የኤርትራው ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፍወርቂ ትላንት ማታ በሀገራቸው ቴሌቪዝን በቀጥታ በተላለፈ ቃለ-መጠይቅ የኢትዮጵያና ኤርትራ የደንበር ውዝግብ ጉዳይ በከፋ ሁኔታ ላይ መሆኑ ገለፁ፡፡
በሌላ በኩል ፕሬዝደንቱ አዲሱ ምዕራፍ የኢትዮጵያና ኤርትራ ግንኙነት በመልካም ሁኔታ ላይ መሆኑ ጠቁመዋል፡፡በፈረንጆቹ አዲሱ ዓመት የመጀመሪያ ቃለ መጠይቅ የሰጡት ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፍወርቂ በኢትዮጵያ ሕገ መንግስት፣ የ2012 ምርጫ፣ እየተስተዋሉ ያሉ ብሄር ተኮር ግጭቶችና ሌሎች ጉዳዮች ዙርያም አስተያየታቸው ሰጥተዋል፡፡ ከኢትዮጵያ ጋር ከተያያዙ አጀንዳዎች ውጪ ኤርትራ አሁናዊ የሱዳን ፖለቲካዊ ሁኔታ በትኩረት እየተከታተለች መሆኑ የገለፁ ሲሆን የቀይባህር አካባቢ ሀገራት መርህ መሰረት ያደረገ ትብብር እንደሚያስፈልጋቸውም ተናግረዋል፡፡
Via DW
@YeneTube @FikerAssefa

1650 በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ ለአገር ውስጥ ገበያ ቀርቧል!
ኢትዮጵያ የራሷን የነዳጅ ምርት ለአገር ውስጥ ፍጆታ መጠቀም የጀመረች ሲሆን፤ የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር ባለፉት 6 ወራት 1650 በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ ለሀገር ውስጥ ገበያ መቅረቡን አስታውቋል፡፡በመጪው ሣምንት ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ሊቀርብ በተዘጋጀው የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር የ6 ወራት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት፤ በሶማሌ ክልል ኦጋዴን ከአንድ አመት ተኩል በፊት በሙከራ ደረጃ መመረት የጀመረው ነዳጅ፤ ባለፉት 6 ወራት ለሀገር ውስጥ ገበያ ሲቀርብ መቆየቱን ያመለክታል፡፡
‹‹ኒው ቢዝነስ ኢትዮጵያ›› የተሰኘው ድረ ገጽ፣ ማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴርን ጠቅሶ ባወጣው መረጃ፤ በሙከራ ደረጃ ካለፈው ሐምሌ 2011 ጀምሮ ላለፉት 6 ወራት 1650 በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ ለሀገር ውስጥ ገበያ መቅረቡንና በዚህም ሀገሪቱ ከውጭ ተገዝቶ ለሚገባ ነዳጅ ታወጣ ከነበረው የውጭ ምንዛሪ፣ 55ሺህ 994 ዶላር ማዳን መቻሏን ጠቁሟል፡፡
በኦጋዴን ያለውን የነዳጅ ምርት ከሀገር ውስጥ ገበያ ባሻገር ወደ ውጪ ለመላክ፣ ከኦጋዴን እስከ ጅቡቲ የውስጥ ለውስጥ ነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ግንባታ በቅርቡ እንደሚጀመርም ታውቋል፡፡የኢትዮጵያን ነዳጅ ከሚረከቡ 3 የውጭ ሀገር ኩባንያዎች ጋር ስምምነት መፈረሙም በሥራ አፈፃፀም ሪፖርቱ ላይ ተገልጿል፡፡ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ የማዕድን ዘርፍ በአመቱ ከ60ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጐች የስራ እድል መፈጠሩንም ለማወቅ ተችሏል፡፡
Via Addis Admas

የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የኮሮና ቫይረስ የላቦራቶሪ ምርመራ እዚሁ በተቋሙ ማድረግ ጀመረ::
ኢንስቲትዩት የኮሮና ቫይረስ የላቦራቶሪ ምርመራ እዚሁ በተቋሙ ማድረግ የጀመረ ስሆን 6 የኮሮና ቫይረስ በሽታ ምልክት ታይቶባቸው በለይቶ ማቆያ ማዕከል ክትትል እየተደረገላቸው እንደሆነና ለኮሮና ቫይረስ ምርመራ ናሙና የተወሰደላቸው መሆኑንና የ3ቱ ናሙና ወደ ደቡብ አፍሪካ የተላከ መሆኑን በትላንትናው ዕለት መግለጹ ይታወሳል፡፡ በዛሬው ዕለት የ3ቱ ናሙናዎች ውጤት የደረሰ ሲሆን ከቫይረሱ ነጻ መሆናቸዉ ተረጋግጧል፡፡ በተጨማርም እዚሁ በኢንስቲትዩቱ የተወስዱ 3ቱ ናሙና በተቋሙ ምርመራ ተደርጎ ነጻ መሆኑ ተረጋግጧል::
Via Ministry of Health

#Coronavirusupdate
Updated 4hrs ago.
የቫይረሱ ተጠቂዎች ቁጥር ከሰላሳአራት ሺህ ያለፈ ሲሆን የሟቾች ቁጥር ደግሞ 723 ደርሷል።
Via AFP

የአፍሪካ ኀብረት የመሪዎች ጉባዔ ዛሬ ይጀመራል
የአፍሪካ ኀብረት 33ኛው የመሪዎች መደበኛ ጉባዔ ዛሬና ነገ አዲስ አባበ በሚገኘው የኀብረቱ ዋና መስሪያ ቤት ይካሄዳል።
መሪዎቹ ለሁለት ቀናት በሚኖራቸው ጉባዔ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መክረው ውሳኔ ያሳልፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ለአፍሪካ ልማት ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ”የጦር መሳሪያ ድምጽን ማጥፋት” በሚል መሪ ሃሳብ የሚካሄደው የህብረቱ የመሪዎች ጉባኤ ሲጀመር ህብረቱን ለአንድ አመት በሊቀመንበርነት ያገለገሉት የግብጹ ፕሬዚዳንት አብዱልፈታህ አል ሲሲ ሃላፊነቱን ለሚቀጥለው አንድ አመት ለሚይዙት የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ሳይሪል ራማፎሳ ያስረክባሉ።
የመክፈቻ ንግግሮች ከቀረቡና የጉባኤው መሪ ሃሳብ ይፋ ከተደረገ መሪዎቹ በዝግ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።
መሪዎቹ በዝግ ይመክሩባቸዋል ተብለው ከሚጠበቁ ጉዳዮች መካከል የአፍሪካ ህብረት ተቋማዊ ለውጥ እና በአህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ዙሪያ የተሰሩ ስራዎችን የተመለከተ ሪፖርት ማዳመጥና ቀጣይ አቅጣጫ ማስቀመጥ እንደሚገኙበት መረጃዎች ያመለክታሉ።
ሰላምና ጸጥታን በተመለከተም የሰላምና ጸጥታ ምክር ቤት እና አህጉራዊ የሰላምና ጸጥታ ሁኔታ ላይ ምክክር ይደረጋል።
በተጨማሪም እ.አ.አ በ2020 በአህጉሩ ጸጥታ ለማስፈን የተዘጋጀው የተግባር ፍኖተ ካርታ አፈጻጸም ላይ መሪዎቹ ይመክራሉ።
ምንጭ፦ ኢዜአ
@YeneTube @Fikerassefa

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በኢትዮጵያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት በማድረግ ላይ ለሚገኙት የካናዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ ማምሻውን ለክብራቸው የእራት ግብዣ አዘጋጅተዋል።
በግብዣውም ላይ በርካታ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ትሩዶ ባለፈው አርብ ነበር ይፋዊ የስራ ጉበኝት ለማድረግ ወደ ኢትዮጵያ የመጡት።
ትናንትናም ከፕሬዚዳንት ሳህለወረቅ ዘውዴ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አህመድ ጋር ተገናኝተው በሁለትዮሽ እና በሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።
Photo: JustinTrudeau
Via:- FBC

