YeneTube
118K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.88K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
እኛን አይወክልም በቀለ ገርባ

በአዳማ ከተማ በነበረ የኦፌኮ መድረክ ላይ በተላለፈው መልዕክት ዙሪያ ሃላፊነቱን እንደማይወስዱ አቶ በቀለ ገርባ ተናገሩ፡፡

በአዳማ ከተማ የሴቶች ቀንን ምክንያት በማድረግ በተዘጋጀ የምክክር መድረክ ላይ በአንዲት ተሳታፊ የተላለፈው መልዕክት እኛን ወይም ፖርቲን አይወክልም ፤እንደሚባለውም የእርሷን ሀሳብ ደግፈን አላጨበጨብንም ብለዋል አቶ በቀለ፡፡

በእለቱ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ከፍተኛ አመራሮች የተገኙበትና በኦኤምኤን ቴሌቪዥን በቀጥታ በተላለፈው በዚህ ዝግጅት የመጡት ታዳሚያንን በግል የጠራናቸው ሳይሆኑ በሚዲያ በተላለፈ መልዕክት የመጡ ናቸው ብለዋል።

ማን ምን ሊል እንደመጣ እንኳን ማወቅ በማንችልበት ሆኒታ ተሳታፊዋ የተሰማትን ተናግራለች ፤የግለሰብን መብት መጋፋት አንችልም ማንም የተሰማውን መግለጽ ይችላል ይህ ጥፋት አይደለም ነው የሚሉት አቶ በቀለ፡፡

ይሁን እንጂ ከእርሷ ንግግር በኋላ ሀሳቧን ደግፈው አጨብጭበዋል መባሉ ስህተት ነው ሲሉ ያክላሉ፡፡

ለመሆኑ ፓርቲው ንግግሩ ከባድ እና መታረም ያለበት እንደሆነ አምኖ ስለምን ማስተካከያ አልሰጠም ላልናቸው አቶ በቀለ በእለቱ ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና የመክፈቻ ንግግር እኔ ደግሞ የመዝጊያ ንግግር አድርገናል፡፡

በፓርቲያችን ውስጥ የሴቶች ተሳትፎን በተመለከተም ጥናታዊ ጽሁፍ ቀርቧል በእነዚህ ነገሮች ላይ ልንጠየቅ ይገባል ፤ተሳስተን ከሆነ በወንጀልም ልንጠየቅ ይገባል፡፡

አሁን የሆነው ግን ከተሳታፊዎች ሀሳብ እንዳለ ብለን በጠየቅነው መሰረት እጇን ያወጣች እድል ታግኝ አታግኝ በውል ባላወቅናት አንዲት ሴት የተሰጠ በመሆኑ እኛ ልንጠየቅ አይገባም ብለዋል አቶ በቀለ፡፡

ከነገሩ በኃላ በማህበራዊ ደረገጾች በመገናኛ ብዙሀን እና በግለሰቦች የተከፈተብን ዘመቻ ግን ቀድሞዎኑ ሲጠበቅ የነበረ ነው የሚመስለው፡፡

ከልጅቷ ሀሳብ በላይ በእኛ ላይ እየተሰነዘረ ያለው ዘመቻ ጥላቻው የማን እንደሆነ እያሳየ ነው ብለዋል አቶ በቀለ፡፡

ስለዚህ እኛ በዚህ ላይ ትክክል ነው ብለን አናስብም ፤ነገር ግን ከእኛ ቁጥጥር ውጪ በሆነ ሁኔታ በተፈጠረው ነገር እንዲህ አምርሮና አግዝፎ መመልከቱ የፈጠረው ስሜት ግን አሳዛኝና የጥላቸውን ደረጃ ያሳየ ነው ብለዋል፡፡

Via:- Ethio FM
@YeneTube @Fikerassefa
ዛሬ ደቡብ አፍሪካ በኮሮና ቫይረስ የተጠቁ ሰዎች መኖራቸው የሀገሪቷ ጤና ሚንስትር አስታውቋል።

