YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.92K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የኮቪድ-19 ወረርሽኝን በመከላከል ሂደት የሚባክን ጊዜ መኖር የለበትም - ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም

የዓለም የጤና ድርጅት ቀዳሚው ትኩረቱ ሁሉንም የሕብረተሰብ ክፍል ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ መጠበቅና ወረርሽኙን መቆጣጠር መሆኑን የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ተናገሩ፡፡

"እስካሁን ኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመቆጣጠር ባደረግነው ጉዞ የተማርነው ነገር ቢኖር በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ለመለየት ቶሎ ምርመራ ማድረግ፣ ቫይረሱ ከተገኘባቸውም ቶሎ ለይቶ ወደ ማቆያ መውሰድ እና ድጋፍ መስጠት የቫይረሱን ስርጭት ለመቆጣጠር ዓይነተኛ መንገድ መሆኑን ነው" ብለዋል፡፡

ይህ መርህ የሰዎችን ህይወት ከኮሮናቫይረስ ከመታደጉም በላይ በሽታው በኢኮኖሚ ላይ የሚያሳድረውን ተፅዕኖ ለመከላከልም ይረዳል ነው ያሉት፡፡

ድርጅቱ የቫይረሱን ስርጭት ለመቆጣጠር የሚረዱ እንደ የፊት መሸፈኛ (ማስክ)፣ የእጅ ጓንት እና የተለያዩ የህክምና ቁሳቁስን ለአፍሪካ ሀገራት ማሰራጨቱንም ዶ/ር ቴድሮስ በትዊተር አካውንታቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ ጠቅሰዋል፡፡

Via:- EBC
@Yenetube @Fikerassefa
IMF ለ32 የአፍሪካ አገራት 11 ቢሊዮን ዶላር ሊለግስ ነው!

አለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት አይ ኤም ኤፍ ከሳህራ በርሃ በታች ለሚገኙ 32 የአፍሪካ አገራት 11 በሊዮን ዶላር ሊሰጥ መሆኑን አስታውቋል፡፡ድጋፉ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል እና ቫይረሱ ካሳደረው ምጣኔ ሃብታዊ ተጽህኖ ለማገገም የሚውል ነው፡፡ተቋሙ ያደረገውን ድጋፍ ከአለም ባንክ፣ከአለም ጤና ድርጅት፣ ከአፍሪካ ሕብረትና ልማት ባንክ ጋር ተግባራዊ በማድረግ ለበሽታው ተጋላጭ የሆኑ ሰዎችን ለማገዝ እንዲሁም የገንዘብና የፋይናንስ ፖሊሲዎችን ለማሻሻል እንደሚንቀሳቀስ ተነግሯል፡፡

በወረርሽኙ የተነሳ አፍሪካ አይታው የማታውቀው የጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት ውድቀት እንደሚያጋጥማት ነው የተነገረው፡፡በዚህም መሰረት በ2020 የአፍሪካ ጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት 1.6 በመቶ እንደሚሆን ተተንብዩአል፡፡ በአፍሪካ የኮሮና ወረርሽኝ ከሚያደርሰው ሁሉን አቀፍ ቀውስ ለማገገም 100 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ማስታወቁን ያስታወሰው ብሉንበርግ ነው፡፡፡

Via ENA
@YeneTube @FikerAssefa
የአፍሪካ ሀገራት ብዙ ኮሮና ቫይረስ መመርመር የቻሉ ሀገራት ዝርዝር

1. ደቡብ አፍሪካ (83,663)

2.ጋና ( 44,421 )

3. ግብፅ (25,000)

4.ቱኒዝያ (11,825)

5.ሞሮኮ (9,609)

6.ኬንያ ( 8,123)

7. ሞሪሺየስ ( 7,077)

8. ሩዋንዳ ( 6,237)

9. ኡጋንዳ ( 5,025)

10. ናይጄሪያ ( 5000+ )
@Yenetube @Fikerassefa
#ዓለም በኮሮና እየታመሰች ባለበት በዚህ ወቅት በደቡብ ኮሪያ ሀገራዊ ምርጫ ህዝቡ በነቂስ ወጥቶ እየመረጠ መሆኑ አነጋግሯል።

በደቡብ ኮሪያ በተከፈተው ምርጫ መራጩ ህዝብ ጭምብል ፣ጓንትና ሳኒታይዘር ይዞ ካልተገኘ ወደ ምርጫ ጣቢያ መግባት እንዳማይችል ታውቋል::

