግ ቡድኖች ቢኖሩ በሚል ያቀረበችውን ሀሳብ ሱዳን መቀበሏን የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታወቀ።በኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብፅ መካከል በህዳሴ ግድብ ዙሪያ ሲካሄድ የነበረው ድርድር ትናንትም ቀጥሎ ውሏል።በእለቱ በነበሩ ቴክኒካዊ ጉዳዮች ላይ በተካሄደ ድርድር ኢትዮጵያ የግድቡን ውሃ አሞላል በተመለከተ ባቀረበችው ሃስብ ላይ ንግግር መደረጉን ሚኒስቴሩ አስታውቋል።በዚህም የመጀመሪያው ዙር የግድቡን የውሃ አሞላል የሚገዛበት መመሪያን በተመለከተ ኢትዮጵያ ባቀረበችው ሃሳብ ለመቀጠል ከመግባባት መደረሱን ነው ያመለከተው።

በድርድሩም በግብፅ በኩል ኢትዮጵያ ቀደም ሲል ሳትቀበለው የቀረችውን ረዘም ያለ ደረቃማ ዓመትና የድርቅ ጊዜን በተመለከተ “ዝርዝር ህግ መኖር አለበት” የሚለውን ሃሳቧን በድጋሚ ለውይይት አቅርባለች።ረዥም ድርቅን በተመለከተ የቴክኒክ ኮሚቴ የውሃ አለቃቁ ላይ ህግን እንዲያዘጋጅ ሃላፊነት እንዲሰጠው እና ዝርዝር አለቃቀቅን በተመለከተ ግን ድርድር እንደሚያስፈልግ ከመግባባት ላይ ተደርሷል።በተመሳሳይ የግድቡን ደህንነት የተመለከተ ህግ እና ግድቡ በሚኖረው አካባቢያዊ እና ማህበራዊ ተፅእኖ ጥናት ማስፈለግ ላይ መግባባት ላይ መደረሱን ነው የተገለጸው።

የግብፅ ተደራዳሪዎች በእለቱ የነበራቸው ተሳትፎ የተቀዛቀዘ ነበር ያለው መግለጫው፤ ከተራዘመ የድርቅ ሁኔታ ጋር ያላቸውን ፍላጎት በማሳወቁ ላይ ብቻ መሳተፋቸውን አመልክቷል።ነገር ግን በመጨረሻ ሰዓት የግብፅ ተደራዳሪዎች ውይይት ሲደረግበት በነበረው እና ከዚህ በፊት ራሳቸው ሊያሰራ የሚችል ሰነድ ነው ብለው አስተያየት የሰጡበትን ሱዳን ያቀረበችውን ሰነድ መልሰው ተቃውመዋል።ነገም በእስካሁኑ ድርድር የተገኙ ለውጦችን በመገምገም ስምምነት ባልተደረሰባቸው ጉዳዮች ላይ ድርድሩ እንደሚቀጥል ሚኒስቴሩ በላከው መግለጫ ማስታወቁን ኢዜአን ጠቅሶ ኢቢሲ ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 179 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ተገኘባቸው።

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 4845 የላብራቶሪ ምርመራ 179 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸውና የ2 ሰዎች ህይወት ማለፉን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ፡፡በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 3ሺህ 345 ደርሷል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ ተጨማሪ የ2 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን ፣ ባጠቃላይ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 57 ደርሷል፡፡

ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ ህይወታቸው ያለፈ ሁለቱም ሰዎች በአስከሬን ምርመራ በተወሰደ ናሙና የተለዩ ሲሆን አንድ ወንድና አንድ ሴት ፣ ሁለቱም የአዲስ አበባ ነዋሪዎች መሆናቸው ታውቋል ።

@YeneTube @FikerAssefa
ዛሬ ቫይረሱ የተገኘባቸው 179 ሰዎች ሲሆኑ በዜግነት 176 ኢትዮጵያውያን፣ 3ቱ የውጭ ሀገር ዜጎች ናቸው። በፆታ ሲታይ ደግሞ ወንድ(116) ሴት(63) ናቸው!

