YeneTube
ከኖቭል ኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ የተሰጠ ወቅታዊ ጋዜጣዊ መግለጫ! የዓለም ጤና ድርጅት የኖቭል ኮሮና ቫይረስ በሽታ ከታሕሳስ 21, 2012 ዓ.ም. ጀምሮ በቻይና ዉሃን (Wuhan) ግዛት የተከሰተ መሆኑን አሳውቋል፡፡ በድርጅቱ ሪፖርት መሰረት ይህ በሽታ ከተከሰተበት ቀን ጀምሮ እስከ ጥር 24, 2012 ድረስ ከ 23 ሀገራት በጠቅላላ 14, 557 ታካሚዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሪፖርት ያደረጉ ሲሆን ከቻይና…
የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በኮሮናቫይረስ ሳይያዙ አይቀሩም የተባሉ ሌሎች አራት ሰዎች መገኘታቸውን አስታወቀ።
የጤና ኢንስቲትዩቱ ይህንን ያሳወቀው በዛሬው እለት በሰጠው መግለጫ ሲሆን፤ በቫይረሱ የተጠረጠሩት ሶስቱ ኢትዮጵያውያን አንዱ ደግሞ ቻይናዊ መሆናቸው ተነግሯል።በበሽታው ከተጠረጠሩ አንዱ በአክሱም እንደሚገኝ የተቀሩት ደግሞ በቦሌ ጨፌ በለይቶ ማቆያ ክትትል እየተደረገላቸው እንደሆነ ኢንስቲቲዩቱ ያሳወቀ ሲሆን፤ የአራቱም ግለሰቦች ናሙናቸው ተወስዶ ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመላክ ዝግጅት መጠናቀቁ ተነግሯል።
Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa

አንጋፋው ሙዚቃ አቀናባሪ ሻለቃ መላኩ ተገኝ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ!
ሻለቃ መላኩ ተገኝ ጥላሁን ገሰሰ፣ መሀሙድ አህመድ እና ብዙነሽ በቀለን ጨምሮ የበርካታ አንጋፋ ድምፃውያንን ሙዚቃ ያቀናበረ አንጋፋ የሙዚቃ ሰው ነበር።ካቀናበራቸው ሙዚቃዎች ውስጥም የጥላሁን ገሰሰ የ13 ወር ፀጋ፣ ምን ታደርጊዋለሽ፣ አታላይ ነሽ እና ይገርማል እንዲሁም የብዙነሽ በቀለ ጭንቅ ጥብብ የሚሉት ሙዚቃዎች ተጠቃሽ ናቸው። ሻለቃ መላኩ ተገኝ በክቡር ዘበኛ የሙዚቃ ቡድን ውስጥም ለረዥም ጊዜ አገልግሏል።የሙዚቃው ሰው በተወለደ በ75 ዓመቱም ትናንት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።አንጋፋው የዜማ ደራሲ ዓየለ ማሞ ሻለቃ መላኩ ተገኝ አሻራው እስከዛሬ የዘለቀ፣ ዜማን በጥሩ ሁኔታ የሚረዳ እና ብቁ የሙዚቃ ሰው ነበር ሲል ገልፆታል። የሻለቃ መላኩ ተገኝ የቀብር ስነ ስርዓት ዛሬ ከቀኑ 9 ሰዓት ላይ በምስራቅ ፀሃይ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ይፈፀማል።
Via FBC

የገናሌ ዳዋ ሦስት ኃይል ማመንጫ ግድብ ነገ ጥር 26/2012 ኃይል የማምረት ሥራውን እንደሚጀምር የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ። ግድቡ 2 ነጥብ 57 ቢሊዮን ሜትር ኪዩብ ውሃ የመያዝ አቅም ያለው ሲሆን፣ 254 ሜጋ ዋት ኃይል የማመንጨት አቅም ያለው ነው። የፕሮጀክቱን የሲቪል እና የኤሌክትሮ ሜካኒካል ሥራዎችን የሠራው ሲጂጂሲ (CGGC) የተሰኘ የቻይና ኩባንያ ሲሆን፣ የማማከር ተግባሩን ደግሞ የአሜሪካው ኤም. ደብሊው. ኤች (MWH) ከአገር በቀሎቹ አኪዩትና ኢንቲግሬትድ ጋር በጥምረት እንዳከናወኑት ተገልጿል።
Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
የLTE Advanced አገልግሎት በአዲስ አበባ ከተማ የሞባይል ኢንተርኔት አጠቃቀም ከፍተኛ በሆነባቸው ቦታዎች ተግባራዊ ማድረጉን Ethio Telecom አስታውቋል።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
ቤተ እሰራኤላውያን ስደተኞች ከፍልስጤም ቅሬታ ቀረበባቸው!