በሪያድ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በሪያድ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የሰጠው ማሳሰቢያ👇👇
በሪያድ ከተማ ውስጥ ቱማማ፣ መኽረጅ 28፣ መኽረጅ 29 እና መኽረጅ 30 በሚባሉ ቦታዎች በተደጋጋሚ ኢትዮጵያዊያን ዜጎች የሚታገቱበት ሁኔታ መኖሩንና ከዚህ በፊት ታግተው የነበሩ ሃያ የሚሆኑ ዜጎቻችንን ከእገታ ማዳን የተቻለ መሆኑን መግለጻችን ይታወሳል። በርካታ ቁጥር ያላቸው እህቶቻችን በደላሎች አማካኝነት ወደ እነዚህ አካባቢዎች ለሥራ ከሄዱ በኋላ ስልካቸውን ተነጥቀው ከማንም ጋር እንዳይገናኙ ተከልክለው እየታገቱ መሆኑን በተደጋጋሚ መረጃዎች ይደርሱናል።
አሁንም በተጠቀሰው አካባቢ ሄደው የሚሰሩ ኢቃማ ያላቸውና የሌላቸው ዜጎቻችን ተመሳሳይ እጣ ፈንታ እየገጠማቸው መሆኑን መረዳት ችለናል። የኢፌዲሪ ኤምባሲ ከሚመለከተው የሳዑዲ አረቢያ መንግስት ወገን ጋር በመተባበር የዜጎችን ደህንነት የመጠበቅ ኃላፊነት ያለው መሆኑ ይታወቃል። በመሆኑም ከሳዑዲ የህግ አስከባሪ አካላት ጋር በመሆን ጉዳዩን እየተከታተልን ያለንበት ሁኔታ ላይ የምንገኝ በመሆኑ፣ ዜጎቻችን ለጊዜው በተጠቀሱት አካባቢዎች ለሥራ እንዳይሄዱ ኤምባሲው ይመክራል።
ምንጭ: ኤምባሲው

ደቡብ አፍሪካ የአፍሪካ ህብረት የወቅቱ ሊቀመንበርነት ስፍራን ተረከበች!
ደቡብ አፍሪካ የአፍሪካ ህብረት የወቅቱ ሊቀመንበርነት ስፍራን ተረከበች።ዛሬ በተጀመረው 33ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች መደበኛ ጉባኤ ላይ ነው ደቡብ አፍሪካ የፈረንጆቹ 2020 የህብረቱ የወቅቱ ሊቀመንበርነትን ስፍራ የተረከበችው።የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳም ከግብፅ ፕሬዚዳንት አብዱልፈታህ ኤልሲሲ ሊቀመንበርነቱን ተረክበዋል።
Via FBC

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ከደብረ ብርሀን ወደ ዓለም ከተማ የሚወስደው መንገድ በአካባቢው ወጣቶች መዘጋቱ ተገለጸ።
መንገዱ በመዘጋቱ ምክንያትም ወደ መርሀቤቴ፣ ሚዳ ወረሞ እና እንሳሮ ወረዳዎች የሚሄዱ መንገደኞች መቸገራቸውን ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል።እንደ የአይን እማኞቹ አስተያየት ከሆነ መንገዱ የተዘጋው በአካባቢው ወጣቶች ሲሆን መንገዱ ወደ አስፓልት ይቀየርልን ብለን ለመንግስት ብናመለክትም የሚሰማን አጣን በሚል ምክንያት እንደዘጉት ተናግረዋል።በተለይም ህጻናት የያዙ ወላጆች ምግብና ውሀ በማጣታቸው ለእንግልት ተዳርገናል የሚመለከተው የመንግስት አካል መንገዱን በአፋጣኝ ያስከፍትልን ሲሉ ጠይቀዋል።የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ተፈራ ወንድምአገኝ በጉዳዩ ዙሪያ ምላሽ እንዲሰጡን ተደጋጋሚ ሙከራ ብናደርግም አልተሳካም።
Via Ethio FM

የኖርዌዩዋ ጠቅላይ ሚኒስትር ኤርና ሶልበርግ በአዲስ አበባ ከተማ የካሳንቺስ ጤና ጣቢያን ጎብኝተዋል።
የኖርዌዩዋ ጠቅላይ ሚኒስትር ኤርና ሶልበርግ በአዲስ አበባ ከተማ የካሳንቺስ ጤና ጣቢያን በጎበኙበት ወቅት እንደገለፁት ኢትዮጵያ በምዕተ ዓመቱ የጤና የልማት ግቦች በተለይ የእናቶችና የህፃናትን ሞት በመቀነሱ ረገድ ባለፉት ዓመታት አበረታች ስራዎችን ሰርታለች።
በወሊድ ወቅት በእናቶችና ህፃናት ላይ የሚደርሰውን የሞት እና ተያያዥ ችግሮችን ለመቀነስ በሚደረገው ጥረትም የኖርዌይ መንግሥት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኤርና ሶልበርግ ተናግረዋል ።በኢትዮጵያ በፕሮጀክት ደረጃ ተግባራዊ ለሚደረጉ ሴፍ ሊትል ላይፍስ እና ካንጋሮ ማዘር ኬር ለተሰኙ የእናቶችና የህፃናት ጤናን ለመጠበቅ የኖርዌይ መንግሥት የአምስት ሚሊየን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ማድረጉን በጉብኝቱ ወቅት ተገልጿል ።
ምንጭ: የአዲስ አበባ ከተማ ፕሬስ ሴክሬተሪያት

