YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.86K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
መከላከያ ሰራዊት የግንዘቤ ማስጨበጫ በራሪ ወረቀቶችን በሄሊኮፕተር ሊበትን ነው!

የሀገር መከላከያ ሰራዊት በነገው እለት በአዲስ አበባ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት የሚያግዙ መልዕክቶችን የያዙ በራሪ ወረቀቶችን በሄሊኮፕተር እንደሚበትን አስታውቋል፡፡በተጨማሪም በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች በመንቀሳቀስ በማርሽ ባንድ የታጀበ የማንቂያ ቅስቀሳ እንደሚያደርግም ተጠቁሟል፡፡የከተማዋ ነዋሪም ነገ በሚኖረው ሁነት ሳይደናገጥ ከሄሊኮፕተር የሚበተኑ በራሪ ወረቀቶችን በማንበብ ወደ በተግባር እንዲያውልም ተጠይቋል፡፡

Via Walta
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ቁጥር 25 ደርሷል።

አዲስ በቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች የ30ና የ37 አመት ግለሰቦች ሲሆኑ ሁለቱም በተመሳሳይ በረራ ከዱባይ የገቡ መሆናቸውን የጤና ሚኒስቴር አሳውቋል ።

ሶስተኛው የ60 አመት የአዲስ አበባ ነዋሪ ሲሆኑ መጋቢት 6 ነው ከፈረንሳይ የገቡት።

@YeneTube @FikerAssefa
በድሬዳዋ አስተዳደር የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመቆጣጠር የተቋቋመው ግብረኃይል ዛሬ ተጨማሪ ውሳኔዎችን አስተላልፏል::

ከነገ መጋቢት 23/2012 ጀምሮ ተግባራዊ እንዲሆኑ የተላለፉ ውሳኔዎች:-

1- ወደ ድሬዳዋ ከተማ የሚገቡም ሆነ የሚወጡ ከፍተኛ እና መለስተኛ ሀገር አቋራጭ የህዝብ ትራንስፓርት አገልግሎት ዝግ ሆኗል::

2- ማንኛውም አይነት የድሬዳዋ ከተማ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ከባጃጅ እስከ ሚኒባስ ላልተወሰነ ጊዜ ምንም አይነት አገልግሎት መስጠት እንዲያቆሙ::

3- በየትኛውም አቅጣጫ የሚገኙ የድሬዳዋ መግቢያ በሮች ከነገ ጀምሮ ከእንቅስቃሴ ዝግ ተደርገዋል::

4- የእለት ተእለት መሰረታዊ ፍጆታ እቃዎችን መሰረት ያደረጉ የግብይት ስፍራዎችን ሳይጨምር እንደ ታይዋን አሸዋ እና ሌሎችም የገበያ ቦታዎች ከነገ ጀምሮ ዝግ እንዲሆኑ ተወስኗል::

5- ከፍተኛ የሰው ኃይል ያላቸው ፋብሪካዎች እረፍት በመስጠት እና በሽፍት በማሰራት የሰው ኃይል ቁጥር እንዲቀንሱ ተወስኗል::

መግለጫ:- በጅቡቲ መስመር እና በሌሎች መግቢያዎች የሚገቡ የተለያዩ ለሀገር ጠቃሚ የሆኑ ነዳጅ እና እህልን ጨምሮ ሌሎች የሎጂስቲክ እንቅስቃሴዎችን ይህ ክልከላ አይመለከትም::

በመጨረሻም ግብረኃይሉ በመልእክቱ ከላይ የተዘርዘሩትን ውሳኔዎች መላው የድሬዳዋ ህብረተሰብ እና የፀጥታ አካላት ተግባራዊ እንዲሆን በማድረግ የኮሮና ቫይረስን በመከላከል ሂደት የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ አሳስቧል::

ምንጭ: ድሬ ማስሚዲያ
@YeneTube @FikerAssefa
በዓለም የጤና ድርጅት አማካኝነት የተሰጡ የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19)ን የሚመለከቱ የምክር ሀሳቦች ፦

➡️ የኮቪድ-19 ቫይረስ ሞቃታማ እና እርጥበት የአየር ጠባይ ባለባቸው አካባቢዎችም ሊተላለፍ ይችላል

➡️ በረዶዋማ እና ቀዝቃዛማ የአየር ጠባይ አዲሱን የኮሮና ቫይረስ ሊያጠፋ አይችልም። ውጫዊው የአየር ሁኔታ ምንም ይሁን ምን መደበኛው የሰውነታችን የሙቀት መጠን ከ 36.5 °C እስከ 37 °C ያህል ሆኖ ይቆያል ፡፡