@YeneTube @Fikerassefa
በኢትዮጵያ እስካሁን በኮቢድ-19 (ኮሮና ቫይረስ) የተጠቃ ሰው እንደሌለ ተገልጧል፡፡ ይህን ያስታወቀው ቫይረሱን ለመከላከል የተቋቋመው ብሄራዊ አስተባባሪ ኮሚቴ ነው፡፡ ኮሚቴው ለጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ሪፖርት ማቅረቡን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡
@Yenetube @Fikerassefa
ኦኤምኤን በፌስቡክ ገጹ ንግግሩ በቀጥታ በመሰራጨቱ ይቅርታ ጠይቋል እንዲሁም ከሳተላይት ላይ ቪዲዮዎን ማውረዱን ገልጷል።

@Yenetube @Fikerassefa
YeneTube
ኦኤምኤን በፌስቡክ ገጹ ንግግሩ በቀጥታ በመሰራጨቱ ይቅርታ ጠይቋል እንዲሁም ከሳተላይት ላይ ቪዲዮዎን ማውረዱን ገልጷል። @Yenetube @Fikerassefa
"OMN ላይ ላኮረፋቹብን ተመልካቾቻችን ሁሉ ይቅርታ እንጠይቃለን"

የሚለው ዕርፍተ ነገር OMN #ስህተት አልሰራውም እንደማለት ነው የምንወስደው ሲሉ አቤቱታቸውን አቅርበዋል። እርሶ ምን ይላሉ ?
Anonymous Poll
83%
ትክክለኛ አገላለፅ አይደለም።
17%
ትክክለኛ አገላለፅ ነው።
የኖቭል ኮሮና ቫይረስ መተላለፊያ መንገዶች ምንድን ናቸው ?

የኖቬል ኮሮና ቫይረስ መተላለፊያ መንገድ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች በሚያስሉበት እና በሚያስነጥሱበት ወቅት ከትንፋሽ ጋር በሚወጡ ፈሳሾች ጋር በሚደረግ ንክኪ ነው።

#Share
@Yenetube @Fikerassefa
ለሲያትል እና አካባቢ ነዋሪዎች በቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን አማካኝነት በቤት ውስጥ የኮሮና ቫይረስ መመርመሪያ ኪት ለነዋሪዎች ለማከፋፋል እየተዘጋጁ መሆኑ ተሰምቷል።

@YeneTube @Fikerassefa
እስራኤል ኮሮና ቫይረስ ከተከሰተባቸው ሀገራት ወደ ሀገሯ የሚገቡትን 14 ቀን ለይቶ ማቆያ ማስገባት መጀመሯን አስታውቋል።

#ኮቪድ19
@Yenetube @Fikerassefa
በኢትዮጵያ የነበረ አንድ የአሜሪካ የባህር ሀይል የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ መሆኑ ተገልጿል።

ቶክ ሚዲያ የአሜሪካ መከላከያ ሀይል መግለጫን ዋቢ አድርጎ በሰራው ዘገባ በኢትዮጵያ ጉብኝት አድርጎ ወደ ዋሸንግተን የተመለሰ አንድ የባህር ሀይል ወታደር በኮሮና ቫይረስ መጠቃቱ ተገልጿል።

ይሁንና ወታደሩ ወደ ኢትዮጽያ የመጣው መቼ እንደሆነ ዘገባው አልጠቀሰም።

የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እስካሁን በኢትዮጵያ በዚህ ቫይረስ የተጠቃ ሰው አለመኖሩን ማስታወቁ ይታወሳል።



http://www.talkmedianews.com/featured/2020/03/09/marine-back-from-ethiopia-tests-positive-from-covid-19-at-ft-belvoir-virginia/

Via:- Ethio FM
@Yenetube @Fikerassefa
የመንግስትም ሆነ የግል፣ የውጪም ሆነ የሀገር ውስጥ ሚድያዎች ዛሬ የሚከናወነውን የET-302 የመታሰብያ ፕሮግራም በስፍራው ተገኝተው እንዳይዘግቡ ተደርጓል!

