YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.87K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚንስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁ ወደ ለይቶ ማቆያ ሊገቡ መሆኑ ተዘገበ።

አንድ የእስራኤል ጋዜጣ እንደዘገበው ከሆነ የጠቅላይ ሚንስትር ኔታኒያሁ አማካሪ የሆኑ ግለሰብ በኮቪድ-19 መያዛቸው መረጋገጡን ተከትሎ ጠቅላይ ሚንስትሩ ወደ ለይቶ ማቆያ ይገባሉ ተብሏል።

የጠቅላይ ሚንስትሩ ጽ/ቤት እንደዘገበው ኔታኒያሁን ጨምሮ ከሌሎች ቅርብ አማካሪዎቻቸው ጋር ወደ ለይቶ ማቆያ እንዲገቡ ይደረጋል።

-BBC
@Yenetube @Fikerassefa
ኮቪድ-19 ቀድሞ ከተስፋፋባቸው ሀገራት አንዷ ደቡብ ኮሪያ የነበረች ቢሆንም በአጭር ጊዜ ውስጥ የቫይረሱን ስርጭት በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ ችላለች።ጠ/ሚር አብይ ከዚህችው ሀገር መሪ ጋር በስልክ እንደተወያዩ ጠቅሰው በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው "የኮሪያ ሪፐብሊክ የ#ኮቪድ19ን ሥርጭት እንዴት በቁርጠኝነት መግታት እንደሚቻል አርአያ ናት። ከፕሬዚደንት ሙን ጄኢን ጋር እንዴት ውጤታማ እንደሆኑ፣ #ኢትዮጵያ ተሞክሯቸውን በምን መንገድ ልትጠቀምበት እንደምትችል እንዲሁም ሀገራቸው አስፈላጊዎቹን የሕክምና መገልገያዎች በመለገስ ድጋፍ በምታደርግበት ሁኔታ ላይ ተነጋግረናል።" ብለዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
አሜሪካ የፀረ ወባ መድሃኒት ለኮሮና ቫይረስ ህክምና እንዲውል ፈቃድ ሰጠች።

የአሜሪካ መንግስት እንዳስታወቀዉ ሁለት የፀረ ወባ መድሃኒቶችን ለኮቪድ 19 መፈወሻ ይዉል ዘንድ የአገሪቱ የምግብ እና የመድሃኒት አስተዳደር ፍቃድ እንደሰጠዉ ታዉቋል፡፡የአሜሪካዉ የጤና እና የሰዉ ሃይል ዲፓርትመንት ባወጣዉ መግለጫ እንዳስታወቀዉ ክሎሮኪን እና ሃይድሮክሲክሎሮኪን የተሰኙት የጸረ ወባ መድሃኒቶች ለኮቪድ 19ን እንደሚፈዉሱ ተረጋግጧል ብሏል፡፡

ባለስልጣኑ እንዳለዉ ሁለቱ የመድሃኒት አይነቶች በህክምና ባለሙያዎች ለህመምተኞች እንዲታዘዙ እና በተለያዩ ሆስፒታሎች እንዲሰራጩ እየተደረገ ይገኛል ነዉ ያለዉ፡፡ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ባለፈዉ ሳምንት እነዚህን ሁለት መድሃኒቶች ከፈጣሪ የተሰጡን ሲሉ መግለፃቸዉን ፍራንስ 24 ዘግቧል፡፡

በርካታ ተመራማሪዎች እና የዘርፉ ኤክስፐርቶች ግን በመድሃኒቶች ላይ ተጨማሪ ምርመራ እስኪደረግ ድረስ ዜጎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስበዋል፡፡ይህንንም ተከትሎ የአገሪቱ የምርምር ማእከላት በመድሃኒቶቹ ላይ ምርመራ እያደረጉ እንደሚገኙ ዘገባዉ አስታዉቋል፡፡በአሁኑ ወቅት አሜሪካ ከ140 ሺ በላይ ዜጎቿ በኮሮና ቫይረስ የተያዙባት ሲሆን ከ2 ሺኅ 500 የሚሆኑት ደግሞ ህይወታቸዉ አልፏል፡፡

