YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.88K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የኢትዮጵያ ሕዝብ በሀገሩ ሕልውናና ክብር ከመጡበት ሞት የማይፈራ ጀግና ሕዝብ መሆኑን አይደለም ግብጽ ዓለም እንደሚያውቀው የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኤታ ማዦር ሹም ጀነራል ብርሃኑ ጁላ አስታወቁ።

የተሳሳተ የመሪዎቿ አስተሳሰብ ግብጽን በከፍተኛ ደረጃ እንደሚጎዳትም አመልክተዋል።ጀነራል ብርሃኑ ጁላ በተለይ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንዳመለከቱት ግብጾች ኢትዮጵያዊያን ጦርነት ከመጣ እንዴት ጦርነትን መሥራት እንደሚችሉ በሚገባ ያውቁታል። የኢትዮጵያ ሕዝብ በሀገሩ ሕልውናና ክብር ከመጡበት ሞት የማይፈራ ጀግና ሕዝብ መሆኑን አይደለችም ግብጽ ዓለም ያውቃል። በሀገሩ ጥቅምና ሕልውና የሚደራደር ኢትዮጵያዊ የለም።የጦር መሣሪያ በገፍ መሰብሰብ ብቻ በጦርነት ውስጥ ለድል አያበቃም ያሉት ጄኔራል ብርሃኑ፤ በጦርነት ውስጥ ለድል የሚያበቁ ሳይንሳዊ የሆኑ የጦርነት መሰረታውያን የሚባሉ ሕጎች እንዳሉ ጠቁመዋል።

ጀነራል ብርሃኑ እንዳሉት ለድል የሚያበቁት የመሰረታውያኑ ቁልፎች በሙሉ በኢትዮጵያውያን እጅ ናቸው፤ ግብጾች 30 እና 40 ዓመት ሙሉ የሰበሰቡት ብዙ አይነት የጦር መሣሪያ አላቸው፤ በዚህ አስፈራርተው የጋራ የሆነውን ውሃ እንዳትነኩ ለማለት ይሞክራሉ። መሪዎቿ በዚህ መልኩ ማሰብ አልነበረባቸውም።ግብጻዊያን ከኢትዮጵያ ጋር በጭራሽ መጣላት ሳይሆን ኢትዮጵያንን ተንከባክበው በመያዝ ውሃውን እንዴት አድርገን በጋራ እንጠቀም ማለት ነበረባቸው ያሉት ጀነራሉ፣ ፈጣሪ ውሃውን ኢትዮጵያ ውስጥ ፈጠረው፤ ወደ ሱዳንና ግብጽ እንዲፈስ አደረገው፤ የወንዙ ውሃ ኢትዮጵያ፤ ሱዳን፤ ግብጽም ላይ ጥቅም ላይ ይውላል ብለዋል።

ሙሉ ዘገባው👇👇👇
https://telegra.ph/General-Birhanu-Jula-latest-interview-with-Addis-Zemen-06-12
⬆️⬆️
መንግሥት በህገ ወጥ መንገድ የሥልጣን ጊዜ አራዝሟል በማለት ኦነግ እና ኦፌኮ ያወጡት የጋራ መግለጫ፣

@YeneTube @FikerAssefa
ህብረት ባንክ ለ22 አመት ሲጠቀምበት የነበረውን አርማ(Logo) ቀይሯል። ከላይ በምስሉ ላይ የሚታየው አዲሱ ሎጎ ሲሆን ከዚህ በፊት የወጋገንና ንብ ኢንተርናሽናል ባንክን አርማ በመስራት በሚታወቀው በስቱዲዮኔት ሀገር በቀል የብራንዲንግ ኃ/የተ/የግ/ኩ የተሰራ ነው።

ምንጭ: ፎርቹን
@YeneTube @FikerAssefa
ፈንቅል ከተባለው የትግራይ ወጣቶች እንቅስቃሴ ጀርባ እጄ የለበትም ሲል የትግራይ ክልል የብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት አስታወቀ።
አሁን በትግራይ ላይ ያለው እንቅስቃሴ ነፃነት ፍለጋ መሆኑን ነው የገለፀው።