➡️ ሙቅ በሆነ ውኃ ገንዳ ውስጥ መዘፍዘፍም ከኮሮና ቫይረስ አይከላከልም። ይልቁንስ የሚመከረው ቶሎ ቶሎ እጅን በሳሙና እና ውኃ በደንብ መታጠብን ነው።

➡️ አዲሱ የኮሮና ቫይረስ በወባ ትንኝ ወይም ቢንቢ አማካኝነት ከአንድ ሰው ወደ ሌላኛው አይተላለፍም። በሽታው የሚተላለፈው በበሽታው የተያዘ ሰው በሚስል ወይም በሚያስነጥስበት አልያም ከአፉ እና ከአፍንጫው በሚወጡ እንደ ምራቅ የመሳሰሉ ፈሳሾች ነው።

➡️ የሰውነት ሙቀት መለኪያ መሣሪያዎች አንድ ሰው መደበኛ የሰውነት ሙቀቱ ከፍ ብሎ እንደው ለመለካት አገልግሎት ላይ ሊውሉ ይችላሉ። ይሁንና መሣሪያው በበሽታ የተያዘውን ሰው ለይቶ ማወቅ አይችልም። ምክንያቱም በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች የትኩሳት ምልዕክት እስኪያሳዩ ከ 2 እስከ 10 ቀናት ሊወስድ ይችላል።

➡️ አልኮል ወይም ክሎሪን መላ ሰውነትን በመቀባት ሰውነት ውስጥ ዘልቆ የገባ ቫይረስን ለመከላከል አይረዳም። እንደዚህ አይነት ነገሮችን ሲጠቀሙ ደግሞ ዓይን እና አፍ ውስጥ እንዳይገቡ መጠንቀቅ ያስፈልጋል። ይሁንና አልኮል እና ክሎሪን ብዙ ሰዎች የሚነኳቸውን ወለሎች ለማፅዳት አገልግሎት ላይ ሊውሉ ይችላሉ።

➡️ የጉንፋን ወይም ሌሎች የመከላከያ ክትባቶች ከዚህኛው ቫይረስ ሊከላከሉ አይችሉም። ይህ ቫይረስ አዲስ እና ከሌሎች የተለየ ስለሆነ የራሱ ክትባት ያስፈልገዋል።

➡️ ጨዋማ የአፍንጫ ስፕሬ በመጠቀም የኮሮና ቫይረስን መከላከል አይቻልም። ይሁንና አልፎ አልፎ ይህንን የተጠቀሙ እና ጉንፋን የያዛቸው ሰዎች በቶሎ ሲሻላቸው ተስተውሏል።

➡️ ነጭ ሽንኩርት አንዳንድ ፀረ-ተሕዋስያን ሊኖረው የሚችል ጤናማ ምግብ ነው። ሆኖም ነጭ ሽንኩርት መብላት ሰዎችን ከአዲሱ የኮሮና ቫይረስ እንደሚከላከል የተረጋገጠ መረጃ የለም።

➡️ በየትኛውም የዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ሰዎች በአዲሱ የኮሮና ቫይረስ ሊጠቁ ይችላሉ። አዛውንቶች እና ቀደም ሲል እንደ አስም ፣ የስኳር በሽታ ፣ የልብ ህመም ያላቸው ሰዎች በቫይረሱ የበለጠ ተጋላጭ ሲሆኑ ይስተዋላል ፡፡

➡️ አንቲባዮቲክስ መውሰድ ኮሮናን አይከላከልም። አንቲባዮቲክስ የሚወሰደው ባክቴሪያን ለመከላከል እንጂ ቫይረንስ ለመከላከል አይረዳም። ይሁንና በኮቪድ 19 የተያዙ ሰዎች ተያያዥ የባክቴሪያ በሽታዎች ገጥሟቸው ከሆነ አንቲባዮቲክስ እንዲወስዱ ሊደረግ ይችላል።

#Share
Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ሁሉም የሙስሊም ማህበረሰብ ቤቱ ውስጥ የመስገድ ግድታ ኃይማኖታዊ ብያኔን በዛሬው እለት ሰጠ።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በኢትዮጵያ በተከሰተው የኮሮናቫይረስ (ኮቪድ-19) ስርጭትን አስመልክቶ በዛሬው እለት መግለጫ ሰጥቷል።