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
በተያያዘ ዜና፣ የማሳቹሴትስ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የኬሚስትሪ ልሂቃን በላብራቶሪ የቀመሩት ፔፕታይድ የተባለ ንጥረነገር ከCovid-19 ጋር የመጣበቅ አቅም ስላለው ወደ ሰው ልጅ ህዋሳት ዘልቆ እንዳይገባ መከላከል እንደሚችል ደርሰንበታል ብለዋል።

ሙሉውን ጽሑፍ ማስፈንጠሪያውን ከፍተው ያንብቡ👇👇

http://news.mit.edu/2020/peptide-drug-block-covid-19-cells-0327
የሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ 13 ሺሕ ሰራተኞች ደመወዝ ተከፍሏቸው ላልተወሰነ ጊዜ ስራ እንዲያቆሙ መወሰኑን አስተዳደሩ አስታወቀ። ከ30 ሺሕ በላይ ትራንስፖርት የሚጠቀሙ ሰራተኞች አሉት ተብሏል። ወደ ሐዋሳ ከተማ የሚደረጉ የህዝብ ማጓጓዣዎች ተቋርጠዋል።

Via Eshete Bekele
@YeneTube @FikerAssefa
የምግብና ምግብ ነክ ሸቀጦች እጥረት እንዳይኖር በቂ ዝግጅት ተደርጓል - ኮሚሽኑ

ከኮሮና ቫይረስ ስጋት ጋር ተያይዞ ሊያጋጥም የሚችል የምግብና ምግብ ነክ ሸቀጦች እጥረት እንዳይኖር በቂ ዝግጅት መደረጉን የአደጋ ስጋትና ስራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ፡፡የኮሚሽኑ የሥትራቴጂ የምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ ክምችት አስተዳደር ዳይሬክትር ዓለምሸት ከበደ ኮሚሽኑ በሚያስተዳድራቸው ስምንት የክምችት መጋዘኖች ውስጥ ከ182ሺህ ሜትሪክ ቶን በላይ እህል ክምችት ላይ እንዳለ ገልጸው፣ ከ244ሺህ ሜትሪክ ቶን በላይ እህል ከጅቡቲ ወደ ኢትዮጵያ በመጓጓዝ ላይ እንዳለ ተናግረዋል፡፡

በአገሪቱ አስጊ ሁኔታ ቢፈጠር እንኳን ዜጎችን መመገብ የሚያስችል በቂ የእህል ክምችት መኖሩንና ተጨማሪ ግብዓቶችንም እያሰባሰበ መሆኑን ነው ኮሚሽኑ ለዋልታ የገለፀው፡፡አሁን በመጋዘኖች ውስጥ ያለው እህል ክምችት አስቸጋሪ ሁኔታ ቢፈጥር እንኳን ከስድስት ወራት በላይ ዜጎችን መመገብ የሚያስችል መሆኑን ገልጸው ተጨማሪ አማራጭ ምግቦችን ለመግዛት ኮሚሽኑ በሂደት ላይ እንዳለ አቶ ዓለምሸት ተናግረዋል፡፡

የእህል እጥረት ያጋጥማል እያሉ ዋጋ የሚጨምሩ ግለሰቦችን ህብረተሰቡ ሳይሰማ ተረጋግቶ ትኩረቱን የቫይረሱን ስርጭት መከላከል ላይ እንዲያደርግም ኮሚሽኑ አሳስቧል፡፡

Via Walta
@YeneTube @FikerAssefa
በአማራ ክልል በኮሮና ወረርሽኝ ተጋላጭ መሆናቸው ከተረጋገጡት ሁለት ግለሰቦች ጋር ቅርርብ የነበራቸው 24 ሰዎች ወደ ለይቶ የሕክምና ክትትል ማድረጊያ እንዲገቡ መደረጉን የአማራ ክልል ጤና ቢሮ አስታወቀ።የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ መልካሙ (ዶክተር) በሽታው መከሰቱ ከታወቀበት ጀምሮ የመሽታው ምልክት የታየባቸው 27 ተጠርጣሪዎች ክትትል ሲደረግላቸው እንደነበር አስታውቀዋል።

የተሰጠው መግለጫ👇👇👇
https://telegra.ph/Covid-19-Amhara-03-30
በኮሮና ከተያዙት ኢትዮጵያውያን አንዷ በድጋሚ በተደረገላት ምርመራ ነፃ ሆነች።

ከቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ከተወሰደ ናሙና ውስጥ አንዲት የ24 አመት ታካሚ ላይ የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባት መግለጫ መሰጠቱ ይታወቃል።

ይሁንና በዚች ግለሰብ ላይ በድጋሚ ሶስት ተከታታይ ምርመራ ተደርጎላት ከቫይረሱ ነጻ መሆኗ መረጋገጡን የጤና ጥበቃ ሚንስቴር አስታውቋል።

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
⬆️⬆️የኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ሁኔታ መግለጫ።

@YeneTube @FikerAssefa
የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ወደ ሐረሪ ክልል እንዳይገቡ መወሰኑን የክልሉ የኮምዩንኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት አስታወቀ። የከተማ ታክሲ አገልግሎት ተከልክሏል፤ ግብአቶችን የሚያመላልሱ የጭነት ተሽከርካሪዎች ከሹፌርና ረዳት ውጪ መጫን አይችሉም።

Via Eshete Bekele
@YeneTube @FikerAssefa
"ትምህርት እንዲቀጥል፣ የተማሪዎች ምርቃት እንዲመጣ፣ ህይወት እንዲቀጥል ዛሬ መጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡" (ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ)

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከልና ለመግታት ሲል መጋቢት 15 ቀን 2012 ዓ.ም ሁሉም የዩኒቨርስቲ ተማሪዎቻችን ወደየቤተሰቦቻቸው እንዲሄዱ ውሳኔ ላይ መድረሱ ይታወቃል፡፡

Via MoSHE
@YeneTube @FikerAssefa
ዩኒቨርስቲዎች ለኮሮና ቫይረስ ተጠርጣሪዎች ለይቶ ማቆያና ለተያዙት ማገገሚያ እንዲሆኑ ለማስቻል ዝግጅት እየተደረገ እንደሆነ ተገለጸ፡፡

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ሂሩት ወ/ማርያም ዛሬ ከሁሉም ዩኒቨርስቲዎች ፕሬዚዳንቶች ጋር በቪዲዮ ኮንፈረንስ ተወያይተዋል፡፡ በውይይታቸውም ዩኒቨርስቲዎችን ለኮሮና ቫይረስ ተጠርጣሪዎች ለይቶ ማቆያና በቫይረሱ ለተያዙት ማገገሚያ እንዲሆኑ ለማስቻል ዝግጅት እንዲያደርጉ ቀድም ተብሎ በተሰጣቸው አቅጣጫ መሰረት ያሉበትን ደረጃ ግምገማ አካሂደዋል፡፡

Via MoSHE
@YeneTube @FikerAssefa
የ70 ዓመቱ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚንስትር ቤንያሚን ኔትናሁ የኮሮና ቫይረስ የላብራቶሪ ውጤታቸው ነጻ(ኔጋቲቭ) መሆናቸውን አሳይቷል። ውጤቱ ነጻ መሆናቸውን ቢያሳይም ከጤና ሚንስትር ተጨማሪ ማረጋገጫ እና ፈቃድ እስኪነገራቸው ራሳቸውን ለይተው ይቆያሉ።

Via Sheger FM
@YeneTube @FikerAssefa
የሶማሌ ክልል መንግስት ኮማንድ ፖስት ውሳኔ አስተላለፈ።

በአገር አቀፍ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች 23 መደረሱን ተከትሎ ዛሬ ማምሻ ላይ በሶማሌ ክልል የተቋቋመው ኮማንድ ፖስት ውሳኔ አሳልፏል።
በዚህም መሰረት:―

1.የክልሉም የፌዴራል ጸጥታ አካላት ከምግብና አስፈላጊ ቁሳቁስ በስተቀር ምንም አይነት የትራንስፖርት እንቅስቃሴ በድንበር አከባቢዎች እንዳይገቡ ማድረግ፤

2.የትራንስፖርት አገልግሎትን በተመለከተ ከጭነት አቅማቸው 50 በመቶ ቀንሰው ዋጋ ሳይጨመር 12 ሰዎች የሚጭኑ ሚባሶች 6 ሰዎች በመጫንና ከፍተኛ ጥንቃቄ በማድረግ የትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት እንደሚችሉ፤

3.የምሽት መዝናኛዎች፣ጭፈራ ቤቶች እና ሰው በሚበዛበትና የመዝናኛ ስፍራዎች እንደ DSTV፣ጫት ቤቶችና የመሳሰሉት ሙሉ በሙሉ እንዲዘጉ፤