ደቡብ ኮሪያዊያን አካላዊ ርቀትን ጠብቀው የህዝብ እንደራሴዎችን ለመምረጥ ድምጽ እየሰጠ መሆኑን #አልጀዚራ ዘግቧል።

@Yenetube @Fikerassefa
የኢትዮጵያ GDP በግማሽ እንደሚያሽቆለቁል አይ ኤም ኤፍ ተነበየ፡፡

የአለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (I.M.F) ከሰዓታት በፊት ይፋ ያደረገው ከሰሀራ በታች አገራት የኢኮኖሚ ሁኔታ ትንበያ እንደሚያሳየው እ.ኤ.አ በ2020 የኢትዮጵያ አመታዊ ጥቅል ምርት እድገት (G.D.P) ወደ 3.2 በመቶ ያሽቆለቁላል ብሏል፡፡
ይሄው ተቋም ከወራት በፊት የሀገሪቱ የ2012 ዓመታዊ የጥቅል ምርት እድገት 6.2 በመቶ እንደሚሆን ተንብዮ እንደነበር ይታወሳል፡፡

Via Sheger Times
@YeneTube @FikerAssefa
የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ለኮሮናቫይረስ (ኮቪድ-19) መከላከያና ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የ10 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ።ተቋሙ ዛሬ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል ሰባት ሚሊዮን ብር ሲለግስ፤ ለግድቡ ግንባታ ማስፈፀሚያ እንዲውል 3 ሚሊዮን ብር ሰጥቷል።

Via ENA
@YeneTube @FikerAssefa
በአማራ ክልል የትንሳኤ በአል የእንስሳት ግብይት በከተሞች መግቢያና መውጫ በሮች እንዲካሄድ ተወሰነ!

በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የትንሳኤ በዓል የእንስሳት ግብይት በከተሞች መግቢያና መውጫ በሮች ላይ እንዲካሄድ መወሰኑን የአማራ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ አስታወቀ። ቢሮው ለትንሳኤ በአል የእንስሳት ግብይት የሚካሄድበትን ቦታና ህብረተሰቡ ማድረግ ያለበትን ጥንቃቄ አስመልክቶ ዛሬ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥቷል።የቢሮው ምክትል ሃላፊ አቶ ተዋቸው ወርቁ በሰጡት መግለጫ በክልሉ የሚገኙ የገበያ ቦታዎች የተጨናነቁ በመሆናቸው ለኮሮና ቫይረስ ስርጭት እንዳያጋልጡ ጥንቃቄ ተደርጓል።

Via ENA
@YeneTube @FikerAssefa
ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ አለመለቀቃቸው ተገለጸ

ለሦስት ሳምንታት በእስር ላይ የነበሩት ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ በፍርድ ቤት የዋስ መብታቸው ተከብሮላቸው እንዲለቀቁ የተወሰነ ቢሆንም አለመለቀቃቸውን ቤተሰቦቻቸው ለአዲስ ማለዳ አስታወቁ። ያየሰው ዛሬ ሚያዚያ 7/2012 በዋለው ችሉት በ25 ሽሕ ብር ዋስ እንዲፈቱ እና ዛሬ ከቀኑ 8 ሰዓት ላይ ከእስር ቤት እንደሚወጡ ጠበቃቸው ለአዲስ ማለዳ ማስታወቃቸው የሚታወስ ነው። ይሁን እንጂ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ ያየሰው እንዳልተፈቱ ቅርብ ቤተሰቦቻቸው አስታውቀዋል።

Via:- Addis Maleda
@Yenetube @Fikerassefa
ጅቡቲ ዛሬ 72፣ ኬንያ ደሞ 9 በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎችን እንዳገኙ የሀገራቱ ዜና ምንጮች ዘግበዋል፡፡ የጅቡቲ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 435 ሲደርሱ፣ የኬንያ ደሞ 225 ሆኗል፡፡

@Yenetube @Fikerassefa
ታንዛኒያ በ24 ሰዐት ውስጥ 29 አዲስ ኬዝ ተመዝግቧል ዛሬ ኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሁሉም ታዛናዊያን ናቸው። በአጠቃላይ በታንዛኒያ 88 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
ከኬኒያ ገብተው በዲላ ዩኒቨርስቲ የለይቶ ማቆያ ማዕከል ለ14 ቀናት የቆዩ 215 ዜጎች፣ የኮረና ቫይረስ ምልክት ባለማሳየታቸው ማሰናበቱን ዩኒቨርስቲው አስታውቋል። በለይቶ ማቆያ ማዕከሉ በአሁኑ ጊዜ 223 ሰዎች ይገኛሉ።

@Yenetube @Fikerassefa
ፈረንሳይ በቅርቡ የሞቱና እስካሁን ያልተቆጠሩ ሰዎችን ጨምሮ 1438 ሞት በ24 ሰዓት ውስጥ ሪፖርት አድርጋለች። ይህንንም ተከትሎ የሟቾች ቁጥር 17,000 አልፏል።

@YeneTube @FikerAssefa
ግብፅ ባለፈው 24 ሰዓት ውስጥ 155 አዲስ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂና 5 በበሽታው የሞቱ ሰዎችን ሪፖርት አድርጋለች። ይህንንም ተከትሎ በሀገሪቱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 2505 ሲደርስ 183 ሰዎች ደግሞ ሞተዋል።553 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል።

ምንጭ:Daily News Egypt
@YeneTube @FikerAssefa
እርማት ወስደናል!

የስራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን ኮሚሽነር
ዶ/ር ኤፍሬም ተክሌ በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት በአጠቃላይ በቀጣይ ሶስት ወራት 2 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ከስራ ገበታቸው ሊፈናቀሉ እንደሚችሉ #አዲስ_ማለዳን_ዋቢ አድርገን በገፃችን ላይ ያሰፈርነው መረጃ የተሳሳተ መሆኑ የስራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን የክቡር ኮሚሽነር ልዩ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ #ሙሉእመቤት_አሸብር በተላከልን መረጃ መሰረት ዜናው ከገፃችን ላይ አንስተናል።

@Yenetube @Fikerassefa
በሁሉም አቅጣጫ ከደቡብ አፍሪካ ጋር የምትዋሰነው ሌሶቶ አንድም የተረጋገጠ የኮሮና ቫይረስ ኬዝ ሳይመዘገብባት ለቅድመ ጥንቃቄ ስትል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጃለች። በተጨማሪም በሀገሪቱ ለአንድ ሳምንት የሚቆይ የእንቅስቃሴ እገዳ ተላልፏል።

ምንጭ:CGTN
@YeneTube @FikerAssefa
አፕል iPhone SE 2 የተባለ አዲስ ሞዴል አስተዋውቋል። ይህ ሞዴል ውጫዊ ገፅታው iPhone 8 የሚመስል ሲሆን ውስጣዊ ይዘቱ ከiPhone 11 ጋር ይመሳሰላል ተብሏል። መነሻ ዋጋውም በአንፃራዊነት ረከስ ያለ ሲሆን በአሜሪካ ገበያ $399 ፣በእንግሊዝ ደግሞ £419 ብቻ መሆኑን The Independent ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
ፖስኮ የተሰኘ እና መቀመጫውን በደቡብ ኮሪያ ያደረገ ብረታ ብረት ፋብሪካ በኢትዮጵያ ሥራ ለመጀመር የአዋጭነት ጥናት ሠርቶ ማጠናቀቁ ተገለጸ። ኩባንያው በኢትዮጵያ በሚጀምረው የብረታ ብረት ፋብሪካ ከዚህ ቀደም በብረታ ብረት ፋብሪካዎች ይሠራ የነበረውን የብረት ምርት ማምረቻ ግብዓት እዚሁ ማምረት ይጀምራል ተብሏል።

Via:- Addis Maleda
@Yebetube @Fikerassefa
ትራምፕ ቫይረሱ የከፋ ጉዳት ሊያስከትል የሚችልበትን ጊዜ አልፏል አሉ።

ትራምፕ ጨምረውም ቫይረሱ በቻይናዋ ዉሃን ከተማ ሳይሆን ከዉሃን ላብራቶሪ ነው የወጣው ስለሚባለው ያልተረጋገጠ ሪፖርት አሜሪካ ትመለከተዋለች ብለዋል።

Via:- BBC
@Yenetube @Fikerassefa
ዶ/ር ፅዮን ፍሬው በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከፍተኛ በሆነባት የአሜሪካዋ ኒው ዮርክ ነው የሚሰሩት።

ዶ/ር ፅዮን የኮሮናቫይረስ ይዟቸው እንዳገገሙ በትዊተር ገጻቸው ላይ አስታውቀዋል።

ስለ ኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ እንዲሁም ኢትዮጵያ በሽታውን ለመከላከል እየወሰደች ስላለችው እርምጃ ዶ/ር ፅዮንን BBC Amharic አናግሯቸዋል።

መስፈንጠርያውን በመንካት ሙሉውን ያንብቡ⬇️
https://bbc.in/3acI7WT
የብራዚሉ ፕሬዝዳንት "ከኮሮናቫይረስ ነፃ ነኝ "ያሉበትን የህክምና ማስረጃ እንዲያቀርቡ ተጠይቅዋል

"ባለፈው መጋቢት ወር ሁለቴ የኮሮኖቫይረስ ምርመራ አድርጌያለው ውጤቴም ከቫይረሱ ነፃ መሆኔን " ነው ያሳየው ያሉት የብራዚሉ ፕሬዝዳንት ጃየር ቦልሶናሮ ማስረጃቸውን ለህዝብ በ30 ቀን ውስጥ ይፋ እንዲያደርጉ በሀገሪቱ ኮንግረስ ተጠይቀዋል። ቦልሶናሮ አስከ አሁን በጉዳዩ ላይ ዝምታን መምረጣቸው ቫይረሱ ይኖርባቸው ወይ ይሆን? የሚል ግምት በብዙ ብራዚሊውያን ዘንድ ጭሯል ሲል ዘ ጋርዲያን ጋዜጣ ዘግቧል።

Via:- Tesfay Getnet
@Yenetube @Fikerassefa