YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
አሜሪካ ሳንዲያጎ ግዛት በተካሄደ የግማሽ ማራቶን ውድድር መሰረት ደፋር በሴቶች አንደኛ ሆና ስታሸንፍ በወንዶች ፈይሳ ለሊሳ ሁለተኛ በመሆን አጠናቋል፡፡

መሰረት በሳንዲያጎ የተደረገውን የማራቶን ውድድር ለማጠናቀቅ የፈጀባት ጊዜ 1 ሰዓት ከ8 ደቂቃ ከ27 ሰከንድ ነው፡፡

@yenetube #sport
#sport ኢትዮጵያን ወክሎ በካፍ ቻምፒዮንስ ሊግ ቅድመ ማጣሪያ ወደ ጂቡቲ አቅንቶ ጅቡቲ ቴሌኮምን የገጠመው የ2010 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮ ጅማ አባጅፋር 3ለ1 በሆነ ውጤት አሸንፏል።የማሸነፊያ ግቦቹንም ሲድቤ(2x) እና አስቻለው አስቆጥረዋል።
@Yenetube @Fikerassefa
#Ethiopia #Sport በዓምላክ ተሰማ የአፍሪካ ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታን እንዲመራ ተመረጠ

በአፍሪካ ዋንጫ ወሳኝ ጨዋታዎችን እየዳኘ
የሚገኘው ኢትዮጵያዊው በዓምላክ ተሰማ
የፍፃሜው ጨዋታ እንዲመራ በካፍ የዳኞች
ኮሚቴ ተመርጧል።

በግብፅ አስተናጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው
ውድድር ሁለት የምድብ፣ አንድ የሩብ ፍፃሜ እና
ትላንት ወደ ፍፃሜ ለማለፍ ወሳኝ የነበረው
የሴኔጋል እና ቱኒዚያን የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታን
የመራ ሲሆን የፊታችን ዓርብ በካይሮ ስታዲየም
በአልጄርያ እና ሴኔጋል መካከል የሚደረገውን
የፍፃሜ ጨዋታም የሚመራ ይሆናል። ይህም
በ1980 የአፍሪካ ዋንጫ #ናይጄርያ#አልጄርያ ያደረጉትን ጨዋታ ከመሩት ተስፋዬ ገብረየሱስ (አሁን የኤርትራ እግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ናቸው) በኋላ የፍፃሜ ጨዋታን የሚመራ ኢትዮጵያዊ ያደርገዋል።

Via :- Soccer Ethiopia
@YeneTube @FikerAssefa
#Sport 🇪🇹 13ተኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች

ጨዋታው ተጠናቋል

ሀዋሳ ከተማ 1-0 ጅማ አባጅፋር
ውልዋሎ አ.ዩ 1-4 ቅዱስ ጊዮርጊስ
ድሬደዋ ከተማ 1-1 ሰሑል ሽረ
ባህር ዳር ከተማ 3-2 ሰበታ ከተማ
@YeneTube @Fikerassefa