በትግራይ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች ላይ እየታዩ ያሉት ሰልፎች እና መንገድ መዝጋት በክልሉ የሚታየውን የመልካም አስተዳደር ችግር የሚያሳዩ ናቸው ብሏል።ፈንቅል የተባለው የወጣቶች ንቅናቄ ላይ ብልፅግና ከጀርባው አለበት የተባለው ከእውነት የራቀ ነው ብሎ የወጣቶች እንቅስቃሴ የትግራይ ህዝብ እየደረሰበት ያለውን በደል በመገንዘብ ለለውጥ እየተንቀሳቀሱ መሆኑን አስታውቋል።

Via Ahadu Radio
@YeneTube @FikerAssefa
የትግራይ ክልል ምክርቤት 6ተኛ ክልላዊ ምርጫ በትግራይ እንዲካሄድ በሙሉ ድምፅ ውሳኔ አስተላለፈ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በትግራይ ኮረና ለመከላከል የወጣው አስቸኳይ ግዜ አዋጅም ለ75 ቀናት ተራዝሟል፡፡

Via Million HaileSelasie
@YeneTube @FikerAssefa
#ኦሪጂናል ሞባይል ስልኮች በዋስትና

A01 2019 /16 GB/ 5,500 ብር
A10S 2019 /32 GB/ 7,200 ብር
A20S 2019 /32 GB/ 8,500ብር
A30S 2019 /64 GB/ 11,300 ብር
A30S 2019 /128 GB/ 11,900 ብር

A50S 2019 /128 GB/ 4GB 14,000
A50S 2019 /128 GB/ 6GB 14,500
A31 2020 /128 GB/ 4GB 13,999
A51 2020 /128 GB/ 6GB 14,999 ብር

A60 2019 /64 GB/ 6GB 13,500 ብር
A70 2019 /128 GB/ 6GB 16,500 ብር
A71 2020 /128 GB/ 6GB 21,500 ብር
A71 2020 /128 GB/ 6GB 22,000 ብር

M30S 2019 /64 GB/ 4GB 11,500
M30S 2019 /128 GB/ 4GB 13,500
📌M31 2020 /128 GB/ 6GB 15,400

አድራሻ :- ከቦሌ መድሃኔአለም ቤተ ክርስቲያን ወደ ቦሌ ብራስ የሚወስደው መንገድ ላይ

Contact US
0953964175 @heymobile
0925927457 @eBRO4
0910695100 @Roviii

@HEYOnlinemarket
የጤና ሚኒስቴር እና የኦሮሚያ ጤና ጥበቃ ቢሮ 234 አምቡላንሶችን ለኦሮሚያ ክልል አስረክበዋል።

በርክክቡ ወቅት አምቡላንሶቹ በፌደራል፣ በክልል መንግስት እና በህብረተሰቡ ተሳትፎ የተገዙ መሆኑ ታውቋል።አምቡላንሶቹ ከቀረጥ ነፃ 284 ሚሊየን 778 ሺህ ብር ወጪ እንደተደገባቸውም ተገልጿል።የእናቶችን ሞት ለመቀነስ እና የጤና አገልግሎትን ለማፋጠን ድርሻቸው የጎላ እንዲሚሆን ይታመናል መባሉን ከክልሉ ጤና ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
በኮቪድ 19 ምክንያት ለኩላሊት እጥበት (ዲያሊስስ ህክምና) የሚሆኑ ግብአቶችን ከውጭ ማምጣት ባለመቻሉ ህሙማኑ ለከፋ የጤና ችግር እየተጋለጡ ነው ተባለ፡፡

በዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል የሚገኘው የኩላሊት ህመምተኞች እጥበት በጎ አድራጎት ድርጅት ለሸገር በላከው መግለጫ እንዳለው በወረርሽኙ ምክንያት የውጭ ምንዛሬ ማግኘት አልተቻለም፡፡የውጭ ምንዛሬ እጦቱም ለኩላሊት እጥበት ህክምና የሚሆኑ ግብአቶችን ከውጭ ገዝቶ ለማምጣት ችግር ፈጥሯል፡፡በአሁኑ ሰዓት በርካታ የኩላሊት ህመምተኞች ኩላሊታቸው ሙሉ በሙሉ ስራ በማቆሙ በሕይወት ለመኖር በሳምንት ሶስቴ የኩላሊት እጥበት አገልግሎት ማግኘት ይጠበቅባቸዋል፡፡