4.የክልሉ ህዝብ ከጸጥታ አካላትና ጤና ባለሙያዎች ጎን እንዲቆሙና አስፈላጊውን ድጋፍና ትብብር እንዲያደርጉ፤

5.ጡረታ የወጡ የህክምና ባለሙያዎችና ዘንድሮ በጤና ዘርፍ የሚመረቁ ተማሪዎች በሙሉ ለጥሪው ዝግጁ አንዲሆኑና ወደ ክልሉ ጤና ቢሮ መጥተው እንዲመዘገቡ ጥሪ ተደርጓል።

Via Sheger Times
@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
ልብ ይበሉ፥ በአለም ላይ ፈጣኑ ወረርሽኝ ፍርሃት ነው‼️

🚦በ2002 እ.ኤ.አ ማርቲን ሪየስ የተሰኘ ወደረኛ ኮስሞሎጂስት አንድ ልተለመደ ውርርድ ይፋ አደረገ፡፡ እንዲህም አለ፡- “በ2020 በባዮ-ቴረር ወይም በባዮ-ኢረር በሚከሰት አደጋ በአንድዬ ብቻ 1 ሚሊዮን ህዝብ ይረግፋል/BY 2020, BIOTERROR OR BIOERROR WILL LEAD TO ONE MILLION CASUALTIES IN A SINGLE EVENT.”

ፕሮፌሰር ስቴቨን ፒንክር ግን “ለእንዲህ አይነት ጥንቆላ ነክ ትንበያዎች እውን ቢሆኑ እንኳን አለም መጨረሻ ነው ብላችሁ እንዳትሰጉ” የሚል መልዕክት ያለው “Enlignmenet Now” የሚል ግሩም መጽሃፍ ጻፈ፡፡

እ.ኤ.አ 2015 ላይ “የአለም መጪው ፈተና ኑክሊየር ቦንብ ሳይሆን የቫይረስ ቦንብ ነው” ብሎ ያስጠነቀቀው ቢሊየነሩና በጎ አደራጊው ቢል ጌት ሳይቀር የፒንከርን መጽሃፍ “የምንጊዜም ምርጡ መጽሀፌ” ብሎ አሞካሸለት፡፡ “የምክነያታዊ ተስፈኞች መጽሃፍ ቅዱስ” የሚል የዳቦ ስም የተሰጠው የፕሮፌሰር ስቴቨን ፒንከር ተስፋ ሰጪ መጽሀፍ ለጨለመው እይታችን ያለጥርጥር ብርሃንን ያላብሰናል።

ፕሮፌሰር ፒንከር በአብዛኛው መልዕክቶቹ በምክኔታዊ አወንታዊነት እና አብርሆት ላይ ያተኮሩ ናቸው፡፡ ፕሮፌሰር ፒነከር ይሄንን ለማለት በቂ ምክነያቶች አሉን ባይ ነው፡፡ ቢያነቡት ጊዜውን ይዋጁበታል። መጽሃፉ አሁን በሀገራችን በገበያ ላይ ይገኛል፡፡ ፍርሃቱን ቀነስ ጥንቃቄውን ጨመር አድርገው ዘና ይበሉ፡፡ #ተስፋ አለን! በእርግጥም እናሸንፈዋለን!

እያነበብን ክፉቀኑን እንለፈው! Be more informed and less panicked!
ለበለጠ መረጃ ወይም መጽሃፉን ለማግነት 0911124036 ወይም 0961004364 ላይ ይደውሉ፡፡
‹‹ሶደሬ ሪዞርት በኦሮሚያ ክልል መንግሥት ትዕዛዝ ተዘግቷል›› ዲንቁ ደያሳ