#ኤልያስ_መሰረት

አዘጋጆቹ "ቪድዮ ቀርፀን እና ፎቶ አንስተን እኛ እንሰጣለን። ሚድያ ያልተጋበዘው በቤተሰቦች ጥያቄ ነው" ያሉ ሲሆን በዚህም ምክንያት ከቦታው ሳንደርስ እየተመለስን እንገኛለን።

Via:- eliasmeseret
@Yenetube @Fikerassefa
በዚምቧብዌ በኮሮና ቫይረስ ተይዟል ተብሎ የተጠረጠረ አንድ ግለሰብ ማምለጡ ተገለጸ።

በዚምባብዌ መዲና ሀራሬ ከተማ አንድ ታይላንዳዊ የኮሮና ምልክቶች ቢታዩበትም ሳይመረመር ከሆስፒታሉ መጥፋቱ እስካሁን ኮሮና ላላገኛት ሀገር አሳሳቢ ሆኗል፡፡

በበሽታው ተይዟል ተብሎ የተጠረጠረው ይህ ታይላንዳዊ በፖሊስ እየታሰሰ እንደሆነ ተነግሯል፡፡

የዚምባብዌ ጤና ሚኒስቴር እስካሁን በሀገሬ በኮሮና ቫይረስ የተያዘ የለም ብሏል፡፡

በተያያዘ ዜና በቡርኪና ፋሶ የመጀመርያ የሆኑ 2 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተይዟል፡፡

የሀገሪቱ ጤና ሚ/ር እንዳለው ከሰሀራ በታች በኮሮና ስንጠቃ ስድስተኛ ሀገር ሆነናል ብሏል፡፡ በቫይረሱ የተጠቁት ባልና ሚስቶች ከፈረንሳይ ጉዟቸው በቅርቡ የተመለሱ ሲሆኑ በለይቶ ማቆያ ተቀምጠዋል ተብሏል፡፡

በደቡብ አፍሪካ ደግሞ ተጨማሪ 4 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተይዘዋል፡፡

እነዚህ ተጠቂዎች ጣልያን ሄደው ባለፈው ሳምንት ከተመለሱት 10 ሰዎች መካከል ናቸው ተብሏል፡፡

ይህ አዲስ ጥቃት በደቡብ አፍሪካ በበሽታው የተያዙትን ሰዎች ቁጥር ወደ ሰባት ያደረሰው ሲሆን በጆሀንስበርግ አንድ መምህር ከጣልያን ስለመጣ የሚያስተምርበት ት/ቤት ለ 1 ቀን ተዘግቷል፡፡

እንዲሁም በቱኒዚያ ተጨማሪ ሶስት አዳዲስ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ተገኝተዋል።

የጤና ባለሙያዎች እንደገለፁት በመዲናዋ በቱኒዝ፣በሰሜን ቱኒዝያ በምትገኘው የወደብ ከተማ ቢዜርቴ እና በደቡብ በምትኘው ሜህዲያ ከተማ ነው በበሽታው የተጠቁት ሰዎች የተገኙት፡፡

ሁለቱ ከጣልያን ተጉዘው የመጡ እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን ከጤና ሚኒስቴር የወጣ ይፋዊ የሆነ ደብዳበቤ ሁሉም ቱኒዚያውያን ስብሰባዎችን ለሌላ ጊዜ እንዲያስተላልፉ፣በኮሮና ቫይረስ ከተጠቁ ሀገራት እንግዶችን ፣መጋበዝ እንዲያቆሙ አሳስቧል፡፡

Via:- Ethio FM
@Yenetube @Fikerassefa
ትምህርት ሚኒስቴር አዲሱን ሎጎ አስተዋውቋል።
@Yenetube @Fikerassefa
🏷CLARKS
🏷🇮🇹 ITALY 🇮🇹
🏷Size:39 40 41 42 43 44
🏷️Price: 2300 ETB
🏷Free Delivery
🏷contact @babeyos
🏷call +251955352406
BABYO BRAND|always unique

Join👇👇
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAFhWm3MuPyJdztBwSQ
ባለፈው መስከረም ኢትዮጵያ መጥተው የነበሩት የፈረንሳይ ባህል ሚኒስትር በኮሮና ቫይረስ ተያዙ


በፈረንሳይ መንግስት እርዳታ እየተዳሰ የነበረውን የላሊበላ ውቅር ቤተክርስቲያንን ለመገምገም ባለፈው መስከረም ኢትዮጵያ የመጡትና ከጠ/ሚ ከዶ/ር አብይ አህመድ ጋር ውይይት ያረጉት የፈረንሳይ የባህል ሚኒስትር ፍራንክ ሬይስተር በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተነግሯል ።