Via Sheger FM
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 245 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው።

በ24 ሰዓታት ውስጥ 245 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው፤ የ7 ሰዎች ህይወት አለፈ።ኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 5709 የላብራቶሪ ምርመራ 245 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 2915 መድረሱንም የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታውቀዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ ተጨማሪ የ7 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን ፣ ባጠቃላይ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 47 ደርሷል፡፡

ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ ህይወታቸው ያለፈ 7 ሰዎች ሁኔታ

1.በህክምና ላይ የነበሩ የ75 አመት የአዲስ አበባ ነዋሪ (ወንድ)

2.በአስክሬን ምርመራ ቫይረሱ የተገኘበት የ48 አመት የአዲስ አበባ ነዋሪ

3.በአስክሬን ምርመራ ቫይረሱ የተገኘባቸው የ80 አመት የአዲስ አበባ ነዋሪ(ወንድ)

4.በአስክሬን ምርመራ ቫይረሱ የተገኘባት የ21 አመት የአዲስ አበባ ነዋሪ

5.በአስክሬን ምርመራ ቫይረሱ የተገኘባቸው የ70 አመት የአዲስ አበባ ነዋሪ(ሴት)

6.በአስክሬን ምርመራ ቫይረሱ የተገኘባት የ29 አመት የአዲስ አበባ ነዋሪ

7.በአስክሬን ምርመራ ቫይረሱ የተገኘባቸው የ85 አመት የአዲስ አበባ ነዋሪ(ሴት)

@YeneTube @FikerAssefa
ዛሬ ቫይረሱ የተገኘባቸው 245 ሰዎች ሲሆኑ በዜግነት 241 ኢትዮጵያውያን፣ አራቱ የውጭ ሀገር ዜጎች ናቸው። በፆታ ሲታይ ደግሞ ወንድ(172) ሴት(73) ናቸው!

➡️ዕድሜያቸው ከ1-85 አመት የሆኑ

➡️ተጨማሪ 17 ሰዎች ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 451 ነው።

➡️የተገኙት ከአዲስ አበባ(190)፣ ከኦሮሚያ ክልል(17)፣ከአማራ ክልል(3)፣ ከደቡብ ክልል(4)፣ ከሶማሌ ክልል(16) ፣ ከትግራይ ክልል(15) በድምር 245 ሰዎች ናቸው።

➡️በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 2915 ደርሷል።

➡️በጠና የታመሙት ቁጥር ደግሞ 38 ነው።

➡️በ24 ሰዓት ውስጥ 7 ሞት የተመዘገበ ሲሆን፣ እስካሁን በቫይረሱ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 47 ነው።

@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ በ 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ አንድ መቶ ዘጠና (190) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፤የ ሰባት ኢትዮጵያውያን ህይወት አልፏል።

በአዲስ አበባ በ 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ አንድ መቶ ዘጠና (190) ሰዎች ቫይረሱ የተገኘባቸው ሲሆን በከተማዋ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ሁለት ሺህ አንድ መቶ ሰላሳ ስድስት(2136) ደርሷል፡፡

ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ በሃያ አራት ሰዓታት ውስጥ አዲስ አበባ ከተማ የ ሰባት (7) ኢትዮጵያውያን ህይወት አልፏል።

በዚህም በአዲስ አበባ በ24 ሰዓት ውስጥ ቫይረሱ ከተገኘባቸው 245 ሰዎች መካከል 85 ሰዎች ቦሌ ክፍለ ከተማ እንዲሁም 22 ሰዎች ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ይገኛሉ።

በተጨማሪም ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ 22፣ አራዳ 16 ፣ ልደታ 10 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል።

በአጠቃላይም እስካሁን በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ 496 ሰዎች ቫይረሱ ሲገኝባቸው ቦሌ 375 እንዲሁም በጉለሌ ክፍለ ከተማ 256 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል።