ምክር ቤቱ በመግለጫው፥ ስርጭቱ እየጨመረ የመጣውን የኮሮናቫይረስ (ኮቪድ-19) ለመግታት ከዚህ ቀደም ካሳለፋቸው ውሳኔዎች በተጨማሪ ሌላ ኃይማኖታዊ ብያኔ (ፈትዋ) መስጠቱን አስታውቋል።

በዚህም መሰረት፦

1. በበሽታው የተያዙ እና በዕድሜ የገፉት ብቻ ሳይሆን ሁሉም የሙስሊሙ ማህበረሰብ አባላት እቤታቸው ውስጥ መስገድ ግዴታ ነው፤

2. የጤና ተቋማት እና ጉዳዩ የሚመለከታቸው ወገኖች የሚያወጧቸውን መመሪያዎች እና የሚሰጧቸውን ጥንቃቄና መከላከያ አቅጣጫዎች መቀበልና ስራ ላይ ማዋል ኃይማኖታዊ ግዴታ ነው ፤

3. በሽታው (ወረርሽኙ) ዛሬ ከተደረሰበት ደረጃ እና ስርጭቱ መንገድ ፍጥነት ከአስቸጋሪነቱ እና ከጉዳቱ አንፃር የጁምአና የጀመአ ሰላትን ለማስቆም የሚያስገድድ ሸሪአዊ ምክንያት በመሆኑ ፈትዋ ከተሰጠበት ከዛሬ መጋቢት 22 ጀምሮ በሽታው በሰው ልጅ ላይ የሚያደርሰው ጉዳት መቆሙ በጤና ባለሙያዎች እስከሚረጋገጥ ጊዜ ድረስ የጁምዓ ሰላትና የጀምአ ሰላት ታግዶ እንዲቆም የዑለማ ምክር ቤት ወስኗል።

4. በአምስቱም ወቅት ሶላት ሙኢዝኖች አዛን ያደርጋሉ፤ በአብዛኛው ሰው ወደ መስጂድ እንዲሄድ ሳይህን በየቤቱ እንዲሰግድ በማለት መናገር እንዳለባቸውም ተወስኗል።

5. በገጠርም ሆነ በከተማ በስብሰባ መልክ ኃይማኖታዊ ትምህርት መስጠት የበሽታውን ስርጭት ስለሚያባብስና ለህመምና ለሞት ምክንያት ስለሚሆን በሽታውን አላህ እስከሚያነሳው ድረስ የመማር ማስተማር ስራው እንዲቋረጥና እንዶቆም የዑለማ ምክር ቤት ወስኗል።

6. በህክምና ረገድ በሽታው የሚሰራጨው በእጅ ንክኪ ስለተረጋገጠ የበሽታውን ስርጭት ዛሬ በደረሰበት ደረጃ በእጅ በመጨባበጥ ሰላምታ መለዋወጥ የተከለከለ መሆኑንም ምክር ቤቱ አስታውቋል።

ምክር ቤቱ በመግለጫው፥ “በመስጂድ የሚከናወን ማናቸውም የጁመአ እና የጀመአ ሶላት የቂራትም፣ የዘኪር ስብሰባ እንዲቆም የተወሰነበት ሸሪዓዊ መሰረት ከነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ከሶሃቦች የተሰሙት ሐዲሶችና ነፍንስ ወይም ህይወትን የመጠበቅ ከሸሪዓዊ ተልእኮዎች አንዱና ዋንኛው ምክንያት በመሆኑ ነው” ሲልም ገልጿል።

Via:- FBC
@Yenetube @Fikerassefa
በስፔን በሃያ አራት ሰዓታት ውስጥ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት 849 ሰዎች መሞታቸው ተገለጸ።

#BBC
@YeneTube @FikerAssefa
የሀረሪ ክልል ጠቅላይ አቃቢ ህግ ለ133 የህግ ታራሚዎች ምህረት አደረገ፡፡

በአለም አቀፍ ደረጃ የተከሰተውን ኮሮና ቫይረስ በሽታን አስቀድሞ ከመከላከልና ጉዳቱን ለመቀነስ በተለያዩ የሕግ ከለላ ስር ለሚገኙ 133 የሕግ ታራሚዎች ምህረት መደረጉን የክልሉ ጠቅላይ አቃቢ ህግ ገልጿል፡፡የክልሉ ጠቅላይ አቃቢ ህግ አቶ አዩብ አህመድ እንደገለጹት ኮሮና ቫይረስ በአለም ደረጃ አሳሳቢና ከፍተኛ የሕዝብ እልቂት እያስከተለ የሚገኝ በሽታ በመሆኑ መንግስት በሃገርም ሆነ በክልል ደረጃ በሽታውን ከመከላከል አንጻር የተለያዩ ውሳኔዎችን እያሳለፈ ይገኛል ብለዋል፡፡

