YeneTube
118K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.88K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ከአድዋ ጦርነት ቡኃላ እራሱን ያጠፋው ጄኔራል ኦሬስቴ ባራቴሬ

አፄ ሚኒሊክ የጣሊያንን ጦር ለመጋፍጥ ሲወስኑ፣ የጣሊያንን ጦር እየመሩ ከመጡት ጀነራሎች ዋነኛው ጄኔራል ኦሬስቴ ባራቴሬ ነበር። ጄኔራል ባራቴሬ የአፄ ሚኒሊክን ከዚህ ቀደም ይከተሉት የነበርን የጦር ስትራቴጂ አጥንቶ ስለነበር፣ የአድዋን ጦርነትም በድል እንደሚወጣው እርግጠኛ ነበር።

አፄ ሚኒሊክ ቀደም በአብዛኛው ይከተሉት የነበርው የጦር ስትራቴጂ ፈረንጆቹ (Battle of annihilation) የሚሉት ወይም ሙሉ ሃይልን በመጠቀም ጠላትን ነጥሎ መደምሰስ ነበር። በአድዋ ጦርነት ላይ ግን ስልታቸውን ቀይረው በተለያየ ግንባር ጀነራሎቻቸውን አሰልፈው ስለነበር፣ የጣሊያን ጦርን በመበተን ታሪካዊ ድል ተጎናፅፈዋል። ጄኔራል ባራቴሬም የአፄ ሚኒሊክን የጦር አሰላለፍ ባለመረዳት አሳፋሪ ሽንፈትን ቀምሷል።

ተጨማሪ እዚህ ላይ ገብተው ያንብቡ ⬇️

https://telegra.ph/Adawa-03-01
#Adawa #አብን

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ለንቅናቄያችን አባላትና ደጋፊዎች፣ ለአማራ እና መላ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንኳን ለ124ኛው የአድዋ የድል በዓል በሰላም አደረሳችሁ ይላል፤

አፍሪካን እንደ ቅርጫ ሥጋ ለመከፋፈል የአውሮጳ ሃያላን በጀርመን በርሊን ኮንፈረንስ ከተሰባሰቡና ስምምነት ላይ ከደረሱ በኋላ ጣሊያን ኢትዮጵያን ቅኝ ግዛት ለማድረግና ሀብቷን ለመመዝበር፣ በሂደትም ኮሎኒያሊስት ሰፋሪዎችን አየሩ ተስማሚ በሆነው በኢትዮጵያ ደጋማ መሬቶች ለማስፈር ቋመጠች። ኢትዮጵያን አንበርክካ የቅኝ ግዛትን ኅልሟን ለማሳካት የጦር ክተት ዘመቻዋን አወጀች፡፡

ጠንቃቃና ብልህ የነበሩት የወቅቱ የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገሥት ግርማዊ ዳግማዊ አፄ ምኒሊክ (እምየ ምኒሊክ) የፋሽስት ጣሊያንን ኅልም ለማምከን መስከረም 17 ቀን 1888 ዓ.ም ሕዝባቸው ለአገሩ ነፃነትና ለማንነቱ እንዲፋለም ብሔራዊ የክተት ዘመቻ ጥሪ አወጁ፡፡

ተጨማሪ⬇️
https://telegra.ph/Adawa-03-01-2
የሚንስትሮች ምክር ቤት አዲስ የቋንቋ ፖሊሲ አጽድቋል::
በዚህም መሰረት 4ቱ ቋንቋዎች:-
1. አፋን ኦሮሞ
2. ትግሪኛ
3. ሱማሊኛ እና
4. አፋርኛ

ከአማርኛ በተጨማሪ የፌዴራል የስራ ቋንቋ ይሆናሉ ማለት ነው::

እንኳን ደስ አለን! #Fistumarega
@YeneTube @FikerAssefa
የአለም ስጋት ከሆነው የኮሮና ቫይረስ እራሳችንን ለመከላከል ልንወስዳቸው የሚገቡ ቀላልና