የዛሬው የNew York Times እትም ኢትዮጵያ እና ግብጽ ስለሚወዛገቡበት የአባይ ውኃ እና የታላቁ ህዳሴግድብ ሰፊ ዘገባ ይዞ ወጥቷል። ጋዜጣው በአሜሪካ እና ዓለም ባንክ አሸማጋይነት የሚደረገው ድርድር ግብጽ "ተስፋ ያደረገችውን ያህል አልተጓዘም" ሲል ጽፏል።
@YeneTube @Fikerassefa
@YeneTube @Fikerassefa
#Sport 🇪🇹 13ተኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች
⏰ ጨዋታው ተጠናቋል
ሀዋሳ ከተማ 1-0 ጅማ አባጅፋር
ውልዋሎ አ.ዩ 1-4 ቅዱስ ጊዮርጊስ
ድሬደዋ ከተማ 1-1 ሰሑል ሽረ
ባህር ዳር ከተማ 3-2 ሰበታ ከተማ
@YeneTube @Fikerassefa
⏰ ጨዋታው ተጠናቋል
ሀዋሳ ከተማ 1-0 ጅማ አባጅፋር
ውልዋሎ አ.ዩ 1-4 ቅዱስ ጊዮርጊስ
ድሬደዋ ከተማ 1-1 ሰሑል ሽረ
ባህር ዳር ከተማ 3-2 ሰበታ ከተማ
@YeneTube @Fikerassefa
#Coronavirusupdate
Updated 1hr ago.
የቫይረሱ ተጠቂዎች ቁጥር ከሰላሳሰባት ሺህ ያለፈ ሲሆን የሟቾች ቁጥር ደግሞ 813 ደርሷል።
በዚህም መሰረት ያለፈው 24 ሰዓት ከእስካሁኑ ትልቁ የሟቾች ቁጥር የተመዘገበበት ሆኗል።
Via AFP
@YeneTube @FikerAssefa
Updated 1hr ago.
የቫይረሱ ተጠቂዎች ቁጥር ከሰላሳሰባት ሺህ ያለፈ ሲሆን የሟቾች ቁጥር ደግሞ 813 ደርሷል።
በዚህም መሰረት ያለፈው 24 ሰዓት ከእስካሁኑ ትልቁ የሟቾች ቁጥር የተመዘገበበት ሆኗል።
Via AFP
@YeneTube @FikerAssefa
በየኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የኖቭል ኮሮና ቫይረስን አስመልክቶ የተዘጋጀ ወቅታዊ መግለጫ
➡️ በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ በኖቭል ኮሮና ቫይረስ በሽታ መያዙ የተረጋገጠም ሆነ በለይቶ ማቆያ ማዕከሉ ሆኖ ክትትል የሚደረግለት ሰው የለም፣
➡️ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የኖቭል ኮሮና ቫይረስ የላቦራቶሪ ምርመራ እዚሁ በተቋሙ ማድረግ የጀመረ በመሆኑ ወደ ደቡብ አፍሪካ ሊላክ የነበረ የ3 ሰዎች ናሙና ምርመራ በማድረግ ከቫይረሱ ነጻ መሆናቸውን ማረጋገጥ ችሏል፡፡ በተጨማሪም የ3ቱ ወደ ደቡብ አፍሪካ ተልከው የነበሩ ናሙናዎች ውጤት የደረሰን ሲሆን ከቫይረሱ ነጻ መሆናቸዉ ተረጋግጧል፡፡
➡️ የኖቭል ኮሮና ቫይረስን በሽታ የመከላከል ዝግጁነትን ለማጠናከር ኢንስቲትዩቱ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ እና በአዲስ አበባ ለሚገኙ 13 ሆስፒታሎች የተለያዩ ግብዓቶችን አሰራጭቷል፤ እንዲሁም ለክልል ሆሲፒታሎች ለማሰራጨት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ተጠናቀዋል፡፡
➡️ የቫይረሱን ስርጭት አስመልክቶ እስከ አሁን ድረስ 31 ጥቆማዎች ለኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የድንገተኛ አደጋዎች ምላሽ ማስተባበሪያ ማዕከል (Emergency Operation Center) ደርሰው ማጣራት ተደርጎባቸዋል፣ ከነዚህ ውስጥ 14ቱ በልየታ ቆይተው ናሙናቸው ተመርምሮ ከቫይረሱ ነጻ መሆናቸው በመረጋገጡ ከለይቶ ማቆያ ማዕከሉ እንዲወጡ ተደርጓል፡፡
➡️ የበሽታውን ልየታ ስራ ለማጠናከር የልየታ ቡድኑን ለሚቀላቀሉ የጤና ባለሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡
➡️ በሐዋሳ ቫይረሱን የመከላከል ዝግጁነትን ለመደገፍ ቡድን ተልኳል፡፡
➡️ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስተር ክቡር አቶ ደመቀ መኮንን የሚመራው ብሔራዊ ግብረ ሃይል ጥር 29/2012 ስብሰባ አካሂዷል፡፡
➡️ ለሆቴሎች፣ ታክሲ ሾፌሮች እና ለመገናኛ ብዙሀን ባለሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ለመስጠት ዝግጅቶች ተጠናቀዋል፡፡
📌ጥንቃቄ መደረግ ያለባቸው ጉዳዮች
➡️ በተጨማሪም ሕብረተሰቡ በሀገራችን እስካአሁን በቫይረሱ መያዙ የተረጋገጠ ሰው አለመኖሩን አውቆ ሳይዘናጋ የበለጠ ጥንቃቄ ኢንዲያደርግ ኢንስቲትዩቱ ያሳስባል፡፡
➡️ የኖቭል ኮሮና ቫይረስ ከታየባቸው ሀገራት የመጡ መንገደኞች ወይም በዚህ ቫይረስ ከተያዙ ግለሰቦች ጋር ንክኪ የነበራቸው ሰዎች ላይ የበሽታው ምልክቶች (ትኩሳት፤ ሳል፤ የትንፋሽ መቆራረጥ፣ የመተንፈስ ችግር) ከታዩ፣ ማንኛውም የሕብረተሰቡ አካል በአስቸኳይ በ8335 ነጻ የስልክ መስመር ላይ በመደወል ሪፖርት እንዲያደርግ እናሳስባለን፡፡
➡️ የበሽታው ምልክት የታየባቸው ሰዎች በሚያስነሠጥሱበት እና በሚያስሉበት ወቅት አፍና አፍንጫቸውን በሶፍት ወይም በክንድ እንዲሸፍኑ፤ የተጠቀሙበትን ሶፍት ወደ ቆሻሻ ማጠራቀሚያ እንዲጥሉ እና እጃቸውን በውሃና ሳሙና በመታጠብ የቫይረሱን ስርጭት እንዲከላከሉ እንመክራለን፡፡
የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
አዲስ አበባ
01/06/2012 ዓ.ም