➡️ዕድሜያቸው ከ2 ወር-80 አመት የሆኑ

➡️ተጨማሪ 50 ሰዎች(41 ከአዲስ አበባ፣ 4 ከአማራ፣ 3 ከአፋር፣ 2 ከትግራይ ክልሎች) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 545 ነው።

➡️የተገኙት ከአዲስ አበባ(111)፣ ከኦሮሚያ ክልል(15)፣ከአማራ ክልል(23)፣ ከደቡብ ክልል(2)፣ ከሀረሪ ክልል(1) ፣ ከትግራይ ክልል(9)፣ ከሶማሌ ክልል(5)፣ከድሬዳዋ(2) እና ከአፋር ክልል(11) በድምር 179 ሰዎች ናቸው።

➡️በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 3345 ደርሷል።

➡️በጠና የታመሙት ቁጥር ደግሞ 30 ነው።

➡️በ24 ሰዓት ውስጥ 2 ሞት የተመዘገበ ሲሆን፣ እስካሁን በቫይረሱ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 57 ነው።

@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ በ 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ 111 ሰዎች ቫይረሱ የተገኘባቸው ሲሆን በከተማው ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ሁለት ሺህ ሶስት መቶ ስድሳ ስምንት (2479) ደርሷል፡፡

ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ በ ሃያ አራት ሰዓታት ውስጥ በከተማው የ2 ኢትዮጵያውያን ህይወት አልፏል።

በሌላ በኩል ደግሞ በትላንትናው እለት 41 ሰዎች ከአዲስ አበባ ከኮሮና በሽታ አገግመዋል፡፡

በ24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች በክፍለ ከተማ፦
አዲስ ከተማ 18፤
ልደታ 16፤
ጉለሌ 18፤
ኮልፌ ቀራንዮ 19፤
ቦሌ 14፤
አራዳ 13፤
የካ 2፤
ንፋስ ስልክ ላፍቶ 5፤
አቃቂ ቃሊቲ 1፤
ቂርቆስ 5፤

@YeneTube @FikerAssefa
የሰባት ክልል ርእሳነ መስተዳድሮች ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ጎበኙ!

የሰባት ክልል ርእሳነ መስተዳድሮች በታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ጉብኝት አድርገዋል።የሰባቱ ክልሎች ርዕሳነ መስተዳድሮቹ በኢኖቬቭንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር እና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ዶ/ር ኢንጂነር አብርሃም በላይ እና በተቋሙ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አሸብር ባልቻ በመመራት የግድቡን ግንባታ ጎብኝተዋል።ዶ/ር አብርሃም በላይ፣ በግድቡ ላይ ስለተከናወኑት ተግባራትና በመጪው ክረምት ውሃ ለመያዝ የሚሰሩትን ስራዎች በተመለከተ ገለፃ አድርገውላቸዋል።

በወሳኝ ምዕራፍ ላይ ትልልቅ ስራዎች በሚሰሩበት ጊዜ ርዕሰ መስተዳድሮቹ ግድቡን መጎብኘታቸው የተለየ ትርጉም እንደሚሰጠውም ዶ/ር አብርሃም ተናግረዋል።ርዕሰ መስተዳድሮቹ በበኩላቸው፣ የግድቡ ወቅታዊ የግንባታ ሂደት አበረታች እንደሆነ መመልከታቸውን ገልፀዋል።ይህም ስለግድቡ ለሚመሩት ህዝብ በተገቢው ሁኔታ ለመግለፅ እና በተለያዩ ወገኖች የሚሰነዘሩ አሉታዊ አስተያየቶችን ለማክሸፍ ያስችለናል ብለዋል።

ርዕሳነ መስተዳድሮቹ ከጉብኝቱ በኋላ ግድቡ እየተገነባ ባለበት ስፍራ ችግኞችን በመትከል የአረንጓዴ አሻራቸውን አሳርፈዋል።የታላቁ ህዳሴ ግድብ የመሃከለኛው ክፍል የኮንክሪት ሙሊት ለዓመታት ከነበረበት ከባህር ጠለል በላይ ከ525 ሜትር አሁን ላይ 552 ሜትር ደርሷል። ውሃ ለመያዝም ስምንት ሜትሮች ብቻ ቀርተውታል።የግድቡ ግንባታ አጠቃላይ አፈፃፀም 74 በመቶ መድረሱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዘገባ ያመለክታል።

Via ETV
@YeneTube @FikerAssefa
የጥንቃቄ መረጃ!