ውጤታማ እርምጃዎች፥

- አዘውትሮ በአግባቡ እጅን በሳሙና መታጠብ

- ለሰላምታ በእጅ አለመጨባበጥ

- ፊትን በእጅ አለመንካት

- ትኩሳት፣ ሳል፣ ማስነጠስ ያሉ ምልክቶች ካጋጠሙን የአፍ መሸፈኛ ማስክ ማድረግ

- በሚያስነጥሱ እና በሚያስሉ ጊዜ ክርንዎን አጥፈው በመጠቀም ሌሎችን እንዳይበክሉ መጠንቀቅ።
@Yenetube @Fikerassefa
124ኛው የዓድዋ ድል በዓል በአዲስ አበባ ከተማ ምንሊክ አደባባይ እየተከበረ ነው፡፡

124ኛው የዓድዋ ድል በዓል በአዲስ አበባ ከተማ ምንሊክ አደባባይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስራ ሓላፊዎች ፣ አባት እና እናት አርበኞች እንዲሁም በርካታ የከተማዋ ነዋሪዎች በተገኙበት በድምቀት በመከበር ላይ ይገኛል።
በድል በዓሉ የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር ሊቀመንበር ልጅ ዳንኤል ጆቴ ባስተላለፉት መልዕክት እንዳሉት ኢትዮጵያ በዓድዋ ድል የከፈለችው መስዋዕትነት ከራሷ አልፎ ለአፍሪካ እና ለጥቁር ህዝቦች በሙሉ መሆኑን ተናግረዋል።

በአሁኑ ሰዓት አገራችን ኢትዮጵያ እጅግ ፈታኝ ወቅት ላይ ትገኛለች ያሉት ልጅ ዳንኤል ጆቴ ከልዩነት ይልቅ አንድነትን ከጥላቻ ይልቅ መፈቃቀርን በመስበክ ሁሉም ለአገሩ ዘብ ሆኖ ሊቆም እንደሚገባው አሳስበዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር አወቀ ኃ/ማሪያም ፣የከንቲባ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወ/ሮ አለምጸሀይ ጳውሎስ እና የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር ሊቀመንበር ልጅ ዳንኤል ጆቴ በጋራ የአበባ ጉንጉን አስቀምጠዋል፡፡

ለ124ኛ ጊዜ በመከበር ላይ በሚገኘው የዓድዋ ድል በዓል ላይ አርበኞች ፉከራ እና ሽለላ ያቀረቡ ሲሆን በርካታ የከተማዋ ነዋሪዎች በአንድነት በዓሉን በማክበር ላይ ይገኛሉ፡፡

Via:- Addis Ababa City Administration
@YeneTube @Fikerassefa
አንኳን ለ124 አድዋ ድል በዓል በሰላም አደረሳችሁ ።

ግራፊክሱን የሰራልን ለይኩን ማስታወቂያን እናመሰግናለን።

@leykunadvertising
@leykunadvertising
Forwarded from YeneTube
የአድዋ ድል በዕል በተለያዩ ከተሞች እየተከበረ ይገኛል።
የኦነግ አመራሮች በከፊል ተፈተዋል

በቁጥጥር ስር ውለው የነበሩት የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ከፍተኛ አመራሮች ትላንት እሁድ አመሻሹ ላይ ከእስር የተፈቱ ሲሆን የቀድሞው የኦነግ ጦር አዛዥ የነበሩት እና አሁን የስራ አስፈፃሚ አባል የሆኑት አብዲ ረጋሳ ግን እስካሁን ያለመፈታታቸውን ፓርቲው አስታውቋል።

የፓርቲው ነባር አባል የሆኑት ለሚ ቤኛ ለአዲስ ማለዳ እንደተናገሩት አመራሮቹ እሁድ ማታ ታስረው ከቆዩበት በተለምዶ ሶስተኛ ተብሎ ከሚጠራው ፖሊስ ጣቢያ የተፈቱ ሲሆን ‹‹ እንዲሁ ተለቀቁ እንጂ ዋስትናም ጥሩ አልተባሉም›› ሲሉ ተናግረዋል።

‹‹አብዲ እስካሁን ያሉበትን አናውቅም›› ያሉት ለሚ በቁጥጥር ስር ከዋሉበት ግዜ ጀምሮ ቤተሰብም ሆነ ጠበቃ እንዲያገኛቸው ባለመደረጉ ምክኒያት ፓርቲያቸው ስጋት እንደገባውም ገልፀዋል።