ቁጥራቸው እየበዛ የመጣው ቤተ እስራኤላውያን እና የሩስያ ስደተኞች አይሁዳውያን ናቸው ተብለው ወደ እስራኤል መግባታቸው ትክክል እንዳልሆነ እና እስራኤልንም የአይሁድ መንግሥት ናት ብለው እንደማይቀበሉ የፍልስጤሙ ፕሬዝዳንት መሐሙድ ኣባስ ተናገሩ።
አንድ ነጥብ አምስት ሚሊዮን የነበሩት ሩስያውያን በአሁኑ ወቅት ኹለት ሚሊዮን መድረሳቸውን የጠቀሱ ሲሆን፤ ቀደም ሲል ቁጥራቸው አነስተኛ የነበረው የቤተ እስራኤላውያን ቁጥር እየጨመረ መምጣቱንም አስታውቀዋል።
የእስራኤሉ ፕሬዝዳንት ሬዩቭን ሪቪሊን በበኩላቸው ‹‹የአይሁዳውያን መንግሥት እኛ ነን እንጂ ሌላ መንግሥት የላቸውም። ሁሉም ዜጎች ለእኛ አኩል ናቸው።›› ሲሉ ምላሻቸውን ለፍልስጤሙ ፕሬዝዳንት ሰጥተዋል።
አክለውም ‹‹እኔ የተወለድኩት ከ80 ዓመት በፊት በዚህ አገር ላይ ሩብ ሚሊዮን የሚሆኑ አይሁዳውያን በነበሩ ወቅት ነው። አሁን ፕሬዝዳንት በመሆን በማገለግልበት ጊዜ ዘጠኝ ሚሊዮን ዜጎችና ሰባት ሚሊዮን አይሁዳውያን ይገኛሉ።›› ብለዋል። ከማንኛውም ሰው ጋር በሰላም ለመኖር ነው በዚህ የተገኘነው ማለታቸውንም ታይምስ ኦፍ ኢስራኤል አስታውቋል።
ምንጭ: አዲስ ማለዳ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ከአባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ከሰጡት ምላሽ የተወሰዱ አንኳር ነጥቦች፡-
• ከለውጥ በፊት ኢትዮጵያ በሁሉም መስክ እንደ አገር መቀጠል የማትችልበት ደረጃ ላይ ደርሳ ነበር፡፡
• ከለውጥ በኋላ እስረኞች መፍታት ተችሏል፤ በተለያዩ አገራት ታስረው የነበሩ ኢትዮጵያንን ማስፈታት ተችሏል
• በተለያዩ አገራት የነበሩ ፖለቲካኞች ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ተደርጓል ሚዲያዎች ብሎክ እንዳይደረጉና ሰዎች ሐሳባቸውን እንዲገልጹ ማድረግ ተችሏል
• አፋኝ ሕጎችን ለማሻሻል ጥረት ተደርጓል ኢትዮጵያ ውስጥ ለነበሩት አብዛኛዎቹ ችግሮች ምንጭ ራሱ ገዢ ፓርቲ ነበር፡፡
• አሁን እየሰራን ያለነው ሀገረ-መንግሥቱን ማስቀጠል የሚችል ተቋም መፍጠር ላይ ነው፤ ይህ የለውጡ ኃይሉ የሞት የሽረት ጉዳይ ነው።
• ከዚህ ቀደም በመንግሥት ውስጥ የነበረንን ኔትወርክ በመጠቀም የፈለግነውን ለማድረግ የመሞከር የሴራ ጨዋታ መቆም ይኖርበታል፣ ያልተገባ ሞት ያስከትላል።
• የሴራ፣ የተንኮል፣ የደባ እና የሽብር ፖለቲካውንም አሸንፈን ኢትዮጵያን የምናስቀጥል መሆናችንን በልበ ሙሉነት ልገልጽላችሁ እፈልጋለሁ።
• በፌዴራል እና በክልል መንግሥታት መካከል ምን አይነት ትስስር፣ መተጋገዝ እና የሥራ ክፍፍል እንዳለ በሕገ-መንግሥቱ ተለይቶ ተቀምጧል።
• የፌዴራል መንግሥት በሦስት ጉዳዮች ማለትም ክልሎች ድጋፍ ሲጠይቁ፣ የከፋ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ሲያጋጥም እና ሀገረ-መንግሥቱ አደጋ ላይ በሚወድቅበት ጊዜ የፌዴራል መንግሥት ጣልቃ ሊገባ ይችላል።