ባለፉት 24 ሰዓት ዉስጥ በአዲስ አበባ የኮሮና ቫይረስ በሽታ (COVID-19) ላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ የኮሮና ቫይረስ በሽታ እንዳለበት የተረጋገጠበት አንድ ዕድሜው 20 የሆነ ግለሰብ ትክክለኛ ባለሆነ መንገድ ተደብቆ ህብረተሰቡን ለአደጋ ሊያጋልጥ በሚችል መልኩ ቤተሰቦቹ ወደሚገኙበት ወላይታ ዞን ከገባ በኋላ በህብረተሰቡ ትብብርና በመንግስት በኩል በተደረገ ብርቱ ክትትል እንዲያዘ ተደርጎ ወደ ህክምና ማዕከል እንዲገባ የተደረገ ሲሆን ግለሰቡ ወደ ወላይታ የመጣበትን ተሸከርካሪ በቁጥጥር ስር ለማዋል የሚመለከታቸው አካላት ከጸጥታ ኃይሎች ጋር በመተባበር ክትትል እያደረጉ የሚገኝ በመሆኑ ህብረተሰቡ የተለመደውን ትብብሩን እንዲያደርግ ቢሮው ጥሪውን እያስተላለፈ
ቫይረሱ ከተስፋፋባቸዉ የሀገራችን ክልሎች የምትመጡ የክልላችን ነዋሪዎች ራሳችሁን ከቫይረሱ ይበልጥ በመጠበቅ ለራሳችሁ፣ ለቤተሰባችሁ፣ ብሎም ለአጠቃላይ ማህበረሰቡ ያላችሁን ፍቅርና አክብሮት እንድትገልፁ ቫይረሱን በጋራ በመከላከል እንድንደጋገፍ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡በመሆኑም መላዉ የክልላችን ህብረተሰቦች በየትኛዉም አጋጣሚ በቫይረሱ የተያዘ ሰዉ ሊያጋጥመን እንደሚችል በመረዳት ሳትደናገጡ የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት መንግስት እያደረገ ያለዉን ጥረት በነቃ ተሳትፎ እንድታግዙ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

-የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ/ ጤና ቢሮ
@YeneTube @FikerAssefa
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ከፒያሳ ወደ አራት ኪሎ የሚወሰደው መንገድ ለተሽከርካሪ ዝግ ሆኖ ሞተር አልባ መንገድ ብቻ እንዲሆን ታስቧል። መንገዱ የእግረኞች መጓጓዧ፣አረንጓዴ ቦታዎች፣የተለያዪ መዝናኛዎችና የብስክሌት መንገድን ያካተተ ነው።የመንገዱን መልሶ እድሳት በተመለከተ የተዘጋጀውን ቪዲዮ ከላይ ተያይዟል።

Via Mayor Office
@YeneTube @FikerAssefa
በቻይና ቤጂንግ በሚገኝ አንድ የምግብ ገበያ የተነሳው ኮሮናቫይረስ ዳግም ስጋት ፈጠረ!

በቻይና ቤጂንግ በሚገኝ ዤንፋዲ በተባለ የጅምላ ምግብ ገበያ በተነሳ ኮሮኖቫይረስ በከተማዋ 36 ሰዎች በኮሮናቫይረስ መያዛቸውን አርቲ ሚዲያ ዘግቧል።አንድ ወር ለሚሞላ ያክል ምንም አዲስ የኮሮና ታማሚ ያልተገኘባት ቻይና በቤጂንግ ቫይረሱ እንደ አዲስ መከሰቱን ተከትሎ ዤንፋዲ የተባለውን የምግብ ገበያ የዘጋች ሲሆን በገበያው የሚገኙ አሰር መንደሮች ላይ ከትናንት ጀምሮ የእንቅሳቃሴ ገደብ ጥላ የኮሮና ምርመራ እያከናወነች ነው ። የቫይረሱ ስርጭት ዳግም እንዳይባባስ ስጋት መኖሮኑም ተጠቁማል።ቀደም ሲል በዉሀን በሚገኝ የምግብ ማርኬት የተነሳው ኮሮና አለምን አዳርሶ እሰከ ዛሬ ከ400 መቶ ሺ በላይ የሚሆን ሰው ሒወት አሳጥቷል ።

Via @tesfaget55
@YeneTube @FikerAssefa
በርካታ የአውሮጳ አገራት ድንበሮቻቸውን መክፈት ጀመሩ!