ምንጭ: የክልሉ መ/ ኮምኒኬሽን
@YeneTube @FikerAssefa
የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከፍተኛ አመራሮች ለኮሮና ቫይረስ መከላከል ስራ እንዲውል የአንድ ወር ደሞዛቸውን ለገሱ፡፡

የምክር ቤቱ አፈ-ጉባኤ፣ ምክትል አፈ-ጉባኤ እንዲሁም አራቱ የመንግስት ረዳት ተጠሪ ሚኒስትር ዴኤታዎች በአገሪቱ የተከሰተውን የኮሮና ቫይረስ/ ኮቪድ-19/ ስርጭትን ለመከላከል ለሚደረገው ስራ አንዲውል ሙሉ የአንድ ወር ደሞዛቸውን ለግሰዋል፡

Via Reporter
@YeneTube @FikerAssefa
በዛሬው እለት ወደ 12 የሚጠጉ የግል እና የመንግስት ተቋማት ከ47 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ማድረጋቸው ተገልጿል።

በዚሁ መሰረት፦
➡️ሜድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ 20 ሚሊየን ብር
➡️ዳሽን ባንክ 10 ሚሊየን ብር
የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን 10 ሚሊየን ብር
➡️ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ 5 ሚሊየን ብር
➡️አዋሽ ኢንሹራንስ 3 ሚሊየን ብር
ዓባይ ባንክ 3 ሚሊየን ብር
➡️ደቡብ ግሎባል ባንክ 2 ሚሊየን ብር
➡️ሆራ ትሬዲንድ 2 ሚሊየን ብር
➡️ትራኮን ትሬዲንግ 1 ሚሊየን ብር
➡️ሳንታማሪታ 1 ሚሊየን ብር
➡️ኢየሩሳሌም መታሰቢያ ድርጅት 200 ሺህ ብር
➡️ቲ ኬ ፒ.ኤል.ሲ 50 ሺህ ብር ድጋፍ አድርገዋል።

የድጋፍ ማሰባሰብ መርሃ ግብር በጥሬ ገንዝብ እና በቁሳቁሶች የሚደረጉ ድጋፎች ተጠነባክረው ቀጥለዋል፡፡

Via Ministry of Health
@YeneTube @FikerAssefa
በባህርዳር፣ እንጅባራ፣ አዲስ ቅዳም እና ቲሊሊ የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል የእንቅስቃሴ እገዳ ተጣለ!

በባህርዳር፣ እንጅባራ፣ አዲስ ቅዳም እና ቲሊሊ ከነገ መጋቢት 23 ከቀኑ ስድስት ሰአት ጀምሮ የተሽከርካሪም ሆነ የህዝብ እንቅስቃሴ እንዳይደረግ የአማራ ክልል የኮሮና ቫይረስ መከላከል ኮማንድ ፖስት ውሳኔ አስተላለፈ።የአማራ ክልል መንግስት ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ፅፈት ቤት ሀላፊ አቶ ጌትነት ይርሳው ወረርሹኙን ለመከላከል የተላለፉ አዳዲስ ውሳኔወችን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል።

በክልሉ በባህርዳርና በአዲስ ቅዳም ቫይረሱ ከተገኘባቸው ግለሰቦች ጋር ንክኪ አላቸው ተብሎ የሚጠረጠሩ ግለሰቦችን ወደ ለይቶ ማቆያ ለማስገባት እየተሰራ መሆኑን አቶ ጌትነት ይርሳው ገልፀዋል።በቀጣይም እንደ ሁኔታው እየታየ በሌሎችም ከተሞች የእንቅስቃሴ እገዳ ሊጣል እንደሚችል አስታውቀዋል። እገዳውን ለማስፈፀም የፀጥታ ሀይሉ ሀላፊነት እንደተሰጠውም ገልፀዋል። በክልሉ የፈሳሽና ደረቅ ጭነት ትራንስፖርት እንደቀጠለ መሆኑን ጠቁመዋል።

ምንጭ:ኢቲቪ
@YeneTube @FikerAssefa
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ኮቪድ19ን በተመለከተ የሰጡት መግለጫ።