እስክንድር ነጋ የባልደራስ እውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ፕሬዝደንት ሆኖ ተመረጠ!
ጠቅላላ ጉባኤው ዛሬ በሶስት ተወዳዳሪ የፓርቲውን ፕሬዝደንት ሚስጥራዊ ምርጫ በማከናወን 60 አባላት ያሉት የብሔራዊ ም/ቤት በምርጫ የተጠናቀቀ ሲሆን የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፕሬዝደንት እስክንድር ነጋ ሆኗል።
Via:- Sintayehu Chekol // ኤልያስ መሰረት
@YeneTube @FikerAssefa
ጠቅላላ ጉባኤው ዛሬ በሶስት ተወዳዳሪ የፓርቲውን ፕሬዝደንት ሚስጥራዊ ምርጫ በማከናወን 60 አባላት ያሉት የብሔራዊ ም/ቤት በምርጫ የተጠናቀቀ ሲሆን የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፕሬዝደንት እስክንድር ነጋ ሆኗል።
Via:- Sintayehu Chekol // ኤልያስ መሰረት
@YeneTube @FikerAssefa
⚠️WARNING ⚠️ *GRAPHIC*
26 ሰዎችን የገደለው አንድ የታይላንድ ወታደር በፖሊስ ተገደለ ፡፡ ቢያንስ 42 የሚሆኑ ሰዎች ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል።
ጥቃት አድራሹ ግድያውን የጀመረው በሀገሪቱ የሰዓት አቆጣጠር ትናንት ከሰዓት በኋላ ነበር። የ32 ዓመቱ ግለሰብ በመጀመሪያ ኮራት በመባል የሚታወቅ ቦታ የሚገኝ ወታደራዊ ሰፈር ውስጥ አለቃውን እና ሌሎች ሁለት ሰዎች ገድሎ ሸሽቷል።
ከዛም ጠመንጃ እና ጥይቶች ሰርቆ በወታደራዊ መኪና ያመለጠው ይሄው ግለሰብ በዘፈቀደ ሰዎች ላይ እየተኮሰ መግደሉን እና ይህንን ድርጊቱንም በቪዲዮ እየቀረፀ ኢንተርኔት ላይ ይለቅ እንደነበር ተገልጿል።
በመጨረሻም ወደ ገበያ አዳራሽ በመግባት ሰዎች ላይ ሊተኩስ እና በአስራዎቹ የሚቆጠሩ ሰዎችንም ማገቱን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
ግለሰቡም ከ 17 ሰዓታት በኋላ በልዩ ኃይል ፖሊስ ሊገደል ችሏል። የድርጊቱ ምክንያት በውል አልታወቀም።
Via:- DW #Photo social media