የአውሮጳ ኅብረት ከዛሬ ሰኞ ጀምሮ አባል አገራቱ ድንበራቸውን እንዲከፍቱ እያበረታታ ይገኛል።ዛሬ ድንበር ሙሉ በሙሉ እንከፍታለን ካሉት መካከል ቤልጂየም፣ ክሮሺያ፣ ስዊዘርላንድና ጀርመን ይገኙበታል፡፡

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
አውሮፓ 400 ሚሊዮን ብልቃጥ የኮሮናቫይረስ ክትባት ለማግኘት ከአምራች ኩባንያ ጋር ውል ተፈራርሟል፡፡

አራት የአውሮፓ ኅብረት አባል ሀገራት አህጉሩን በመወከል ከመድኃኒት አምራች ኩባንያው አስትራዜኒካ ጋር የኮሮናቫይረስ ክትባት ለማግኘት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተዋውለዋል፡፡በቂ ክትባት በማምረት የኮሮናቫይረስን ለመከላከል ያለመ ውል መሆኑን የጣልያን ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡በስምምነቱ መሠረት የእንግሊዝና ስዊድን ጥምረት የሆነው ግዙፍ የመድኃኒት አምራች ኩባንያ አስትራዜኒካ 400 ሚሊዮን ብልቃጥ ክትባቶችን ለአውሮፓ የሚያመርት ይሆናል፡፡ ክትባቱ በኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ እየበለጸገ የሚገኝ ነው፡፡ ኩባንያው ወረርሽኙን ለመከላከል ያለምንም ትርፍ ክትባቱን እንደሚያቀርብም አስታውቋል፡፡ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ክትባቱ ክሊኒካዊ ሙከራ (የሕክምና ሙከራ) ላይ ነው፡፡

በዚህ ክረምት ሙከራው እንደሚጠናቀቅም ይጠበቃል፡፡የሙከራ ውጤቶቹ ደኅንነቱ የተጠበቀና ውጤታማ መሆኑ የክትባት ተቆጣጣሪ አካላትን ካሳመነ በአውሮፓውያኑ 2020 መገባደጃ ክትባቱን ለሰዎች ለመስጠት ታቅዷል፡፡ኩባንያው አዲስ የገባው የውል ስምምነትም ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ኔዘርላንድና ጣሊያንን ባቀፈው ከአውሮፓው የክትባት ጥምረት ቡድን ጋር የተደረገ ነው፡፡ እነዚህ ሀገራት ክትባቱን ለአውሮፓ አባል ሀገራት የሚያቀርቡም ይሆናል፡፡ኩባንያው ከዚህ ቀደምም ከተለያዩ ሀገራት ጋር ስምምነት መፈጸሙ ይታወሳል፤ ቻይና፣ ብራዚል፣ ጃፓንና ሩሲያም ተመሳሳይ ፍላጎት እንዳላቸው ሲ ጂ ቲ ኤን ዘገባ ያመለክታል፡፡

Via AMMA
@YeneTube @FikerAssefa
በሶማሊ እና ኦሮሚያ ክልሎች አጎራባች የሆኑ በቱሉ ጉሌድ እና ጭናክሰን ወረዳዎች የሚገኙ ተፈናቃዮች ወደየቤቶቻቸው መመለሳቸውን ተገለፀ፡፡

በሁለቱም ወረዳዎች የሚኖሩ ወንድማማች ህዝቦች መሃል ተፈጠሮ የነበረው ለብዙ አመታት የቆየ የእርስ በእርስ ግጭት ፀቡን ለማርገብ እና የማቀራረብ ስራዎች የክልሉ መንግስት ሲተገበር ቆይተዋል ብሏል የክልሉ ኮ/ቢሮ፡፡በሁለቱም ወረዳዎች ላይ ያሉ የጎሳ መሪዎችም የተጀመረውን የሰላም ድባብ ለመጠበቅ ሕብረተሰቡን አስተባብረው እንደሚሰሩ ገልፀዋል፡፡የሶማሊ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ሞክትል ሗላፊ አቶ ዓብዲላሂ መሐመድ እንደገለፁት የአከባቢውን ሰላም የመጠበቅ ጉዳይ ላይ ክልሉ አጠናክሮ ይሰራል ብለዋል፡፡ተፈናቃዮቹን ወደቀዬዎቻቸው ከተመለሱ በሗላም የኑሯቸውን ደረጃ ወደነበረበት ለመመለስ እና ሁኔታቸውን ለመከታተል የክልሉ መንግስት ቃል ገብቷል፡፡

ምንጭ: የክልሉ መ/ኮ/ቢሮ
@YeneTube @FikerAssefa