#PMOEthiopia
ቪዲዮ 20.6mb ነው።
@YeneTube @FikerAssefa
በፒያሳ አትክልት ተራ የሚስተዋለውን ርቀትን ያለመጠበቅ ውስንነት የማስተካከል እና አካባቢውን የማፅዳት ስራ መሰራቱን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

የሚደረገው ግብይት ርቀትን የጠበቀ አለመሆኑ ያሳሰባቸው የመንግስት አካላት በተለያዮ ጊዜያት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን እየሰሩ ይገኛሉ፡፡ መጋቢት 22 ቀን 2012 ዓ/ም የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽንና በየደረጃው የሚገኙ የአስተዳደር አካላት በመቀናጀት አካባቢው በኬሚካል እንዲታጠብ ከማድረጋቸው ባሻገር ግብይቱ እርቀትን የጠበቀ እንዲሆን የመንገድ ላይ ንግድ እንዲቆም ማድረጋቸውን የአራዳ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የወንጀል መከላከልና የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት ኃላፊ ኮማንደር ጉማታ ውገዳሙ አስታውቀዋል፡፡

Via Addis Ababa Police Commission
@YeneTube @FikerAssefa
በሰባራ ባቡር አልኮል መሸጫ አትራፊዎችን ለመከላከል የገዢዎች ጣት ኮፒ ሲቀባ ታይቷል!

ከኮሮና ቫይረስ ስጋት ጋር ተያይዞ ባለፉት 15 ቀናት በቀን ቢያንሰ 2,000 ሰው ሲያስተናግድ የነበረው ሰባራ ባቡር የሚገኘው ባለ ዛፍ የአልኮልና መጠጥ ፍብሪካ አትርፎ ሻጮች ሲያስቸግሩት በእያንዳንዱ ገዢ ላይ እጅ አውራ ጣት ላይ ኮፒ ሲቀባ ታይቷል።

ይሄ ለምን ሆነ? በማለት fidelpost.com የፋብሪካውን አንዲት የሽያጭ ሰራተኛ ጠይቀን ” አትርፎ ሻጮች ሰሞኑን ከበውን ነበር። 70 ብር የሚሸጠውን አልኮል ከእኛ ይገዙና መልሰው አጠገባችን 300 ብር ድረስ ይሸጡታል። እኛም አልኮሉ ለሰው እንዲዳረስ በማሰብ አንዴ የገዙ ሰዎች ደግሞ ተሰልፎ እንዳይገዙ የእጃቸውን አውራ ጣትን ኮፒ በመቀባት ደግመው ቢመጡ ቶሎ የመለየት ዘዴን ምርጫ ስንመርጥ እንደሚደረገው ላለፉት አራት ቀናት ተጠቅመንበት ነበር ።
” ሆኖም ግን አንዳንድ ሰዎች የተቀቡትን ኮፒ በኬሜካል በማስለቀቅ ደግመው ለመግዛት ሲሞክሩ አስተውለናል።” “ለአሁኑ መሸጥ አቁመናል ።አልኮላችን በሁሉም ክፍለ ከተማ ላይ ባሉ በሸማቾች ማህበር በኩል እንዲሸጥ ተስማምተናል ” ስትል ነግራናለች ብሏል።

Via fidelpost.com
@YeneTube @FikerAssefa
የሀዋሳ ኢንዱስትሪያል ፓርክ 14 000 ሰራተኞቹን ከዛሬ ጀምሮ በጊዚያዊነት ከስራ ማሰናበቱን አስታወቀ።

የፓርኩ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ፍጹም ከተማ ዛሬ ለዶቼ ቬለ ( DW ) አንዳሰታወቁት ሰራተኞቹ ከስራ የተሰናበቱት ቀደምሲል በአሜሪካና በአውሮፓ ገበያዎች የምርቶቹ ዋነኛ ተቀባይ የነበሩት ድርጅቶች በኮሮና ተህዋሲ ወረርሽኝ ምክንያት የገበያ ፍላጎታቸው እየተቀዛቀዘ በመምጣቱ ነው።

ተጨማሪ👇👇👇
https://telegra.ph/Hawasa-Industry-Park-03-31
ሼህ ሁሴን አሊ አላሙዲ የኮሮና ወረርሽኝን ስርጭት ለመግታት የ120 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረጉ!