በሌላ በኩል ደግሞ በትላንትናው እለት አስራ ስድስት (16) ሰዎች ከአዲስ አበባ ከኮሮና በሽታ ማገገማችውን የጤና ቢሮ አስታውቋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ጸጥታ ሃይሎች የሚፈጽሟቸውን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች የኢትጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን እንዲመረምር ኦፌኮ በደብዳቤ ጠይቋል፡፡ ፓርቲው በፌስቡክ ገጹ ባሰራጨው ደብዳቤ፣ በኦሮሚያ እና አማራ ክልል ኦሮሚያ ልዩ ዞን ግድያ እና ሕገወጥ እስር ተፈጽሞባቸዋል ያላቸውን የበርካታ አባላቱን፣ ደጋፊዎቹን እና ሌሎች ዜጎችን ስም ዘርዝሯል፡፡ ኮሚሽኑ በአቤቱታው ላይ ምርመራ ማድረግ እና የእርምት ዕርምጃ ማስወሰድ አለበት፡፡

Via Wazema
@YeneTube @FikerAssefa
የመተንፈሻ ቀዳዳ የተገጠመላቸው የፊት መሸፈኛ ጭምብሎች ኮሮናቫይረስን ከመከላከል ጥቅማቸው ጉዳታቸው ያመዝናል!

የመተንፈሻ ቀዳዳ የተገጠመላቸው ጭምብሎች /ማስኮች/ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ከጥቅማቸው ይልቅ ጉዳታቸው ያመዝናል ሲል የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን አስታወቀ።ባለስልጣኑ ኮሮናቫይረስን መከላከል የሚያስችሉ የጭምብል /ማስክ/ አጠቃቀሞችን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል። የባለስልጣኑ የመድኃኒትና የሕክምና መሳሪያዎች ምዝገባና ፈቃድ ዳይሬክተር አቶ አብደላ ቃሶ፣ ምን አይነት የፊት መሸፈኛ የት ቦታ፣ በምን አይነት አግባብ መጠቀምና ማስወገድ አለብን የሚለውን መመሪያ በመተግበር በሽታው የከፋ ጉዳት ሳያስከትል በመተጋገዝ መሻገር ይገባናል ብለዋል።የኮሮና ቫይረስን ከመከላከል ይልቅ ጉዳታቸው ያመዝናል ስለተባሉት የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብሎችም ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የመተንፈሻ ቀዳዳ የተገጠመላቸው ጭምብሎች /ማስኮች/ በቀዳዳው የሚወጣው ትንፋሽ በቀጥታ በአካባቢው ለሚገኝ ሰውና ቁስ ስለሚለቀቅ መሰል ጭምብሎችን ባለማድረግ የቫይረሱን ስርጭት መከላከል ይገባል ነው ያሉት።አቶ አብደላ ቫይረሱን መከላከል የሚያስችሉ ግብዓቶችን በአገር ውስጥ ማምረት እንዲቻል እየተሰሩ ያሉ ስራዎችንም አብራርተዋል።የአገር ውስጥ መድሃኒት አምራቾች ሳኒታይዘር ማምረት የሚያስችል ጊዜያዊ ፈቃድ አውጥተው ወደ ስራ መግባታቸው ያለውን እጥረትና ከውጭ ለማስገባት የነበረውን ውጣ ውረድ ማቅለሉንም ተናግረዋል።

ባለስልጣኑ በመደበኛነት ሲጠቀምባቸው የነበሩ ህጎች፣ ደንቦችና አሰራሮችን ከተገቢነታቸው አንፃር በማሻሻል ወረርሽኙን ለመከላከልና መቆጣጠር እየሰራ እንደሆነም ገልጸዋል።መስሪያ ቤቱ ያለበትን የኅብረተሰቡን ጤና የመጠበቅ ኃላፊነት ከህግ አስከባሪና ሌሎች አካላት ጋር በመሆን በህገ-ወጥ መልኩ እየተሸጡ ያሉ የፊት መሸፈኛ ጭምብሎችና ሌሎች መድኃኒቶችን ለመቆጣጠር ጥረት እያደረገ ስለመሆኑም አስረድተዋል።
የባለስልጣኑ የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ኃላፊ አቶ አበራ ደነቀ በበኩላቸው ‘’አስመጪዎች ወደ መስሪያ ቤቱ መጥተው የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል የወጡ ጊዜያዊ መመሪያዎችን መሰረት በማድረግ እየሰሩ መሆናቸውን’ ገልጸዋል።