‹‹አብዲ መንግስት እና ፓርቲው ባደረገው ድርድር ከኤርትራ በሰላም ለመታገል የተመለሱ ሲሆን የኦነግ ሰራዊት ዋና አዛዥ የነበሩ ናቸው። ስለዚህ የእሳቸውን ጉዳይ በቀላሉ የምናየው አይደለም›› ሲሉ ለሚ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።

እሁድ የካቲት 22/2012 ጠዋት በጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት ተካሂዶ የነበረው የጋዲሳ ሆገንሳ ኦሮሞ ጉባኤ ላይ ኦነግ ሳይገኝ መቅረቱን የተናገሩት ለሚ ለዚህም ‹‹አመራሮቻችን ታስረውብን ለማስፈታት እየተሯሯጥን ስለነበር በጉባኤው አልተሳተፍንም›› ብለዋል።

‹‹ጉባኤው መንግስት እና ፓርቲዎች መካከል ውይይት ለማሰለጥ ተጀመረ እንጂ ተቋማዊ አይደለም። አሁን ባለው ሁኔታ ብዙም ለውጥ አይታይበትም፤ ከዚህ በኋላም እያየን ወይ እንሄዳለን ወይ እንቀራለን›› ብለዋል።

‹‹ኦነግ ለጋዲሳው ከፍተኛ አስተዋፅኦ ሲያደርግ ነበር አሁንም ይህንን እንቀጥላለን፤ ነገር ግን ተቃውሞ ሲኖረን ተቃውሟችንን እናሰማለን›› ሲሉ ገልፀዋል።

አብዲ ረጋሳ፣ ሚካኤል ቦረና፣ ሽጉጥ ገለታ (ዶ/ር)፣ ያዲ አብዱልሽኩር፣ ኬናሳ አያና፣ ተስፋዬ ማኮ፣ አብዱልከሪም አብዱራህማን፣ ሙሄ ራያ፣ ሶሎሞን ተሾመ፣ ደቻሳ ዊርቱ በቁጥጥር ስር ውለው አንደነበር ይታወሳል።

ምንጭ:- አዲስ ማለደ
@Yenetube @FikerAssefa
አሜሪካ በዛሬ አንድ በኮሮና ቫይረስ ተጠቅቶ መሞቱን ዋሽንግተን ፓስት የዋሽንግተን ስቴት የጤና ባለስልጣናትን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።

Join @Coronavirusupdatess
@YeneTube @FikerAssefa
#ሊደመጥ_የሚገባው⬇️

አሜሪካ ህዳሴ ግድብ ላይ እንድተገባ በር ማን ከፈተ? ሀይለማርያም ፣አብይ ፣ ደብረፅዮን ወይስ ሜቴክ ?

በተስፋዬ ጌትነት( fidelpost.com ) ተፃፈ በየኔቲዩብ ተነበበ

https://youtu.be/R-ZgpeGaM_o
Forwarded from HEY Online Market
#ኦሪጂናል ሞባይል ስልኮች ዋስትና

🔸SAMSUNG
#GALAXY A SERIES 
A10S 2019 /32 GB/ 5,599ብር
A20S 2019 /32 GB/ 7,199ብር
A30S 2019 /64 GB/ 8,499 ብር
A50 2019 /64 GB/ 9,499 ብር
A50 2019 /128 GB/ 10,499 ብር
A50S 2019 /128 GB/ 4GB 11,199
A50S 2019 /128 GB/ 6GB 11,999
A51 2020 /128 GB/ 6GB 12,799 ብር
A70 2019 /128 GB/ 6GB 13,899 ብር

🔸SAMSUNG #GALAXY M SERIES 
M10 (2019) /32 GB/ 5,699 ብር
M10S (2019) /32 GB/ 6,200 ብር
M30S (2019) /36 GB/ 9,200ብር

አድራሻ :- ከቦሌ መድሃኔአለም ቤተ ክርስቲያን ወደ ቦሌ ብራስ የሚወስደው መንገድ ላይ

Contact US
0953964175
0925927457
0910695100
@Roviii

@HEYOnlinemarket