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ስርጭት ለመግታት የተለያዩ ተቋማት እና ግለሰቦች ድጋፋቸውን ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እያደረጉ ነው። በዚህም ሼህ ሁሴን አሊ አላሙዲ የ120 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ለከተማ አስተዳደሩ አድርገዋል።

ምንጭ: ኢቲቪ
@YeneTube @FikerAssefa
ለህክምና ባለሙያዎች በነዳጅ ማደያዎች ቅድሚያ እንዲሰጣቸው መወሰኑን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚንስትር አቶ መላኩ አለበል አሳውቀዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለአማራ፣ ደቡብ እና ኦሮሚያ ክልሎች ለእያንዳንዳቸው 15 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ ድጋፍ እንደሚያደርግ የከተማው ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ አስታውቀዋል።

የከተማ አስተዳደሩ ለክልሎቹ የሚያደርገው 45 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ ድጋፍ ከከተማው በጀት ላይ የሚበረከት እንደሆነም ተገልጿል።
የከተማ አስተዳደሩ የኮሮናን ወረርሽኝን አስመልክቶ የሚደረጉ ድጋፎችን ለመረከብ የሚሆኑ አምስት ቦታዎችን እንዳዘጋጀም አስታውቋል።

ድጋፍ ለማድረግ የሚፈልጉ ወገኖች እና ተቋማት በኤግዚቢሽን ማእከል እና በሀገር ፍቅር ቲአትር ቤት በመገኘት ድጋፋቸውን ለመለገስ እንደሚችሉም የከተማ አስተዳደሩ አስታውቋል።

Via ETV
@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ የቤንዚን እጥረት ያጋጠመው በኮሮናቫይረስ ምክንያት ሱዳን ድንበሯን በመዝጋቷ መሆኑን የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ገልጿል።

የቤንዚን እጥረቱን አስመልክቶ የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ታደሰ ኃይለማርያምን ኢዜአ በስልክ አነጋግሯል፡፡ኢትዮጵያ ነዳጅ የምታስገባባቸው አገሮቹ በኮሮናቫይረስ ሳቢያ በድንበር አካባቢ የትራንስፓርት እንቅስቃሴ ዝግ በማድረጋቸው እጥረቱ መከሰቱን ገልፀዋል፡፡

ከአዲስ አበባ ከተማ የቤንዚን ፍጆታ 50 በመቶ የሚሆነው የሚገባው ከሱዳን መሆኑ ይነገራል።በዚህም ካርቱም ያለው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከሱዳን መንግስት ጋር ዲፕሎማሲያዊ ውይይት አድርጓል። በተደረገው ውይይትም 15 የሚሆኑ የቤንዚን ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ወደ ሱዳን ለመግባት መተማ አካባቢ መድረሳቸውን የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ታደሰ ኃይለማርያም ገልጸዋል።

ጅቡቲ በአሁኑ ወቅት በቫይረሱ ምክንያት ድንበሯን ብትዘጋም ኢትዮጵያ በጅቡቲ በኩል ነዳጅ በልዩ ሁኔታ እንድታስገባ እየተደረገ መሆኑን ዋና ሥራ አስፈጻሚው ተናግረዋል።ሆኖም በጅቡቲ በኩል የሚገባው ቤንዚን አገሪቱ የሚያስፈልጋትን ፍጆታ ማሟላት እንደማይችል አስረድተዋል።እንደ ዋና ሥራ አስፈፃሚው ገለፃ ከሆነ አሁን የተፈጠረው ጊዜያዊ የቤንዚን እጥረት በሚቀጥለው ሳምንት ሙሉ ለሙሉ ይወገዳል።

ምንጭ: ኢዜአ
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ የጀርመን እና የካናዳ ኤምባሲዎች ወደ የአገራቸው መመለስ የሚሹ የአገሮቻቸው ዜጎች በአፋጣኝ የጉዞ ቲኬት እንዲቆርጡ አስጠነቀቁ። የካናዳ ኤምባሲ በረራዎች ቀንሰዋል ዋጋ እየጨመረ ነው ብሏል።በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደር ብሪታ ቫግነር በበኩላቸው እስከ መቼ ይኼ ዕድል ሊኖር እንደሚችል አይታወቅም ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

Via Eshete Bekele
@YeneTube @FikerAssefa
በአዳማ ከተማ የኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ከተገኘበት ግለሰብ ጋር ንክኪ ነበራቸው ተብለው ከተጠረጠሩት ውስጥ 29 ሰዎች ከቫይረሱ ነፃ እንደሆኑ መረጋገጡን የከተማዋ አስተዳደር ጤና መምሪያ አስታውቋል።

Via Tesfaye Getinet
@YeneTube @FikerAssefa