በኹለት ወር የጤፍ ዋጋ አምስት መቶ ብር ጨመረ
ከኅዳር ወር መጀመሪያ አንስቶ ጭማሪ ማሳየት የጀመረው የጤፍ ዋጋ፣ እስከተገባደደው ሳምንት መጨረሻ ድረስ እስከ 500 ብር የዋጋ ጭማሪ አሳየ። ማኛ ነጭ ጤፍ እስከ 4 ሺሕ 500 ብር ድረስ በመሸጥ ከፍተኛው የዋጋ ንረት የታየበት ሲሆን፣ ቀይ ጤፍ በኩንታል የ300 ብር ጭማሪ እና ሰርገኛ ጤፍም በተመሳሳይ የ300 መቶ ብር ጭማሪ በማሳየት ወደ 3 ሺሕ 400 ብር ከፍ ማለቱን አዲስ ማለዳ በገበያ ላይ ያደረገችው ቅኝት ያሳያል።
ካዛንቺስ አካባቢ የሚገኘው ድል በጌ ገበያ ውስጥ ነጭ ጤፍ በ 4 ሺሕ 500 ብር ሲገዙ አዲስ ማለዳ አግኝታ ያነጋገረቻቸው ሳምሶን ታዬ እንደሚሉት፣ ከኹለት ወራት በፊት በ4 ሺሕ ብር ተመሳሳይ ነጭ ጤፍ መግዛታቸውን ይናገራሉ።
ከአራት ወር በፊት በ3 ሺሕ 300 ብር ሲሸጥ የነበረው ኹለተኛ ደረጃ ነጭ ጤፍ፣ የ 700 ብር ጭማሪ በማሳየት 4 ሺሕ ብር የገባ ሲሆን፣ እምቡር የተሰኘው የነጭ ጤፍ አካባቢ የሚመጣው ጤፍ ሙሉ በሙሉ ከገበያ መጥፋቱን አዲስ ማለዳ ያነጋገረቻቸው ነጋዴዎች ተናግረዋል።
የጤፍ ምርት የሚሰበሰብበት የመኸር ወቅት ላይ ዘንቦ የነበረው ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ እየጨመረ ለመጣው የጤፍ ዋጋ በምክንያትነት የተጠቀሰ ሲሆን፣ በተጨማሪም የሕገወጥ ደላሎች መበራከት የንግድ ሰንሰለቱን እንዳረዘመው እና ይህም ለዋጋ መጨመሩ ምክንያት መሆኑን ነጋዴዎች ገለፀዋል።
የድል በጌ ጤፍ መሸጫና ማስፈጫ ባለቤት የሆኑት ሀያት በረከት እንደሚሉት፣ ከዚሀ በፊት ከገበሬዉ በቀጥታ በመረከብ ለገበያ ያቀርቡ ነበር። አሁን ግን ደላሎች ይህንን ሂደት በመከልከል ተፅእኖ እስከማሳደር መድረሳቸውን ተናግረዋል። ከጊዜ ወደ ጊዜ የደላሎች ቁጥር መብዛት እና በተያዘው ሳምንትም የጤፍ ዋጋ ላይ ጭማሪ መደረጉን ደላሎች እንደነገሯቸዉና፣ ከዚህ በላይ አልጨምርም ብለዉ እንዳልገዙ ነግረዉናል። የደላሎች ትስስርም በኹለት ቦታ መሆኑን ሀያት ጨምረዉ ተናግረዋል።
የሰብር ወፍጮ ቤት ሠራተኛ የሆኑት ከሚል አሕመድ እንደሚሉት ደግሞ፣ አንደኛ ደረጃ ጤፍ ዋጋው በመወደዱ ምክንያት ደንበኞቻቸው መግዛት በማቆማቸው እርሳቸውም ጤፍ ማቅረብ ማቆማቸውን ገልፀዋል። ከኹለተኛ እስከ አራተኛ ደረጃ ያለ ነጭ ጤፎ እያንዳንዱ እስከ ሦስት መቶ ብር በኩንታል መጨመሩንም ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።