• ስለተማሪዎች እገታ ኃላፊነት የወሰደ አካል የለም፤ የደረሱንን መረጃ ስናጣራ በቆየንበት ጊዜ የታገተ የለም የሚል አቋም እንድንወስድ ግፊት ሲደረግብን ነበር፤ እኛ ግን የጠራ መረጃ ሳይኖረን ተጣድፈን ይህን ማለት አልፈለግንም፡፡
• አጋች ኃላፊነት ሲወስድ ታጋቾችን መልሶ ለማግኘት መደራደርም አለ፤ በዚህ ሁኔታ ግን ኃላፊነት የወሰደ አልነበረም፡፡
• ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩን ያሳተፈ ኮሚቴ ተዋቅሮ በትኩረት እየሰራ ነው፤ የደረሰበትን በየጊዜው ያሳውቃል፡፡
• መከላከያም የራሱን ስራ እየሰራ ነው፤ እስካሁን የደረሰ የከፋ ችግር ስለመኖሩ ያገኘነው መረጃ የለም፡፡
• በተማሪዎቹ እገታ ተጠቂው ቤተሰብ ብቻ ሳይሆን ሀገር ጭምር ነው፤ ሰላም ወዳድ ሕዝብ ጭምር ነው፤ እነዚህ ተባብረው መሥራት አለባቸው።
• የመንግሥት ዋና ፍላጎት ምንም ሰው ሳይሞት ችግሩ እንዲፈታ ማድረግ ስለሆነ በጉዳዩ ላይ ብዙ መናገር አልተቻለም።
• አሁን ያለነው 2012 ላይ ነው፤ አንዳንድ ሰዎች ግን ገና 1966 ላይ ነው ያሉት።
• በአንድ ሀገር ሁለት የታጠቀ መንግሥት መኖር አይችልም፤ ሕጋዊ መንግሥት ሕጋዊ እርምጃ መውሰዱ አይቀርም።
• መንግሥትን በሁለት መንገድ አጣብቂኝ ውስጥ በመክተት ለማዳከም እየተሰረ ነው፤ በአንድ በኩል ሰላም ማስከበር አልቻላችሁም፣ በሌላ በኩል ደግሞ ሰው እየገደላችሁ ነው የሚል።
• ይህ ወገን ለጊዜው መንግሥትን ያጥቃ እንጂ በኋላ ላይ ሕዝብን ከሕዝብ ወደማጋጨት መዞሩ የማይቀር ነው።
• ማሸነፊያው መንገድ ውይይት፣ ምክክር፣ የአንዱን ክፍተት ሌላው መሙላት ነው፤ መገዳደል ግን ሁሉ ሟች፣ ሁሉ ገዳይ የሚሆንበት ነው።
• ሁሉም በኃላፊነት እና በሕግ አግባብ መንቀሳቀስ ስላለበት የፖለቲካውን ምኅዳር ጥርቅም አድርጎ በመዝጋት ወይም አላግባብ በመክፈት ፈንታ አማካይ መስመሩን መያዝ ግድ ይላል።
• አሁን ያለንበት ወቅት ፈታኝ፣ የሞት እና የሽረት ቢሆንም ይህን አሸንፈን ብልፅግናችንን ማስቀጠል ይኖርብናል።
• ዳሰነችን በተመለከተ ከኬንያ መንግሥት ጋር የጋራ የድንበር አካባቢ የልማት ሥራ ለመሥራት እየተነጋገርን ነው፤ ያ ሲሆን በአካባቢው ዘላቂ ሰላም ይፈጠራል የሚል እምነት አለን።
Via:- ETV
@YeneTube @Fikerassefa

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የልማት ድርጅቶችን፣ ቴሌኮም፣ መብራት ኃይልና ሌሎች ጉዳዮችን በተመለከተ ከፓርላማ አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ከሰጡት ምላሽ የተወሰዱ አንኳር ነጥቦች:-
➡️ የመንግስት የልማት ድርጅቶች ከ1980 አጋማሽ ጀምሮ ላለፉት 20 ዓመታት 287 የመንግስት ድርጅቶች ወደ ግል ተዘዋውረዋል፡፡
➡️ ከረፎርም በኋላ አንድ ወደ ግል የተዘዋወረ የመንግስት ተቋም የለም፡፡
➡️ የባንክ ሴክተር የአገር ውስጥ ባለሀብቶች በሁለት እግራቸው እስኪቆሙ ድረስ ለውጭ ባለሀብቶች ክፍት እንዳይሆኑ ተደርጓል፡፡
➡️ ባለፈው አንድ ዓመት 8 ሚሊዮን አዳዲስ የሞባይል ሰብስክራይበሮች ማፍራት ተችሏል፡፡