የፈረንሳይ የጤና ሚኒስትር ኦሊቨር ቬራን ቢ ኤፍ ኤም ቴሌቭዥን ላይ ቀርበው እንደተናገሩት ” ሬይሰተር አሁን እቤቱ አረፍ ብሏል።ደህና ነው ።” በማለት ሚኒስትሩ እቤታቸው ሆነው ህክምና እያገኙ መሆናቸውን ገልፀዋል።

የ46 አመቱ ሬይስተር በቅርቡ በኮሮና ቫይረስ ከተጠቁት አምስት የፈረንሳይ የፓርላማ አባላት ከአንዱ ጋር በመገናኘታቸው ቫይረሱ ሊይዛቸው እንደቻለም ተነግሯል።

ሬይስተር ከፈረንሳይ ባለስልጣኖች መሀከል ግብረሰዶማዊ ነኝ በማለት በ2010 ዓ.ም መናገራቸው የሚታወስ ሲሆን የተመሳሳይ ፆታ ጋብቻን አጥብቀው ይደግፋሉ።
ሬይስተር ዛሬ ማክሰኞ ከፊልም ኢንደስትሪ ሰዎች ጋር እና ከአርቲስቶች ጋር በኮሮና ቫይረስ መከላከል ዙርያ ዉይይት ለማድረግ ቀጠሮ ይዘው ነበር።

በፈረንሳይ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት 25 ሰዎች ሲሞቱ 1,412 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ተይዘዋል።

Via:- Fidelpost.com
@Yenetube @Fikerassefa
ትናንት ምሽት በሰሜን ሸዋ ዞን መሀል ሜዳ ከተማ አንድ ግለሰብ ቦንብ ወርውሮ 3 ሰዎችን የገደለ ሲሆን ተጨማሪ 3 ሰዎችን አቁስሏል። ይህው ግለሰብ በሽጉጥና በጩቤ ተጨማሪ 13 ሰዎች ላይ ጉዳት አድርሷል።

ድርጊቱ የተፈጸመው በከተማው በሚገኘው ወይዘሮ ትርንጎ መጠጥ ቤት ሲሆን፣ ፖሊስ ተጠርጣሪውን ለመያዝ ጥረት እያደረገ መሆኑን ገልጿል።

በተጨማሪም በተመሳሳይ ሰዐት በከተማው በተለምዶ ወልደመድን ጫካ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ አንድ ሌላ ሰው ጭንቅላቱ ላይ በስለት ተመቶ ወድቆ የተገኘ ሲሆን፣ ይህም የሟቾቹን ቁጥር ወደ 4 ከፍ አድርጎታል።

Via:- Elu
@Yenetube @Fikerassefa
ኢትዮጵያን ፕረስ ጋዜጠኞች ከስራ ታገዱ!!

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ከደቂቃዎች በፊት፤ ቦርዱ የምርጫ ክልሎችን ካርታ ቅዳሜ ይፋ ያደርጋል” በሚል ርዕስ በሰራው ዜና ስር የተጠቀመው ምስል የተሳሳተ መሆኑን እየገለጽን፤ ለተፈጠረው ስህተት ይቅርታ እንጠይቃለን ብሏል።

ድርጅቱ ይህንን ስህተት የፈጠሩ ጋዜጠኞቹን ከስራ ያገደ መሆኑን እየገለጽን፤ በቀጣይ የሚወሰደውን እርምጃም እናሳውቃለን ሲል በፌስቡክ ገፁ ገልጷል።

@Yenetube @Fikerassefa
የአሜሪካ አምስት ሴናተሮች ራሳቸውን በለይቶ ማቆያ ስፍራ አስቀምጠዋል፡፡

አምስቱ የአሜሪካ ሪፐብሊካን ሲናተሮች የቲክሳሱን ሴናተር ቴድ ክሩዝን ጨምሮ ራሳቸውን አግልለው ያስቀመጡት በኮሮና ቫይረስ ከተጠቃ ሰው ጋር መጨባበጣቸውን ተለከትሉ ነው፡፡

የኮንግረስ አባላቱ የተጨባበጡት በየካቲት መጨረሻ ላይ በነበረ አንድ ኮንፍረንስ ነው፡፡
በዚህ ኮንፈረንስ ላይ ፕረዝደንት ዶናልድ ትራንፕም ተገኝተው እንደነበረ ተነግሯል፡፡ይጨባበጡ አይጨባበጡ ግን የቢቢሲ ዜና ያለው ነገር የለም፡፡

ፕሬዝደንቱ ምርመራ ባያደርጉም በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡
በሌላ ዜና የቻይናው ፕሬዝደንት ዢ ፒንግ ቫይረሱ የተነሳባት ውሃን ከተማን ጎብኝተዋል፡፡

ከሁለት ወር በፊት ከዚህች ስፍራ የተነሳው የኮሮና ቫይረስ አሁን ትልቅ የአለም ስጋት ሆኗል፡፡
እርግጥ በውሃን የቫይረሱ ስርጭት እየቀነሰ እንደመጣ ተነግሯል፡፡

እስካሁን በቻይና ከ67 ሺህ በላይ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሲሆን አብዛኛዎቹ ወረሽኙ ያጠቃቸው ሰዎች በሁቤይ ግዛት ባለችው የውሃን ከተማ ነዋሪዎችን ነው ፡፡

በዚህ የኮሮና ቫይረስ ከሞቱት 3 ሺህ 136 ሰዎች ውስጥ 112ቱ ብቻ ከሁቤይ ግዛት ውጪ የሞቱ ዜጎች ናቸው፡፡

Via:- Ethio FM
@Yenetube @Fikerassefa
#Coronavirus_Update_Spain

ስፔን ዛሬ ብቻ 415 ሰው በኮሮና ቫይረስ ተይዘዋል። እንዲሁም በኮሮኛ ቫይረስ ምክንያት ከ5 ሰው በላይ መቷል በአጠቃላይ በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች 1646 ሲሆን የሟቾች ቁጥር ከ35 ደርሷል።

@Yenetube @Fikerassefa
በሻሸመኔ ከተማ 200 ኪሎ ግራም የሚመዝን የካናቢስ አደንዛዥ እጽ መያዙን የከተማዋ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

200 ኪሎ ግራም የሚመዝን የካናቢስ እጽ ከነ አዘዋዋሪዎቹ በቁጥጥር ስር ማዋሉን በሻሸመኔ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የወረዳ ሁለት ጽ ህፈት ቤት ለኢትዩ ኤፍ ኤም አስታውቋል፡፡

አደንዛዥ እጹ በቁጥጥር ስር የዋለው በተለየ መንገድ እንደ ዶካ (አነስተኘ ወንበር) አድርጎ በመስራት በህዝብ ማመላለሻ መኪና ከሻሸመኔ ከተማ ወደ ሞያሌ ለማሻገር ሲሞክሩ ነው፡፡

አንድ ተሳፋሪ ነገሩን በመጠራጠሩ ለፖሊስ ባደረሰው ጥቁማ መሰረት ፖሊስ ክትትል በማድረግ 200 ኪሎ ግራም ካናቢሱን በቁጥጥር ስር እንደዋለው የወረዳው ፖሊስ ጽ/ቤት አዛዝ ሳጂን ሙዲን መሀመድ ለኢትዩ ኤፍ ኤም አስታውቀዋል፡፡

ከእጽ ዝውውሩ ጋር በተያያዘ ሶስት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር እንዳዋሏቸው ሳጂን ሙዲን ለጣቢያችን ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም ፖሊስ በከተማዋ ውስጥ ባደረገው አሰሳ ከግለሰቦች ቤት እና ከሆቴሎች 200 የሺሻ ማስጨሻ ቁሳቁሱችን በቁጥጥር ስር ማዋለቸውንም ተናግረዋል፡፡

የከተማዋ ከንቲባ አቶ ተማም ሀሰን በበኩላቸው ህብረተሰቡ ከፖሊስ ጎን እንዲቆም ጠይቀው መንግስትም በነዚህ ግለሰቦች ላይ የህግ እርምጃ ይወስዳል ብለዋል፡፡

Via:- ethio fm
@Yenetube @Fikerassefa