ከ70 ዓመታት በፊት በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ የተቋቋመው እና በኋላም ወደ ግሉ ዘርፍ እንዲዞር የተወሰነው የሶደሬ ሪዞርት በኦሮሚያ ክልል ባለሥልጣናት ትዕዛዝ ባሳለፍነው ሐሙስ መጋቢት17/2012 መዘጋቱን ሪዞርቱ አስታወቀ።አዲስ ማለዳ ያነጋገረቻቸው የድርጅቱ ከፍተኛ ባለድርሻ ዲንቁ ደያሳ እንደገለፁት ‹‹ለጊዜው ሪዞርቱ ለምን እንደተዘጋ አላውቅም። እኔ የማምነው ግን ያለአግባብ ግፍ እየተፈፀመብኝ እንደሆነ ነው›› ሲሉ ለአዲስ ማለዳ ከአሜሪካ በስልክ ገልፀዋል። የሪዞርቱ አመራሮች ታስረው እንደነበር ዲንቁ አረጋግጠዋል። ‹‹ከእሱ ጋር ስብሰባ ነበረን። ስብሰባውን ትቶ ወደ አሜሪካ ሄዷል›› በሚል ምክንያት እንደያዟቸው ሰምቻለሁ ሲሉም በሪዞርቱ የሚሠሩ አንድ የሥራ ኃላፊ ተናግረዋል።

ዝርዝር👇👇👇
https://telegra.ph/Sodere-Shutdown-03-31
የቀድሞው የኮንጎ ፕሬዚዳንት ጃኩዊስ ጃኩዊም የሆምቢ ኦፓንጎ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ህይወታቸው አለፈ።

የ81 አመቱ ቀድሞው ፕሬዚዳንት በፈረንሳይ ፓሪስ ውስጥ ህክምና ሲደረግላቸው ቆይቶ ነው ህይወታቸው ያለፈው።የሆምቢ ኦፓንጎ በሌላ ህመም ህክምና ይከታተሉ እንደነበርም ቤተሰቦቻቸው ገልፀዋል።የሆምቢ ኦፓንጎ በአሁኑ ፕሬዝዳንት ደኒስ ሳሱዎ ከስልጣን ከመውረዳቸው አስቀድሞ ኮንጎ ብራዛቢልን እኤአ 1977 እስከ 1979 ድረስ መምራታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

Via EBC
@YeneTube @FikerAssefa
በሀዋሳና አዳማ ከተማ መንገዶች ላይ የፀረ ተዋህስ መድሃኒት ርጭት ተከናወነ!

በሀዋሳ እና አዳማ ከተማ ዋና ዋና መንገዶች ላይ የፀረ ተዋህስ መድሃኒት ርጭት ስራ በዛሬው እለት ተከናውኗል። በሀዋሳ ከተማ የፀረ ተዋህስ መድሃኒት ርጭት ስራው ከማለዳው 12:00 ሰዓት እስከ 4:00 ሰዓት ድረስ የተካሄደ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ አስታውቋል። የከተማዋ ጎዳናዎች ከማንኛውም ተሽከርካሪዎች ነፃ በማድረግ የፀረ ተዋህስ መድሃኒት ርጭት ስራው መከናወኑን ነው የተገለፀው።በተመሳሳይ በአዳማ ከተማ የፀረ ተዋህስ መድሃኒት ርጭት ስራው በተለይም የህብረተሰቡ እንቅስቃሴ በሚበዛቸው አካባቢዎች ላይ በዛሬው ዕለት በስፋት መካሄዱን የከተማ አስተዳደሩ ባወጣው መረጃ አስታውቋል።

ምንጭ: ፋና
@YeneTube @FikerAssefa
የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ የኬሚስትሪ ትምህርት ክፍል ሳኒታይዘር እየመረተ መሆኑን ተገለጸ።

-ዩኒቨርሲቲው
@YeneTube @FikerAssefa
#Breaking
በምዕራብ ወለጋ በጸጥታ ምክንያት እየተካሄደ በነበረው ኦፕሬሽን ምክንያት ተቋርጦ የነበረው ኢንተርኔት ከዛሬ ጀምሮ ይለቀቃል፡፡

የኦሮሚያ ክልል መንግስት ይህ እንዲሆን የወሰነው፤ በክልሉ ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ የሚመራው ልዑክ አካባቢውን ለቀናት ከጎበኙ በኋላ ነው፡፡

አቶ ሽመልስ ከጉብኝታቸው መልስ ዛሬ እየሰጡ ባለው መግለጫ በአከባቢ አንጸራዊ ሰላም በመስፈኑ ከዛሬ ጀምሮ በተወሰኑ አካባቢዎች ተቋርጦ የነበረው የኢንተርኔትና የስልክ አገልግሎት ወደ ቦታው ይመለሳል ብለዋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa