YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ቻይና በኮሮና ቫይረስ ላይ እየወሰደች ያለው እርምጃ በቂ አለመሆኑን አመነች፡፡

የቻይና አንድ ከፍተኛ አመራር በሀገሪቱ በከፍተኛ መጠን እየተሰራጨ የሚገኘው እና ገዳዩን የኮሮና ቫይረስ ለመቆጣጠር እየወሰደች ያለችው እርምጃ ክፍተቶች እና ጉድቶች እንዳሉበት እናምናለን ሲሉ ተደምጠዋል፡፡በኮሮና ቫይረስ ዙሪያ ያለው የብሔራዊ የአስቸኳይ ጊዜ አስተዳደር ስርዓቱም መሻሻል አለበት ብለዋል ፡፡እስከ ትላንት ማምሻ በቻይና ብቻ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 20 ሺህ ደርሷል፡፡

በየቀኑም ቢያንስ 3 ሺህ አዳዲስ በኮራና ቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ስለመኖራቸውም ተነግሯል፡፡በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 425 የደረሰ ሲሆን በትላንትናው እለት ብቻ 60 ያህል ቻይናውያን ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡በሌሎች ሀገራትም 150 የኮሮና ቫይረስ ምልክቶች መታየታቸውን እና 1 ሞትም በፊሊፒንስ መመዝገቡን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
254 ሜጋዋት የሚያመነጨው የገናሌ ዳዋ III የውሃ ኃይል ማመንጫ ግድብ ምረቃ እየተካሄደ ነው።

በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይም የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ፣ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ እና የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር አብረሃም በላይን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛየመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል። በዛሬው እለት እየተመረቀ ያለው የገናሌ ዳዋ III የውሃ ኃይል ማመንጫ ግድብ 254 ሜጋ ዋት ኃይል የማመንጨት አቅም ያለው መሆኑ ተገልጿል።የገናሌ ዳዋ III የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ 2 ነጥብ 57 ቢሊየን ሜትር ኪዩብ ውሃ የመያዝ አቅምም አለው።ለግንባታው 451 ሚሊየን ዶላር ወጪ የተደረገ ሲሆን፥ 60 በመቶው ከቻይናው ኤክዚም ባንክ በብድር እንዲሁም ቀሪው 40 በመቶው ደግሞ በመንግስት ወጪ የተሸፈነ ነው።

ምንጭ:ፋና
@YeneTube @FikerAssefa
በሴቶችና ህጻናት ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን ምላሽ ለመስጠት የተቋቋሙ የአንድ ማእከል አገልግሎት (one stop service center) በኢትዮጵያ::

ምንጭ: የሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ሚንስቴር
@YeneTube @FikerAssefa
በአርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ የሰጎ እና የሲሌ ወንዝ በመሙላቱ በተከሰተ የጎርፍ አደጋ በቆላ ሸሌ ፣ሸሌ ሜላ እና ኤልጎ ቀበሌዎች በንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ።

ጥር 25 ለሊት11 ፡00 በጣለው ዝናብ በአርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ የሰጎ እና ሲሌ ወንዝ በመሙላቱ ቆላ ሸሌ ቤሌ ንኡስ ፣ሸሌ ሜላ እና ኤልጎ ቀበሌዎች ላይ የተፈጥሮ አደጋ ተከስቷል።
በተፈጠረው የጎርፍ አደጋ አብዛኛው ቤቶች በውሀ ተውጠዋል።የቤት ንብረት ወድሟል ፣በማሣ ላይ ያለ ቋሚ ሰብል እና ንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል።

በዞኑ አስተዳዳረ ተወካይ አቶ ደርሶ በላይ የተመራ የዞንና የአርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ ከፍተኛ አመራሮችም በስፍራው በመገኘት የደረሰውን ጉዳት ተመልክተዋል።2012ዓ.ም የሰጎ እና የሲሌ ወንዝ ሞልቶ በአካባቢው ተደጋጋሚ ጉዳት ያደርሳል። የሲሌ ወንዝ ሙላት ገለዳ ቀጠና አንድ እና ጨፌ ላይ ጉዳት አድርሷል።ሰብአዊ እርዳታ በአፋጣኝ በሚደርስበት ዙሪያም እንቅስቃሴ ተጀምሯል።

Via Gamo Zone PR Office
@YeneTube @FikerAssefa
የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ጃኮብ ዙማ በፍርድ ቤት ለተመሰተባቸውን ክስ በተሰጣቸው ቀጠሮ ባለመገኘታቸው ዳኛው ዳሃይ ፒላይ የእስር ማዘዣ አውጥተዋል።

ምንጭ:SABC
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
በአርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ የሰጎ እና የሲሌ ወንዝ በመሙላቱ በተከሰተ የጎርፍ አደጋ በቆላ ሸሌ ፣ሸሌ ሜላ እና ኤልጎ ቀበሌዎች በንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ። ጥር 25 ለሊት11 ፡00 በጣለው ዝናብ በአርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ የሰጎ እና ሲሌ ወንዝ በመሙላቱ ቆላ ሸሌ ቤሌ ንኡስ ፣ሸሌ ሜላ እና ኤልጎ ቀበሌዎች ላይ የተፈጥሮ አደጋ ተከስቷል። በተፈጠረው የጎርፍ አደጋ አብዛኛው ቤቶች በውሀ ተውጠዋል።የቤት ንብረት…
#Update
በአርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ በሰጎ እና በሲሌ ወንዝ ሙላት በተከሰተው የጎርፍ መጥለቅለቅ 2ሺ77 አባወራዎች ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸው ተገለፀ፡፡

የአርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መስፍን ደነቀ እንደገለፁት እስካሁን ባለ መረጃ በሰው ህይወት ላይ የደረሰ ጉዳት የለም። ጥር 25 በጣለው ዝናብ በዙሪያ በወረዳው በሰጎ እና በሲሌ ወንዝ ሙላት ሳቢያ በተከሰተ የጎርፍ መጥለቅለቅ አደጋ በቆላ ሸሌ ፣በሸሌ ሜላ እና በዘይሴ ኤልጎ ቀበሌ የሚገኙ 2ሺ77 አባወራዎች13 ሺ885 ቤተሰቦች ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸው ታውቋል።2 ሺ 731.2 ሄክታር ሰብል ተጥለቅልቋል። 31.25 ሄክታር ቋሚ ሰብልም ሙሉ በሙሉ ወድሟል።
ዋና አስተዳዳሪው አክለውም ቁጥራቸው በውል ባይታወቅም የቤት እንሰሳቶች ሞተዋል። ዝናቡ የሚቀጥል ከሆነም በንብረት ላይ የሚደርሰው ጉዳት መጠንም ሊጨመምር ይችላል ብለዋል።

በተፈጥሮ አደጋው በተከሰተው ሰብአዊ ቀውስ የተፈናቀሉትን ህይወት ለማትረፍ ምግብ፣የመጠለያ ድንኳን፣አልባሳት እና የህክምና ቅድመ ዝግጅት በጊዜ ለህዝቡ ለማድረስ፤ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣የሐይማኖት ተቋማት እና ግለሰቦቸች አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጡ ጠይቀዋል።የሰጎ እና የሲሌ ወንዝ በየጊዜው እየሞላ ፈሰኛው ጎርፍ አካባቢውን በተደጋጋሚ ያጠቃል። የዘንድሮው ግን እጅግ የከፋ ነው ተብሏል ። በሲሌ ወንዝ ሙላትም ገለዳ ቀጠና አንድ እና ጨፌ ላይ ጉዳት አድርሷል።

Via Gamo Zone PR Office
@YeneTube @FikerAssefa
አንድ የፖሊስ አባል የቀድሞ ፍቅረኛውን እና የራሱን ሕይወት አጠፋ!

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ በተለምዶ ቶታል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ቅዳሜ ጥር 23 /2012 አመሻሽ 11 ሰዓት አንድ አካባቢ አንድ የፌደራል ፖሊስ አባል የቀድሞ ፍቅረኛውን እና የራሱን ሕይወት በጠመንጃ እንዳጠፋ የክፍለ ከተማው ፖሊሰ መምሪያ የወንጀል ምርመራ ኃላፊ ኢንስፔክተር ተዘራ ክፍያለው ለአዲሰ ማለዳ ገለጹ።ግለሰቡ ከእኔ ሌላ ፍቅረኛ ይዛለች በሚል ጥርጣሬ እና ከዚህ ቀደም በነበራቸው አለመግባባት የተነሳ፣ የቀድሞ ፍቅረኛው ቤተሰቦቿ በከፈቱላት የመዋቢያ መደብር ውስጥ በመግባት በተኮሰው ሦስት ጥይት ሕይወቷ ሊያልፍ እንደቻለም ምክትል ኢንስፔክተሩ አስታውቀዋል።

እንዲሁም የራሱን ሕይወት ወደ አንገቱ በተኮሰው ኹለት ጥይት ያለፈ ሲሆን የኹለቱም ሕይወት ሆስፒታል ሳይደርሱ እዚያው ማለፉንና በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በኩል አስከሬናቸው ወደ ምኒልክ ሆስፒታል ተልኮ ምርመራ መከናወኑንም አክለዋል።የሟች ምሕረት አድማሱ የቀብር ስነ ስርዓትም፣ ባሳለፍነው እሁድ ጥር 24/2012 ከሰዓት በኋላ ቃሊቲ በሚገኘው ሳለ ጊዮርጊስ ቤተክርስትያን እንደተፈጸመ አዲስ ማለዳ ያነጋገረቻቸው የሟች አብሮ አደግ ገልፀዋል።

Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
የደኅንነት ቀበቶ ዋጋ በአራት እጥፍ ጨመረ!

የትራንስፖርት ባለሥልጣን በታኅሳስ ወር ከፊት ወንበር የሚቀመጡ ተሳፋሪዎች የደኅንነት ቀበቶ እንዲያደርጉ ያወጣውን መመሪያ ተከትሎ በገበያ ላይ የደኅንነት ቀበቶ ዋጋ ከ250 ወደ 1200 ከፍ አለ።
ከዋጋ ጭማሪው ባሻገርም የደኅንነት ቀበቶው ከገበያ ላይ የጠፋ ሲሆን፣ የቀበቶው መለዋወጫዎችም ከገበያ ላይ መጥፋታቸውን አሽከርካሪዎች እና ነጋዴዎች ተናግረዋል። ነጋዴዎቹ በውጪ ምንዛሬ ችግር ምክንያት የደኅንነት ቀበቶ ከውጪ አገር ታዝዞ እስኪመጣ መዘግየቱ እንደማይቀር እና በድንገት የተፈጠረው ከፍተኛ ፍላጎት በፈጠረው እጥረት የቀበቶ ዋጋው እንዲጨምር ማድረጉን ለአዲስ ማለዳ ገልፀዋል።

ምንጭ: አዲስ ማለዳ
@YeneTube @FikerAssefa
ምርጫ ቦርድ ኢህአዴግ መፍረሱን አስታወቀ።

የአዴፓ፣ኦዴፓ፣ህወሃት እና ዴኢህዴን ስብስብ የሆነው ኢህአዴግ እንዲፈርስ በሊቀመንበሩ በኩል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድን በደብዳቤ ጠይቆ ነበር። ግንባሩ መፍረሱን ለቦርዱ ያሳወቀ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ህዝባዊ ወያነ ሐርነት ግንባር (ሕወሃት) በሊቀመንበሩ በኩል በተጻፈ ደብዳቤ ግንባሩ በመፍረሱ የንብረት ክፍፍልን አስመልክቶ ቦርዱ ውሳኔ እንዲሰጥበት ጥያቄም አቅርበው ነበር፡፡

የግንባርን መፍረስ የመወሰን ስልጣን የቦርዱ በመሆኑ ግንባሩም ሆነ ህወሃት ግንባሩ መፍረሱን መጥቀሳቸው የማይገባ ቢሆንም ቦርዱ ሁለቱ ሊቃነመናብርት ያቀረቧቸውን የጽሁፍ ጥያቄዎ መሰረት በማድረግ ግንባሩ መፍረስ አለበት ወይ? ከፈረሰስ ውጤቱ ምን ይሆናል በሚል ቦርዱ መርምሮ ውሳኔ መስጠቱን አስታውቋል። በመሆኑም ቦርዱ የግንባሩ አባል ሶስት ፓርቲዎች ከግንባሩ ወጥተው አዲስ ውህድ ፓርቲ መመስረታቸውን የብልጽግና ፓርቲን አመሰራረት ከሚያሳየው መዝገብ መረዳቱንም ገልጿል፡፡

በመሆኑም ኢህአዴግ በተግባር መፍረሱን ቦርዱ በሙሉ ድምጽ የወሰነ ሲሆን የግንባሩ መፍረስ ተከትሎ ቦርዱ የኢህአዴግን ንብረት አስመልክቶ ውሳኔ መስጠት እንደሚያስፈልግም ተረድቷል፡፡ በመሆኑም የኢህአዴግ አባል ድርጅት የነበሩት ሶስቱ ማለትም አዴፓ ኦዴፓ እና ደኢህዴን ብልጽግና የሚባል ፓርቲ መመስረታቸው፣ በሌላ በኩል ደግሞ ህወሃት ህልውናውን ጠብቆ የቆየ ፓርቲ በመሆኑ በህጉ መሰረት በብልጽግና እና በህወሃት መካከል የኢህአዴግን ንብረት ክፍፍል ማድረግ እንደሚገባ ቦርዱ ተገንዝቤያለሁ ብሏል፡፡

በመሆኑም ቦርዱ የኢህአዴግን ንብረት አስመልክቶ የሚከተሉትን ውሳኔዎች ወስኗል፡፡

1.ብልጽግና እና ህወሃት የኢህአዴግ ንብረትና ሂሳብ የሚያጣራ አጣሪ በጋራ እንዲሰይሙ

2.በኢህአዴግ ስም ያለ ማናቸውም እዳ ተጣርቶ እንዲከፈል

3.ከእዳ ክፍያ ቀሪ የሆነ ሃብት 3/4ተኛው ለብልጽግና ፓርቲ ( የሶስቱ የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች ውህደት በመሆኑ) ¼ተኛ ደግሞ ለህወሃት ድርሻ መሆኑ ታውቆ በዚያ መሰረት ክፍፍል እንዲያጠናቅቁ

4.ከላይ የተጠቀሱትን ተግባራት በህጉ መሰረት በ6 ወር ውስጥ ለቦርዱ እንዲያሳውቁ መወሰኑን አስታውቋል።

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
የጅብ መንጋ በድሬዳዋ ከተማ ስጋት አሳድሯል ተባለ!

በድሬዳዋ ከተማ የገንደ ሮቃ አካባቢ ነዋሪዎች የጅብ መንጋ ጥቃት እያደረሰባቸው በመሆኑ የሚመለከተው አካል መፍትሔ እንዲፈልግላቸው ጠየቁ። ባለፈው ቅዳሜ አንድ የ3 ዓመት ህፃን በመንጋው ህይወቱ አልፏል።በድሬዳዋ ከተማ ባለፈው ቅዳሜ ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት አካባቢ ልዩ ስሙ ገንደ ሮቃ ከሚባለው ገደላማ ስፍራ የወጣ የጅብ መንጋ በሰፈሩ በመጫወት ላይ ከነበሩ ህፃናት መካከል አንድ የ3 ዓመት ጨቅላ ህፃን አንጠልጥሎ ወስዷል።ህፃናቱ ተደናግጠው ባሰሙት ጩኽት የሰፈሩ ሰው ግልብጥ ብሎ የወጣ ቢሆኑም በተለይ የተጠቂው ህፃን አባት እስከ የጅብ መንጋው ጎሮ ድረስ እየሮጠ በመከተል የአንዱን ጅብ ጭራ በመያዝ ጭምር የልጁን ህይወት ለማትረፍ ያደረገው ሙከራ ሳይሳካለት መቅረቱን የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢዜአ ተናግረዋል።

Via EBC
@YeneTube @FikerAssefa
የካቲት 1 እና 2/2012 ለ33ኛ ጊዜ በሚካሄደው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ የዓለም የጤና ድርጅት ዳይሬክተር ጄነራል ቴዎድሮሰ አድሃኖም(ዶ/ር) እንደሚገኙ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ ጥር 26/2012 በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አስታወቀ።

በመሪዎቹ ጉባኤ ላይ 45 አገሮች የሚሳተፉ ሲሆን 31 ፕሬዝዳንቶች ሦስት ምክትል ፕሬዝዳንት እና አራት ጠቅላይ ሚኒቴሮች እንዲሁም 14 ቀዳማይ እመቤቶች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል ሲሉ የሚኒስቴሩ የፕሮቶኮል ጉዳዮች ተጠባባቂ ዳይሬክትር ጄነራል ግስላ ሻወል ገልጸዋል።

በዚህ ጉባኤ ላይ ከአፍሪካ አባል አገራት በተጨማሪ ከአሃጉሩ ውጪ የሚመጡ አገራት መሪዎች የሚገኙ ሲሆን የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስቴር ጀሰቲን ቱድሮ አንዱ እንደሚሆኑ ይጠበቃል። የህብረቱ የመሪነት ቦታ ላይ የነበረችው ግብፅ ቦታዋን ለደቡብ አፍሪካ እንደምትሰጥ ግስላ ተናግረዋል።

Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
በቻይና የተከሰተውን እና እስካሁን ለ426 ሰዎች ሞት ምክንያት የሆነውን ኮሮና ቫይረስ ለመግታት በዓለም አቀፍ ጉዞ እና ንግድ ላይ የተደረጉት እገዳዎች አላስፈላጊ እንደነበሩ የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ጄነራልቴድሮስ አድሃኖም (ዶ/ር) ገለፁ። ሁሉም አገሮች በማስረጃ ላይ የተመሠረተ እና ወጥነት ያላቸውን ውሳኔዎች እንዲተገብሩ ጥሪ እናቀርባለን ሲሉ ባለፈው ሳምንት ያስተላለፉትን መልክት ለዓለም ጤና ድርጅት ሥራ አስፈፃሚ ቦርድ በድጋሚ አስታውሰዋል።

ቫይረሱ ከቻይና ውጭ ያሳየውን መዛመት በተመለከተም ቴድሮስ ‹‹አነስተኛ እና ስርጭቱም ዘገምተኛ እንደሆነ፣ ነገር ግን ከዚህ በላይ አደገኛ ሊሆን ይችል ነበር›› ሲሉ አስታውቀዋል።በዓለም ጤና ድርጅት የሥራ አስፈፃሚ ቦርድ ስብሰባ ላይ የተገኙት የቻይና ልዑካን በበኩላቸው ቫይረሱ ለመጀመሪያ ጊዜ የተከሰተባት የሁቤይ ግዛት ፓስፖርትን የያዙ ሰዎች ወደ ሀገራቸው እንዳይገቡ የከለከሉ ሀገራት የወሰዱት እርምጃ ትክክል አይደለም ሲሉ ማውገዛቸውን ሮይተርስን ጠቅሶ አዲስ ማለዳ ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
#Coronavirusupdate

የቫይረሱ ተጠቂዎች ቁጥር ከሃያ ሺህ ያለፈ ሲሆን የሟቾች ቁጥር ደግሞ 426 ደርሷል።

Via AFP
@YeneTube @FikerAssefa
ትልልቅ የስፖርት ትጥቅ አምራች ኩባንያዎች የተመሰረቱበት አመተ ምህረት (በጎርጎሳዊያን አቆጣጠር)

አንደር አርመር :- 1996

ናይኪ :- 1964

አዲዳስ :- 1949

ፑማ :- 1948

ኮንቨርስ :- 1908

ኒው ባላንስ : - 1906

ሪቡክ :- 1895

@YeneTube @Fikerassefa
የአፈጉባኤዋ የትራምፕን ንግግር መቅደድ አነጋጋሪ ሆኗል።

የአሜሪካው ፕሬዝዳናት ዶናልድ ለአገሪቱ ምክር ቤት አመታዊውን ንግግራቸውን ካደረጉ በኋላ አፈ ጉባኤዋ የንግግሩን ቅጂ ሲቀዱ መታየታቸው አነጋጋሪ ሆኗል። ፕሬዝዳንቱ ንግግር ሲያደርጉ ከኋላቸው ተቀምጠው የሚታዩት የዴሞክራቲክ ፓርቲ አባልና የምክር ቤቱ አፈጉባኤ ናንሲ ፔሎሲ በንግግሩ ማብቂያ ላይ እጃቸው ላይ የነበረውን የፕሬዝዳንቱን ንግግር ቅጂ ሲቀዱ ታይተዋል።ይህም የተከሰተው ፕሬዝዳንት ትራምፕ አፈጉባኤዋን ላለመጨበጥ ካንገራገሩና ረጅሙን ንግግራቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ነበር።

አፈ ጉባኤ ናንሲ ፔሎሲ ፕሬዝዳናት ትራምፕ ስልጣናቸውን ያለአግባብ ተጠቅመዋል በሚል ክስ እንዲመሰረትባቸውና ጉዳያቸው በምክር ቤቱ እንዲታይ ማስደረጋቸው ይታወሳል።
የዴሞክራቲክ ፓርቲ ከፍተኛ ባለስልጣን የሆኑት አፈጉባኤዋ መነጋገሪያ ከሆነው የፕሬዝዳንቱን ንግግር ቅጂ የያዘውን ወረቀት ከቀደዱበት ድርጊታቸው በኋላ ለምን ይህንን እንዳደረጉ በጋዜጠኞች ተጠይቀው መልስ ሰጥተዋል።
አፈጉባኤዋም የፕሬዝዳንቱ ንግግር "ቆሻሻ ንግግር ስለነበረ የፈጸምኩት የሚገባ ነገር ነው" ሲሉ ድርጊታቸውን አወድሰዋል።

ፕሬዚዳንት ትራምፕ ለአንድ ሰዓት ከ18 ደቂቃ ስለተለያዩ ጉዳዮች አንስተው ለምክር ቤቱ አባላት ንግግር አድርገዋል። ፕሬዝዳንቱ ዓመታዊ ንግግራቸውን አጠናቀው ከምክር ቤቱ ሲወጡ የፓርቲያቸው የሪፐብሊካን አባላት ከአፈጉባኤዋ ከናንሲ ትችት በተለየ ፕሬዝዳንቱ ያደረጉት ንግር "ድንቅ" እንደነበር ሲናገሩ ተሰምተዋል። ዴሞክራቶች ፕሬዝዳንቱ ባደረጉት ንግግር ላይ ከአፈጉባኤዋ ጀምሮ በግልጽ ደስተኛ አለመሆናቸውን አሳይተዋል። አንዳንዶቹ እንዲያውም ፕሬዝዳንቱ እየተናገሩ ምክር ቤቱን ለቀው ሲወጡም ታይተዋል።

ምንጭ: ቢቢሲ/AFP
@YeneTube @FikerAssefa
አሳዛኝ ዜና!

⬆️⬆️⬆️
በበርካታ ዓለም አቀፍ እና አህጉራዊ ውድድሮችን ማለትም በኦሎምፒክና፣ በዓለም ሻምፒዮና ሀገሩን በመወከል የሚታወቀው የ22 ዓመት ወጣት አትሌት የሆነው አባዲ ሀዲስ በህመም ምክንያት በመቀሌ ሃይደር ሆስፒታል በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ጥር 26/2012 ዓ.ም. ምሽት ላይ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡

አትሌት አባዲ ሃዲስ በትግራይ ክልል ማይጨው ከተማ ልዩ ስሙ እንዳመሆኒ ወረዳ ጥር 27 1990 ዓ.ም የተወለደ ሲሆን የአትሌቲክሰ ህይወቱን በእንዳመሆኒ የአትሌቲክሰ ማሰልጠኛ ጣቢያ የጀመረ ሲሆን በመቀጠልም በማይጨው አትሌቲክሰ ማሰልጠኛ ማዕከል ገብቶ መደበኛ ስልጠናውን ሲያጠናቅቅ ትራንስ ኢትዮጵያ አትሌቲክሰ ክለብ በመቀላቀል ህይወቱ እስካለፈበት እለት ድረስ በውጤታማነት ክለቡን፣ ክልሉንና ሃገሩ ሲያስጠራ የነበረ ሲሆን ካስመዘጋባቸው ድሎችም ውስጥ፡-
በኦሎምፒክ ጨዋታዎች

• በብራዚል ሪዮ ዴ ጄኔሮ በተካሄደው የ2016 የኦሎምፒክ ጨዋታዎች በ10000ሜትር በ27፡36.34 በሆነ ሰዓት 15ኛ ደረጃ በመያዝ አጠናቋል፡፡

ዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና
• በዶካ ኳታር በተካሄደው የ2019 የዓለም አትሌቲክሰ ሻምፒዮና በ5000ሜትር ተሳትፏል
• በለንደን በተካሄደው የ2017 የዓለም አትሌቲክሰ ሻምፒዮና በ10000ሜትር በ26፡59.19 በሆነ ሰዓት 7ኛ ደረጃ አግኝቷል፡፡

በዓለም አገር አቋራጭ
• በኡጋንዳ ካምላ በ2017 በተካሄደው የዓለም አገር አቋራጭ ሻምፒዮና በአዋቂ ወንዶች 10ኪ.ሜ. ውድድር በ28፡43 በሆነ ሰዓት 3ኛ ደረጃ በመያዝ የነሃስ ሜዳልያ አግኝቷል፡፡

በመላ አፍሪካ ጨዋታዎች
• በሞሮኮ ራባት በ2019 በተካሄደው የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች በ10000 ሜትር በ28፡27.38 7ኛ ደረጃ ይዞ ያጠናቀቀ ሲሆን በኢትዮጵያ አትሌቲክሰ ሻምፒዮና
• በ2016 በተካሄደ የኢትዮጵያ አትሌቲክሰ ሻምፒዮና በ10000ሜትር በ28፡43.2 በሆነ ሰዓት 1ኛ ደረጃ ይዞ ያጠናቀቀበት ከተወዳደረባችው በጥቂቱ የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

የአትሌት አባዲ ሀዲስ የቀብር ስነ ስርዓት በነገው እለት የኢትዮጵያ አትሌቲክሰ ፌዴሬሽን አመራሮች፣ የትግራይ ክልል አትሌቲክሰ ፌዴሬሽንና የክለቡ አመራሮችና ሌሎች ኃላፊዎች በተገኙበት በትውልድ ስፍራው የሚከናወን ሲሆን የኢትዮጵያ አትሌቲክሰ ፌዴሬሽን ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት፣ ማኔጅመንት ኮሚቴ አባላትና መላ ሰራተኞች የተሰማቸውን ልባዊ ሀዘን እየገለፁ ለቤተሰቡና ወዳጅ ዘመዶቹ መፅናናት ይመኛሉ፡፡

-የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን
@YeneTube @FikerAssefa
በመንግስት ድጎማ የሚቀርበው የፓልም የምግብ ዘይት የጥራት ደረጃ መሻሻሉ ተነገረ፡፡

የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት እንደተናገረው በድጎማ ከውጪ የሚገባውና ከዚህ ቀደም የጥራት ደረጃው ላይ ጥያቄ ሲነሳበት የነበረው የፓልም የምግብ ዘይት የጥራት ደረጃ እንዲሻሻል አዲስ የአቅርቦትና ስርጭት መመሪያ እንደተሰናዳለት ተነግሯል፡፡

ዘይቱ በውስጡ ካለውና በረጅም ጊዜ የጤና ስጋት ሊሆን ይችላል በተባለው የስብ መጠን እና ከአስመጪዎች መረጣ ፍትሃዊነት ጋር ተያይዞ ሲነሱ የነበሩ ቅሬታዎችን ለመፍታት መመሪያው መዘጋጀቱን ሰምተናል፡፡ከታህሳስ ወር ጀምሮ ተግባራዊ ሆኗል በተባለው በዚሁ መመሪያ መሰረትም ከዚህ በኋላ የሚቀርበው የምግብ ዘይት ቀደም ሲል ፓልም ዘይት /በተለምዶ የሚረጋው ዘይት ሳይሆን ፓልም ኦሊን የተባለ ፈሳሽ የምግብ ዘይት መሆኑ ተነግሯል፡፡

ከዚህ ቀደም በመንግስት ድጎማ የሚሰራጨው ፓልም ዘይት የጥራት ደረጃው ተሻሽሎ ፓልም ኦሊን በተባለ የምግብ ዘይት የጥራት ደረጃ ቀርቧል የተባለ ሲሆን ቫይታሚን A እና B የሟላ መሆን እንዳለበትም መመሪያው ያስረዳል ተብሏል፡፡ከጥራት ደረጃው በተጨማሪም የአስመጪዎች ምልመላ የዋጋ ትመና እና የትርፍ አወሳሰን በመመሪያው የተካተተ ሲሆን በክልሎችና በከተማ አስተዳደሮች 24 የምግብ ዘይት አስመጪዎች ተመርጠዋል ወደ ስራም ገብተዋል መባሉን ከንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሰምተናል፡፡

Via Sheger
@YeneTube @FikerAssefa