የተለያዩ መጠን ያላቸው ቀዳዳ አልባ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብሎች በአምራችና እርዳታ ሰጪ ድርጅቶች፣ በንግድ ተቋማትና ግለሰቦችም ጭምር ወደ አገር እንዲገቡ በማድረግ ጥቅም ላይ እንዲውሉ እየተደረገ ስለመሆኑ ተገልጿል።ቬንትሌተር በአገር ውስጥ ለማምረት ፍላጎት ያላቸው ድርጅቶችም የወጣውን ጊዜያዊ መመሪያ በመከተል ወደ ስራ መግባት እንደሚችሉም ጥሪ ቀርቧል።ባሕላዊ መድኃኒቶችን ለማምረትም የሕክምና ሙከራ መመሪያ መዘጋጀቱም ተገልጿል።ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል፣ ለመመርመርና ለማከም ጥቅም ላይ የሚውሉ ግብዓቶችም ሆኑ የሕክምና ሙከራዎች ፈቃድ ካገኙ በኋላም ክትትልና ቁጥጥር እያደረገ መሆኑም ተነግሯል።

Via ENA
@YeneTube @FikerAssefa
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
" የፌዴሬሽን ምክር ቤት ከምርጫና ተያያዥ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ የሰጠው የእፎይታ ጊዜ የወቅቱን ፈተና ለማለፍ ከማገዝ ባለፈ እንደ ሃገር ዴሞክራሲን መለማመድ እንድንችል አንድ እርምጃ ወደፊት የገፋ አጋጣሚ ነው።"

-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

ዴሞክራሲ እንዲያብብና ሀገራዊ መግባባት እንዲቀጥል ገዢው ፓርቲ በቀጣይ ጊዜያት በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር እየተወያየ መስራቱን ይቀጥላልም ብለዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአመቱ የተማሪዎች የምረቃ መርሐ ግብር በኮሮና ወረርሽኝ ሳቢያ በቪዲዮ እንደሚካሔድ አስታወቀ።

አንጋፋው ዩኒቨርሲቲ ዛሬ ባወጣው መግለጫ እንዳለው 80ኛው የተማሪዎች የምረቃ መርሐ-ግብር በመጪው ሐምሌ 4 ቀን 2012 ዓ.ም ይካሔዳል። በወረርሽኙ ምክንያት በመሰብሰብ ላይ ዕገዳ ቢጣልም ተማሪዎች ስኬታቸውን የሚያከብሩበት ዕለት ደማቅ እንደሚሆን ዩኒቨርሲቲው ለተመራቂዎች ተስፋ ሰጥቷል። ለወትሮው የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ሲመረቁ ቀድሞ ስድስት ኪሎ በሚገኘው ልደት አዳራሽ ኋላ በሚሊኒየም አዳራሽ ሞቅ ደመቅ ያለ መርሐ ግብር ይካሔድ ነበር። በመርሐ ግብሮቹ የተመራቂዎች ቤተሰቦች፣ የዩኒቨርሲቲው በርካታ መምህራን እንዲሁም ባለስልጣናት ይታደማሉ። የዘንድሮው ግን ተመራቂዎች እንደወትሮው በጋራ "እንኳን ደስ አላችሁ" እያሉ የሚዘምሩበት አልሆነም። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ድረ-ገፅ፣ በፌስቡክ እና በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን በቀጥታ ሊተላለፍ በታቀደው የምረቃ ሥነ-ሥርዓት አነቃቂ ንግግሮች ይደረጋሉ፤ የተማሪዎች ስም ከፍ ብሎ ይጠራል።በወረርሽኙ ምክንያት የመደበኛ ቅድመ ምረቃ ተማሪዎች ዘንድሮ እንደማይመረቁ ቀድሞ መገለፁ ይታወሳል።

ምንጭ: ዶይቸ ቨሌ
@YeneTube @FikerAssefa
በአፍሪካ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ቁጥር እየጨመረ ሲሆን የCDC አሁናዊ መረጃ የሚከተለውን ይመስላል:

➡️ሁሉም የአፍሪካ ህብረት አባላገራት ቫይረሱን ሪፖርት አድርገዋል።

➡️218,229 ሰዎች በቫይረሱ ተጠቅተዋል።

➡️5,791 ሰዎች ተይዘው ሞተዋል።

➡️97,891 ሰዎች አገግመዋል።

ምንጭ:CDC Africa
@YeneTube @FikerAssefa
ምርጫን የማስፈፀም ስልጣን የተሰጠው በህግመንግስቱ አንቀፅ 102 የተቋቋመው ምርጫ ቦርድ ስለሆነ ሌላ አካል በዚህ ጉዳይ ላይ ጣልቃ ልግባ ቢል ከስልጣን ገደቡ በላይ የምርጫ ቦርድን ስልጣን መጋፋት እና መዳፈር ስለሚሆን መንግስት የምርጫ ቦርድን ውሳኔ አክብሮ ይፈጽማል ሲሉ የጠቅላይ ሚንስትር ጽህፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ሃላፊው አስታወቁ።

ሀላፊው አቶ ንጉሡ ጥላሁን ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት፤ በህገመንግስቱ መሰረት ምርጫን የማስፈጸም ስልጣን ለአስፈጻሚው ስላልተሰጠ ከምርጫ ጋር በተያያዘ ማንኛውንም ነገር ሊያደርግ የሚችለውና ህገመንግስታዊ ስልጣን ያለው ምርጫ ቦርድ ብቻ ነው፡፡“አስፈፃሚ አካሉ በምርጫ ቦርድ ስራ እና ውሳኔ ጣልቃ በመግባት ቢፈትፍት ያለ ሀላፊነቱ መንቀሳቀስ ስለሆነ መንግስት የምርጫ ቦርድን ውሳኔ ያከብራል፣ይፈፅማል” ነው ያሉት አቶ ንጉሡ፡፡

በኢትዮጵያ ታሪክ ምርጫ ቦርድ የተሸለ እና ገለልተኛ ሆኖ እንዲቋቋምና ለእውነተኛ ዴሞክራሲ መጎልበት በር አድንዲከፍት ሆኖ ተደራጅቷል ያለት አቶ ንጉሡ፤ የክልልም ሆነ የፌዴራል መንግስት በዚህ ጉዳይ ላይ ጣልቃ ልግባ ቢል ከስልጣን ገደቡ በላይ የምርጫ ቦርድን ስልጣን መጋፋት እና መዳፈር ይሆናል ሲሉ ነው ያብራሩት።
እንደ አቶ ንጉሡ ገለጻ፤ የኢትዮጵያ መንግስት በአሁኑ ወቅት ዋነኛ ትኩረቱ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በመከላከል የህዝብን ደህንነት መጠበቅ፣ የህዳሴ ግድብን በተመለከተ የሚገጥመን የማደነቃቀፍ ፈተና በማለፍ ውሀ መሙላት መጀመር እና ለጥቅም ማብቃት እንዲሁም ወረርሽኙ ሊያደርስ የሚችለውን ኢኮኖሚያዊ ጉዳት ሊቀንሱ የሚችሉ ስልቶችን ነድፎ መረባረብ ነው፡፡

የምርጫው ጉዳይ ገለልተኛው እና በህገመንግስቱ ስልጣን የተሰጠው ምርጫ ቦርድ ስራ ይሆናል ያሉት አቶ ንጉሡ፤ ምርጫ ቦርድ ደግሞ በህገ መንግስቱ በተሰጠው ስልጣን መሰረት የሚያደርገውን ያደርጋል የሚል እምነት አለኝ ሲሉ አስታውቃዋል። ይህም ልክ መከላከያ ሰራዊቱ ገለልተኛ ሆኖ የሀገርን ሉዋላዊነት እና ህገመንግስቱን እንደሚያስከብር ሁሉ ምርጫ ቦርድም በህገመንግስቱ የተሰጠውን ስልጣንና ሃላፊነት ያስከብራል ማለት እንደሆነ አብራርተዋል።የትግራይ ክልል ምክር ቤት በትናንትናው ዕለት የክልሉን ምክር ቤት ምርጫ በዘንድሮው አመት አካሂዳለሁ ብሎ መወሰኑ ይታወሳል፡፡

Via EPA
@YeneTube @FikerAssefa