➡️ የቴሌኮም ዋጋ ቅናሽ ተደርጎ፤ ከቴሌኮም ከፍተኛ ገቢ እንዲያገኝ ተደርጓል፡፡
➡️ የኢትዮጵያ ዋነኛ የኃይል ምንጭ የኃይድሮ የኃይል ምንጭ ስለሆነ ዋናው ትኩረት የውሃ ሀብትን መምራት ላይ ነው፡፡
➡️ ከውጭ አገራት ጋር የዲፕሎማሲ ስራ መስራት የፌዴራል መንግስት ስልጣን ነው፡፡
➡️ የትግራይን ህዝብ ያገለለ መንግስት በኢትዮጵያ ውስጥ ሊፈጠር አይችልም፤ የትግራይ ህዝብ የካቢኔ ውክልና በፊት ከነበረው ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡
➡️ ደቡብ ክልልን በተመለከተ ህዝቡ የሚፈልገውንና ለህዝቡ የሚበጀውን እናደርጋለን፡፡
➡️ የክልሎች አደረጃጀት ወጪ ቆጣቢና ህዝብን በሚጠቅም መልኩ መሆን አለበት።
➡️ በዓለም ደረጃ የሚታየውን የሃብት ክፍፍል ልዩነት ለማስተካከል እንደ ሀገር የስራ እድል ፈጠራን አጠናክረን እየሰራን እንገኛለን።
➡️ በሀገሪቱ የተጀመሩ እንደ ስኳር፣ ህዳሴ ግድብና ሌሎች ትልልቅ ስራዎችን ለማጠናቀቅ በጥሩ ሁኔታ እየተሰራ ነው።
➡️ ከለውጡ በኋላ ኢትዮጵያን ከፍተኛ የእዳ ጫና ስላለባትና ተጨማሪ ብድር ለማግኘት ስለማትችል ያለውን ሀብት ተጠቅሞ አዲስ ካፒታል እና አዲስ እውቀት ለሚያመጡ በር መክፈት ነበረብን።
➡️ ከአዲስ አበባ ኤርፖርት ወደ አብዮት አደባባይ ያለው መንገድ ላይ ቦሌ መንገድ አካፋይ ያሉ የአበቦች ስርቆት ይታያል፤ ይሄ መስተካከል ያለበት ነው።

“በእገታው ተጠቂው ሀገር፣ ሰላም ወዳዱ ህዝብ፣ እና ሁሉም ወላድ ነው”
--ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ--
ከወራት በፊት በታገቱ ተማሪዎች ተጠቂው ሀገር፣ ሰላም ወዳዱ ህዝብ፣ እና ሁሉም ወላድ እንደሆነ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ተሃገሩ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከወራት በፊት በደንቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ በተፈጠረው ችግር ሸሽተው ከአካባቢው በመውጣት ላይ የነበሩና ማንነታቸው ባልታወቁ ሀይሎች የታገቱ ተማሪዎችን ጉዳይ በተመለከተ ከም/ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማብራሪያቸው "አልቃይዳ፣ቦካሀራም… ጉዳት ሲያደርስ ወይም እገታ ሲፈፅም ኃላፊነት ይወስዳል፤ እኛ አገር ከተማሪዎች እገታ ጋር በተያያዘ እስካሁን ድረስ እገታውን ፈፅሜያለሁ ብሎ ሀላፊነት ለመውሰድ የቀረበና የተደራጀ ሀይል የለም ብለዋል፡፡ ይህ አካል ባለመኖሩም ችግሩን ውስብስብ አድርጎታል፡፡
መንግስትም ፈጥኖ መግለጫ ያልሰጠው ባልተሟላ መረጃ ጠንከር ያለ መግለጫ መስጠት ያልተደራጁ ግለሰቦች የፈፀሙት እገታ ከሆነ ራሳቸውን ለማዳን ሲሉ ታጋቾችን አደጋ ውስጥ ሊከቱ ይችላሉ ብሎ በማሰብ እንደሆነ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡
የመንግስት ዋና ፍላጎት ምንም ሰው ሳይሞት በህይወት እንዲገኝ ስለሆነ ከመናገር ይልቅ በህይወት የማስገኘቱን ስራ የማሳለጡን ጉዳይ ቅድሚያ እንዲሰጠው ተደርጎ እየተሰራ እንደሆነም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማብራሪያቸው ገልፀዋል፡፡
ችግሩ የተከሰተው ከሩቅ በመጣ ጠላት ሳይሆን በእኛ ስብዕና ግንባታ ችግር የመጣ ስለሆነ እንደውጪ ጠላት በቀላሉ ማስወገድ አልተቻለም፤ እንክርዳዱን ለመንቀል ብለን ስንዴውን እንዳንነቅል የምናደርገው ጥረት ጥንቃቄ ይፈልጋል፡፡
ከቤተሰብና አካባቢ ሽማግሌዎች ጋር ባደረግነው ውይይት እስከአሁን በዚህ ረገድ ጥቃት ደርሶ ህይወቱ ያለፈ የአንድም ሰው ሪፖርት አልደረሰንም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመራ አጣሪ ኮሚቴ ስለተቋቋመ ኮሚቴው የሚደርስበትን ውጤት ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርግ ገልፀዋል፡፡
Via:- EPA

"ባለፉት 6 ወራት ለ1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ወጣቶች የስራ እድል ተፈጥሯል!"
ባለፉት 6 ወራት ለ1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ወጣቶች የስራ እድል መፍጠር መቻሉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ተናገሩ፡፡ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ከአባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምለሽ በሰጡበት ወቅት በአመቱ ለ3 ሚሊዮን ዜጎች የስራ እድል ለመፍጠር ታቅዶ የነበረ ቢሆንም እቅዱ የተጋነነ እንደነበር አስታውሰዋል፡፡
እቅዱን ለማሳካት በአሁኑ ሰዓት ቢያንስ ለ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ወጣቶች የስራ እድል መፍጠር የሚገባ እንደነበር የገለፁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የስራ እድል ከተፈጠረላቸው ውስጥ 65 በመቶዎቹ ቋሚ እንዲሁም 35 በመቶዎቹ ደግሞ ጊዜያዊ እንደሆኑ ገልፀዋል፡፡ይህ ከአምናው ጋር ሲወዳደር ሰፊ እድገት እንዳሳየ የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የስራ እድል ፈጠራ ኮሚሽን ከአጋዥ ሀገራት 240 ሚሊዮን ዶላር በእርዳታ መልክ አምጥቶ ራሱን በማደራጀት ሰፊ ስራ እየሰራ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
ከነበረው ውጤት አንጻር እጅግ ላቅ ያለ ቢሆንም ካለብን የስራ አጥነት ችግር አንፃር ግን ሰፊ ስራ የሚጠይቅ ዘርፍ እንደሆነ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አብራርተዋል፡፡
Via EPA

የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስትን በይፋ ለመመስረት የሚያስችለውን ዝግጅት ማጠናቀቁን የዞኑ መስተዳድር ዛሬ አስታወቀ።
የመስተዳድሩ የህዝብ ግንኙነት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ገነነ አበራ የክልላዊ መንግስት ምስረታውን ወደ ተግባር ለማሸጋገር የብሄሩ ሙሁራንና የፖለቲካ ሊህቃንን ጨምሮ ከተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች የተውጣጡ አባላት የተካተቱበት ራሱን የቻለ የፕሮጀክት ጽህፈት ቤት ተቋቁሞ የዝግጅት ስራዎችን ሲያከናውን መቆየቱን ገልጸዋል። በአሁኑ ወቅትም የክልሉን ህገ መንግስት ማርቀቅን እና በታችኛው እርከን የሚኖረውን የአስተዳደር መዋቅር ማዘጋጀትን ጨምሮ የክልል ምስረታውን ለማከናወን የሚያስፈልጉ ቅደመ ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውን የጽህፈት ቤቱ ሃላፊ አስረድተዋል።
በአንዳንድ ወገኖች የክልል ምስረታው ዘግይቷል በሚል እየቀረቡ በሚገኙ ቅሬታዎች ዙሪያ የተጠየቁት አቶ ገነነ << << ከዝግጅት አንፃር በእኛ በኩል የሚያስፈልጉ መሰናዶዎችን አጠናቀን እንገኛለን ። መዘግየቱ ያጋጠመው ከነባሩ ክልል ጋር ከሀብት ክፍፍል እና ከርክክብ ጋር የተያያዙ ስራዎች የተወሰነ ጊዜ በመውሰዳቸው ነው። አሁን አብዛኞቹ ሂደቶች በመጠናቀቃቸው የክልል ምስረታው በቅርቡ ተፈጻሚ ይሆናል >> ብለዋል።
ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ በአዳማው ስብሰባ ላይ የሚገኙ የሲዳማ ፖለቲከኞችን ከጌዲኦ ዞን ፣ ከአማሮ አና ከቡርጂ ወረዳዎች የሚመሰረተው የሲዳማ ክልል አካል አድርጎ ለማዋቀር ህዝቡን እንዲያሳምኑ ነግረዋቸዋል በተባለው ጉዳይ ላይ የሚያውቁት ነገር አለ ወይ? በሚል ከዶቼ ቨለ ( DW ) ለቀረበላቸው ጥያቄም << እኛ ይህን ጉዳይ የሰማነው ከማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ነው ። ያም ሆኖ የአዳማውን ስብሰባ እየተሳተፉ የሚገኙ አመራሮች ጋር ደውለን ለማጣራት ሞክረናል ። ጠቅላይ ሚንስተሩ በዚህ ጉዳይ ላይ የነሱት ነገር እንደሌለ አመራሮቹ አረጋግጠውልናል >> ብለዋል።
ክልሉ ሲመሰረት በየትኛው የፖለቲካ ፓርቲ ነው የሚመራው? በሚል የተጠየቁት አቶ ገነነ << አሁንባለው ሁኔታ ክልሉን የሚያስተዳድረው ቀደምሲል በገዢ ፓርቲነት ሲመራ የቆየውና በአሁኑወቅት ብልፅግና ፓርቲ በሚል የሚታወቀው ድርጅት ነው። ለወደፊቱ ግን ህዝቡ በቀጣዩ ምርጫ የሚወስነው ጉዳይ ይሆናል >> ብለዋል ።የሲዳማ ብሄር ባለፈው ህዳር ወር ባካሄደው ህዝበ ውሳኔ ከደቡብ ክልል በመነጠል እራሱን በቻለ ራስ ገዝ ( ክልል ) ለመደራጀት የሚያስችለውን የውሳኔ ድምጽ ማሳለፉ ይታወሳል። ተቃዋሚው የሲዳማ አርነት ንቀናቄ ( ሲአን ) በበኩሉ የክልላዊ መንግስት ምስረታው እንዲፋጠን ፣ የሀምሌ 11 ግጭትን ተከትሎ በአስር ላይ የሚገኙ ወጣቶች ሰብእዊ መብታቸው እንዲጠበቅና ጉዳያቸው ተጣርቶ እንዲፈቱ ሲል ሰሞኑን ባወጣው የአቋም መግለጫ መጠየቁ ይታወቃል ።
ዘገባው የዶይቸ ቨለ ነው!

"የኢትዮጵያ ገዢው ፓርቲ ብልጽግና ፓርቲ ነው፡፡ ብልጽግና ፓርቲ በምክር ቤት አብላጫ ድምጽ ስላለው መንግስት ብልጽግና ፓርቲ ነው፡፡ በትግራይ ክልል ህወሀት አብላጫ ድምጽ ስላለው መንግስት ህወሀት ነው፡፡በትግራይ ክልል እና በፌደራል መንግስት መካከል ህጋዊ የሆኑ ትስስሮች እና የስራ ግንኙነት ነው ያለው፡፡ በፌደራል መንግስት የትግራይ ተወላጆች እየተገፉ ነው የሚባለው ትክክል አደለም፡፡ አንድ ሚኒስትር ተነስተዋል ከስራቸው ሆኖም በርካታ ሚኒስትሮች አሉ አልተነሱም፡፡ ድሮም በካቢኔ ያላቸው ቁጥር እንዳለ ነው፡፡የትግራይን ህዝብ እንደ ህዝብ ያገለለ መንግስት መመስረት አይቻልም፡፡ የትግራይ ህዝብ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ የመሳተፍ ሙሉ አቅሙም መብቱም አላቸው፡፡ ህወሀት ለረዥም ጊዜ ከእኛ ጋር የሰራ በቀላሉ ልንግባባ የምንችል እና ወደፊትም አብረን የምንሰራ በመሆናችን የተባለው መግፋት አልተደረገምም አይደረግም፡፡" ጠ/ሚር ዶ/ር አብይ አህመድ ከህዝብ ተወካዮች ምክር 1ኛ ልዩ ስብሰባ ላይ ከተናገሩት ተወሰደ
Via አዲስ ሚድያ ኔትወርክ
@YeneTube @FikerAssefa
Via አዲስ ሚድያ ኔትወርክ
@YeneTube @FikerAssefa
ህፃናትን ከልጅነት ልምሻ (ፖሊዮ ) በሽታ ለመከላከል የሚያስችል የፖሊዮ 1 ክትባት ዘመቻ ከጥር 26-29/ 2012 ዓ.ም ጀምሮ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደርን ጨምሮ ፣በሀዲያ ፣በሲዳማ ፣በሀላባ፣ በወላይታ፣በጉራጌ ፣በስልጤ ዞኖች ለመስጠት አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት በማጠናቀቅ ላይ መሆኑን የ /ደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግሥት ጤና ቢሮ አስታዉቋል።
ምንጭ: የክልሉ ጤና ቢሮ
@YeneTube @FikerAssefa
ምንጭ: የክልሉ ጤና ቢሮ
@YeneTube @FikerAssefa
በአዊ ብሄ/አስተዳደር በባንጃ ወረዳ ከሳ ቸውሳ ቀበሌ ዘንገና ሀይቅ አከባቢ አንድ ተሳበቢ የነዳጅ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ወድቆ መንገድ ስለተዘጋ የሚመለከተው አካል አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጠው ተጠይቋል።
Via Awi Communication
@YeneTube @FikerAssefa
Via Awi Communication
@YeneTube @FikerAssefa
በቻይና ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን ነዋሪዎች የኮሮና ቫይረስን አስመልክቶ በኢትዮጵያ ለሚገኙ ሚዲያዎችና የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት በህብረት የተሰጠ መልዕክት(ማሳሰቢያ)።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
#FactCheck
በትናንትናው የጠ/ሚር አብይ የፓርላማ ንግግር በበጀት አመቱ አጋማሽ ለ1.2 ሚልዮን ዜጎች የስራ እድል መፈጠሩን መናገራቸው ይታወሳል። የስራ ፈጠራ ኮሚሽንም በቅርቡ ባወጣው የ6 ወር የ
አፈፃፀም ሪፖርቱ ለ1.18 ሚሊዮን ዜጎች ቋሚና ጊዜያዊ የስራ እድል መፈጠሩን አሳውቆ ነበር።
ነገር ግን ትናንት አመሻሽ ላይ ፎርቹን በሰራው አጭር ዘገባ ጠ/ሚሩ ያቀረቡት ያለፈውን ሙሉ በጀት አመት ቁጥር የዘንድሮውን ግማሽ አመት በማስመሰል ነው የሚል አንድምታ ያለው መሆኑን ተገንዝበናል።
የመረጃው ተአማኒነት የሚያጠራጥር፣ ወይም ቁጥሩ የተጋነነ ከሆነ የማጣራት ስራ መስራት ነው እንጂ በግርድፉ ጠ/ሚሩ እንደተሳሳቱ ወይም እንደዋሹ አድርጎ ዘገባ መስራት የሚዘገብለትን ሰው ማደናገር ይሆናል።
ይህንን የፎርቹን ዘገባ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረትም ተቀብሎ ማጋራቱን ተመልክተናል!

የቀድሞው የኬንያ ፕሬዚዳንት ዳንኤል አራፕ ሞይ በ95 አመታቸው ከዚህ አለም በሞት መለየታቸውን ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬኒያታ ከደቂቃዎች በፊት አሳውቀዋል።
ምንጭ:CGTN
@YeneTube @FikerAssefa
ምንጭ:CGTN
@YeneTube @FikerAssefa