የጤፍ ዋጋ ላይ በስድስት ወር ውስጥ የአንድ ሺሕ ብር ጭማሪ መታየቱን አዲስ ማለዳ በተለያዩ የጤፍ መሸጫ ቦታዎች ተዘዋውራ ያነጋገረቻው ነጋዴዎች አረጋግጠዋል።
የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የንግድ ክትትልና ቁጥጥር ኃላፊ ሀብታሙ ጥላዬ፣ የዋጋ ንረቱ እዚህ መድረሱን እንደማያውቁ ተናግረዋል። ከዚህ በፊት የነበረዉ የጤፍ ዋጋ ከ3 ሺሕ 200 እስከ 3 ሺሕ 500 መሆኑንና እየታየ የመጣውን የዋጋ ንረት ለማስተካከልም በጥናት ላይ ተመስርቶ እርምጃ እንደሚወሰድም አስታውቀዋል።
ከዚህ በፊት የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ሕገ ወጥ ነጋዴዎችንና ደላሎችን ለመቆጣጠር ንብረታቸዉን የመዉረስና በሕግ የማስቀጣት ሥራ እየሠራ መቆየቱና አሁን ያለዉ የሕገ ወጥ ደላሎች ዝዉዉር አዲስ መልክ ይዞ መምጣቱን ሀብታሙ ጠቅሰዋል።
ሀብታሙ እንደሚሉት፣ ወቅቱ የመኸር ወቅት ከመሆኑ አንፃር የገበያ ሁኔታዉ መቀነስ ሲኖርበት፣ ነገር ግን ሊቀንስ ባለመቻሉ ምክንያቱን ለማወቅ የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ጥናት እያደረገ መሆኑን ገልፀዋል። ችግሩን የአድስ አበባ ንግድ ቢሮ ብቻ ሊያስቆመዉ ስለማይችል፣ ሌሎች የሚመለከታቸዉ አካላት ተሳትፎ እንደሚያስፈልግም ለአዲሰ ማለዳ ተናግረዋል።
ምንጭ:- አዲስ ማለዳ

የፍልስጤም ፕሬዚደንት ማህሙድ አባስ የአፍሪካ መንግስታት ለፍልስጤም ትግል ለሚያደርጉት ድጋፍ ምሥጋናቸውን ልከዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ለቀጣናው ሰላምና መረጋጋት የተጫወቱትን ሚናም አድንቀዋል
ፍልስጤምን ወክለው የቀረቡት
የፍልስጤም ጠቅላይ ሚኒስትር መሀመድ ሻተይ በተጨማሪም "ፍልስጤማውያን የሚፈልጉት ርዳታና ዳቦ ሳይሆን ነፃነትና ፍትህ ነው" ሲሉ በ33 ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሩዎች ጉባኤ ላይ ተናገሩ። ለፍልስጤምና ለእስራኤል መስማማት ፕሬዚደንት ትረምፕ ያቀረቡት የሰላም ዕቅድም ተቀባይነት የለውም ብለዋል።
ምንጭ:- አሐዱ ሬዲዮ